5. የጠፉ መረጃዎችን መልሶ ማግኘት የሚቻለው እንዴት ነው?

Updated2010

መመሪያው በወቅቱ አልተሻሻለም፤ በቅርቡ ይሰረዛል

ዲጂታል መረጃዎችን ለማከማቸት እና ለማስተላለፍ የሚፈጠሩ አዳዲስ ዘዴዎች የመረጃ አያያዝን የሚያሻሽሉትን ያህል መረጃዎች የሚጠፉበት እና የሚበላሹበት እድልም ተያይዞ ሊጨምር ይችላል። በአንድ ስሕተት ወይም በቸልተኝነት፣ ምናልባትም ኮምፒውተራችን አለዚያ ሌላ የመረጃ ቋታችን ከእጃችን በውጣቱ ለዓመታት የተጠራቀመ መረጃ ሊሰረቅ፣ ሊበላሽ እና ከነጭራሹም ሊጠፋ ይችላል። የዚህ አደጋ ምንጩ ራሱ የዲጂታል የመረጃ ማጠራቀሚያ ቴክኖሎጂ ተፈጥሯዊ ድክመትም ሊሆን ይችላል። በኮምፒውተር ባለሞያዎች ዘንድ አንድ የተለመደ አባባል አለ፤ " ጥያቄው “ምናልባት ከሆነ ሳይሆን ሆኖ ሲገኝ” የሚል ነው።" በሌላ አነጋገር ጥያቄው “ምናልባት ወደፊት መረጃዎቻችን ቢጠፉብንስ” የሚል ሳይሆን “መረጃዎቻችን መቼ ይጠፋሉ” ነው። መረጃዎቻችንን በድንገት ማግኘት ሲያቅተን፣ ከዚያ አስቀድመን ወዳስቀመጥነው የመጠባበቂያ ክምችት (up-to-date backup) እና የጠፉ መረጃዎችን መልሶ ወደሚያገኝልን (restoring) አሠራር መሔድ ይኖርብናል። በአብዛኛው ስለመጠባበቂያ ክምችት (backup system) አስፈላጊነት የምናስታውስበት ቀን የሚመጣው ዘግይቶ የሚሆንበት አጋጣሚ ሞልቷል፤ “በኖረን ኖሮ” ብለው ከተጸጸቱ በኋላ በአስፈላጊነቱ የሚያምኑ ሰዎች አሉ።

ደኅንነቱ የተጠበቀ የኮምፒውተር አሠራር እንዲኖረን የመጠባበቂያ ክምችት ፖሊሲ (backup policy) እጅግ አስፈላጊ ነው፤ ነገር ግን ይህን ፖሊሲ መቅረጽ ከውጭ ሲያዩት እንደሚመስለው በጣም ቀላል ሥራ አይደለም። በብዙ ምክንያቶች ይህን እቅድ ማስፈጸም አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፤ የመረጃዎችን የመጀመሪያ/እናት ምንጭ/ቅጂ ሌሎች ቅጂዎች ከተቀመጡበት በተለየ ቦታ ማኖር፣ መጠባበቂያ ክምችቶችን በምሥጢር የማስቀመጥ አስፈላጊነት፣ በየራሳቸው ተንቀሳቃሽ የመረጃ ቋቶች መረጃዎቹን የሚዋዋሱ ሰዎች ካሉ ይህን ማስተባበር ሁሉ የዚሁ አካል ነው። በዚህ ምእራፍ ከመጠባበቂያ ክምችት የጠፉ ፋይሎችን መልሶ ስለማግኛ ዘዴዎች እናነሣለን። በተጨማሪ ኮቢያን ባክአፕ/Cobian Backup እና አንዴሊት ፕላስ/Undelete Plus የተባሉትን መሣሪዎች በዝርዝር እንተዋወቃለን።

አስረጅ አጋጣሚ

:Snippet

የምእራፉ ዋና ዋና ጭብጦች

  • መረጃዎችን ማደራጀት እና መጠባበቂያ ቅጂ ማስቀመጥ የሚቻለው እንዴት ነው?
  • መጠባበቂያ ቅጂዎቻችንን (ባክአፕስ) ማስቀመጥ የሚገባን የት ነው?
  • መጠባበቂያ ቅጂዎቻችንን (ባክአፕስ) ደኅንነታቸው በተጠበቀ ሁኔታ መያዝ ያለብን እንዴት ነው?
  • በስሕተት የተሰረዘ (ዴሊት የተደረገ) መረጃን መልሶ ማግኘት የሚቻለው እንዴት ነው?

መረጃዎችን መለየት እና ማደራጀት

ደኅንነታችንን ለማረጋገጥ አስፈላጊ የሆኑ እርምጃዎችን አስቀድመን መውሰዳችን የግድ ነው፤ ለምሳሌ ኮምፒውተራችንን ከማልዌር ነጻ ማድረግ፣ አስተማማኝ ፋየርዎል መጠቀም፣ ጠንካራ የይለፍ ቃል መጠቀም የዚሁ የጥንቃቄ እርምጃ አካሎች ናቸው። ሆኖም እነዚህ እርምጃዎች በቂ አይደሉም። ነገር ግን ጉዳት ሊያደርሱብን የሚችሉ የቫይረስ ጥቃቶችን የመሳሰሉ ሌሎች አደጋዎች አሉ፤ ሰርጎ ገቦች/ሐከርስ፣ የኤሌክትሪክ መቆራረጥና የኀይል መለዋወጥ፣ ኮምፒውተራችን ላይ የፈሳሽ መግባት፣ ስርቆት፣ የኮምፒውተራችን መወረስ፣ የኦፐሬቲንግ ሲስተም አለመስራት፣ ዲማግኒታይዜሽን ወዘተ. ሳናስብ ለአደጋ ሊያጋልጡን የሚችሉ ጥቂት መንስኤዎች ናቸው። አደጋ ሊደርስ እንደሚችል አውቆ መዘጋጀት የመከላከል ሒደት የመጀመሪያ ደረጃ ነው።

