8. ማንነትን መደበቅ እና የኢንተርኔት ሳንሱርን/እገዳን ማለፍ

Updated2010

መመሪያው በወቅቱ አልተሻሻለም፤ በቅርቡ ይሰረዛል

የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች የተወሰኑ ድረ ገጾችን እንዳይመለከቱ ወይም አገልግሎቶችን በኢንተርኔት እንዳያገኙ የሚከለክሉ ሶፍትዌሮችን የሚጭኑ አገሮች አሉ፤ የክልከላ ምክንያታቸው የተለያየ ነው። ኩባንያዎች/ድርጅቶች፣ ትምህርት ቤቶች፣ የሕዝብ አብያተ መጻሕፍትም እንዲሁ ሠራተኞች፣ ተማሪዎች እና ተጠቃሚዎች “ሥራ ያደናቅፋሉ” የሚሏቸውን ድረ ገጾችና አገልግሎቶች ለማግኘት እንዳይችሉ የሚያደርጉ ሶፍትዌሮችን ይጭናሉ። ይህን መሰሉ ክልከላ በተለያየ መልኩ ሊመጣ ይችላል። አንዳንድ ክልከላዎች በድረ ገጹ አይፒ አድራሻ (IP address) ላይ የሚያነጣጠሩ ናቸው፤ ሌሎቹ ደግሞ የድረ ገጹን የዶሜን ስም (የኢንተርኔት መጠሪያ) (domain names) በክልከላ መዝገብ በማስገባትና በማገድ የሚሠሩ ናቸው። የተወሰኑ ቁልፍ ቃላትን ወይም ኢንክሪፕትድ ባልሆነ የኢንተርኔት ግንኙነቶች የሚደረጉ ፍለጋዎችን በማደን የሚከለክሉም አሉ።

የትኛውም የመከልከያ/የሳንሱር መንገድ ጥቅም ላይ ቢውል ሁሉንም ለማለፍና የተከለከለውን ድረ ገጽ መክፈት ወይም አገልግሎቱን ማግኘት ግን ይቻላል። ክልከላው ከተደረገበት አገር ውጭ በሚገኝ አገናኝ (intermediary) ኮምፒውተር አማካኝነት የተከለከለውን ድረ ገጽ/አገልግሎት ማግኘት ይቻላል። ይህ በተለምዶ ሴንሰርሺፕ ሰርከምቬንሽን (censorship circumvention) (ሳንሱርን ማለፍ) ወይም በአጭሩ ሰርከምቬንሽን (circumvention) ይባላል፤ በተከለከለው ኮምፒውተርና በአገልግሎቱ መካከል ሆነው የሚያገናኙት አገናኝ ኮምፒውተሮች ደግሞ ፕሮክሲ/ዎች (proxies) ይሰኛሉ። ፕሮክሲዎች (proxies) በተለያየ መንገድ አገልግሎት ይሰጣሉ። ይህ ምእራፍ ስለብዙኀ ፕሮክሲ ስምአልባ መረቦች (multiple-proxy anonymity networks) አጭር ማብራሪያ ይዟል። ምእራፉ ስለሰርከምቬንሽን (circumvention) ፕሮክሲ/ዎች (proxies) ዝርዝር ማብራሪያ ያቀርባል፤ እንዴት እንደሚሠሩም ያስረዳል።

እነዚህ ሁለት መንገዶች የኢንተርኔት ክልከላን (Internet filters) ለማለፍ የሚያስችሉ ናቸው፤ የመጀመሪያው የኢንተርኔት እንቅስቃሴዎቻችንን በተቻለ መጠን ማንነታችን ሳይታወቅ እንድናከናውን ቢያስችለንም የግንኙነታችንን ፍጥነት ግን ይቀንሰዋል። የፕሮክሲ (proxy) አገልግሎት የሚሰጠንን ግለሰብ ወይም ድርጅት የምናውቅውና የምናምነው ከሆነ፣ መሠረታዊ የሚባለው ሰርከምቬንሽን (circumvention) ፕሮክሲ(proxy) የተሻለ አገልግሎት ሊሰጠን ይችላል።

አስረጅ አጋጣሚ

:Snippet

የምእራፉ ዋና ዋና ጭብጦች

- በአገራችን በተለያየ ምክንያት የታገዱ ድረ ገጾችን እንዴት ማግኘትና ማንበብ ይቻላል?
- የምንጎበኘው ድረ ገጽ ያለንበትን ትክክለኛ አድራሻ እንዳያውቀው ለማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?
- የየግላችን [*የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢ (አይኤስፒ/ISP)*](/am/glossary#ISP) ወይም ሌላ በአገራችን የሚገኝ የስለላ ተቋም 

የምንጎበኘውን ድረ ገጽም ሆነ በኢንተርኔት ያገኘነውን አገልግሎት እንዳያውቁብን ለማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?

የኢንተርኔት ሳንሱር ምንድን ነው? የሚሠራውስ እንዴት ነው?

ኦፕንኔት ኢኒሺዬቲቭ (ኦኤንአይ) - OpenNet Initiative (ONI) እና ድንበር የለሽ ሪፖርተሮች Reporters Without Borders (RSF) የተባሉ እና ሌሎችም ድርጅቶች ያደረጉዋቸው ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ብዙ አገሮች የተለያዩ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና የአገር ደኅንነት ጉዳዮችን ይመለከታሉ የሚሏቸውን የኢንተርኔት/ድረ ገጾች ወይም ይዘቶች ሳንሱር ያደርጋሉ። ዜጎቻቸው የሚያገኙትን የኢንተርኔት ይዘት መቆጣጠር የሚፈልጉ መንግሥታት ደግሞ ከዚህም አልፈው ዜጎች የሳንሱር ግድግዳዎችን እንዲያልፉ የሚያስችሉ ፕሮክሲዎችን (proxies) ወይም ስለዚሁ ምክርና እገዛ የሚሰጡ ድረ ገጾችን ሳይቀር እንዳይታዩ ለማድረግ ይሞክራሉ።

የዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ (Universal Declaration of Human Rights) አንቀጽ 19 መረጃን በነጻነት ማግኘት የሰብአዊ ፍጡራን ሁሉ መብት መሆኑን ቢደነግግም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የኢንተርኔት ሳንሱር የሚያደርጉ አገሮች ቁጥር እየጨመረ ነው። የኢንተርኔት ድረ ገጾችን ለይቶ ማገድ (Internet filtering) እየተስፋፋ የመሆኑን ያህል ክልከላዎቹን ለማለፍ የሚያስችሉ የማለፊያ መሣሪያዎችም በብዛት መፈጠር፣ መተወዋወቅ እና ጥቅም ላይ መዋል ጀምረዋል። ለዚህም የመረጃ ነጻነት አቀንቃኞች፣ የኢንተርኔት ፕሮግራም ፈጣሪዎች (ፕሮግራመሮች) እና የበጎ ፈቃድ አገልጋዮች ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል። የኢንተርኔት ሳንሱርን ማለፍ ስለሚቻልባቸው ዘዴዎች ከመነጋገር በፊት የኢንተርኔት ሳንሱሩ/ማጥለል (ድረ ገጽን ለይቶ ማገድ) እንዴት እንደሚሠራ መረዳት ይጠቅማል። ለዚህ እንዲረዳን የኢንተርኔት ግንኙነትን እጅግ በቀለለ መንገድ ለማየት እንሞክር።

የኢንተርኔት ግንኙነት

ወደ ኢንተርኔት ግንኙነት የምንገባበት የመጀመሪያው ነጥብ ኮምፒውተራችን በሚገኝበት ቦታ (ቤት፣ ቢሮ፣ ቤተ መጻሕፍት፣ ኢንተርኔት ካፌ…) የኢንተርኔት አገልግሎት በሚሰጠን የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢ (Internet Service Provider) (አይኤስፒ/ISP) በኩል ነው። የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢ (አይኤስፒ) ለምንጠቀምበት ኮምፒውተር የተለየ የአይፒ አድራሻ (IPaddress) ይሰጠዋል፤ የተለያዩ የኢንተርኔት አገልግሎቶችን የምናገኘው፣ መልእክት የሚላክልን እና ኮምፒውተራችን የሚታወቀውም በዚሁ አድራሻ ይሆናል። የኢሜይል እና ድረ ገጽ የማመመልክት ጥያቄዎቻችን ጭምር የሚስተናገዱት በዚሁ “አድራሻችን” ነው።

የአይፒ አድራሻችንን (IPaddress) ማግኘት የቻለ ሰው በየትኛው ከተማ እንዳለን በቀላሉ ለማወቅ ይችላል። በምንኖርበት አገር የሚገኙ በሚገባ የተደራጁ ተቋማት ደግሞ በዚሁ መረጃ ያለንበትን ትክክለኛ ቦታ ማወቅ ይችላሉ።

 • የኤይኤስፒ አድራሻችን (ISP) በየትኛው ሕንጻ ውስጥ እንደምንገኝ ወይም በስልካችን ከኢንተርኔት ጋራ ተገናኝተን ከሆነ በየትኛው የስልክ መስመር እየተጠቀምን እንደሆነ ማወቅ ይችላል፤

 • ኢንተርኔት ካፌ፣ ቤተ መጻሕፍት፣ የሥራ ቦታዎች የትኛውን ኮምፒውተር በየትኛው ሰዓት እንደተጠቀምን፣ ኢንተርኔት የተገናኘንበት መንገድ ገመድ አልባ ይሁን አይሁን ጭምር ሁሉ ማወቅ ይችላል፤

 • የመንግሥት ተቋማት ቀደም ሲል በጠቀስናቸውን ድርጅቶች ላይ ባለቸው ተጽእኖ/ቁጥጥር በመጠቀም እነዚህን መረጃዎች በሙሉ በቀላሉ ሊያገኙ ይችላሉ፤

የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢያችን (አይኤስፒ) የሚወሰነው ከሌላው ዓለም ጋራ ለመገናኘት በሚያስችለን የአገራችን የግንኙነት መረብ መዋቅር ነው። በሌላ በኩል ያለው የግንኙነታችን ጫፍ፣ ከድረ ገጽ ወይም ከኢንተርኔት ጋራ የምናደርገው ግንኙነት በተራው በአገሩ ከሚገኝ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢው (አይኤስፒ) የራሱ አይፒ አድራሻ (IP addresses) ይሰጠዋል። ወደ ቴክኒካዊ ዝርዝሩ መግባት ሳያስፈልገን፣ የኢንተርኔት ሳንሱርንና ለይቶ ማገድን ለማለፍ የሚያስችሉ መሣሪያዎችን ለመምረጥ ይህን መሠረታዊ ሞዴል ማስተወስ ይጠቅማል።

ድረ ገጾች የሚታገዱት እንዴት ነው?

አንድን ድረ ገጽ ለመመልከት ስንሞክር፣ በተግባር የድረ ገጹን የአይፒ አድራሻ (IPaddress) ለአይኤስፒው (ለኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢው) (ISP) በመስጠት ከዌብ ሰርቨሩ አይኤስፒ (ISP) ጋራ እንዲያገናኘን እየጠየቅነው ነው። የኢንተርኔት ግንኙነታችን ክልከላ ካልተደረገበት ወይም በተናጠል የታገደብን ድረ ገጽ ከሌለ (unfiltered) ጥያቄያችን በቀጥታ ይስተናገዳል። ኢንተርኔትን ሳንሱር በሚያደርግ አገር ውስጥ ከሆንን ግን ከጠየቅነው ድረ ገጽ ጋራ ከመገናኘታችን በፊት፣ ድረ ገጹ “በጥቁር መዝገብ” (blacklist) ውስጥ መኖሩ ወይም አለመኖሩ ይጣራል።

