አቫስት! ጸረ ቫይረስ

Updated24 November 2014

መመሪያው በወቅቱ አልተሻሻለም፤ በቅርቡ ይሰረዛል

አቫስት! ማልዌርን እና ቫይረሶችን በኮምፒውተራችን ውስጥ ፈልጎ የሚያገኝና የሚያስወግድ የተሟላ አገልግሎት የሚሰጥ ጸረ ቫይረስ ፕሮግራም ነው። አቫስት! ለቤት ውስጥ እና ለግል አገልግሎት በነጻ የሚገኝ ነው፤ ሆኖም ይህ ነጻ አገልግሎት ለማግኘት ፕሮግራሙን ከጫንን በኋላ መመዝገብ ይኖርብናል። ካልተመዘገብን ግን አገልግሎቱ በ30 ቀናት ውስጥ ይቆማል። የተመዘገቡ ተጠቃሚዎች ከዚህም ሌላ የአቫስትን! የተሻሻሉ የፕሮግራም አይነቴዎችን (versions)፣ እንዲሁም የቫይረስ መከታተያ መረጃዎችን በየጊዜው በነጻ ማግኘት ይችላሉ።

ዋናው ገጽ/ Homepage፡

www.avast.com

ከኮምፒውተሩ ምን ይፈለጋል?

 • ሁሉም የዊንዶውስ አይነቴዎች ይሠራሉ

ለዚህ መመሪያ የተወሰደው አይነቴ/ቨርዥን

 • 5.0

ፈቃድ/ላይሰንስ

 • ነጻ ሶፍትዌር (Freeware)

አስፈላጊ ንባብ

ይህን መሣሪያ መጠቀም ለመጀመር የሚፈጀው ጊዜ ፤ 20 ደቂቃ

ምን ጥቅም እናገኛለን

 • በኮምፒውተራችን ውስጥ የሚገኙ ቫይረሶችን የማደን (scan) እና የማስወገድ ክህሎትን እናገኛለን
 • ኮምፒውተራችን በአዲስ ቫይረሶች እንዳይበከል/እንዳይጠቃ መከላከል እንችላለን
 • አዳዲስ የፕሮግራም አይነቴዎችን እና የቫይረስ መለያዎችን በየጊዜው ከኢንተርኔት ማግኘት እንችላለን

ከጂኤንዩ ሊኑክስ፣ ከማክ ኦኤስ እና ከሌሎች ማይክሮሶፍት ዊንዶውስ ጋራ ሊሠሩ የሚችሉ ፕሮግራሞች

ምንም እንኳን በዚህ ምእራፍ አቫስት! ነጻ ጸረ ቫይረስን እንድንጠቀም ብንመከረም ከማይክሮሶፍት ዊንዶውስ ጋራ ሊሠሩ የሚችሉ ሌሎችም ነጻ ጸረ ማልዌሮች መኖራቸውን ማስታወስ ይገባል፤ ጥቂቶቹንም እዚህ መጥቀስ ይቻላል፦

ለማይክሮሶፍት ዊንዶውስ የሚዘጋጁ በግዢ ብቻ የሚገኙ ጸረ ቫይረስ ሶፍትዌሮች ገዝተው መጠቀም ለሚችሉ የበለጠ የተሟላ ጥበቃ ሊሰጡ ይችላሉ።

ምንም እንኳን ጂኤንዩ ሊኑክስ እና ማክ ኦኤስን የመሳሰሉት ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች ከሞላ ጎደል ከቫይረስ የጸዱ እንዲሆኑ ተደርገው የተሠሩ ቢሆኑም ጸረ ማልዌር ፕሮግራሞችን እንድንጭንባቸው የሚያስገድዱ ምክንያቶች አሉ። በቅድሚያ፣ እነዚህን ኦፐሬቲንግ ሲስተሞች ሊበክሉ የሚችሉ ቫይረሶች መፈጠራቸው አይቀርም፤ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ የእኛ ኦፐሬቲንግ ሲሰተም ለጉዳት ባያጋልጡም ባለማወቅ ቫይረሶችን ወደሌሎች ልናሰራጭ እንችላለን።

በአሁኑ ወቅት “ለሊኑክስ” እና “ለማክ” ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ ብለን በመተማመን ልንጠቅሳቸው የምንችላቸው በነጻ የሚገኙ ጸረ ቫይረስ ፕሮግራሞች የሉም። በግዢ የሚገኙ ተጨማሪ አገልግሎቶችን እና የተሻለ ጥበቃ የሚያደርጉ ጥቂት ፕሮግራሞች ግን አሉ። ከእነዚህ ገበያ ላይ ከሚገኙት መካከል በጣም የታወቁት የሚከተሉት ናቸው፤

ከእነዚህ አንዱን መግዛት የሚችሉ ገዝተው እንዲጠቀሙ ይመከራሉ።

አቫስትን መጫን/ Installing

 • የአጠቃቀም መመሪያውን አጭር መግቢያ ማንበብ
 • በዚህ ሳጥን ግርጌ የሚታየውን የአቫስት! ምልክት በመንካት የአቫስት! የሚገንበትን ድረ ገጽ መክፈት www.avast.com
 • “Free Antivirus” በሚለው ክፍል ስር የሚገኘውን “Download” የሚል ማዘዣ መንካት/ክሊክ፤ ከዚያም በቀጣዩ ገጽ የሚከፈተውን “Download Now” የሚለውን ማዘዣ መጫን/ክሊክ
 • “Save File” የሚለውን በማዘዝ/በመንካት የፕሮግራሙ መጫኛ የሆነውን “setup_av_free.exe” ወደ ኮምፒውተራችን ማምጣት፤ አስከትሎ ይህንኑ “setup_av_free.exe” በእጥፍ-ንኬት (double click) በመንካት ፕሮግራሙን መጫን (installation) እንዲጀምር ማዘዝ
 • ወደ ቀጣዩ ደረጃ ከመሔድ በፊት 2.0 አቫስትን! መጫን (Install) እና መመዝግብ የሚለውን ክፍል ማንበብ
 • አቫስትን! ጭነን ከጨረስን በኋላ የመጫና ፕሮግራሙን ከኮምፒውተራችን ልናጠፋው እንችላለን

አቫስት (avast!):

1.1 ስለመሣሪያዎቹ በቅድሚያ ማወቅ የሚገቡን ነገሮች

የኮምፒውተር ቫይረሶች ፋይሎቻችን ሊያጠፉብን፣ ኮምፒውተራችንን የመሥራት ፍጥነት ሊያዘገዩ፣ አልፎም የእኛን የአድራሻ ማውጫ በመጠቀም ሌሎች ኮምፒውተሮችን በማግኘት ለመበከል የሚችሉ አደገኛ ፕሮግራሞች ናቸው። አቫስት! ኮምፒውተራችን በተለያዩ መንገዶች በሚተላለፉ ቫይረሶች እንዳይጠቃ ይከላከልልናል። መተላለፊያው ከኢንተርኔት በምናገኛቸው፣ ከኢሜይል መልእክቶች ጋራ በአባሪነት በሚላኩ ፋይሎች፣ ወይም ከተንቀሳቃሽ የመረጃ ቋቶች (ሲዲዎች፣ ዲቪዲዎች፣ የማስታወሻ ማህደሮች/ዩኤስቢ እና የመሳሰሉት) በምናዘዋውራቸው ፋይሎች አማካይነት ሊሆን ይችላል።

 • ሁለት የተለያዩ ጸረ ቫይረሶች በተመሳሳይ ጊዜ እየሠሩ አለመሆኑን አረጋግጥ። አሁን ሌላ ፕሮግራም እየተጠቀምክ ከሆነና ወደ አቫስት!
  መዞር ከፈለክ አቫስትን! ከመጫንህ በፊት ሌላኛውን አልመጫን/ማስወገድ ይኖርብሃል።

 • በየጊዜው አዳዲስ ጸረ ማልዌሮች እና ጸረ ቫይረሶች ይፈጠራሉ። የአቫስት! ኮምፒውተርሽን በሚገባ እንዲከላከል ዳታቤዙ ምንግዜም ጊዜውን የተከተለ እንዲሆን ማድረግ አለብሽ።

 • ከሁሉም እጅግ የከፉት ቫይረሶች አቫስት! ራሱ እንዳይጫን የሚከለክሉ እና/ወይም አቫስት! ፈልጎ የማያገኛቸው ናቸው። ይህን መሰሉ ፈተና ሲገጠም በመጠኑ ረቀቅ ያሉ ዘዴዎችን መጠቀም ያስፈልጋል። ከእነዚህ ዘዴዎች የተወሰኑት በክፍል 4.9 የተራቀቁ የቫይረስ አወጋገድ መንገዶች ተብራርተዋል።

አቫስትን! መጫን እና መመዝገብ (Install and Register)

በዚህ ገጽ የሚገኙት ክፍሎች

2.0 አቫስትን! መጫን (Install)

አቫስት! መጫን (Installing) በአንጻራዊነት ቀላል እና ብዙም ጊዜ የማይፈጅ ነው። ለመጫን የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል ይበቃል፤

ደረጃ 1፤ በዚህ ምልክት የሚወከለውን መጫኛ እጥፍ-ንኬት (Double click)Open File - Security Warning የሚለው ሳጥን ይከፈታል። ይህ ሳጥን ካልመጣ/ካልተከፈተ በመንካት/ክሊክ የመጫን ሒደቱ የደረሰበትን ደረጃ የሚያሳየውን ምልክት ማምጣት እንችላለን፤ እንደኮሚፒውተራችን ፍጥነት ይህ ወደ አንድ ደቂቃ ገደማ ሊወስድ ይችላል። የአቫስት! ልዩ ልዩ ክፍሎች ያሉበት ሳጥን ከተከፈተ በኋላ አንድ የማዘዣ ሳጥን (dialog box) ይከፈታል። ሳጥኑ የሚከተለውን ይመስላል፤