:Snippet

የባክአፕ/የመጠባበቂያ ቅጂ ፖሊሲ (backup policy) ለመፍጠር የመጀመሪያው ደረጃ የግል እና የሥራ መረጃዎቻችን የት እንዳሉ መለየት ነው። ለምሳሌ ኢሜይላችን አገልግሎት በሚሰጠን ድርጅት ሰርቨር ወይም በየራሳችን ኮምፒውተር፣ ምናልባትም በሁለቱም ቦታዎች ሊኖር ይሆናል። በዚያ ላይ ብዙ የኢሜይል አድራሻዎች ይኖሩን ይሆናል። በሌላ በኩል ደግሞ አስፈላጊ የምንላቸው ሌሎች ሰነዶች እና መረጃዎች በሥራ ቦታችን አለዚያም በግላችን ኮምፒውተር ላይ ይኖረን ይሆናል። በርከት ያሉ አድራሻዎችን፣ የቻት (chat) ልውውጦቻችን ታሪክ፣ እና ሌሎችም የግል ምርጫችንን የሚያንጸባርቁ ፕሮግራሞች አበጅተን ይሆናል። ከዚህ ሁሉ ውጭ ደግሞ የተወሰኑ መረጃዎችን በተንቀሳቃሽ የመረጃ መዝገቦች ለምሳሌ በመረጃ ቋቶች (USB memory sticks)፣ ተንቀሳቃሽ ሐርድዌሮች፣ ሲዲዎች፣ ዲቪዲዎች እና አሮጌ ፍሎፒ ዲስኮች ላይ አድርገን ይሆናል። ተንቀሳቃሽ (ሞባይል) ስልኮቻችን ላይም እንዲሁ የምንፈልጋቸው ሰዎች አድራሻዎች፣ እንዲጠፉ የማንሻቸው የአጭር መልእክት ልውውጦች (text messages) ሊኖሩን ይችላሉ። ድረ ገጽ ካለን ደግሞ ለዓመታት የተደከመበት የመረጃ፣ የጽሑፎችና የሰነዶች ክምችት አለን ማለት ነው። ዲጂታል ባልሆኑ ማለትም በማስታወሻ ደብተር፣ በግላዊ የዜና መዋእል መመዝገቢያችን (diaries)፣ በደብዳቤዎች ውስጥ የተቀመጡ ዋጋ ያላቸው መረጃዎቻችንንም መዘንጋት የለብንም።

ሁለተኛው እርምጃ የትኞቹ ፋይሎች/ሰነዶች ‘እናት ቅጂ’ (‘master copies’)፣ የትኞቹ ደግሞ ሁለተኛ ቅጂ እንደሆኑ መለየት ነው። እናት ቅጂ የምንለው በአጠቃላይ የአንድ ሰነድ የመጨረሻ ቅጂ (most up-to-date version) የሆነውን እና በሰነዱ/ፋይሉ ላይ የሚጨመር ወይም የሚስተካከል አዲስ ነገር ቢኖረን ይህን የምናደርግበት ቅጂ ነው። በእርግጥ ይህ ትርጉም እጅግ ጠቃሚ መረጃዎችን የያዙ፣ አንድ ቅጂ ብቻ ያላቸውን ሰነዶች/ፋይሎች አይመለከተም። ሁለተኛ ቅጂዎችን ብቻ በመጠባበቂያ ክምችት ሲያዙ የሚያጋጥመው አንዱ አደጋ እናት ቅጂው በመካከል ሊጠፋ ወይም ሊሰረቅ መቻሉ፤ ይህ ማለት በእናት ቅጂው ላይ ያደረግናቸው የመጨረሻ ማስተካከያዎች አብረው ሊጠፉ ይቻላሉ ማለት ነው። ለምሳሌ አንድ ሳምንት በሚፈጅ ጉዛ ላይ ያለ አንድ ሰው በመረጃ ቋቱ ላይ ባለው አንድ ፋይል ቅጂ ላይ አዳዲስ ማስተካከያዎችን እየጨመረ ነው እንበል። ሰውየው የመጨረሻ ማስተካከያውን እያደረገ ያለው በዚህ በያዘው ቅጂ ላይ በመሆኑ፣ ይህ ቅጂ እናት ቅጂ ሆነ ማለት ነው። ምክንያቱም ቢሮ ባለው ኮምፒውተሩ የመጠባበቂያ ክምችቱ (ባክአፕ) ውስጥ ያስቀመጠው ቅጂ ከዚህ በኋላ የመጨረሻ ቅጂ ስለማይሆን እና ራሱን በራሱ አዲስ ከተሻሻለው የመጨረሻ ቅጂ ጋራ የሚያገናኝበት መንገድ ስለሌለው ነው።
ቀደም ሲል የተመለከትናቸውን እናት እና ሁለተኛ ቅጂ መረጃዎች የት እንደሚገኙ በጽሑፍ አስፍረን ማስቀመጥ ይገባል። ይህ ዝርዝር ምን አይነት የባክአፕ ፖሊሲ እንደሚያስፈልገን ለመወሰን ግልጽ ግንዛቤ እንዲኖረን ይረዳናል። ከዚህ በታች የሚገኘው ሳጥን መሠረታዊ ምሳሌ ተደርጎ ሊታይ ይችላል። በእርግጥ የአንዳንዶቻችን ዝርዝር እጅግ የረዘመ ሊሆን፣ ከአንድ የዳታ ታይፕ ('data type') የሚበልጡ የመረጃ መዝገቦችን ('storage devices') ተጠቅመንም ይሆናል። የመረጃው/ዳታ አይነት Data Type እናት/ሁለተኛ ቅጂ Master/Duplicate የሚገኝበት ማከማቻ Storage Device ያለበት ቦታ Location ኤሌክትሮኒክ ሰነዶች/ዶክመንቶች እናት ቅጂ ኮምፒውተር ላይ ቢሮ ጥቂት በጣም አስፈላጊ ኤሊክትሮኒክ ሰነዶች ሁለተኛ ቅጂዎች የመረጃ ቋት እኔ ዘንድ (የማይለየኝ) ፕሮግራሞች ውስጥ የሚገኙ (ፎቶ፣ አድራሻዎች፣ ቀን መቁጠሪያ) እናት ቅጂ ኮምፒውተር ላይ ቢሮ ጥቂት ኤሌክትሮኒክ ሰነዶች ሁለተኛ ቅጂዎች ሲዲዎች ቤት ኢሜይል እና የኢሜይል አድራሻዎች እናት ቅጂ ጂሜይል አካውት ኢንተርኔት አጭር መልእቶች እና የስልክ አድራሻዎች እናት ቅጂ ሞባይል ስልክ እኔ ዘንድ (የማይለኝ) በወረቀት የታተሙ (ፕሪንትድ) ሰነዶች (የውል ስምምነቶች፣ ደረሰኞች ወዘተ) እናት ቅጂ የጠረጴዛ ኪስ ቢሮ

