ሲክሊነር - አስተማማኝ የፋይል ድምሰሳ እና ጽዳት

Updated 9 August 2014

መመሪያው በወቅቱ አልተሻሻለም፤ በቅርቡ ይሰረዛል

:Introduction

ዋናው ገጽ (Homepage)

www.ccleaner.com

ኮምፒውተራችን ምን ያስፈልገዋል?

  • ሁሉም የዊንዶውስ አይነቴዎች

ለዚህ መመሪያ የተወሰደው የሲክሊነር አይነቴ

  • 3.04

በሲክሊነር ለመጠቀም የሚያስፈልግ ፈቃድ/ላይሰንስ

  • ነጻ ሶፍትዌር (Freeware)

አስፈላጊ ንባብ

የኢንተርኔት ደኅንነት መጽሐፍ ምእራፍ [6. ስሱ መረጃዎችን በጥንቃቄ ማጥፋት የሚቻለው እንዴት ነው?] (/am/chapter-6)

ሲክሊነርን መጠቀም ለመጀመር የሚፈጀው ጊዜ

  • 15 ደቂቃ

ከሲክሊነር ምን ጥቅም እናገኛለን?

  • በኮምፒውተራችንን ያከናወናቸውን ነገሮች ዱካ እና በኮምፒውተራችን ላይ የሚጠራቀሙ ጊዜያዊ ፋይሎችን በቋሚነት ለመደምሰስ/ለማጥፋት (permanently delete) ያስችላል፤

  • ከኮምፒውተራችን ጋራ በተገናኙ ዲስኮች ላይ የሚገኘውን ባዶ ቦታ (free space) ለማጽዳት ያስችለናል፤

  • የዊንዶውስ ሬጂስትሪን (Windows Registry) ለማጽዳት እንችላለን፤

  • ኮምፒውተራችን ሲከፈት አብረው ሥራ የሚጀምሩ ፕሮግራሞችን ለመወሰንና ለመቆጣጠር ያስችለናል፤

ከጂኤንዩ ሊኑክስ፣ ማክ እና ከሌሎች የማይክሮሶፍት ዊንዶውስ ጋራ/ላይ በሚገባ የሚሠሩ ፕሮግራሞች

ከጂኤንዩ ሊኑክስ እና ከማይክሮሶፍት ዊንዶውስ ጋራ ሊሠራ የሚችል በጣም ጥሩ የጊዜያዊ ፋይሎች ማስወገጃ እና ድጋሚ እንዳይነበብ አድርጎ መሰባበሪያ ሌላም ፕሮግራም አለ፤ እርሱም ብሊችቢት (BleachBit) ይባላል። ብሊችቢት (BleachBit) በጣም ከሚታወቁት መካከል 70 ከሚደርሱት አፕሊኬሽኖች፣ የኦፐሬቲንግ ሲስተም ጊዜያዊ ፋይሎች እና ባዶ የሐርድ ዲስክ ቦታዎች ውስጥ የሚገኙ ጊዜያዊ ፋይሎችን ለማጽዳት (wipe) ያስችለናል። ብሊችቢት (BleachBit) በነጻ የሚገኝ፣ መዋቅራዊ አሠራሩም ለማንኛውም ሰው ክፍት የሆነ (open-source)፣ በተጨማሪም በተንቀሳቃሽ ማጠራቀሚያዎች ለመጠቀም የሚያስችል “ተንቀሳቃሽ አይነቴ” (portable version) ያለው ፕሮግራም ነው። ብሊችቢት በ32 ቋንቋዎች ለአገልግሎት ቀርቧል፤ በአማርኛ ግን ገና አልተዘጋጀም። የኡቡንቱ ሊኑክስ (Ubuntu Linux) ተጠቃሚዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህንን የአጠቃቀም መመሪያ Cleaning up all those unnecessary junk files… እንዲያነቡ ይመከራሉ።