ስእል 1፤ የአቫስት! መጫኛ ሰሌዳ/Installation screen

ደረጃ 2፤ ቀጣዩን የማዘዣ ሳጥን ሥራ ለማስጀመር መጫን/መንካት

ስእል 2፤ የአቫስት! የመጫኛ መዘዣ ሳጥን

አቫስት! በመጫን ላይ እያለ Participate in the avast! community የሚል አማራጭ የያዘ የአቫስት! የማዘዣ ሳጥን ይከፈታል። ቀደም ብሎ በስእል 2 እንደተመለከተው ይህን አለመቀበልና እንዳይሠራ ማድረግ ይመከራል።

ደረጃ 3Participate in the avast! community ከሚለው አማራጭ ፊትለፊት በሚገኘው ሳጥን ውስጥ ያለውን (የራይት) ምልክት ማጥፋት (Uncheck) ። በማስከተል ማዘዣ በመንካት/መጫን ቀጣዩን የማዘዣ ሳጥን ሥራ ማስጀመር፤

ስእል 3፤ የአቫስት! የይሁንታ ገጽ (recommends screen)

አቫስት!ን በመጫን ላይ ሳለን፣ ዘወትር እንደሚሆነው አቫስት! የተለያዩ አገልግሎቶችን አብረን እንድንወስድ ይጋብዘናል። እዚህ ላይም የአቫስት የማስመረጫ ሳጥን (avast! Recommends) ጉግል ክሮም የተባለውን የድረ ገጽ ማሰሻ አብረን እንድንጭን እንዲህ የሚል ግብዣ ያቀርብልናል Yes, also install the Google Chrome web browser ። ይህን ግብዣ/ይሁንታ ከላይ በስእል 3 እንደተመለከተው አለመቀበል ወይም ውድቅ ማድረግ ይመከራል።

ደረጃ 4፤ የጠቀስነውን ግብዣ ላለበቀበል No, do not install the Google Chrome web browser የሚለውን አማራጭ መምረጥ (click)፣ ከዚያም “ቀጥል” የሚለውንን ይህን ማዘዣ በመንካት/ክሊክ አቫስት! መጫኑን እንዲቀጥል ማድረግ።

ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ የመጫን ሒደቱ መጠናቀቁን የሚገልጽ ማስታወሻ ይመጣል።

ደረጃ 5፤ ሶፍትዌሩን የመጫን ሒደቱን ለማጠናቀቅ ይህንን መጫን (Click) ያስፈልጋል። ከአፍታ በኋላ የአቫስት! (avast!) ምልክት በተለምዶ በኮምፒውተራችን ስክሪን የቀኝ ግርጌ በሚገኘው ሲስተም ትሬይ (System Tray) ላይ ይታያል። ይህን ይመስላል፤

ስእል 4፤ የአቫስት አርማ/ምልክት በሲስተም ትሬይ ውስጥ በጥቁር ሳጥን ተከቦ ይታያል

ከጥቂት ቆይታ በኋላ አቫስት! በተሳካ ሁኔታ መጫኑንና ለሥራ ዝግጁ መሆኑን የሚያበስር መልእክት ቀጥሎ በሚታየው መልኩ ይታያል፤

ስእል 5፤ አቫስት! በትክክል መጫኑን ለማረጋገጥ የሚያሳየው መልእክት

አቫስት! በየጊዜው በራሱ ፕሮግራሙን እና የቫይረስ አይነቶችንና ዝርዝሮችን ሲያሻሽል በተመሳሳይ መንገድ በሲስተም ትሬይ ላይ ይህንኑ የሚያስታውቅ ማስታወሻ ያሳያል። በስክሪኑ ላይ የሚታየው ማስታወሻ የሚከተለውን የመሰለ ነው፤

ስእል 6፤ የአቫስት! መልእክት ምሳሌ

ማስታወሻ፤ የአቫስት! ሶፍትዌራችን ወቅቱን እየጠበቀ ራሱን እንዲያድስ፣ እንዲሁም የአዳዲስ ቫይረሶችን ምንነት በወቅቱ እንዲያገኝና እንዲለያቸው ለማስቻል የምንጠቀምበትን አቫስት ማስመዝገብ ይኖርብናል።

አንድ ጊዜ አቫስት!ን በተገቢው መንገድ ካስመዘገብን የእኛን ትእዛዝ ሳይጠብቅ በራሱ ከቫይረሶች እና ከማልዌሮች ጥቃት ይጠብቀናል። እንደሁኔታውም የተከላከላቸውን አደጋዎች በሚከተለው መልኩ ያሳውቀናል፤

ስእል 7፤ አቫስት! ኮምፒውተራችንን ሊበክሉ ወይም ሊያጠቁ ሲሞክሩ የደሰባቸውና እርምጃ የወሰደባቸውን በተመለከተ የሚያሳየን ማስታወሻ፣ እንደ ምሳሌ የቀረበ

ደረጃ 6በሲስተም ትሬይ (System Tray) ላይ የሚታየውን ይህን ምልክት በእጥፍ-ንኬት (ደብል ክሊክ) በመንካት/ክሊክ የአቫስትን! ዋና የመቆጣጠሪያ ሳጥን ሥራ ማስጀመር። ከዚያም ይህን በመጫን አሁን ያለበትን ደረጃ (Current Status) ከዚህ በታች እንደሚታየው መመልከት ይቻላል፤

ስእል8፤ የአቫስት! ዋና የመቆጣጠሪያ ሳጥን

ማስታወሻ፤ አዳዲስ የፕሮግራም አይነቴዎችን (ቨርዥን) እና ቫይርሶችን ያለማቋረጥ እንድናገኝ የምንጠቀምበት አቫስት! መመዝገብ አለበት። ይህ ኮምፒውተራችንን ከተለያዩ አደጋዎች ለመጠበቅ በጣም አስፈላጊ ነው።

2.1 አቫስትን ለማስመዝገብ

ማስታወሻ የምንጠቀምበትን አቫስት! ካላስመዘገብነው በ30 ቀናት ውስጥ መሥራት ያቆማል። ምዝገባውን ለማከናወን የኢንተርኔት ግንኙነት ያስፈልጋል።

የሚጠቀሙበትን አቫስት! ለማስመዝገብ የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል ነው።

ደረጃ 1፤ ይቺን ምልክት መበጫን የአቫስት! የመቆጣጠሪያ ሳጥን እንዲከፈት ማዘዝ (ስእል 10)

ደረጃ 2፤ በስተግራ በኩል ከተደረደሩት አማራጮች MAINTENANCE የሚለውን ከፍቶ ይህን ሲጫኑ የሚከተሉት ሁለት ሳጥኖች ይከፈታሉ።

ስእል 9፤ ነጻ የጸረ ቫይረስ ምዝገባ መስኮት

የአቫስት! ነጻ የጸረ ቫይረስ አገልግሎት (avast! Free Antivirus Registration) መስኮት ይከፈታል፤ ከዚያም መረጃዎችን በማሰባሰብ ላይ እንደሆነ ያስታውቀናል። ወዲያው ደግሞ አቫስት! በ30 ቀናት ውስጥ የአገልግሎት ጊዜው እንደሚያበቃ የሚያስጠነቅቅ ሌላ መስኮት ይመጣል። (ይህ መስኮት በተጨማሪም ለሽያጭ የቀረቡ ሶፍትዌሮችን እና ሌሎች ማስታወቂያዎችን ያሳያል።)

ስእል 10፤ የምዝገባ ሒደት መከታተያ መስኮት (Registration Status)

ደረጃ 3፤ ይህንን የምዝገባ ምልክት በመጫን በስእል 2 የሚታየውን ሥራ ስናስጀምር የሚከተለው መስኮት ይመጣል፤

ስእል 11፤ የጸረ ቫይረስ ነጻ ምዝገባ ቅጽ

ማስታወሻ በምዝገባ ቅጹ ውስጥ ከሚገኙት ክፍት ቦታዎች የግድ መሞላት ያለባቸው ስም () እና ኢሜይል ብቻ ናቸው። እነዚህም ተለይተው እንዲታዩ በቀይ መስመር ተከበዋል። ሌሎቹ ክፍት ቦታዎች ሳይሞሉ ሊታለፉ ይችላሉ።

ደረጃ 4 በተገቢው ቦታ ስምን እና የኢሜይል አድራሻን ማስገባት፤ ከዚያም ከዚህ በታች የሚታየው መስኮት እንዲከፈት ይህንን ቀድሞ መጫን

ስእል 12፤ ስለመመዝገባችን የሚያመሰግን መስኮት

ደረጃ 5 ይህንን በመጫን የምዝገባ ገጹን (YOUR REGISTRATION) ከዚህ በታች እንደሚታየው መክፈት፤

ስእል 13፤ የምዝገባ ማረጋገጫ

እዚህ ስንደርስ የአቫስት! ምዝገባችንን ጨርሰናል ማለት ነው። ፕሮግራሙን እና የቫይረስ መከታተያችንን እኛው ራሳችን (manually) በየጊዜው ለማደስ (update) የምንችልበትን ዘዴ ለመማር ዝግጁ ሆነናል ማለት ነው። ይህን ለማወቅ 3.0 አቫስትን! በራስ ማደስ (Manually Update) የሚለውን ክፍል ይመልከቱ።

አቫስትን! በራስ ማደስ (Manually Update)