የመረጃው/ዳታ አይነት Data Type እናት/ሁለተኛ ቅጂ (Master/Duplicate) የሚገኝበት ማከማቻ ቦታ
ኤሌክትሮኒክ ሰነዶች/ዶክመንቶች እናት ቅጂ ኮምፒውተር ላይ ቢሮ
ጥቂት በጣም አስፈላጊ ኤሊክትሮኒክ ሰነዶች ሁለተኛ ቅጂ የመረጃ ቋት/USB memory stick እኔ ዘንድ
ፕሮግራሞች ውስጥ የሚገኙ (ፎቶ፣ አድራሻዎች፣ ቀን መቁጠሪያ) እናት ቅጂ ኮምፒውተር ላይ ቢሮ
ጥቂት ኤሌክትሮኒክ ሰነዶች ሁለተኛ ቅጂ ሲዲዎች መኖሪያ ቤት
ኢሜይል እና የኢሜይል አድራሻዎች እናት ቅጂ ጂሜይል አካውት ኢንተርኔት
አጭር መልእቶች እና የስልክ አድራሻዎች እናት ቅጂ ሞባይል ስልክ እኔ ዘንድ
በወረቀት የታተሙ (ፕሪንትድ) ሰነዶች (የውል ስምምነቶች፣ ደረሰኞች ወዘተ) እናት ቅጂ የጠረጴዛ ኪስ ቢሮ

የሰንጠረዡ ባለቤት ካሰፈረው በመነሳት የሚከተሉትን ነገሮች መታዘብ ይቻላል፦

  • በሆነ አደጋ የቢሮው ኮምፒውተር መስራት ቢያቆም (crashes) ለባለቤቱ በቅጂ መልክ የሚቀሩለት በተንቀሳቃሽ የመረጃ ቋት (USB memory stick) ያሉት እና በሲዲ ተደርገው በመኖሪያ ቤት የሚገኙት ብቻ ናቸው፤

  • ሰውየው የኢሜይል መልእክቶቹም ሆነ አድራሻዎቹ “ከኢንተርኔት-ውጪ” (offline) ቅጂ የለውም፤ ምናልባት የኢሜይል የይለፍ ቃሉን ቢረሳው፣ ወይም ሌላ ሰው ቢቀይርበት እዚያ ያለውን መረጃ በሙሉ ያጣዋል ማለት ነው፤

  • በሞባይል ስልኩ ያሉት መረጃዎች ቅጂም የለውም፤

  • በወረቀት የታተሙ ሰነዶች ዲጂታልም ይሁን አካላዊ/የወረቀት ቅጂዎችም የሉትም። እነዚህም ሰነዶች፣ ኮንትራቶች እና የክፍያ መጠየቂያዎች ሊሆኑ ይችላሉ።

የመጠባበቂያ ቅጂ/ባክአፕ ስትራቴጂያችንን ምንነት መወሰን

ቀደም ሲል ለጠቀስናቸውንና ለሌሎችም የመረጃዎች አይነቶች የመጠባበቂያ ቅጂ (ባክአፕ) ለማዘጋጀት ሶፍትዌሮችና ሌሎች መሣሪያዎች (process solutions) ያስፈልጉናል። እያንዳንዱ የመረጃ አይነት ቢያንስ በሁለት የተለያዩ ቦታዎች መቀመጡን ማረጋገጥ ይኖርብናል።