በአንዳንድ ሁኔታዎች በአይኤስፒዎች (ISP) ምትክ ክልከላዎቹን/ሳንሱሩን የሚያደርጉ ራሳቸውን የቻሉ ድርጅቶች ሊኖሩ ይችላሉ። ብዙውን ጊዜ “በጥቁር መዝገብ” (blacklist) ውስጥ የሚሰፍረው የድረ ገጹ የአይፒ አድራሻ (IPaddress) ሳይሆን የዶሜን ስሙ (domain names) ነው። የዶሜን ስም ስንል www.blogger.com እነደሚለው ማለት ነው። በአንዳንድ አገሮች ጥቅም ላይ የሚውሉ የሳንሱር/ክልከላ ሶፍትዌሮች የአንድን ድረ ገጽ የኢንተርኔት አድራሻ ከማገድ ይልቅ ጭራሹን የኢንተርኔት ግንኙነታችንን እስከመፈተሽና ማገድ የሚሔዱ ናቸው። እነዚህ ሶፍትዌሮች በኢንተርኔቱ የሰጠነውን መረጃ/ያቀረብነውን ፍለጋ እና ለፍለጋችን የሚመጣልንን መልስ በሙሉ ይፈትሻሉ፤ ከዚያም ለእገዳ የተመረጡትን ቁልፍ ቃላት ካገኙ የመጣልን የፍለጋ ውጤት እንዳይደርሰን ያግዱታል።

ነገሩን የበለጠ የከፋ የሚያደርገው፣ አንድ ድረ ገጽ መታገዱን/ሳንሱር መደረጉን (blocked) እንኳን ላናውቅ የምንችልበት አጋጣሚ መኖሩ ነው። አንዳንድ እገዳዎች ድረ ገጹ መታገዱን እና አልፎ አልፎም የታገደበትን ምክንያት ይገልጻሉ። ሌሎቹ ግን ሆን ብለው የተሳሳት መልስ ይሰጣሉ። መልሶቹ ድረ ገጹ ሊገኝ እንዳልቻለ የሚያስመሰሉ ናቸው፤ ለምሳሌ አደራሻው በትክክል እንዳልተጻፈ ሊገልጹ ይችላሉ።

በአጠቃላይ በየአገሩ ጥቅም ላይ የሚውለውን የእገዳ ሶፍትዌር ጥንካሬ እና ድክመት ለማጥናት ከመሞከር ይልቅ እጅግ የከፋውን የእገዳ ስልት ከግምት በማስገባት ለእኛ የሚያስፈልገንን የመፍትሔ አማራጭ መውሰድ ይቀላል። በሌላ አነጋገር፣ የሚከተሉት ክልከላዎች እንደተደረጉብን ቆጥረን መነሣት እንችላልን፤

ብዙዎቹ ውጤታማ የእገዳ ማለፊያ ሰርከምቬንሽን መሣሪያዎች የትኛውም አይነት የእገዳ ዘዴ ጥቅም ላይ ቢውል የሚሠሩ ናቸው። ስለዚህም እጅግ የከፋው ክልከላ እንደተደረገ አድረጎ ማሰቡ አይጎዳንም።

:Snippet

የሳንሱር ሰርከምቬንን መረዳት

አንድ ድረ ገጽ በጠቀስናቸው ዘዴዎች በመታገዱ የተነሣ በቀጥታ ልንጎበኘው ካልቻልን ክልከላውን የምናልፍበትን መንገድ መፈለግ አለብን። አስተማማኝ ፕሮክሲ (proxy) ሰርቨር፣ ኢንተርኔትን በማያግድ አገር የሚቀመጥ ሲሆን እኛ ልናገኘው ያልቻልነውን ድረ ገጽ ፈልጎ በማግኘት ያሳየናል/ይከፍትልናል። ከእነዚህ ፕሮክሲ ሰርቨሮች ጋራ ስንገናኝ እኛ የምንጠቀምበት አይኤስፒ (የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢያ) ከአንድ በኢንተርኔት ውስጥ ከሚገኝ “የማይታወቅ ኮምፒውተር” (ማለትም ፕሮክሲ (proxy) ሰርቨሩ) ጋራ ደኅንነቱ የተጠበቀ ግንኙነት ማድረጋችንን እንጂ ሌላ የሚያውቀው ነገር አይኖረውም።

በእርግጥ የኢንተርኔት ሳንሱሩን የሚያካሒደው የመንግሥት ተቋም ወይም ለእገዳ ሶፍትዌሩ መረጃዎችን የሚያቀብለው ኩባንያ በመጨረሻ ይህ “የማይታወቅ ኮምፒውተር” የሰርከምቬንሽን ፕሮክሲ (proxy) እንደሆነ ማወቃቸው አይቀር ይሆናል። ከዚህ በኋላ የፕሮክሲው አይፒ አድራሻ (IPaddress) ራሱ በጥቁር መዝገብ (blacklist) ውስጥ ስለሚገባ ይታገዳል። ፕሮክሲዎች (proxies) ታውቀው እስኪታገዱ ድረስ የተወሰነ ጊዜ መኖሩ ግን አይቀርም። የሰርከምቬንሽን መሣሪያዎችን የሚፈጥሩ እና የሚያሻሽሉ ሰዎች ይህንን ሐቅ ያውቁታል፤ ስለዚህም ከሚከተሉት ሁለት መንገዶች አንዱን ወይም ሁለቱንም ይከተላሉ፤

 • ስውር ፕሮክሲዎች (Hidden proxies) ለመገኘት/ለመታወቅ በጣም አስቸጋሪ ናቸው። በቀላሉ የማይታዩ ደኅንነታቸው የተጠበቀ ፕሮክሲዎችን (proxies) መጠቀም የሚያስፈልገው ለዚህ ነው። ኢንክሪፕሽን (Encryption) የመፍትሔው አንድ አካል እንጂ ብቸኛ ቁልፍ አይደለም። ፕሮክሲ (proxy) ሰርቨሮችን የሚያንቀሳቅሱ ሰዎች ለአዳዲስ ተጠቃሚዎች የፕሮክሲውን አድራሻ ሲሰጡ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል።