በዚህ ገጽ የሚገኙዩ ክፍሎች

3.0 ከመጀመራችን በፊት

በመሠረቱ ኮምፒውተራችን ከኢንተርኔት ጋራ በተገናኘ ቁጥር አቫስት! የእኛን ትእዛዝ ሳይፈልግ ራሱን ያድሳል፣ ማለትም አዲስ የፕሮግራም ማሻሻያዎችን እና የቫይረስ ክትትል መረጃዎችን ይቀበላል። ሆኖም የኢንተርኔት ግንኙነታችን የሚቋረጥበት ወይም ውሱን በሚሆንባቸው አጋጣሚዎች አቫስት! ራሱን ማደስ ስለማይችል፣ እኛ ራሳችን እድሳቱን እንዲፈጽም ብናደርገው የበለጠ ጠቃሚ ነው።

ማስታወሻአቫስትን! በራሳችን ልናድስበት (updating manually) የምንችልባቸው ሁለት መንገዶች አሉ። አንደኛው በአቫስት! ዋና የመቆጣጠሪያ መስኮት በኩል ነው፤ ሁለተኛው ደግሞ በሲስተም ትሬይ ላይ የሚገኘውን የአቫስት! አርማ በቀኝ-ንኬት (right click) ስንከፍተው በሚመጣው ድንገቴ መስኮት (pop-up menu) በኩል ነው። በተጨማሪ ግን አቫስት! ራሱን በራሱ የሚያድስበትን አሠራር ማስቆም እንችላለን። ይህን ለማድረግ በዋና መቆጣጠሪያ መስኮቱ አናት በስተቀኝ የሚገኘውን ይህን ክፍል ስንጫን ወደሚከፈተው BASIC SETTINGS ወደሚለው ክፍል በመሔድ ማስተካከል እንችላለን።

3.1 በዋናው መቆጣጠሪያ አቫስትን ማደስ (Manual Update)

የሚከተሉትን ደረጃዎች በመከተል በዋናው የመቆጣጠሪያ መስኮት አቫስትን በራሳችን ለማደስ እንችላለን።

ደረጃ 1አቫስት!ን የተጠቃሚዎች ዋና መቆጣጠሪያ መስኮት ለመክፈት ይህንን ምልክት መጫን፤ የመቆጣጠሪያ መስኮቱ የሚከተለውን ይመስላል።

ስእል 1፤ Summary የሚለው ክፍል ፕሮግራማችን ያለበትን የመጨረሻ ደረጃ ያሳያል። በተለምዶ ተጠቃሎ የሚቀርበውን መረጃ የሚያሳይ

አዲስ የፕሮግራም ወይም የቫይረስ ማሻሻያ ካለ በብርቱካንማ ቀለም መካከል የቃል አጋኖ ምልክት የተቀመጠበት አርማ ይታያል። በሌላ ጊዜ ግን የሚታው አረንጓዴ “የራይት” (check mark) ብቻ ነው። የፕሮግራሙ ወይም የቫይረሱ አዲስ አይነቴ (ቨርዥን) በቀይ ቀለም ተጽፎ ይታያል፤ በዚህ ወቅት አሻሽል/አድስ (Update) የሚለውም ማዘዣ አብሮ ይታያል።

ስእል 2፤ አዲስ የፕሮግራም ማሻሻያ መኖሩን የሚየሳይ ማስታወሻ

ደረጃ 2 ይህን ምልክት በመንካት የፕሮግራም አይነቴውን በሚከተለው ምስል እንደሚታየው ማሻሻል፤

ስእል 3፤ ፕሮግራሙ ከተሻሻለ በኋላ (updated)

ከማሻሻያው ከኋላ የፕሮግራም አይነቴው (ቨርዥን) ከ5.0.545 ወደ 5.0.594 ተቀይሯል።

የሚከተለው ዝርዝር በCurrent Status SECURED ሰሌዳ ላይ የሚገኙትን ክፍሎች ወይም የሒደት ማሳያዎች በአጭሩ ያመለክታል፤

ጥቆማ፤ በCurrent Status ሰሌዳ ላይ የሚገኘውን መረጃ ለመደበቅ ወይም ለማየት ይህንን መጫን/መክፈት

Real-time shields ይህ ምስልየአቫስት የማያቋርጥ የመከላከያ መስመር (real-time shields) በትክክል እየሠራ መሆን አለመሆኑን የሚያሳይ ነው። መከላከያው ከኮምፒውተሩ ጋራ የተያያዙ እንቅስቃሴዎችን ሁሉ ይከታተላል። ለኢሜይል፣ ለፋይሎች፣ ለመካነ ድር (ዌብ) እና ለሌሎችም ሲስተሞች ሁሉ መከላከያው ይሠራል። ከመከላከያው የተለያዩ ክፍሎች አንዱ በተጠቃሚው ምርጫ ወይም በማልዌር ጥቃት እንዳይሠራ ቢደረግ በሲስተም ትሬይ ላይ የሚታየው የአቫስት! አርማ ተቀይሮ እንደሚከተለው ምስል ይታያል፤

Definitions auto updates ፤ ይህ ክፍል አቫስት ራሱን በቀጥታ የሚያሻሽልበት (automated update) መንገድ እየሠራ መሆን አለመሆኑን፣ ክፍት ይሁን አይሁን የሚያሳይ ነው።

Virus definitions version (የቫይረስ መለያ አይነቴዎች) ይህ ምስል የመጨረሻውን የቫይረሶች ዝርዝር መረጃ የተዘጋጀበትን ቀን ያሳያል። ቀኑ የሚታየው በሚከተለው ቅደም ተከተል ነው፤ 10 ዓመተ ምህረቱን 2010ን፣ 06 ወሩን እንዲሀም 29 እለቱን ያሳያሉ።

Program version (የፕሮግራም አይነቴ)፤ ይህ አርማ በመጨረሻ የተሻሻለውን የፕሮግራም አይነቴ (ቨርዥን) ያሳያል።

Expiration date (የአገልግሎት ማብቂያ ጊዜ)፤ ይህ ክፍል የምንጠቀምበት የአቫስት! ሥሪት የአግለግሎት ጊዜ የሚያበቃበትን ቀን እና ሰዓት ያሳያል። በድጋሚ መመዝግበና አገልግሎቱን ማደስ የሚችላበትን የመጨረሻ ጊዜም ያስታውሳል።

ደረጃ 3፤ ከዚህ በታች የተሚታየውን መስኮት ለመክፈት ይህንን መግቢያ መንካት።

ስእል 4፤ የተጠቃሚዎች ማዘዣ የማደሻ ክፍል (Maintenance UPDATE)

Maintenance UPDATE ክፍል የተሻሻሉ የፕሮግራም አይነቴዎችን እና የቫይረስ ዝርዝሮችን በራሳችን ለማግኘትና ለማሻሻል ያስችለናል።

ደረጃ 4፤ ፕሮግራሙን እና የቫይረስ መረጃውን ማደስ እንዲጀምር ይህን መንካት/ክሊክ

ደረጃ 5፤ የማደስ ሒደቱ ከተጠናቀቀ በኋላ ወደ Maintenance UPDATE ክፍል ለመመለስ ይህንን መጫን/ክሊክ

የአቫስትን! ፕሮግራም ለማደስ የሚኬድበት ቅደም ተከተል ኤንጂንን እና የቫይረስ ዝርዝሮችን ለማግኘት ከሚኬድበት ጋራ ተመሳሳይ ነው።

ደረጃ 6የፕሮግራም ማደሻውን (Program upgrade) ለማስጀመር ይህንን ምልክት መጫን/ክሊክ

ደረጃ 7፤ የፕሮግራሙ የተሻሻለ አይነቴ ተጭኖ ካለቀ በኋላ ይህን ይሁን የሚለውን ይህን መጫን/ክሊክ ፤ ይህም ወደ Maintenance UPDATE ይመልሰናል።

3.2 አቫስትን በዋናው መቆጣጠሪያ ማደስ (Manual Update)

አቫስት! የፕሮግራም እና የቫይረሶች መከታተያ ዝርዝር ማሻሻያ (virus definition updates) በአቫስት! የፖፕ-አፕ ማዘዣ በኩል ማከናወን ይቻላል። የፖፕ-አፕ ማዘዣ በቀጥታ ማሻሻያውን ወደምናዝበት Maintenance UPDATE ገጽ ለመግባት ያስችለናል።

አቫስትን! የኢንጂን እና የቫይረሶች መከታተያ Engine and virus definitions የመጨረሻ አይነቴዎች በራሳችን ለማሻሻል በፖፕ-አፕ በኩል ለማከናወን የሚከተሉትን ደረጃዎችመከተል ይገባል፤

ደረጃ 1፤ ይህን የፖፕ-አፕ ማዘዣ ለማግኘት በሲስተም ትሬይ ላይ በቀኝ ክሊክ (Right click) በመጠቀም ይህንን መክፈት

ስእል 5፤ የአቫስት! የፖፕ-አፕ ማዘዣ

ደረጃ 2ስእል 4ን ሥራ ለማስጀመር በቅድሚያ ወደ Select Update > Engine and virus definitions መሔድ፤ ከዚያም በደረጃ 4 እና 5 የተመለከተውን ማፈጸም።

ደረጃ 3በስእል 6 እንደተመለከተው ወደ ቀጣዩ ደረጃ ለመሔድ Select Update > Program መሔድ፤ ከዚያም በክፍል 3.1 አቫስትን በዋናው መቆጣጠሪያ በራስ ማደስ (Manual Update) እንደተመለከተው ደረጃ 6 እና 7ን መከተል

3.3 አቫስት! ራሱን በራሱ የሚያድስበትን አሠራር ማቆም የሚቻለው እንዴት ነው

አቫስት! በስሪቱ ወቅት የራሱን ፕሮግራም የተሻሻለ አይነቴ እና የቫይረስ መከታተያዎችን በራሱ በቀጥታ እንዲጭን ተደርጎ ይቀመጣል። ስለዚህ ተጠቃሚዎቹ ይህን የሚያስቆም ትእዛዝ እስካልሰጡት ድረስ በራሱ በቀጥታ መሥራቱን ይቀጥላል። ሆኖም ይህ አሠራሩ በቀላሉ ሊለወጥ ይችላል፤ በዋናው የተጠቃሚዎች ማዘዣ (main user interface) ራስጌ የቀኝ ጠርዝ ወደሚገኘው Settings በመሔድ አሠራሩን መቀየር ይቻላል።