ኤሊክትሮኒክ ሰነዶች - በኮምፒውተራችን ላይ የሚገኙትን ሰነዶች ሙሉ የመጠባበቂያ ቅጂ መፍጠር። ለዚህም ኮቢያን ባክአፕንየመሳሰሉ ፕሮግራሞች መጠቀም እንችላለን፤ በቀጣዮቹ ገጾች ስለኮቢያን ተጨማሪ መረጃዎችን እናገኛለን። የመጠባበቂያ ቅጂዎቻችንን በተንቀሳቃሽ የመረጃ መዝገቦች ላይ ማዘጋጀት በቀላሉ በምንመርጠው እና ከአደጋ የተጠበቀ ቦታ ለማስቀመጥ ያግዘናል። ሲዲዎችን እና ዲቪዲዎችን መጠቀም የመረጃ ቋቶችን ወይም ተንቀሳቃሽ ሐርድ ድራይቭ ከመጠቀም የበለጠ ለጥንቃቄ ይመረጣል፤ ምንክንያቱም አዲስ ባክአፖችን ለመጨመር ስንሞክር አሮጌውን የማጣት አደጋን ስለሚያስቀሩልን ነው። በተጨማሪም ባዶ ሲዶዎች ከሌሎቹ ስለሚረክሱ አዳዲስ ክምችቶችን በፈጠርን ወይም አሮጌውን ባሻሻልን ቁጥር አዲስ ሲዲ መግዛትና መጠቀም እንችል ይሆናል። በዚህ የመረጃ አይነት ውስጥ ሊገኙ የሚችሉ መረጃዎች ብዙውን ጊዜ እጅግ ስሱ ሊሆኑ ስለሚችሉ ወደመጠባበቂያ ቅጂ ስንገለብጥ ኢንክሪፕት ማድረግ (መሰወር) አስፈላጊ ይሆናል። ይህንን እንዴት ማድረግ እንደሚቻል የበለጠ ለመረዳት ምእራፍ 4. በኮምፒውተራችን ውስጥ ያሉ ስሱ መረጃዎችን እንዴት መጠበቅ ይቻላል እና ስለኢንክሪፕሽን/ስወራ የተጻፈውን ማንበብ ይቻላል።

ፕሮግራም ዳታቤዝ - የፕሮግራም ዳታቤዞቻችን ያሉበትን ቦታ ከለየን በኋላ፣ እነርሱንም በተመሳሳይ መንገድ ባክአፕ ማድረግ እንችላለን።

ኢሜይል - ኢሜሎችን በኢንተርኔት ብራውዘር ብቻ ከመክፈት ይልቅ ተንደርበርድ (Thunderbird) ወይም መሰል ፕሮግራሞች በመጫን ከኢሜይል አካውንታችን ጋራ ማገናኘት እንችላለን። ብዙዎቹ የዌብሜይል አገልግሎት ሰጪዎች ስለዚህ ዝርዝር መረጃና እርዳታ ይሰጣሉ፤ በኢሜይላችን ያሉንን አድራሻዎች እንዴት እንደምናመጣቸው ይመሩናል። በዚህ ምእራፍ መጨረሻ ለተጨማሪ ንባብ የሚሰጡትን ምንጮች ማንበብ አስተማማኝ ግንዛቤ ለመፍጠር ይረዳል። ሆኖም የመልእክቶቻችንን ቅጂዎች በሜይል ሰርቨሩ ላይ ብቻ መተዋችንን ማረጋገጥ አለብን፤ በዚህ ምትክ ወደ ኮምፒውተራችን ማምጣት የለብንም። ተንደርበርድ ዝርዝሩን ያብራራል። የሞባይል ስልክ አድራሻዎች - በሞባይል ስልኮቻችን ላይ ያሉትን የስልክ አድራሻዎች ዝርዝር እና አጫጭር መልእክቶች የመጠባበቂያ ቅጂ ለማዘጋጀት ተገቢውን ሶፍትዌር ከጫንን በኋላ ከኮምፒውተራችን ጋራ በማገናኘት መገልበጥ እንችላለን። ብዙውን ጊዜ ሶፍትዌሮቹ በስልኮቹ አምራች ኩባንያ ድረ ገጽ ላይ ይገኛሉ። ምናልባት ይህን ለመፈጸም ልዩ የማገናኛ ገመድ (special USB cable) መግዛት ይኖርብን ይሆናል። እንደ አማራጭ በሲም ካርዳችን ላይ ያለንን መረጃ ወደ ስልኩ በመገልበጥ፣ ከዚያም መልሶ ወደአዲስ መጠባበቂያ ሲም ካርድ ማጋባት እንችላለን። ይህ መንገድ በተለይም በአስቸኳይ ጊዜ ባክአፓ ለመያዝ እጅግ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። አዲሱን የመጠባበቂያ ሲም ካርድ በተገቢው ቦታ ማስቀመጥ ግን አስፈላጊ ነው። አድራሻዎችን እና አጫጭር መልእክቶችን ከሞባይል ወደ ሲም ወይም በተቃራኒው ለመቅዳት ይቻላል፤ ሆኖም ይህንኑ መረጃ ወደ ወጪ ፍላሽ ሜሞሪ መቅዳትን የሚፈቅድ ስልክ የሚጠቀሙ ሰዎች ካሉ ነገሩ እንዲያውም የቀለለ ይሆናል።