 • የሚለወጡ ፕሮክሲዎች (Disposable proxies) እነዚህ እገዳ እንደተጣለባቸው ወዲያውኑ በሌላ የሚተኩ ናቸው። ነገር ግን ተገልጋዮች አዲሶቹን/ተተኪዎቹን ፕሮክሲዎች (proxies) እንዲያውቋቸው ለመንገር የሚኬድበት መንገድ ምሥጢራዊነቱን ለመጠበቅ የማያስተማምን ሊሆን ይችላል። ስለዚህም ይህን መሰል የሰርከምቬንሽን መሣሪያዎች ፕሮክሲዎች (proxies) ታግደው ሊያልቁ ከሚችሉበት ፍጥነት በበለጠ ፍጥነት አዳዲስ ፕሮክሲዎችን እየፈጠሩ ማሰራጨት ተመራጭ አካሔድ ሆኖ የሚሠራበት ጊዜ አለ።

ለማንኛውም አንድ የምናምነው ፕሮክሲ (proxy) ማግኘት እስከቻልን ድረስ አስፈላጊውን የኢንተርኔት አፕሊኬሽን እየተጠቀምን የምንፈልገውን ነገር መጠየቅ እና የሚያመጣልንን ምላሽ መመልከት ነው። በተለምዶ ለዚህ የሚያስፈልጉትን ውስጣዊ አሠራሮች አስቀድመን የምንጭነው የሰርከምቬንሽን ሶፍትዌር ራሱ ያስተካክላቸዋል። ሶፍትዌሩ የኢንተርኔት ማሰሻውን አሠራር በማስተካከል ወይም ማሰሻውን በዌብ ላይ የተመሠረተ ፕሮክሲ (proxy) በማድረግ ነገሩን ያቀልልናል። ወደፊት የምንመለከተው ቶር (Tor) የተባለው ማንነትን የመሰወሪያ መረብ (anonymity network) የመጀመሪያውን መንገድ (ማለትም ስውር ፕሮክሲዎች (Hidden proxies)) ይጠቀማል። ከዚያ በማስከተል መሠረታዊ ነጠላ የፕሮክሲ (proxy) ሰርከምቬንሽን መሣሪያዎችን እንመለከታለን።

የማንነት መሰወሪያ መረቦች እና መሠረታዊ ፕሮክሲ ሰርቨሮች

የማንነት መሰወሪያ መረቦች

የማንነት መሰወሪያ መረቦች የኢንተርኔት ትራፊካችንን ወደ ተለያዩ ፕሮክሲዎች (proxies) ያስተላልፉታል ('bounce')፤ ይህንንም የሚያደርጉት የእኛን ማንነት፣ ምን እንደምንፈልግ እና የት እንደሆንን እንዳይታወቅ ለማድረግ ነው። ይህ በአንጻሩ አንድን ድረ ገጽ ለመክፈት ወይም አገልግሎት ለማግኘት የሚወስደውን ጊዜ ያረዝመዋል። ይሁንና ቶር (Tor) የምንመካበት፣ አስተማማኝ እና ለሕዝብ ክፍት የሆነ የሰርከምቬንሽን አገልግሎት ይሰጠናል፤ ይህም የምንጠቀምባቸውን ፕሮክሲዎች (proxies) የሚያስተዳድረው ሰው/ድርጅት አስተማማኝነት ምን ያህል እንደሆነ ለማወቅ ከመጨነቅ ያድነናል። እንደምንግዜውም፣ ስሱ መረጃዎችን ከማስገባታችን/ከመጻፋችን በፊት “HTTPS”ን በመጠቀም ግንኙነታችንን ኢንክሪፕት ማድረግ ይኖርብናል።

ቶርን (Tor) ለመጠቀም ሶፍትዌሩን መጫን አለብን፤ በውጤቱ ግን ማንነታችንን የሚሰውር እና እገዳዎችን በማለፍ የኢንተርኔት ድረ ገጾችን/አገልግሎቶችን ለማግኘት የሚያስችለን መሣሪያ ባለቤቶች እንሆናለን። ከዚያ በኋላ ከቶር (Tor) መረብ ጋራ በተገናኘን ቁጥር በቀጥታ በሦስት የቶር (Tor) አስተማማኝ ፕሮክሲዎች (proxies) በኩል እናልፋለን። ይህም የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢያችንም (አይኤስፒ/ISP) ሆነ የምናልፍባቸው ፕሮክሲዎች (proxies) የኮምፒውተራችንን የአይፒ አድራሻ (IPaddress) እንዲሁም የኢንተርኔት አገልግሎት ያገኘንበትን ቦታ እንዳያውቁት ያደርግልናል። የተብራራ መረጃ ለማግኘት የቶርን መመሪያ መመልከት ይጠቅማል።

አጠቃቀም! ቶር - የዲጂታል ስወራ እና የሰርከምቬንሽን መመሪያ (Tor - Digital Anonymity and Circumvention Guide)

የቶር አንዱ ጥንካሬ ከማንኛውም የኢንተርኔት ማሰሻ (browser) የሚሠራ መሆኑ ብቻ አይደለም፤ ከተለያዩ የኢንተርኔት ሶፍትዌር አይነቶች ጋራም ያለችግር ይሠራል። ሞዚላ (Mozilla) ተንደርበርድ (Thunderbird) እና ፒድጂንን (Pidgin) የመሳሰሉ የፈጣን መልእክት ፕሮግራሞችም የተከለከሉ አገልግሎቶችን ለማግኘትም ይሁን ማንነትን ለመሰወር በቶር በኩል ያለችግር ይሠራሉ።

መሠረታዊ የሰርከምቬንሽን ፕሮክሲዎች

አንድን የሰርከምቬንሽን ፕሮክሲ (proxy) ከመምረጣችን በፊት ከግምት ልናስገባቸው የሚገቡ ሦስት ጥያቄዎች አሉ። የመጀመሪያው ጥያቄ ፕሮክሲው ዌብን መሠረት ያደረገ (web-based) ወይም አሠራሮችን እንድንቀይር (change settings) አለዚያም ለኮምፒውተራችን አዲስ ሶፍትዌር እንድንጭን የሚጠይቀን መሆኑን ይመለከታል። ሁለተኛው ጉዳይ ደግሞ ምስጢራዊነቱን የማረጋገጥ ጥያቄ ነው። ሦስተኛው “መሣሪያው በግለሰብ ደረጃ የተወሰነ ነው ወይስ ለሁሉም ክፍት የሆነ ነው (private or public)?” የሚል ነው።