ደረጃ 1የአቫስትን BASIC SETTINGS ፖፕ-አፕ መስኮት ሥራ ለማስጀመር ይህንን ምልክት መጫን/ክሊክ ፤ ከዚያም Updates የሚለውን በመምረጥ UPDATE SETTINGS የሚለውን ገጽ መክፈት።

ደረጃ 2፤ ENGINE AND VIRUS DEFINITIONS እና PROGRAM በሚሉት ንዑስ ክፍሎች ውስጥ በመግባት በሁለቱም ሥራ ከሚገኙት አማራጮች Manual update የሚለውን አማራጭ መምረጥ/ክሊክ

ስእል 6፤ አቫስት ራሱን በቀጥታ እንዳያሻሽል መደረጉን የሚያሳይ ማስታወሻ SUMMARY ATTENTION

ከአቫስት! ጋራ በሚገባ የተለማመዱ ተጠቃሚዎች ከዚህም አልፈው አቫስት! ራሱን የሚያድስበትን መንገድ Details እና Proxy Settings ወደሚሉት ክፍሎች በመሔድ በዝርዝር ሊያስተካክሉት ይችላሉ። ይህን ለማድረግ እዚህ የሰፈረውን ቅደም ተከተል መጠቀም።

ደረጃ 3Details እና Proxy Settings የሚሉትን ክፍሎች በመክፈት ማስተካከያዎቹን ለማድረግ ይህንን ምልክት መጫን/ክሊክ

እስካሁን የአቫስት!ን የኤንጂን እና የቫይረስ (Engine and virus definitions) እንዲሁም የፕሮግራም ማሻሻያዎች (program upgrades) በራሳችን በየጊዜው ለማሻሻል/ለማደስ የምንችልበትን መንገድ ተመልክተናል። አሁን አቫስት! መጠቀም ለመጀመር 4.0 አቫስት!ን በመጠቀም ቫይረሶችን ማደን እና ማስወገድ የሚለውን ክፍል መመልከት።

አቫስትን በመጠቀም ቫይረሶችን ማደን እና ማስወገድ

በዚህ ገጽ የሚገኙ ክፍሎች፤

4.0 ከመጀመርዎ በፊት

አቫስት!ን በመጠቀም ማልዌሮችን እና ቫይረሶችን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ሁለት መሠረታዊ ክፍሎች አሉ። የመጀመሪያው ኮምፒውተራችንን ከስጋት ነጻ መሆን አለመሆኑን ለማረጋገጥ መፈተሽ (ስካኒንግ) ነው። ሁለተኛው ደግሞ በፍተሻው የተገኙ የስጋት ምንጮችን መደምሰስ ወይም ወደ አቫስት! የቫይረስ ማጠራቀሚያ (Virus Chest) ማስገባት ነው። ቫይረሶችን እና ማልዌሮችን መደምሰስ እና/ወይም ወደ የቫይረስ ማጠራቀሚያ (Virus Chest) ማስገባት ሌሎች የኮምፒውተራችንን ክፍሎች ለምሳሌ ፋይሎችን/ሰነዶች እና የኢሜይል ፕሮግራሞቻችንን በቫይረሶቹ ከመበከል ያድናቸዋል።

ማልዌሮችን እና ቫይረሶችን አንድ ቦታ ማጠራቀም የሚለው ሐሳብ እንግዳ ይመስል ይሆናል። ሆኖም እነዚህ ቫይረሶችና ማልዌሮች በጣም አስፈላጊ ወይም ምሥጢራዊ ከሆነ መረጃችን ጋራ ሊጣበቁና ሊበክሉት ይችላሉ። በተጫለ መጠን ይህንን የተበከለ ሰነድ፣ ማህደር ወይም ፕሮግራም መልሰን ማግኘት እንፈልግ ይሆናል። እጅግ አልፎ አልፎ ደግሞ አቫስት! ራሱ ትክክለኛ ፕሮግራሞችን ወይም ኮዶችን እንደቫይረስ ወይም ማልዌር ሊቆጥራቸው ይችላል። የእነዚህ ፕሮግራሞች ኮድ ለኮምፒውተራችን መሠረታዊ ቀመር/ሲስተም እጅግ አስፈላጊ ሊሆን እና ተመልሶ እንዲሠራ ማድረግ እንፈልግም ይሆናል። እነዚህ በስሕተት የሚፈረጁ ነገሮች “በስሕተት የተፈረጁ (false positives)” በመባል ይጠራሉ።

አቫስት! የቫይረስ ማጠራቀሚያ (Virus Chest) ኤሊክትሮኒክ “የሙታን ቀጣና” ወይም “ማግለያ/ማቆያ (quarantine)” ቦታ ነው። በዚህ ማጠራቀሚያ ያሉ ነገሮችን መመርመር፣ ምን ያህል አደጋ ሊያስከትሉ እንደሚችሉ መፈተሽ ይቻላል። ይህንንም ኢንተርኔት ላይ በመፈለግ ወይም ደግሞ ወደ አቫስት! የቫይረስ ቤተ ሙከራ (virus laboratory) በመላክ ምርመራውን ማከናወን ይቻላል። የአቫስት!ን የቫይረስ ቤተ ሙከራ አማራጭ በቫይረስ ማጠራቀሚያ ከሚገኙት ቫይረሶች አንዱን በቀኝ-መጫን (right-click) በመንካት ማግኘት ይቻላል። በቫይረስ ማጠራቀሚያ (Virus Chest) ውስጥ የተቀመጠ ፋይረስን ሁለት ጊዜ መጫን/እጥፍ-ንኬት (Double clicking) ማልዌሩን ወይም ቫይረሱን ነፍስ ዘርቶ እንዲያጠቃን ወይም ሥራውን እንዲቀጥል አያደርገውም፤ ምክንያቱም የቫይረስ ማጠራቀሚያው (Virus Chest) ከቀሪው የኮምፒውተራችን ክፍል ጋራ እንዳይገናኝ ስለሚያደርገው ነው።

ጥቆማ፤ ሌላም አማራጭ አለን። በጣም አስፈላጊ ወይም ስሱ የሆኑ መረጃዎችን የቫይረስ ጥቃት በሚገጥመን ወቅት ለአደጋ እንዳይጋለጡ ከሰጋን ወደ አቫስት! የቫይረስ ማጠራቀሚያ (Virus Chest) ልንወስዳቸው እንችላለን።

በዚህ ክፍል የሚከተሉትን ጉዳዮች እንዳስሳለን፤

 • የኮምፒውተራችንን ሲስተም እና መረቦችን (network) የመከላከል ምርጥ ተሞክሮዎች፣
 • የተጠቃሚዎች የማዘዣ መስኮትን ማወቅ፤ በተለይም SCAN COMPUTER እና MAINTENANCE የተባሉን ክፍሎች መረዳት፣
 • የተለያዩ የፍተሻ መንገዶች መማር፣ እና
 • የአቫስት! የቫይረስ ማጠራቀሚያ (Virus Chest) አጠቃቀም ማወቅ

4.1 የቫይረስ ወረርሽኝን መቆጣጠር

ኮምፒውተራችንን ከጥቃት ለመከላከል ልንወስዳቸው የሚገቡ በርካታ የቅድመ ጥንቃቄ እርምጃዎች አሉ። ለምሳሌ አጠራጣሪ ወይም ችግር ያለባቸው የሚመስሉ ድረ ገጾችን አለመክፈት፣ አቫስት! ን እና ስፓይቡትን የመሰሉ ጸረ ቫይረስ ወይም ጸረ ስፓይዌር ፕሮግራሞችን አዘውትሮ መጠቀም ይቻላል። ሆኖም አንዳንድ ጊዜ የቤት ውስጥ መረቦችን/ላን (local-area network (LAN)) ወይም ኢንተርኔትን መጠቀም ግድታ ሊሆንብን ይችላል። ከዚህ በማስከተል የሚቀርቡት ነጥቦች በዚህ መሰል የማኅበረሰብ መረብ ወይም በሥራ ቦታ ሊያጋጥም የሚችል የቫይረስ ጥቃትን ታሳቢ በማድረግ የተመረጡ ናቸው።

 • ኮምፒውተርዎን ከኢንተርኔት እና ከቤት ውስጥ መረብ (ላን) ያለያዩ። ገመድ አልባ መገናኛ የሚጠቀሙ ከሆነ ከእርሱም ይውጡ። የሚቻል ከሆነ የገመድ አልባ መገናኛውን መጣፋት ወይም ማውጣት ይመረጣል።

 • ኮምፒውተርዎ ከመረብ ጋራ የተገናኘ ከሆነ ከመረቡ ጋራ የተያያዙ ሌሎች ኮምፒውተሮችን በሙሉ ወዲያውኑ ከኢንተርኔት ያለያዩዋቸው፤ በተመሳሳይም ከቤት ውስጥ መረቡ ያስወጡዋቸው። እያንዳንዱ ተጠቃሚ ወዲያውኑ መረቡን መጠቀም ማቆም እና አቫስት! ወይም እርሱን የመሰሉ የሚታመኑ ጸረ ቫይረስ ፕሮግራሞች በመጠቀም አዲሱን ቫይረስ ማደን እና መደምሰስ። ይህ የጥንቃቄ እርምጃ በጣም አድካሚ ይመስል ይሆናል፤ ሆኖም የእያንዳንዱን ኮምፒውተርም ሆነ የመረቡን ደኅንነት ለመጠበቅ እርምጃው እጅግ አስፈላጊ ነው።