የታተሙ ሰነዶች - የሚቻል ከሆነ በወረቀት ታትመው የሚገኙ አስፈላጊ ሰነዶችን በሙሉ ስካን አድርጎ ከሌሎች ኤሌክትሮኒክ ሰነዶች ጋራ በመጠባበቂያ ቅጂ ማስቀመጥ የተመረጠ ነው።

በመጨረሻ መረጃ ያጠራቀምንባቸውን ቋቶች፣ የዳታ አይነቶች እና መጠባበቂያ ክምችቶችን (ባካአፖችን) ለጥፋት የመጋለጥ እድላቸውን የበለጠ በሚቀንስ መንገድ ማደራጀት ይኖርብናል።

የዳታ አይነት (Data Type) እናት/ሁለተኛ ቅጂ (Master/Duplicate)( የተቀመጠበት ማከማቻ ቦታ
ኤሌክትሮኒክ ዶክመንቶች እናት ቅጂ ኮምፒውተር ላይ ቢሮ
ኤሌክትሮኒክ ዶክመንቶች ሁለተኛ ቅጂ ሲዲዎች መኖሪያ ቤት
ጥቂት አስፈላጊ ኤሌክትሮኒክ ዶክመንቶች ሁለተኛ ቅጂ ተንቀሳቃሽ የመረጃ ቋት (USB memory stick) እኔ ዘንድ (የማይለየኝ)
የዳታ አይነት እናት/ሁለተኛ ቅጂ (Master/Duplicate) የተቀመጠበት ማከማቻ ቦታ
ፕሮግራም ዳታቤዞች እናት ቅጂ ኮምፒውተር ላይ ቢሮ
ፕሮግራም ዳታቤዞች ሁለተኛ ቅጂ ሲዲዎች መኖሪያ ቤት
የዳታ አይነት (Data Type) እናት/ሁለተኛ ቅጂ (Master/Duplicate) የተቀመጠበት ማከማቻ ቦታ
ኢሜይል እና የኢሜይል አድራሻዎች ሁለተኛ ቅጂ የጂሜይል አካውንት ኢንተርኔት
ኢሜይል እና የኢሜይል አድራሻዎች እናት ቅጂ ታንደርበርድ፣ በቢሮ ኮምፒውተር ቢሮ
የዳታ አይነት (Data Type) እናት/ሁለተኛ ቅጂ (Master/Duplicate) የተቀመጠበት ማከማቻ ቦታ
በሞባይል ስልክ የተያዙ አጫጭር መልእክቶች እና አድራሻዎች እናት ቅጂ ሞባይል ስልክ እኔ ዘንድ (የማይለየኝ)
በሞባይል ስልክ የነበሩ አጫጭር መልእክቶች እና አድራሻዎች ሁለተኛ ቅጂ ኮምፒውተር ላይ ቢሮ
በሞባይል ስልክ የነበሩ አጫጭር መልእክቶች እና አድራሻዎች ሁለተኛ ቅጂ መጠባበቂያ ሲም መኖሪያ ቤት
የዳታ አይነት (Data Type) የዳታ አይነት (Master/Duplicate) የተቀመጠበት ማከማቻ ቦታ
በወረቀት የታተመ ዶክመንቶች እናት ቅጂ የጠረጴዛ ኪስ ቢሮ
ስካን የተደረጉ ዶክመንቶች ሁለተኛ ቅጂ ሲዲዎች መኖሪያ ቤት

:Snippet

ዲጂታል ባክአፕ መፍጠር

ቀደም ሲል ከጠቀስናቸው የዳታ አይነቶች ሁሉ፣ ለአንዳንድ ሰዎች የበለጠ አስጊ መስሎ የሚታየው “የኤሌክትሮኒክ ዶክመንቶች” የባካፕ ፖሊሲ መፍጠር ነው። “ኤሌክትሮኒክ ዶክመንቶች” የሚለው ስያሜ ራሱ ግራ የሚያጋባበት አጋጣሚ አለ፤ በአጠቃላይ ግን ከዚህ ቀደም ያደረግነውን ተመልሰን ለመቃኘት የምንችልበት እና ተጠቃሚዎች ሲፈልጉ ሊከፍቱት (open manually) የሚችሉት ነው። አከፋፈቱ ደብል ክሊክ በማድረግ ወይም ልዩ የሆነ አፕሊኬሽን በፋይል ሜኑ በኩል ሊሆን ይችላል። “ኤሌክትሮኒክ ዶክመንቶች” በተለይ ቴክስት ፋይሎችን (text files)፣ የወርድ ዶክመንቶችን (word processing documents)፣ ገለጻ ወይም ንግግር ለማድረግ በመርጃነት የሚረዱ ፋይሎች (presentations)፣ ፒዲኤፍ (PDFs) እና ስፕሬድሺት (spreadsheets) የሚባሉትን ያካትታል። ከኢሜይል መልእክቶች በተለየ፣ ኤሌክትሮኒክ ዶክመንቶች ቅጂዎቻቸውን አቀናብረው በኢንተርኔት አያኖሩም።