ዌብን መሠረት ያደረጉ እና ሌሎቹ ፕሮክሲዎች

ዌብን መሠረት ያደረጉ (Web-based) ፕሮክሲዎች (proxies) ለአጠቃቀም የቀለሉ ናቸው። ተጠቃሚዎች የሚጠበቅብን የፕሮክሲውን (proxy) ድረ ገጽ አግኝቶ የታገደውንና ልንከፍተው የምንፈልገውን አድራሻ ማስገባት ብቻ ነው። ፕሮክሲው (proxy) የጠየቅነውን ገጽ በራሱ ገጽ ውስጥ ይከፍትልናል። ሌላ ገጽ ማየት ከፈለግን በፕሮክሲው (proxy) ውስጥ የምናገኘውን “ሊንክ” መከተል አለዚያም አዲስ አድራሻ መስጠት ይበቃናል። አዲስ ሶፍትዌር መጫን ወይም የኢንተርኔት ማሰሻችንን አሠራር (browser settings) መቀየር አያስፈልገንም። በአጭሩ ዌብን መሠረት ያደረጉ (Web-based) ፕሮክሲዎች (proxies)

 • ለአጠቃቀም ቀላል ናቸው
 • ኢንተርኔት ካፌን ከመሳሰሉና አዳዲስ ፕሮግራሞችን መጫንም ሆነ አሠራሮችን መቀየር በማይፈቀድባቸው ቦታዎች ከሚገኙ ሕዝብ
  ከሚጠቀምባቸው ኮምፒውተሮች ጭምር ሊገኙ ይችላሉ
 • በኮምፒውተራችን ላይ የሰርከምቬንስን ሶፍትዌር ኖሮ “መያዝ/መታየት” ለማይፈልጉ ሰዎች የተሻሉ አማራጮች ናቸው።

ሆኖም ዌብን መሠረት ያደረጉ (Web-based) ፕሮክሲዎች (proxies) አንዳንድ ድክመቶች እንዳሉባቸው የታወቀ ነው። የጠየቅናቸውን ገጾችን ሁልጊዜም በትክክል ላይከፍቱ ይችላሉ፤ ብዙዎቹ ዌብን መሠረት ያደረጉ (Web-based) ፕሮክሲዎች (proxies) የድምጽና የቪዲዮ አገልግሎቶችን ያዘሉ ድረ ገጾችን ወይም መሰል ውስብስብ ድረገጾችን መክፈት ያስቸግራቸዋል። ማንኛውም ፕሮክሲ (proxy) የኢንተርኔት ግንኙነት ፍጥነትን ሊያዘገይ ይችላል፤ ለሕዝብ ክፍት ወደ ሆኑ ዌብን መሠረት ያደረጉ (Web-based) ፕሮክሲዎች (proxies) ስንመጣም የበለጠ መዘግየት/መንቀራፈፍ ሊኖር ይችላል። ዌብን መሠረት ያደረጉ (Web-based) ፕሮክሲዎች (proxies) የሚሠሩት ወይም የሚያገለግሉት ለድረ ገጾች (web pages) ብቻ ነው። ለምሳሌ ያህል ዌብን መሠረት ባደረጉ (Web-based) ፕሮክሲዎች (proxies) የፈጣን መልእክት ፕሮግራሞችን መጠቀም ወይም በኢሜይል የተከለከለ የኢንተርኔት አገልግሎት ማግኘት አንችልም። በተጨማሪም ዌብን መሠረት ያደረጉ (Web-based) ፕሮክሲዎች (proxies) ምሥጢራዊነትም ውሱን ነው፤ ምክንያቱም ፕሮክሲዎቹ ራሳቸው ወደ እኛ የሚደርሰውን መረጃ ለማግኘትና ለማስተካከል ለመጎብኘት ወደምንፈልገው ድረ ገጽ መሔድ ስላለባቸው ነው። እነርሱ ይህን ካላደረጉ ከፕሮክሲ (proxy) ሳንወጣ ልንከፍት የምንፈልገውን ድረ ገጽ ሊንክ መንካት/ መጫን አንችልም። ይህ በቀጣዩ ክፍል ይብራራል።

ሌላኛው አይነት ፕሮክሲዎች (proxies) በአጠቃላይ አዲስ ፕሮግራም እንድንጭን ወይም በኢንተርኔት ማሰሻ ወይንም በኦፕሬቲንግ ሲስተማችን ውጫዊ ፕሮክሲ (proxy) እንድንጠቀም ግድ ይሉናል። በመጀመሪያው አሠራር የሰርከምቬንሽን ፕሮግራሙን ማጥፋትና ማብራት ይቻላል፤ ፕሮክሲውን (proxy) መጠቀም ይኑርብን ወይም አይኑርብን ይነግረናል። እንዲህ አይነት ሶፍትዌሮች አንዱ ፕሮክሲ (proxy) ሲዘጋ በቀጥታ/ወዲያውኑ በሌላ መተካትን ይፈቅዱልናል። በኢንተርኔት ማሰሻ ወይንም በኦፕሬቲንግ ሲስተማችን ውስጥ ውጫዊ ፕሮክሲ (proxy) እንድናስገባ የሚጠይቀን ከሆነ የፕሮክሲውን (proxy) ትክክለኛ አድራሻ ማወቅ ይኖርብናል። ፕሮክሲው (proxy) ታግዶ ወይም እጅግ ቀርፋፋ ሆኖ ከተገኘ የምናውቀው አድራሻ ተቀይሮ ሊጠብቀን ይችላል።