 • በመረቡ/በኔትወርኩ የተገናኙ ኮምፒውተሮች በሙሉ የቡት-ታይም ፍተሻ (boot-time scan) እንዲያደርጉ ቀጠሮ ማስያዝ። አዲስ የተገኙ ቫይረሶችን ስም መዝግቦ ማስቀመጥ፣ ከዚያም ምንነታውን ማረጋገጥ፣ መደምሰስ ወይም ወደ አቫስት! የቫይረስ ማጠራቀሚያ (Virus Chest) ማስገባት። ስለቡት-ታይም ፍተሻ የበለጠ ለማወቅ ክፍል 4.6 የቡት-ታይም ፍተሻ (Boot-time Scan) ማድረግ የሚለውን ክፍል መመልከት ይቻላል።

 • አንድ ቫይረስ ከዚህ ቀደም ተደምስሶ (deleted) ወይም ተጠግኖ (repaired) ቢሆን እንኳን እዚህ ቀደም ሲል የጠቀስነውን እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ ነው። ከዚያም ሁሉም ኮምፒውተሮች የቡት-ታይም ፍተሻ እንዲያከናውኑ ማድረግ፤ ይህንንም አቫስት! አንዳችን የማስጠንቀቂያ መልእክት ማሳየት እስኪያቆም መደጋገም ይገባል። እንደማልዌሮቹ እና ቫይረሶቹ አደገኝነት የሚወሰን ቢሆንም፣ ከአንድ ጊዜ በላይ የቡት-ታይም ፍተሻ ማድረግ አያስፈልግ ይሆናል።

የማልዌር እና የቫይረስ ወረርሽኝን በተመለከተ የበለጠ መረጃ ለማግኘት 4.9 የተራቀቁ የቫይረስ አወጋገድ መንገዶች የሚለውን ክፍል መመልከት ይቻላል።

4.2 የአቫስት! የተጠቃሚዎች ማዘዣ (Main User Interface) አጭር ዳሰሳ

የአቫስት! የተጠቃሚዎች ማዘዣ (main user interface) በመስኮትዩ በስተግራ በኩል የተደረደሩ አራት ክፍሎች (tabs) አሉት። እነርሱም SUMMARY፣ SCAN COMPUTER፣ REAL-TIME SHIELDS እና MAINTENANCE ናቸው። እያንዳንዱ ክፍልም ንኡስ ክፍሎች (sub-tabs) አሏቸው።

ደረጃ 1፤ ከዚህ በታች የሚታየውን መስኮት ለመክፈት ይህንን ምልክት መጫን/ክሊክ

ስእል 1፤ የ SUMMARY ክፍሉ አቫስት! ፕሮግራማችን ያለበትን የመጨረሻ የደኅንነት ዋስትና መረጃ ያሳያል

ቀደም ሲል የጠቀስናቸው አራት ክፍሎች ምንነት እና ጥቅም ከዚህ በታች በአጭሩ ተብራርቷል።

SUMMARY፤ ይህ ክፍል Current Status እና Statistics የተባሉ ሁለት ንኡስ ክፍሎች አሉት። Current Status የተሰኘው ንኡስ ገጽ ኮምፒውተራችንን ከማልዌር እና ከቫይረሶች ጥቃት የሚከላከሉልን ቁልፍ የአቫስት! አካሎች ሥራቸውን በማከናወን የደረሱበትን ደረጃ ያሳየናል። STATISTICS የሚባለው ንኡስ ገጽ ደግሞ በተራው የአቫስት! አካሎች ባለፉት የተወሰኑ ቀኖች፣ ሳምነት፣ ወር ወይም ዓመት ያከናወኑትን ተግባር መዝግቦ የሚያሳየን ነው።

SCAN COMPUTER፤ ይህ መስኮት ሦስት ንኡስ መስኮቶች/ክፍሎች አሉት። እነርሱም Scan NowBoot-time Scan እና Scan Logs ናቸው። የSCAN NOW (ስካን ናው) ንኡስ መስኮት በራሳችን ፍተሻ ለማድረግ (manual scans) ያሉንን አማራጮች ዘርዝሮ ያሳያል። BOOT-TIME SCAN (ቡት-ታይም ስካን) የሚባለው ሌላው ንኡስ መስኮት በሚቀጥለው ጊዜ ኮምፒውተራችን ጠፍቶ ሲበራ ወይም ሥራ ሲጀምር የቡት-ታይም ፍተሻ እንዲያደርግ ለማዘዝ እድል ይሰጠናል። በመጨረሻ የሚገኘው SCAN LOGS በተጠቃሚዎች በራሳችን ከዚህ ቀደም የተደረጉ ፍተሻዎችን በሰንጠረዥ አስቀምጦ ያሳየናል።

REAL-TIME SHIELDS፤ ይህ መስኮት የኮምፒውተሩን የተለያዩ አገልግሎቶች ለመከታተል እና ለመጠበቅ ('shields') በመከናወን ላይ ያሉ ሥራዎች ሰብስቦ የሚያሳይ ነው። FILE SYSTEM SHIELD ከሚለው ጀምሮ ሌሎችም እዚህ ተዘርዝረው ይታያሉ። ይህም በቀጥታና ወዲያው ለሚደረግ የመከላከል ሥራ (real-time shield) ማስጀመርና ማስቆምን ጨምሮ አሠራሩን ለመወሰን ያስችላል።

MAINTENANCE ይህ መስኮት UpdateRegistrationVirus Chest እና About avast! የሚሰኙ አራት ንኡስ መስኮቶች አሉት። UPDATE ፕሮግራሙን እና የቫይረስ መለያዎችን በራሳችን ለማደስ ያስችለናል። REGISTRATION የምንጠቀምበትን አቫስት! ለማስመዝገብ የምንጠቀምበት ነው። VIRUS CHEST አቫስት! በዘወትር ፍተሻው ያገኛቸው ማልዌሮች እና ቫይረሶች ሌሎችን እንዳይበክሉ ተለይተውና ተዘርዝረው የሚገኙበት ክፍል ነው። ይህም እንደአስፈላጊነቱና እንደምርጫችን እንድንደመስሳቸው፣ ተጨማሪ ምርመራ እንድናደርግባቸው ወይም ለቫይረስ ቤተ ሙከራ ተጨማሪ ምርመራ እንድንልካቸው እድል ይሰጠናል። ABOUT AVAST! በኮምፒውተራችን ላይ ያለውን የመጨረሻውን የአቫስት! አይነቴ (latest version) መለያ ያሳየናል።

ማስታወሻ፤ ማልዌሮችን እና ቫይረሶችን ለመቆጣጠር SCAN COMPUTER እና MAINTENANCE የሚሉት መስኮቶች እጅግ በጣም ጠቃሚዎች ናቸው።

4.3 ማልዌርን እና ቫይረሶችን ማደን (Scan)

በዚህ ክፍል ኮምፒውተራችንን ለመፈተሽ (Scan) ያሉንን አማራጮች እና አማራጮቹን እንዴት ልንጠቀምባቸው እንደምንችል እንመለከታለን። በተጨማሪም ሙሉ ፍተሻ፣ የማህደሮች ፍተሻ እና ቡት-ታይም ፍተሻ (boot-time scan) ስለማድረግ እንረዳለን።

በአቫስት! የተጠቃሚዎች ማዘዣ SCAN COMPUTER በሚለው መስኮት ውስጥ ከሚገኙት ንኡስ መስኮቶች የመጀመሪያው SCAN NOW የሚለው ነው። የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል እንችላለን።

ደረጃ 1፤ ከዚህ በታች የሚታየውን መስኮት ለመክፈት ይህንን የመስኮቱን መግቢያ መጫን/ክሊክ።

ስእል 2፤ SCAN COMPUTER በሚለው መስኮት ስር የሚገኘውና ፍተሻ ለመጀመር የሚያስችለን SCAN NOW የተባለው ንኡስ መስኮት

የሚከተለው አጭር ማብራሪያ በSCAN NOW ክፍል ከተዘረዘሩት የፍተሻ አማራጮቹ መካከል ለመምረጥ ያግዘናል።

Quick scan (ፈጣን ፍተሻ) ይህንን አማራጭ ፍተሻ (scan) ለማድረግ ያለን ጊዜ አጭር ሲሆን ብንጠቀምበት ይመረጣል።

Full system scan (ሙሉ ፍተሻ) ተጠቃሚዎች መሠረታዊና አጠቃላይ ፍተሻ ለማድረግ የሚያስችል ነው። ሆኖም ረዘም ያለ ጊዜ ስለሚፈልግ ተጠቃሚዎች ኮምፒውተራቸውን ከፍተው ለመቆየት በሚችሉበት ወቅት መካሔድ ያለበት ነው። ጸረ ቫይረስ ለመጀመሪያ ጊዜ ስንጠቀምም እንዲሁ ይህንን ሙሉ ፍተሻ እንድናደርግ ይመከራል። ሙሉ ፍተሻ (Full system scan) የሚወስደው ጊዜ በኮምፒውተሩ ላይ እንዳሉት ሰነዶች፣ ፋይሎች፣ ማህደሮች እና እንደ ሐርድ ድራይቩ፣ እንዲሁም እንደኮምፒውተሩ ፍጥነት የተለያየ ሊሆን ይችላል። 4.4 ሙሉ የኮምፒውተር ፍተሻ (scan) ማካሔድ የሚለውን ክፍል ክፍል በማንበብ ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይቻላል።