ኤሌክትሮኒክ ዶክመንቶችን ባክአፕ ስናደርግ (የመጠባበቂያ ቅጂ ክምችት ስንፈጥርላቸው) የፕሮግራም ዳታቤዛችንንም ባክአፕ ማድረግ መርሳት የለብንም። ለምሳሌ ኤሌክትሮኒክ የቀን መቁጠሪያ (ካላንደር) አፕሊኬሽን ወይም የአድራሻ መዝገብ (address book) የምንጠቀም ከሆነ፣ እነዚህ ፕሮግራሞች የያዙትን መረጃ/ዳታ ያስቀመጡበትን ፎልደር ማግኘት ይኖርብናል። አብዛኛውን ጊዜ እነዚህ መረጃዎችን ልክ እንደኤሌክትሮኒክ ዶክመንቶቹ ሁሉ በዊንዶስ ኮምፒውተሮች ማይ ዶክመንትስ/ My Documents ውስጥ ይገኛሉ። ምናልባት እዚህ ካልተገኙ ግን በመደበኛ ባክአፕ መዝገባችን ላይ የተለዩ ፎልደሮችን ልንፈጥርላቸው ይገባል ማለት ነው።

ተንደርበርድን በመሳሰሉ አፕሊኬሽኖች የተከማቹ የኢሜይል መልእክቶች ለፕሮግራም ዳታቤዝ ልዩ ምሳሌዎች ናቸው። የኢሜይል ፕሮግራም የሚጠቀም፣ ነገር ግን የመልእክቶቹን ቅጂ በሰርቨሩ ላይ ለማከማቸት የማይፈልግ ወይም የማይችል ሰው የኢሜይል ዳታቤዙ በባክአፑ መካተቱን ማረጋገጥ ይኖርበታል። እንደአጠቃቀማችን ምስሎችን እና ቪዲዮ ፋይሎችንም በፕሮግራም ዳታቤዝ ውስጥ የኤሌክትሮኒክ ዶክመንት አድርገን ማስቀመጥ እንችላልን። ዊንዶውስ ሚዲያ ፕሌየር እና አይቱንስ የመሳሰሉ አፕሊኬሽኖች እንደዳታ ቤዝ ይሠራሉ። ይህን መሰል ፕሮግራሞችን የምንጠቀም ከሆነ የሚዲያ ፋይሎች የት እንደሚቀመጡ ለማወቅ ሐርድ ድራይቫችን ውስጥ መፈለግ ይኖርብን ይሆናል።

የማከማቻ ቋቶች (Storage devices)

የኤሌክትሮኒክ ዶክመንቶችንን የመጠባበቂያ ክምችት (ባክአፕ) ከመፍጠራችን በፊት ክምችቱን የምናስቀምጥበትን የማከማቻ ቋት አይነት መምረጥ ይኖርብናል።

ኮምፓክት ዲስክ (ሲዲ) እያንዳንዱ ሲዲ ወደ 700 ሜጋባይት (Megabytes- MB) ገደማ ዳታ/መረጃ መያዝ ይችላል። የሲዲ ባክአፕ መፍጠር ከፈለግን ሲዲ በርነር እና ባዶ ሲዲዎች ያስፈልጉናል። በሲዲ ላይ ያከማጀነውን ፋይል ማጥፋት ወይም ማሻሻል/መቀየር ከፈለግን ሲዲ-አርደብሊው መቅረጫ (CD-RW burner) እና በተደጋጋሚ “ሊጻፍበት” የሚችል ሲዲ (rewritable CDs) ያስፈልገናል። ዘመናዊ ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች፣ ዊንዶውስ ኤክስ ፒን ጨምሮ በአሁኑ ጊዜ አብሯቸው የሚሠራ የሲዲ እና የዲቪዲ ላይ መቅረጫ አላቸው። በሲዲዎች ላይ “የሚጻፍ/የሚቀረፅ” መረጃ ከአምስትና አሥር ዓመት በኋላ የአቀማመጥ ጥራቱ እየቀነሰ እንደሚሔድ ግን መርሳት የለብንም። ክምችታችን ከዚህ ለበለጠ ጊዜ እንዲቆይ የምንፈልግ ከሆነ ሲዲዎቹን እንደአዲስ ማዘጋጀት/መፍጠር ይኖርብናል፤ ለዚህም ለረጅም ጊዜ ሊቆዩ የሚችሉ ልዩ ሲዲዎችን (special 'long life' discs) ወይም የተለየ የባክአፕ ዘዴ መጠቀም ይቻላል።

ዲጂታል ቪዲዮ ዲስክ (ዲቪዲ) (Digital Video Discs (DVDs) አንድ ዲቪዲ እስከ 4.7 ጊጋባይት (Gigabytes (GB)) የመያዝ አቅም አለው። ዲቪዲ ከሞላ ጎደል አሠራሩ ከሲዲ ጋራ ተመሳሳይ ነው፤ ነገር ግን የሚፈልገው መሣሪያ ዋጋ በመጠኑ ወደድ ይላል። ዲቪዲ ወይም ዲቪዲ-አርደብሊው በርነር DVD-RW burner እና ትክክለኛ ዲስኮች ያስፈልጉናል። እንደሲዲ ሁሉ፣ በመደበኛ ዲቪዲ ላይ የተከማቸ መረጃም በመጨረሻ የአቀማመጥ ጥራቱ እየቀነሰ መሔዱ አይቀርም።