በአጠቃቀሙ ረገድ ዌብን መሠረት ካደረገ (Web-based) ፕሮክሲ (proxy) ይልቅ በመጠኑ የሚከብድ ቢመስልም ይህ የሰርከምቬንሽን ዘዴ ውስብስብ ድረ ገጾችን በትክክል ለመክፈት ይችላል፤ በፍጥነቱም ቢሆን እጅግ ብዙ ሰዎች ፕሮክሲ (proxy) ሰርቨሩን አውቀውት እስኪጠቀሙበት አይዘገይም። በተጨማሪም ለተለያዩ የኢንተርኔት አፕሊኬሽኖች የሚሆኑ ፕሮክሲዎች (proxies) ይገኛሉ። ለምሳሌ ለኢንተርኔት ማሰሻዎች የ“HTTP” ፕሮክሲዎች (proxies)፣ ለኢሜይል እና ለቻት ፕሮግራሞች የሚሆኑ የ“SOCKS” ፕሮክሲዎች (proxies)፣ እንዲሁም “የቪፒኤን (VPN)” ፕሮክሲዎች (proxies) ይገኛሉ። እነዚህ ፕሮክሲዎች የኢንተርኔት ትራፊካችንን አቅጣጫ በማስቀየር (redirect) እንዳይመረመር/እንዳይታገድ (filter) ይከላከላሉ።

የሚያስተማምኑ እና የማያስተማምኑ ፕሮክሲዎ

ለተገልጋዮቹ ኢንክሪፕት የማድረግ (encrypted) ሥራ የሚያከናውን ማንኛውም ፕሮክሲ (proxy) የሚያስተማምን ፕሮክሲ (proxy) እንለዋለን። የማያስተማምን ፕሮክሲ (proxy) የምንለው የተለያዩ አይነት እገዳዎችን (filtering) እንድናልፍ የሚያስችለን፤ ነገር ግን የኢንተርኔት ግንኙነታችን ቁልፍ ቃላትን እና የድረ ገጽ አድራሻዎችን እየፈተሸ የሚያሳልፍ አሠራር ከገጠመው የማይሠራ ወይም የማያገለግለን ፕሮክሲ ነው። በዚህ አስተማማኝ ባልሆነ ፕሮክሲ (proxy) ኢንክሪፕትድ የሆኑ የኢሜይል አድራሻዎችን እና የባንክ አካውንቶችን መክፈት ለጉዳት ሊዳርገን ይችላል። ስሱ እና በድብቅ ልንይዛቸው የሚገቡ መረጃዎችንም ሊያጋልጥብን ይችላል። ቀደም ሲል እንዳነሣነው፣ አስተማማኝ ያልሆኑ ፕሮክሲዎች (proxies) የኢንተርኔት ሳንሱር ሶፍትዌሮችን ለሚሠሩና ለሚያሻሽሉ፣ እንዲሁም እገዳ ለሚያደርጉ አካሎች በጣም ቀላል ናቸው። ነጻ፣ ፈጣን እና አስተማማኝ ፕሮክሲዎች (proxies) መኖራቸው እነዚህን የማስተማምኑትን የምንጠቀምበት ምክንያት እንዳይኖር/እንዲቀንስ አድርጓል።

ዌብን መሠረት ያደረገ ፕሮክሲ (proxy) አስተማማኝ መሆኑን የምናውቅበት አንዱ መንገድ ራሱን ፕሮክሲውን (proxy) በኤችቲቲፒኤስ (HTTPS) አድራሻ መክፈት ከቻልን ነው። የዌብሜይል አገልግሎቶች ደኅንነቱ የተጠበቀ ወይም ያልተጠበቀ (secure and insecure) ግንኙነትን ሊፈቅዱ ይችላሉ፤ ስለዚህ ግንኙነታችን ደኅንነቱ በተጠበቀ አድራሻ በኩል መፈጠሩን ማረጋገጥ ይኖርብናል። በዚህ መሰሉ ሁኔታ ከኢንተርኔት ማሰሻው (browser) ‘የደኅንነት ሰርተፊኬት ማስጠንቀቂያ’ ('security certificate warning') ማግኘት ይኖርብናል። ቀጥሎ የምንመለከታቸው ሳይፎን (Psiphon) እና ፒስፋየር (Peacefire) የተባሉት ፕሮክሲዎች (proxies) ይህንኑ አሠራር ይከተላሉ። እነዚህ ማስጠንቀቂያዎች የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢያችን (አይኤስፒ) ወይም ሐከሮች በፕሮክሲ (proxy) በኩል የምናደርገውን ግንኙነት እየሰለሉ መሆናቸውን ይነግሩናል። ይህም ቢሆን ግን በሚቻል ጊዜ ሁሉ ደኅንነታቸው የተጠበቁ ፕሮክሲዎችን (proxies) መጠቀም የሚመረጥ ነው። ነገር ግን ፕሮክሲዎችን (proxies) ለሰርከምቬንሽን በምንጠቀም ጊዜ፣ የይለፍ ቃሎችን እና ሌሎች ስሱ መረጃዎችን ከማስገባታችን ወይም በምሥጢር መጠበቅ ያለባቸውን ድረ ገጾች ከመክፈታችን በፊት የፕሮክሲውን (proxy) ኤስኤስኤል (SSL) አሻራ ትክክለኛነት ማረጋገጥ አለብን። ይህን ለማረጋገጥ ከፕሮክሲው (proxy) አስተዳዳሪ ጋራ ግንኙነት መፍጠር የሚያስፈልግበት ጊዜ ሊኖር ይችላል።