Removable media scan (የሚነቀሉ የመረጃ ቋቶች ፍተሻ) ይህ አማራጭ ከኮምፒውተራችን ጋራ የምናገናኛቸውን ውጫዊ የመረጃ ቋቶች (external hard drives) በተለይም ንብረትነታቸው የእኛ ያልሆኑትን ለመፈተሽ የምንጠቀምበት ነው። ፍተሻው በዚህ መሰል ውጫዊ የመረጃ ቋቶች ላይ የሚጫኑና ቋቶቹ ከኮምፒውተራችን ጋራ እንደተገናኘ ጥቃት ማድረስ ወይም መበከል የሚችሉ አደገኛ ፕሮግራሞችን ለመቆጣጠር የሚጠቅም ነው።

Select folder to scan (ማህደሮችን መርጦ መፈተሽ) የተፈለገውን ያህል ማህደሮችን (folders) ለመፈተሽ የሚያስችል አማራጭ ነው። በተለይም የተወሰኑ ፋይሎች ወይም ማህደሮች በቫይረስ ሳይበከሉ እንዳልቀሩ ከጠረጠርን እነርሱኑ ብቻ መርጦ መፈተሽ ይቻላል። ለዝርዝር መረጃ 4.5 ማህደሮችን መፈተሽ የሚለውን ማንበብ ይመከራል።

ጥቆማ፤ እያንዳንዱ የፍተሻ (scan) አማራጭ የፍተሻችንን ዝርዝር ውጤት ያሳየናል። ለምሳሌ፣ የተፈተሸውን ክፍል/አካል ያስታውቀናል። የፍተሻውን የተጠቃለለ መረጃ ለማግኘት ይህንን መጫን/ክሊክ ነው። ስለኮምፒውተር በቂ እውቀት እንዳላቸው የሚያምኑ ተጠቃሚዎች እዚህ በመጫን/ክሊክ እያንዳንዱ የፍተሻ አማራጭ መንገድ የሚሠራበትን ሁኔታ እንደሚፈልጉት ማስተካከል ይችላሉ።

4.4 ሙሉ የኮምፒውተር ፍተሻ (scan) ማካሔድ

ሙሉ የኮምፒውተር ፍተሻ ለማድረግ የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል ይጠቅማል።

ደረጃ 1፤ ከዚህ በታች እንደሚታየው Full system scan (የሙሉ ፍተሻ) አማራጭን ሥራ ለማስጀመር ይህንን ጀምር የሚለውን ማዘዣ መጫን/ክሊክ ያስፈልጋል።

ስእል 3፤ የ SCAN NOW ንኡስ መስኮት Full system scan (ሙሉ ፍተሻ) በመካሔድ ላይ መሆኑን ያሳያል

ሙሉ ፍተሻው ሲጠናቀቅ ኮምፒውተራችን ለጉዳት ሊያጋልጥ የሚችል የስጋት ምንጭ ከተገኘ የፍተሻ ውጤት ማሳያ መስኮቱ የሚከተለውን ስእል ይመስላል።

ስእል 4፤ የፍተሻ ውጤት ማሳያው “አደገኛ ነገር ተገኝቷል” (THREAT DETECTED) የሚል ማስጠንቀቂያ ያሳያል

ይህ የፍተሻ ውጤት ጥቂት አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ ነገሮች መገኘታቸውን ያሳያል። በእነዚህን አደጋ ሊያስከትሉ በሚችሉ ነገሮች ላይ ምን እርምጃ ልንወስድ እንደምንችል ለመረዳት በክፍል 4.7 ቫይረሶችን መቆጣጠር የተዘረዘረውን መመልከት ይጠቅማል።

የአቫስት! የቫይረስ ማጠራቀሚያ (Virus Chest) ገና አቫስት! ወደ ኮምፒውተራችን በሚጫንበት ወቅት የሚዘጋጅ ማህደር ነው። ማጠራቀሚያው ኤሌክትሮኒክ የሙታን ቀጣና ወይም ‘በሽታ’ የሚያስተላልፉ ማልዌር እና ቫይረሶች ሌሎችን እንዳይበክሉ ተገልለው የሚቀመጡበት ስፍራ ነው።

4.5 ማህደሮችን (ፎልደሮችን) መፈተሽ

ፋይሎች የሚጠራቀሙባቸውን ማኅደሮች (ፎልደሮች) ለመፈተሽ የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል ይመረጣል።

ደረጃ 1፤ ከዚህ በታች ባለው ስእል የሚታየውን መስኮት ለመክፈት በመጀመሪያ (በአቫስት ስካን ኮምፒውትር->ስካን ናው ስር) በSelect folder to scan ክፍል ውስጥ የሚገኘውን ይህን ምልክት መጫን/መንካት

ስእል 5፤ ስካን የሚደረጉ ማህደሮችን የመምረጫ Select the areas ሳጥን

Select the areas በተናጠልም ይሁን ከሌሎች ጋራ ልንፈትሸው (ስካን ልናደርገው) የምንፈልገውን ማኅደር (ፎልደር) ለመምረጥ ያስችለናል። ከአንድ በላይ ማኅደሮችን በአንድ ጊዜ መምረጥ እንችላለን። ከመረጥነው ማኅደር አጠገብ ምልክት ስናደርግ በስተግርጌ በሚገኘው የSelected paths ማኅደሩ ያለበት ቦታ ይታያል።

ደረጃ 2፤ ቀደም ሲል በተከፈተው መስኮት ግርጌ የሚገኘውን ይህንን የይሁንታ ምልክት በመጫን የማኀደሩን ፍተሻ የምናስጀምርበት መስኮት እንዲከፈት ማድረግ። የሚከፈተው መስኮት የሚከተለውን ይመስላል፤

ስእል 6፤ የማኅደር ፍተሻ በመካሔድ ላይ ነው

ጥቆማአቫስት! ማንኛውንም ማኅደር/ፎልደር በቀኝ-ንኬት (right click) ስንከፍት በሚያመጣው የተለመደ የዊንዶውስ መስኮት ማኅደሩን ለመፈተሽ/ስካን የሚያስችል አማራጭ አብሮ ያቀርብልናል። በቀላሉ የቫይረስ ፍተሻ ልናደርግለት ከምንፈለገው ማኅደር/ፎልደር አጠገብ የሚገኘውን ይህንን የአቫስት ምልክት መምረጥ ይቻላል።

4.6 ቡት-ታይም ፍተሻ (Boot-time Scan) ማካሔድ

የአቫስት! ቡት-ታይም ፍተሻ (Boot-time Scan) Microsoft Windows Operating System ሥራ ከመጀመሩ በፊት የኮምፒውተራችንን ሐርድ-ድራይቭ ሙሉ በሙሉ ለመፈተሽ ያስችለናል። ቡት-ታይም ፍተሻ በሚከናወንበት ወቅት ብዙዎቹ ማልዌሮች እና ቫይረሶች ገና ሥራ አይጀምሩም፣ “ከእንቅልፋቸው” ተነስተው ጥቃት ለማድረስ የኦፐሬቲንግ ሲስተሙን መነሣት ይጠብቃሉ። ስለዚህም በዚህ “በሚያንቀላፉበት” ወቅት በቀላሉ ሊገኙና ሊወገዱ ይችላሉ።

በተጨማሪም ቡት-ታይም በቀጥታ ዲስኩን (disk) ማግኘት ይችላል፤ ይህም የዊንዶውስ ፋይል ሲስተም ማኅደሮችን ድርይቨሮች ሳይከፍት ሥራውን ለማከናወን ያስችለዋል። እነዚህ የዊንዶውስ ፋይል ሲስተም ማኅደሮች የተለመዱ የጥቃት ኢላማዎች ናቸው። ይህ አሠራር እጅግ የታወቀውን አደገኛ ማልዌር “ሩትኪትስን (rootkits)” ሳይቀር በቀላሉ እንዲገኝ ያደርገዋል። ኮምፒውተራችን ለአደጋ የመጋለጥ ወይም የመበከል እድሉ ዝቅተኛ እንደሆነ ብናምን እንኳን የቡት-ታይም ፍተሻ እንድናደርግ በጥብቅ ይመከራል

የቡት-ታይም ፍተሻ (Boot-time Scan) የበለጠ ተመራጭ የሚሆነው ኮምፒውተራችንን በሙሉ እና በጥልቀት ለመፈሽ ነው። ፍተሻው የሚፈጀው ጊዜ በኮምፒውተራችን ላይ እንዳለን የሐርድ ድራቮች እና የመረጃ ብዛት፣ እንዲሁም እንደኮምፒውተራችን ፍጥነት የሚወሰን ይሆናል። ሆኖም የቡት-ታይም ፍተሻ (Boot-time Scan) ሁልጊዜም የሚካሔደው በቀጣዩ ጊዜ ኮምፒውተራችንን ስንከፍት ነው። በቡት ታይም ኮምፒውተራችንን ለመፈተሽ የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል እንችላለን።

ደረጃ 1የቡት-ታይም ፍተሻ (BOOT-TIME SCAN) መስኮትን ለመክፈት ይህንን መግቢያ መከተል።

ደረጃ 2፤ በሚቀጥለው ጊዜ ኮምፒውተራችን ጠፍቶ ሲበራ/ሲከፈት የቡት-ታይም ፍተሻ እንዲያደርግ ቀጠሮ ለመስጠት ይህን ምልክት በመጫን/ክሊክ ቀጠሮውን ማስያዝ።

ደረጃ 3 የቡት-ታይም ፍተሻውን ወዲያውኑ ማካሔድ ከፈለግን ደግሞ ይህንን ምርጫ በመንካት/ክሊክ ኮምፒውተራችን ወዲያው ጠፍቶ እንዲበራ ማዘዝ እንችላለን።