የማስታወሻ ማህደሮች (USB memory sticks) ይህ የማስታወሻ ቋት እንደ አይነቱ እጅግ በጣም ብዙ መረጃ ሊያከማች ይችላል። የመያዝ አቅማቸው ከሲዲ እና ዲቪዲዎቹ የበለጠም ይሁን ያነሰ የማስታወሻ ማህደሮች ከሲዲ እና ከዲቪዲዎች ጋራ ሲተያዩ ዋጋቸው ውድ ነው። የተጻፉትን መረጃዎች ለማስተካከል ወይም አጥፍቶ በሌላ ለመተካትም የማስታወሻ ማህደሮች ለአሰራር ቀላል ናቸው። ሆኖም እንደ ሲዲ እና ዲቪዲ ሁሉ፣ የማስታወሻ ቅንጣቶች አስተማማኝ የአገልግሎት ጊዜም ውሱን ነው፤ በአብዛኛው ከ10 ዓመት አይበልጥም።

ሩቅ ሰርቨር (Remote server) በሰርቨር ላይ በአግባቡ የተቀመጠ የባክአፕ መረብ (network backup) መጠነ ሰፊ መረጃ የመያዝ አቅም ይኖረዋል። ነገር ግን ይህ አማራጭ የሚያዛልቅ ይሁን አይሁን የሚወስነው የኢንተርኔት ግንኙነታችን ፍጥነትና አስተማማኝነት ነው። ሆኖም በቢሮ የሚገኝ የባክአፕ ሰርቨርን መጠቀም “የባክአፕ ቅጂዎችን ቢያንስ በተለያዩ ሁለት ቦታዎች ማስቀመጥ አለብን” የሚለውን የጥንቃቄ መርሕ የሚጥስ መሆኑ ግልጽ ነው። በኢንተርኔት ላይ ነጻ የማከማቻ አገልግሎቶች አሉ። ነገር ግን መረጃዎቻችንን በማናውቃቸው ወይም በማናምናቸው ድርጅቶች ሰርቨር ላይ በኢንተርኔት ከማስቀመጣችን (uploading) በፊት ኢንክሪፕት ማድረግ አለብን። የዚህን ምእራፍ *የተጨማሪ ንባብ * ክፍል መመልከት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይጠቅማል።

የመጠባበቂያ ክምችት ሶፍትዌር (Backup Software)

ኮቢን-ባክአፕ (Cobian Backup) ለመጠቀም የቀለለ፣ በራሱ አስታዋሽነት በተመደበለት ጊዜ በቀጥታሥራውን የሚጀምር (run automatically) የመጠባበቂያ ክምችት መፍጠሪያ መሣሪያ ነው። ኮቢንባክአፕ መጠባበቂያ ክምችቱን በተመደበለት ጊዜ በቋሚነት ሲያሻሽልም፣ አዲስ መሻሻል/ለውጥ የተደረገባቸውን ለውጦች ብቻ እየመረጠ ለውጡን ወደማከማቻው መጨመር ይችላል። የመጠባበቂያ ክምችቱ ሰፊ ቦታ እንዳይዘም ይጠቀጥቀዋል (compress)።

አጠቃቀም! የኮቢያን ባክአፕ መመሪያ (Cobian Backup Guide)

እንደተለመደው፣ የመጠባበቂያ ክምችታችንን የያዛቸውን ፋይሎች VeraCrypt የመሳሰሉትን መሣሪያዎች በመጠቀም ኢንክሪፕት ማድረግ (መሰወር) ይመከራል። ስለኢንክሪፕሽን በምእራፍ 4: በኮምፒውተራችን ውስጥ ያሉ ስሱ መረጃዎችን እንዴት መጠበቅ ይቻላል በስፋት ቀርቧል፤ መለስ ብሎ መመልከት ይቻላል።

አጠቃቀም! ትሩክሪፕት- አስተማማኝ የፋይል ክምችት መመሪያ (VeraCrypt - Secure File Storage Guide)

የመጠባበቂያ ክምችት መፍጠሪያ መሣሪያዎችን (backup tools) ስንጠቀም፣ የመጠባበቂያ ክምችት ስርዓታችን ያለችግር እንዲሠራ ለማድረግ የሚጠቅሙ ጥቂት ነገሮች አሉ፤ - መዝገቦቹን/ፋይሎቹን በኮምፒውተራችን ላይ ማደረጃት። መጠባበቂያ ክምችት ልንፈጥርላቸው የመረጥናቸውን ኤሌክትሮኒክ ዶክመንቶች የያዙ ፎልደሮችን/መዝገቦችን በሙሉ ወደ አንድ ቦታ መውሰድ፣ ለምሳሌ **በማይ ዶክመንትስ (My Documents)** ውስጥ ማስቀመጥ፤

- ዳታውን/መረጃውን በአፕሊኬሽን ዳታቤዝ የሚያስቀምጥ ሶፍትዌር የምንጠቀም ከሆነ፣ በቅድሚያ ይህ ዳታቤዝ የት እንደሚቀመጥ መወሰን ይኖርብናል። ፕሮግራሙ ዳታቤዙን የምናስቀምጥበትን ቦታ እንድንመርጥ የሚፈቅድልን ከሆነ ቦታውን እንደሚመቸን መቀየር እንችላለን። ይህን ማድረግ የማይፈቅድልን ከሆነ ደግሞ ዳታቤዙን የኤሌክትሮኒክ ዶክመንቶቹ ባሉበት ፎልደር/መዝገብ ውስጥ ማስቀመጥ እንችላለን፤