የማክ (Mac OS) ተጠቃሚዎች የኮምፒውተራቸውን እንቅስቃሴ ዱካ ለማጥፋት በነጻ የሚገኙትን Titanium’s SoftwareOnyX እና Maintenance የተባሉትን መሣሪያዎች ሊጠቀሙ ይችላሉ። ትራሽ (Trash) የተባለውን የማይፈለጉ ፋይሎች ማጠራቀሚያ በአስተማማኝ መንገድ ለማጽዳት በቅድሚያ Finder የሚለውን ማማራጫ፣ ከዚያም Secure Empty Trash የሚለውን መምረጥ ይቻላል። (ሒደቱ በአጭሩ ሲታይ Finder > Secure Empty Trash...)። ትራሽ (Trash) የሚባለውን ማጠራቀሚያ በቋሚነት ለማጽዳት (wipe) ደግሞ መጀመሪያ Finder፣ ከዚያ *Preferencesመምረጥ። *Preferences ውስጥ Advanced የሚለውን ንኡስ ገጽ/ኪስ መንካት፤ በዚያ ስርም Empty Trash securely የሚለውን አማራጭ መምረጥ። (ሒደቱ በአጭሩ Finder > Preferences > Advanced > Empty Trash securely)። በዲስካችን ላይ ያለውን ባዶ ቦታ (free space) ለማድዳት ደግሞ Disk Utility የሚለውን የሲስተም አፕሊኬሽን ሥራ ማስጀመር ማለትም run ማድረግ፤ ከዚያም የዲስክ ክፍሉን (disk partition)መምረጥ (select)Erase የሚለውን የንኡስ ገጽ መክፈቻ መምረጥ (choose)፣ በመጨረሻም Erase Free Space.. የሚለውን መንካት/ክሊክ

:Installation instructions

1.1 ይህን መሣሪያ መጠቀም ከመጀመራችን በፊት ልናውቃቸው የሚገቡ ነገሮች

የኮምፒውተራችንም ይሁን የኢንተርኔት ማሰሻ/መፈለጊያችን በመደበኛ አሠራራቸው (default setting) የምናደርጋቸውን ማናቸውንም ነገሮች ዱካ በሆነ መንገድ መዝግበው እንዲያስቀምጡ ወይም ዱካ እንዲተዉ ሆነው የተቀመጡ ናቸው። እውቀቱ ያለው አደገኛ ወይም ጎጂ አካል እነዚህን ዱካዎች በመከተል በኮምፒውተራችን እና በኢንተርኔት ማሰሻው ምን እንደሰራን ለማወቅ የሚችለበት እድል ሰፊ ነው፤ አዳኙ የሚፈልገውን የዱር እንስሳ በዱካው እንደሚከተለው መሆኑ ነው። የኢንተርኔት ማሰሻችንን ወይም ወርድ ፕሮሰሰር (word processor)፣ ወይም የሆነ ሌላ ፕሮግራም በከፈትን ወይም በተጠቀምን ቁጥር ጊዜያዊ ዳታ እና ፋይሎች እየተፈጠሩ በኮምፒውተራችን ላይ ይጠራቀማሉ። ይህ መረጃ በቅርቡ የከፈትናቸውን ዶክመንቶች ወይም ድረ ገጾች ሊመዘግብና በዝርዝር የሚያሳይ ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ ያህል፣ በኢንተርኔት ማሳሻችን (browser) ላይ አንድ የድረ ገጽ አድራሻ መጻፍ ስንጀምር፣ አድራሻው በሚጀምርበት ፊደል የሚጀምሩ ሌሎች አድራሻዎች በስእሉ እንደሚታው በዝርዝር ይቀርባሉ፤

ስእል 1፤ የኢንተርኔት ማሰሻ የአድራሻ ማስገቢያ የተለያዩ የአድራሻ መታወቂያዎችን (URLs) ያሳያል

የአሰሳ ታሪኮች (browser histories) ከዚህ ቀደም የተጠቀምንባቸውን አድራሻዎች በቀላሉ ለማግኘት ቢረዱም፣ ሌላ ሰው የምንጎበኛቸውን ድረ ገጾች እንዲያውቅብን ሊያደርጉም ይችላሉ። ከዚህም በላይ በቅርብ ያደረግነው ነገር (activities) በጎበኘናቸው ድረ ገጾች ውስጥ ከነበሩ ምስሎች እየተቀዳ በሚጠራቀሙት ጊዜያዊ ፋይሎች አማካይነት በቀላሉ ሊታወቅ ይችላል። ይህም የኢሜይል መልእክቶችን እና በኢንተርኔት ቅጾች/ፎርሞች ላይ የጻፍነውን መረጃ ይጨምራል።