ማስታወሻ፤ የቡት-ታይም ፍተሻ የኮምፒውተራችን ኦፐሬቲንግ ሲስተም እና ሌሎቹም ሥራ ከመጀመራቸው በፊት ፍተሻውን ያካሒዳል። ስለዚህም ፍተሻው በሚካሔድበት ወቅት በኮምፒውተራችን መስኮት የሚታየን በሚቀጥለው ስእል የተመለከተውን የሚመስል ሰማያዊ ቀልም ያለው እና የፍተሻውን ሒደት የሚያሳይ መስኮት ብቻ ይሆናል።

ስእል 7፤ የአቫስት! የቡት-ታይም የፍተሻ ሒደት ማሳያ

በፍተሻው ሒደት ቫይረስ በተገኘ ቁጥር አቫስት! አማራጭ እርምጃዎችን ያቀርብልናል። አማራጮቹ ማጽዳት/Deleteመተው/ Ignoreወደ ሌላ ቦታ መውሰድ/ Move ወይም ማዳን/ Repair ሊሆን ይችላል። ምንግዜም ለዚህ እርምጃ እንድንወስድ ለሚቀርብልን ማሳሰቢያ መልስ መስጠን ችላ ማለት አደጋ ሊያስከትል ይችላል። እነዚህ የመፍትሔ አማራጮች የሚመጡት ግን በፍተሻው ቫይረስ ሲገኝ ብቻ ነው።

4.7 ቫይረሶችን መቆጣጠር

አቫስትን! በምንጭንበት ወቅት አብሮ በሐርድ ድራይቫችን ላይ የቫይረስ ማጠራቀሚያ ይፈጠራል። የቫይረስ ማጠራቀሚያ ከሌላው የኮምፒውተሩ ሲስተም ተለይቶ የሚገኝ ሲሆን፣ በፍተሻ ወቅት የተገኙ ማልዌሮች እና ቫይረሶች፣ እንዲሁም የተበከሉ ሰነዶች፣ ፋይሎች እና ማኅደሮች ተለይተው የሚቀመጡበት ነው።

የአቫስት! ፕሮግራምን እና የቫይረስ መከታተያውን የመጨረሻ የተሻሻለ አይነቴ በራሳችን አድሰን ከሆነ MAINTENANCE የሚባለውን የአቫስት ንኡስ መስኮት አውቀነዋል ማለት ነው። የአቫስት! የቫይረስ ማጠራቀሚያ የሚገኘው እዚሁ ንኡስ ክፍል ውስጥ ነው።

በፍተሻ (ስካን) ወቅት በተገኙ ማልዌሮች እና ቫይረሶች ላይ ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል ይመከራል።

ደረጃ 1፤ የፍተሻ ውጤት የሚገኝበትን ከዚህ በታች የሚገኘውን መስኮት ለመክፈት ይህንን “ውጤቱን አሳይ” የሚል ትእዛዝ መጫን/ክሊክ።

ስእል 8፤ የፍተሻ ውጤት ማሳያ (SCAN RESULTS) መስኮት የተገኙ የስጋት ምንጮችን (THREAT DETECTED) የሚያሳይበት መስኮት

ደረጃ 2በስእል 8 በሚታዩት የስጋት ምንጮች ላይ ሊወሰዱ የሚችሉ አማራጭ እርምጃዎችን ለማየት ይህንን መንካት/ክሊክ።

ማስታወሻ፤ በቀጣዮቹ ደረጃዎች በምሳሌነት የምንመለከተው የተበከለ ፋይልን ወደ “ቫይረስ ማጠራቀሚያ መውሰድ የሚቻልበትን ዘዴ ብቻ ይሆናል። ሆኖም በአማራጭ እርምጃዎቹ ዝርዝር ውስጥ የሚገኙት ሌሎች አማራጮች በተከታታይ እዚህ ተዳሰዋል።

Repair (ጥገና)፤ ይህ እርምጃ የተበከለ ፋይልን ለመጠገን ይሞክራል

Delete (ማጥፋት)፤ ይህ እርምጃ የተበከለውን ፋይል እስከመጨረሻው ያጠፋዋል።

Do nothing (እንዳለ መተው)፤ ይህ አማራጭ ስሙ እንደሚያመለክተው የስጋት ምንጭ ሊሆን የሚችለውን ነገር ለመቆጣጠር ምንም እርምጃ አለመውሰድ፣ እንዳለ መተው ነው። ይህ ፈጽሞ የማይበረታታ (definitely not recommended) አማራጭ ነው።

ደረጃ 3፤ ከዚያም Move to Chest (ወደማጠራቀሚ ውሰድ) የሚለውን አማራጭ ከመረጡ በኋላ፣ እርምጃውን ለማስፈጸም ይህንን “ፈጽም/አድርግ” የሚል ትእዛዝ መጫን/ክሊክ።

ስእል 9፤ ቫይረሱ ወደ ማጠራቀሚያው ተወስዷል

4.8 የቫይረስ ማጠራቀሚያ (Virus Chest) አጠቃቀም

ቫይረሱ ኮምፒውተራችንን ሳይበክል ወደ አቫስት! የቫይረስ ማጠራቀሚያ ከተወሰደ በኋላ የፈለግነውን እርምጃ መውሰድ እንችላለን።

ደረጃ 1፤ በመጀመሪያ ወደዚህ ክፍል መግባት፤ ቀጥሎም ወደ ቫይረስ ማጠራቂሚያው (Virus Chest) በመዝለቅ ከዚህ በታች የሚታየውን መስኮት መክፈት።

ስእል 10፤ የቫይረስ ማጠራቀሚያው (Virus Chest) ሁለት ቫይረሶችን ያሳያል

ደረጃ 2፤ አንዱን ቫይረስ በቀኝ-ንኬት (Right click) በመክፈት በተመረጠው ቫይረስ ላይ ልንወስድ የምንችላቸውን እርምጃዎች ዝርዝር እናገኛለን። ስእሉን መመልከት።

ስእል 11፤ በቫይረስ ማጠራቂሚያ በተሰበሰቡ ቫይረሶች ላይ ሊወሰዱ የሚችሉ እርምጃዎች ዝርዝር

ማስታወሻየቫይረስ ማጠራቀሚያውን በቀኝ-ንኬት መክፈት እርምጃውን እንደመውሰድ ሊቆጠር አይገባም። ይህ የሚያሳየው ያሉትን አማራጮች ብቻ ነው። ስለዚህ አንዱን እርምጃ መምረጥ ያስፈልጋል።

ከዚህ በታች በቫይረሶቹ ላይ ልንወስዳቸው የምንችላቸውን አማራጭ እርምጃዎች ያሳያል።

Delete (ማጥፋት)፤ ይህ እርምጃ የተበከለውን ፋይል እስከመጨረሻው ያጠፋዋል።

Restore (መመለስ)፤ እርምጃው ቫይረሱን ቀድሞ ወደነበረበት ስፍራ ይመልሰዋል።

Extract (ማዛወር)፤ ይህ ፋይሉን ወይም ቫይረሱን በመገልበጥ (ኮፒ በማድረግ) እኛ ወደመረጥነው አዲስ ቦታ እንድንወስደው የሚያስችል እርምጃ ነው።

Scan (ዳግም ፍተሻ)፤ ቫይረሱ በድጋሚ እንዲፈተሽ የሚያደርግ አማራጭ እርምጃ።

Submit to virus lab (ለቫይረስ ቤተ ሙከራ መላክ)፤ ይህ እርምጃ ቫይረሱ ከዚህ ከሚታወቁ ቫይረሶች ጋራ ያለው ዝምድና እንዲመረመር ለመላክ ያስቸለናል። ይህን አማራጭ ስንመርጥ ቫይረሱን ለምርመራ የምንልክበት ቅጽ ይመጣልናል።

Properties (ፕሮፐርቲስ)፤ ስለቫይረሱ ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ የሚሰጥ አማራጭ።

Add (ጨምር)፤ ወደ ቫይረስ ማጠራቀሚያ ሊከተቱ የሚችሉ ሌሎች ፋይሎችን እንደአዲስ የማሰስ እርምጃ ነው። የቫይረስ ወረርሺኝ ቢነሳ እንኳን ልናድናቸው የምንፈልጋቸው ፋይሎች ካሉን ይህ አማራጭ በጣም ጠቃሚ ነው።

Refresh all files (ሁሉንም ፋይል ማነቃቃት)፤ የፋይሎችን የመጨረሻ ቅርጽና ይዘት ለማየት የሚያስችል እርምጃ።

4.9 የተራቀቁ የቫይረስ አወጋገድ መንገዶች

አንዳንድ ጊዜ አቫስት!ኮሞዶ ፋየርዎል (Comodo Firewall) እና ሰፓይቡት (Spybot) የሚሰጡት ጥበቃ በቂ የማይሆንበት ጊዜ አለ። ከፍተኛ ጥንቃቄ ብናደርግም የግላችንም ይሁን የሥራ ቦታ የኮምፒውተሮች መረባችን በማልዌር እና በቫይረሶች ሊጠቃ ይችላል። 4.1 የቫይረስ ወረርሽኝን መቆጣጠር በሚለው ክፍል ቫይረሶችን እና ማልዌሮችን ስለመቆጣጠር የተወሰኑ ዘዴዎች ተጠቁመዋል። ሆኖም፣ ይህን መሰል ስጋቶችን ከኮምፒውተራችን ለማስወገድ ሊወሰዱ የሚችሉ ሌሎችም አማራጮች አሉ።

ዘዴ አንድ፤ ጸረ ማልዌር የመታደጊያ ሲዲ/ዲቪዲ መጠቀም (Anti-malware Rescue CDs/DVDs)

አንዳንድ የጸረ ማልዌር ሶፍትዌር ኩባንያዎች የጸረ ቫይረስ መታደጊያ ሲዲ/ዲቪዲ በነጻ ይሰጣሉ። ይህ ከኢንተርኔት ሊጫንና በቀላሉ ወደሲዲ ወይም ዲቪዲ ለገለበጥ ይችላል። እነዚህን ጸረ ማልዌር ሲዲዎች/ዲቪዲዎች ለመጠቀም የሚከተሉትን አነስተኛ እርምጃዎች መከተል ይገባል፤