- የመጠባበቂያ ክምችታችንን (ባክአፕ) የምናድስበት ቋሚ ፕሮግራም ይኑረን፤

- አስተማማኝ የመጠባበቂያ ክምችት ፖሊሲ የሌላቸው የሥራ ባልደረቦቻችንን የሚጠቀሙበት አሠራር ለመፍጠር እንሞክር። ባልደረቦቻችን የዚህን አሠራር አስፈላጊነት እንዲረዱት እናግዛቸው፤

- ከመጠባበቂያ ክምችት መረጃዎችን መልሶ ለማግኘት መደረግ ያለበትን ነገር በቅደም ተከተል መረዳትና መሞከር አንርሳ። ምክንያቱም የመጠባበቂያ ክምችቱን የመፍጠራችን ግብ ዶክመንቶቹ ቢጠፉብን መልሶ ማግኘት ነውና፣ ከክምችቱ የምናገኝበትን መንገድ በሚገባ ካላወቅነው ድካማችን ውጤት አይኖረውም። 

:Snippet

በስሕተት የተደመሰሱ ፋይሎችን መልሶ ማግኘት

በዊንዶውስ ፕሮግራሞች ላይ አንድን ፋይል ስንደመስስ (ዴሊት ስናደርግ)፣ ፋይሉ ከእይታችን ይጠፋል፤ የፋይሉ ይዘት ግን ከኮምፒውተራችን አይጠፋም። ሪሳይክል ቢናችንን (Recycle Bin) ብናጸዳው እንኳን በደመሰስነው ፋይል ውስጥ የነበሩ መረጃዎች በኮምፒውተራችን ላይ ይቀራሉ። ስለዚህም የበለጠ ለመረዳት ምእራፍ 6፡ ስሱ መረጃዎችን እንዴት መደምሰስ ይቻላል? የሚለውን ምእራፍ ማንበብ አለብን። ብዙውን ጊዜ የምንፈልጋቸውን ፋይሎች ወይም ፎልደሮች በስሕተት ከደመሰስናቸው ይህ አሠራር ሊጠቅመን ይችል ይሆናል። በቅርብ የተደመሰሱ ፋይሎችን መልሰው የሚያድሱ በርካታ ፕሮግራሞች አሉ፤ ከእነዚህ አንዱ ሪኩቫ (Recuva) ነው።፡

አጠቃቀም! ሪኩቫ- የጠፉ ፋይሎች ማደሻ መመሪያ (Recuva - File Recovery Guide)

ነገር ግን እኒዚህ መሣሪያዎች ሁልጊዜም የተደመሰሱ ፋይሎቻችንን መልሰው ማግኘት ይችላሉ ማለት አይደለም፤ ምክንያቱም በመካከል ዊንዶውስ በተደመሰሰው መረጃ ላይ ሌላ አዲስ የሰጠነውን መረጃ ጽፎበት ሊሆን ስለሚችል ነው። ስለዚህ አስፈላጊ ፋይል በስሕተት በደመሰስንበት እና ይህን የተደመሰሰ ፋይል መልሶ ለማደስ ሪኩቫን (Recuva) የመሳሰሉ መሣሪያዎችን በምንሞክርበት ጊዜ መካከል ኮምፒውተራችንን ሌላ ነገር ባንሠራበት እጅግ ይመረጣል። የተደመሰሰውን ፋይል ለማግኘት ከመሞከራችን በፊት ሌሎች ሥራዎችን በኮምፒውተራችን እየሠራን በቆየን መጠን፣ የጠፋውን የማገኘት እድል እየተመናመነ ይሔዳል። ይህ ማለት፣ በአንድ መልኩ፣ የተደመሰሱ መረጃዎችን መልሶ የማግኛ ሶፍትዌሮችን አስቀድምን መጫን አለብን ማለት ነው። ሶፍትዌሩን የምንጭነው፣ እጅግ አስፈላጊ የምንለው መረጃ ከተደመሰሰ በኋላ ከሆነ ግን፣ የምንጭነው ሶፍትዌር መረጃ ራሱ በተደመሰሰውና ልናድሰው በምንፈልገው መረጃ ላይ ሊጻፍ ይችላል። እንዲህ ከሆነ ደግሞ መረጃው እስከመጨረሻው ጠፋ ማለት ነው።

በዚህ ምእራፍ ያነሳናቸውን ፖሊሲዎችና አሠራሮች መተግበር እና የጠቀስናቸውን መሣሪያዎች/ሶፍትዌሮች አሠራር መረዳት እጅግ በጣም ብዙ ሥራ ቢመስለም፣ አሠራሩን አንድ ጊዜ በቦታ በቦታው ካደረግን በኋላ ግን የመጠባበቂያ ክምችታችንን በቀጣይነት መያዝ ቀላል ነው። የመጠባበቂያ ክምችት መፍጠርና መያዝ የመረጃ ደኅንነታችን ቁልፍ አካል ነው። ስለዚህም ይህን አሠራር ለመፍጠር የምናልፍበት ሒደት ከምናገኘው ጥቅም ጋራ ሲነጻጸር የሚያስቆጭ አይሆንም።

ተጨማሪ ንባብ