የሚያስተዳድረውን አካል እስካላወቅነው ድረስ ዌብን መሠረት ባደረገ ፕሮክሲ (proxy) ስሱ መረጃዎቸን መቀበል/መጎብኘት አይኖርብንም። ይህ ጥንቃቄ የፕሮክሲውን (proxy) “የደኅንነት ሰርተፊኬት ማስጠንቀቂያ” ብናገኝ እንኳን የሚተው አይደለም። የፕሮክሲውን (proxy) ባለቤት ብናውቀውና ማሰሻችን ማስጠንቀቂያውን እንዲቀበል ሳናዝዘው የየሰርቨሩን የጣት አሻራ (fingerprint) ለማረጋገጥ ብንችል እንኳን ጥንቃቄው መቅረት የለበትም። ለሰርከምቬንሽን በአንድ ነጠላ ፕሮክሲ (proxy) ብቻ የምንጠቀም ከሆነ፣ የፕሮክሲው አስተዳዳሪ የኮምፒውተራችንን የአይፒ አድራሻ (IPaddress) እና የምንጎበኛቸውን ድረ ገጾች ሊያውቅ ይችላል። ይህ ፕሮክሲ (proxy) በዌብ ላይ የተመሠረተ ከሆነና አስተዳዳሪው ለተንኮል የተዘጋጀ ከሆነ፣ በእኛ እና በምንከፍታቸው ድረ ገጾች መካከል የሚኖረውን የመረጃ ልውውጥ፣ የኢሜይል መልእክቶቻችንን እና የይለፍ ቃሎቻችንን ሳይቀር ሊያገኝብን ይችላል። በዌብ ላይ ያልተመሠረቱ ፕሮክሲዎች (proxies) ግንኙነት ደኅንነቱ የተጠበቀ መሆኑን ወይም አለመሆኑን ለማረጋገጥ ጥቂት ምርመራ ማድረግ በቂ ነው። በዚህ ምእራፍ በይሁንታ የምንጠቅሳቸው ፕሮክሲዎች (proxies) እና የማንነት ስወራ መረቦች (anonymity networks) በሙሉ ደኅንነታቸው የተጠበቀ ናቸው።

የግል እና የሕዝብ ፕሮክሲዎች

የሕዝብ ፕሮክሲዎች (proxies) ከማንኛውም ሰው የሚመጣላቸውን የግንኙነት ጥያቄ ያስተናግዳሉ፤ የግል የምንላቸው ፕሮክሲዎች (proxies) ግን የተጠቃሚ ስም እና የይልፍ ቃል ይጠይቃሉ። የሕዝብ ፕሮክሲዎች (proxies) ለሁሉም በነጻነት የሚገኙ መሆናቸው የሚያስመርጣቸው ቢሆንም በአጭር ጊዜ ውስጥ በተጠቃሚዎች የመጣበብ አዝማሚያ ያሳያሉ። በዚህም ምክንያት የሕዝብ ፕሮክሲዎች (proxies) በቴክኒካዊ ብቃታቸው ከግሎቹ ያነሱ ባይሆኑም በአንጻራዊነት ቀርፋ ይሆናሉ። የግል ፕሮክሲዎች (proxies) ለትርፍ በተቋቋሙ ድርጅቶች ይተዳደራሉ፤ ይህ ካልሆነ ደግሞ በግልም ይሁን በማኅበራዊ አጋጣሚዎች ለሚያውቃቸው ሰዎች አካውንቶችን በሚፈጥሩ አስተዳዳሪዎች ይሰጣሉ። ስለዚህም የግል ፕሮክሲዎች (proxies) ባለቤቶችን ዓላማ እና ፍላጎት መረዳት ቀላል ነው። ሆኖም የግል ፕሮክሲዎች (proxies) በመሠረቱ የበለጠ አስተማማኝ ናቸው ብለን ማሰብ የለብንም። ከዚህ ቀደም ለትርፍ ተየቋቋሙ የኦንላይ አገልግሎት ድርጅቶች የተጠቃሚዎቻቸውን መረጃዎች አሳልፈው የሰጡበት አጋጣሚ እንደነበር አይረሳም።

ደኅንነታቸው የማያስተማምኑ የሕዝብ ፕሮክሲዎች (proxies) ፈልጎ ለማግኘት ቀላል ናቸው፤ 'public proxy' የመሳሰሉትን ሐረጎች በመፈለጊያ ገጾች/ኤንጂን (search engine) ውስጥ ብናስገባ በርካታ ፕሮክሲዎች ይገኛሉ። በዚህ መንገድ በሚገኙ ፕሮክሲዎች (proxies) ፈጽሞ መተማመን የለብንም። አማራጩ ካለ በምናውቃቸው፣ በምናምናቸው እና ሰርቨራቸውን ለመጠበቅ የሚያስችል በቂ ቴክኒካዊ አቅም ባላቸው ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች በሚተዳደሩ አስተማማኝ የግል ፕሮክሲዎችን (proxies) መጠቀም የተሻለ ነው። የምንጠቀምበት ፕሮክሲ (proxy) በዌብ ላይ የተመሠረተ ይሁን ወይም አይሁን የሚለውን የሚወስነው የየግላችን ሁኔታ እና ምርጫ ነው። ማንኛውንም ፕሮክሲ (proxy) ለሰርከምቬንሽን በምንጠቀም ጊዜ ሁሉ በፋየርፎክስ Firefox ማሰሻ መጠቀም እና ለማሰሻው ኖስክሪፕት (NoScript) የተባለውን አጋዥ መጫን በጣም አስፈላጊ ነው። (ለበለጠ መረጃ የፋየርፎክስን መመሪያ (Firefox Guide) መመልከት ነው።) ይህ አካሔድ ከአጭበርባሪ ፕሮክሲዎች (proxies) እና እውነተኛ የአይፒ አድራሻችንን (IPaddress) ለማግኘት ከሚሞክሩ ድረ ገጾች ይጠብቀናል። ኢንክሪፕት የተደረገ (encrypted) ፕሮክሲ (proxy) ብንጠቀም እንኳን ደኅንነቱ ያልተጠበቀ፣ የማያስተማምን ድረ ገጽን አስተማማኝ እንደማያደርጉት ግን መርሳት የለብንም። ስሱ መረጃዎችን ከመላካችንም ሆነ ከመቀበላችን በፊት ግንኙነታችን በHTTPS የተደረገ መሆኑን ማረጋገጥ አለብን።

ባለንበት አገር አስተማማኝ የፕሮክሲ (proxy) አገልግሎት የሚሰጥ ግለሰብ ወይም ተቋም ካላገኘን ቀደም ሲል የተነጋገርንበትን የቶር የማንነት መሰወሪያ መረቦች መጠቀም እንችላለን።