 1. ጸረ ማልዌር ፕሮግራሙን ከኢንተርኔት መገልበጥ እና ወደሲዲ መቅዳት በነጻ የሚገኙ ፕሮግራሞች ለምሳሌ ImgBurn የመሳሰሉትን በመጠቀም ወደ ሲዲ መቅዳት

 2. ሲዲውን/ዲቪዲውን ወደተበከለው ኮምፒውተር ማስገባት፤ ከዚያም ኮምፒውተሩን ከዚህ ሲዲ/ዲቪዲ በድጋሚ መክፈት/ማስነሳት፤ ይህን ለማድረግ ኮምፒውተሩን ካስነሳስ (switching on) በኋላ F10 ወይም F12 የሚባሉትን በመተየቢያ ገበታችን ላይ ያሉትን ቁልፎች በመጠቀም እንችላለን። ከዚህ በኋላ በኮምፒውተራችን መስኮት ላይ በተከታታይ የሚመጡ ትእዛዞችን በጥንቃቄ ማንበብና መከተታል በጣም አስፈላጊ ነው።

 3. ከዚያ ጸረ ማልዌር ፕሮግራሙ የተሻሻለ የቫይረስ መከታተያ ዝርዝር ለማግኘት ይችል ዘንድ ኮምፒውተሩን ከኢንተርኔት ጋራ ማገናኘት። ፕሮግራሙ ወዲያውኑ ሶፍትዌራችንን ሊጎዱ የሚችሉ የስጋት ምንጮችን ለማደን የኮምፒውተሩን ሐርድዌር መፈተሽ ይጀምራል።

በሚከተለው ዝርዝር የተካተቱት ጥቂት የመታደጊያ ሲዲ (rescue CDs) አማራጫች ናቸው፤

በተጨማሪም Windows OS ሥራ ላይ በሚሆንበት ጊዜ ከዚህ በታች የተመለከተውን መሣሪያ በመጠቀም ኮምፒውተራችንን መፈተሽ እንችላለን። ሆኖም ይህ መሣሪያ በትክክል ሊሠራ የሚችሉ ኮምፒውተራችንን የበከለው ቫይረስ ይህን መሣሪያ ጭምር እንዳይሠራ ካላደረገው በቀር ነው።

 • HijackThis እና ሌሎችንም Trend Micro የተባለው ኩባንያ የሚያቀርባቸውን ተመሳሳይ መሣሪያዎች በነጻ ከዚህ ድረ ገጽ Clean-up Tools ማግኘት ይቻላል።

 • ማይክሮሶፍት የሚያቀርበውን RootkitRevealer የተባለውን ደግሞ በዚህ ድረ ገጽ Sysinternals ይገኛል።

ማስታወሻ፤ ኮምፒውተራችንን በተሻለ ብቃት ከቫይረሶች ለማንጻት እነዚህን መሣሪያዎች በተናጠል በየተራ መጠቀም እንችላለለን።

ዘዴ ሁለት፤ ማይክሮሶፍት ዊንዶውስን እንደገና መጫን (Re Installing the Microsoft Windows Operating System)

ማሳሰቢያ፤ በቅድሚያ ትክክለኛ የመጠቀም ፈቃድና የይለፍ ቁጥር፣ የዊንዶውስ ኦፐሬቲንግ ሲስተም (Windows OS) እና ሌሎችም የምንፈልጋቸውን ፕሮግራሞች ለመጫን የሚያስችሉን ቅጂዎች እንዳሉን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው። ይህ መንገድ ጊዜ ሊወስድ የሚችል ቢሆንም፣ በሌሎች መንገዶች የማልዌር እና የቫይረስ አደጋዎችን ማስወገድ ካልቻልን ሊሞክሩት የሚገባ አማራጭ ነው።

እጅግ አልፎ አልፎ ከቫይረሱ አደገኛነት የተነሣ እስካሁን የጠቀስናቸው ሶፍትዌሮች አደጋውን ለማስወገድ ላይረዱን ይችላሉ። እንዲህ አይነቱ ሁኔታ ሲፈጠር ከዚህ በታች የተቀመጡትን የጥንቃቄ እርምጃዎች መውሰድ እጅግ ይመከራል።

1 . በኮምፒውተሩ ላይ ላሉንን ፋይሎች በሙሉ የመጠባበቂያ ቅጂ መፍጠር ወይም ወደሌላ ቦታ መቅዳት

 1. የማይክሮሶፍት ዊንዶውስ ኦፐሬቲንግ ሲስተምን እንደአዲስ መጫን (Reinstall)

 2. የማይክሮሶፍት ዊንዶውስ ኦፐሬቲንግ ሲስተምን እንደአዲስ ከጫኑ (Reinstall) በኋላ የተሻሻለ አይነቴውን ማግኘት (Update)

 3. አቫስት! ወይም ሌላ የምንመርጠውን ጸረ ቫይረስ መጫን፣ አይነቴውን ማሻሻል (Update)

 4. የሚፈልጉዋቸውን ሌሎች ፕሮግራሞች የተሻሻለ አይነቴ መጫን

ማስታወሻ፤ ከላይ የተጠቀሱትን እርምጃዎች በትክክል ሳይፈጽሙ የመጠባበቂያ ቅጂውን በጭራሽ ከኮምፒውተራችን ጋራ መልሶ ማገናኘት አይገባም። ይህ ኮምፒውተሩን እንደገና በቫይረስ እንዲበከል ሊያደርገው ይችላል።

 1. ከዚያ የመጠባበቂያ ቅጂውን ከኮምፒውተራችን ጋራ በማገናኘት ከችግር ነጻ መሆኑን ለማረጋገጥ በሚገባ መፈተሽ (ስካን)

 2. የስጋት ምንጭ ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን ከፈተሽንን እና ካጠፋን በኋላ የምንፈልጋቸውን ፋይሎች ከመጠባበቂያ ቅጂው ወደ ኮምፒውተሩ መገልበጥ እንችላለን።

የሚዘወተሩ ጥያቄዎች እና ክለሳ

5.0 የሚዘወተሩ ጥያቄዎች እና ክለሳ

ሕሊና እና ዘሪቱ አቫስት! ለአጠቃቀም የሚመች ሆኖ አግኝተውታል። ሆኖም አንዳንድ ጥያቄዎች አሏቸው።

ጥያቄኢንተርኔት ካፌ ውስጥ የምጠቀምነት ኮምፒውተር ምንም የቫይረስ መከላከያ የለውም እንበል። በዚህ ኮምፒውተር የከፈትኳቸው ፋይሎች አለመበከላቸውን እንዴት እርግጠኛ መሆን እችላለሁ?

መልስጥያቄው ቫይረሶች ምን ያህል አደገኞችና በቀላሉ ሊዛመቱ የሚችሉ መሆናቸውን እንደተረዳሽ የሚያሳይ ነው። በትክክልም ሕዝብ የሚጠቀምባቸው ኮምፒውተሮች ምን አይነት አደገኛ ሶፍትዌር እንደበከላቸው ለማወቅ የምንችልበት መንገድ ስለሌለን ሊገጥመን የሚችለው አደጋ በቀላሉ የሚታይ አይደለም። ስለዚህ ሌላ ምንም አማራጭ ካላጣን በስተቀር ግላዊ እና ስሱ መረጃዎችን በሕዝብ ኮምፒውተሮች አለመለዋወጥ የተሻለ ነው።

ጥያቄበቢሮ የኮምፒውተር መረባችን ውስጥ በርካታ ኮምፒውተሮች አሉ። ነገር ግን የኢንተርኔት ግንኙነታችን በጣም ቀርፋፋ ነው። ታዲያ የተሻሻሉ የቫይረሶች መቆጣጠሪያ ዝርዝር መረጃዎችን (virus definition updates) በየጊዜው ማግኘት እና በመረባችን ውስጥ ላሉት ኮምፒውተሮች ሁሉ ማከፋፈል የምችለው እንዴት ነው?

መልስየተሻሻሉ ፕሮግራሞችንና መረጃዎችን ከአቫስት! ድረ ገጽ ማግኘት download the latest program updates እንችላለን። ከዚያ በቀላሉ በመረባችን ውስጥ ላሉ ኮምፒውተሮች ማዳረስ እንችላለን።

ጥያቄአቫስት!ን ከኮምፒውተሬ ባስወግደው ወይም ባስወጣው (uninstall) በቫይረስ ማጠራቀሚያው (Virus Chest) ውስጥ የተሰበሰቡት ፋይሎች እጣ ፈንታ ምን ይሆናል?

መልስበቫይረስ ማጠራቂሚያው የተሰበሰቡት ፋይሎች በሙሉ ይደመሰሳሉ (deleted)።

5.1 የክለሳ ጥያቄዎች

 • በአቫስት! አንድን ነጠላ ማኅደር (folder) ለይቶ ከቫይረስ ነጻ መሆኑን ለመፈተሽ (ስካን) የሚቻለው እንዴት ነው?

 • ያልተመዘገበ የአቫስት! ቅጂ ለምን ያህል ጊዜ አገልግሎት ይሰጣል?

 • በቫይረስ ያልተበከለን ሰነድ (document) ወደ ቫይረስ ማጠራቀሚያ (Virus Chest) መውሰድ ወይም መክተት ይቻላል?

 • አንድን ቫይረስ ወደ ቫይረስ ማጠራቀሚያ (Virus Chest) በመውሰድ እና ቫይረሱን በመደምሰስ (deleting) መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?

 • በቡት-ታይም ፍተሻ (boot-time scan) እና በሙሉ ፍተሻ (full-system scan) መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?