ልዩ የሰርከምቬንሽን ፕሮክሲዎች

ከዚህ ቀጥሎ የኢንተርኔት እገዳን ለማለፍ (ሰርከምቬንት ለማድረግ) የሚረዱ ጥቂት መሣሪያዎችን እና ፕሮክሲዎችን (proxies) እንመለከታለን። አዳዲስ የሰርከምቬንሽን መሣሪያዎች በየጊዜው ይፈጠራሉ፤ የነበሩትም ቶሎ ቶሎ ይሻሻላሉ። ስለዚህ በዚሁ ምእራፍ የተጨማሪ ንባብ ክፍል የተጠቀሰውን የኢንተርኔት ደኅንነት መጽሐፍ (Security in-a-Box) ድረ ገጽ አዘውትረን መጎብኘት ይኖርብናል።

ሳይፎን2 (Psiphon2) ማንነትን የሚሰውር የግል የዌብ ፕሮክሲ ሰርቨር ነው። ሳይፎን2ን (psiphon2) ለመጠቀም የድረ ገጹ ትክክለኛ አድራሻ፣ እንዲሁም የተጠቃሚ ስም ከይለፍ ቃሉ ጋራ ያስፈልገናል። ይህን አድራሻ/አካውንት ለመክፈት የሳይፎን2 (psiphon2) ተጠቃሚ የሆነ ሰው ሊጋብዘን ይችላል፤ ወይም የዚህ መጽሐፍ የሕትመት/ወረቀት ቅጂ ውስጥ የሚገኘውን የግብዣ ኮድ መጠቀም ይቻላል። የሳይፎን ተጠቀሚዎች መመሪያ (Psiphon User's Guide) ተጨማሪ መረጃ ይሰጣል።

ሲሶው ሆትስፖት ሺልድ (Sesawe Hotspot Shield) ለሕዝብ ክፍት የሆነ፣ በዌብ ላይ ያልተመሠረተ፣ አስተማማኝ የሰርከምቬንሽን ፕሮክሲ ነው። ሲሶውን ለመጠቀም መጀመሪያ መሣሪያውንዳውንሎድ ማድረግ (download the tool) እና ከዚያም መጫን ያስፈልጋል። “ሆትስፖት ሺልድን” የፈጠረው ኩባንያ ገቢውን ከማስታወቂያ ያገኛል። ስለዚህም በማሰሻው ኢንክሪፕሽን (encryption) የሌላቸውን ድረ ገጾች በጎበኘን ቁጥር በአናቱ ላይ ማስታወቂያ ("banner ad") እናያለን። በገለልተኛ ወገን ማረጋገጥ ባይቻልም፣ ኩባንያው የተጠቃሚዎቹን የአይፒ አድራሻ (IPaddress) ያጠፋዋል፤ ይህም ማለት በማጠራቀም ወይም ማስታወቂያ ለሚሰጡት ድርጅቶች በማስተላለፍ ፋንታ ፈጽሞ ያጠፋዋል ማለት ነው። ሆትስፖት ሺልድ (Hotspot Shield) በቨርቹዋል ፕራይቬት ኔትወርክ (Virtual Private Network -VPN) የሚሠራ በመሆኑ የኢንተርኔት ግንኙነታችን በሙሉ የሚያልፈው በፕሮክሲው በኩል ይሆናል፤ “አየር ላይ” ("connected") እስካለን ድረስም ይኸው ይቀጥላል። በአገራችን የምንጠቀምበት የኢሜይል እና የፈጣን መልእክት ግንኙነት አገልግሎት ሰጪዎች የሚታገዱ/የሚመረመሩ (filtered) ከሆነ ይህ መሣሪያ በጣም ይጠቅመናል። ስለሆትስፖት ሺልድ ከAnchorFree website የበለጠ መረዳት እንችላለን።

ዩር-ፍሪደም (Your-Freedom) ደኅንነቱ የተረጋገጠ፣ በዌብ ላይ ያልተመሠረተ፣ የግል የሰርከምቬንሽን ፕሮክሲ (proxy) ነው። ነጻ የሰርከምቬንሽን አገልግሎት ለማግኘት የሚያስችል ነጻ-ሶፍትዌር (freeware) መሣሪያ ነው። የተሻለ ፍጥነት ያለውን፣ ውሱንነቶቹ አነስተኛ የሆነውን በክፍያ የሚገኘውን አግልግሎቱንም መግዛት እንችላለን። ዩር-ፍሪደምን (Your-Freedom) ለመጠቀም መሣሪያውን ዳውንሎድ ማድረግ እና አካውንት/አድራሻ መክፈት ይጠበቅብናል። ሁለቱንም በቀላሉ ወደ ዩር-ፍሪደም (Your-Freedom) ድረ ገጽ በመሔድ ማከናወን ይቻላል። ከዚያ በማስከተል ከኢንተርኔት ጋራ ስንገናኝ ፕሮክሲውን ለመጠቀም እንችል ዘንድ የኢንተርኔት ማሰሻችንን ማስተካከል አለብን። ይህን እንዴት ማድረግ እንደሚቻል ከሲሶው ፕሮጀክት ድረ ገጽ (Sesawe Project) መረዳት እንችላለን።

ፒስፋየር (Peacefire) ብዛት ያላቸውን በዌብ ላይ የተመሠረቱ የሕዝብ ፕሮክሲዎችን (proxies) ይዟል። ፕሮክሲዎቹን ለማግኘት እንደምንጠቀምበት መንገድ ፕሮክሲዎቹ ደኅንነታቸው የተጠበቀ ሊሆንም ላይሆንም ይችላል። ፒስፋየር (Peacefire) ፕሮክሲ (proxy) ስንጠቀም፣ በእኛ እና በፕሮክሲው (proxy) መካከል የሚፈጠረው ግንኙነት ደኅንነቱ የተረጋገጠ እንዲሆን በአድራሻ መጻፊያው ላይ ኤችቲቲፒኤስ (HTTPS) አድራሻ ማስገባት ይኖርብናል። አዳዲስ ፕሮክሲዎችን (proxies) ተገልጋዮች በየጊዜው በኢሜይል እንዲያውቋቸው ይደረጋል። እያንዳንዳችንም በፒስፋየር ድረ ገጽ (Peacefirewebsite) በመመዝገብ ዜናዎችን/መረጃዎችን ማግኘት እንችላለን።

:Snippet

ተጨማሪ ንባብ