አንድን ፕሮግራም በተጠቀምን ቁጥር የሚፈጠሩትን ጊዜያዊ መረጃዎች/ዳታ ለማስወገድ (remove) በየጊዜው የፕሮግራሙን ዳይሬክተሪ በመክፈት በውስጡ የተጠራቀሙትን ጊዜያዊ ፋይሎች ፈልገን በራሳችን እያንዳንዱን ማጥፋት አለብን። ሲክሊነር ይህን ረጅም አሠራር ያስቀርልናል። ሲክሊነር ጊዜያዊ ፋይሎች እንዲወገዱ የምንፈልግባቸውን ፕሮግራሞች እንድንመርጥ የፕሮግራሞቹን ዝርዝር ያቀርብልናል፤ ከዚያም በመረጥናቸው ፕሮግራሞች ውስጥ ያሉትን ጊዜያዊ ፋይሎች በቀጥታ በራሱ ያጠልናል።

ማስታወሻሲክሊነር ጊዜያዊ ፋይሎችን ብቻ እየመረጠ የሚያስወግድ ነው፤ ኮምፒውተራችን ላይ ያኖርናቸውን (saved) ዶክመንቶች አያጠፋም። ይሁን እነጂ በየጊዜው የዶክመንቶቻችንን የመጠባበቂያ ቅጂ እንድንይዝ በጥብቅ እንመከራለን። (ለተያያዥ ማብራሪያ በኢንተርኔት ደኅንነት መጽሐፍ ምእራፍ 5. የጠፉ መረጃዎችን መልሶ ማግኘት የሚቻለው እንዴት ነው? በሚል የተቀመጠውን ማንበብ ይጠቅማል።)

ሲክሊነር ተግባሩን እንዲያከናውን ካዘዝነውና ይኸው ከተፈጸመ በኋላ የማሰሻ እና የቅርብ ጊዜ ዶክመንቶች (recent document) ታሪካችን፣ እንዲሁም በድጋሚ ለመጠቀም ያኖርናቸው የይለፍ ቃሎች (saved passwords) በሙሉ ይጠፋሉ። የዚህ መሣሪያ ተቀዳሚ ግብም ይኸው ነው፣ ኮምፒውተራችንን ለመሰለል ወይም ለመበከል የሚቻልባቸውን መንገዶች ማጥበብ።

ተንቀሳቃሽ ሲክሊነር

1.0 በሚጫነው (Installed) እና በተንቀሳቃሹ የሲክሊነር (CCleaner) አይነቴዎች መካከል ያለው ልዩነት

ተንቀሳቃሽ መሣሪያዎቹ በምንጠቀምበት ኮምፒውተር ላይ አይጫኑም፣ ይህም ፕሮግራሞቹ እንዳሉንም ሆነ እንደምንጠቀምባቸው እንዳይታወቅብን ሊያደርግልን ይችላል። ሆኖም ተንቀሳቃሽ የውጫዊ ቅንጣቶቻችን (external device) ወይም የማስታወሻ ቋታችን (USB memory stick) እና የተንቀሳቃሽ መሣሪያዎቻችን (portable tools) ደኅንነት እንደምንጠቀምበት ኮምፒውተር ጤንነት እንደሚወሰን መዘንጋት የለብንም። ኮምፒውተሩ የተበከለ ከሆነ ለአድዌር፣ ለማልዌር፣ ለስፓይዌር እና ለቫይረስ ሊጋለጡ ይችላሉ። በተንቀሳቃሽ ሲክሊነር (Portable CCleaner) አይነቴ እና በኮምፒውተር ላይ በሚጫነው አይነቴ መካከል ምንም የአገልግሎት ልዩነት የለም።

2.0 ተንቀሳቃሽ ኢሬዘር መጫን እና መጠቀም (Download and Extract)

ተንቀሳቃሽ ሲክሊነር (Portable ccleaner) ለመጫን እና አውጥቶ ለመጠቀም የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል ያስፈልጋል።

ደረጃ 1፦ ወደ መጫኛው ድረ ገጽ ለመሔድ ይህንን http://www.piriform.com/ccleaner/download/portable መስፈንጠሪያ መንካት/ክሊክ

ደረጃ 2፦ ይህንን ማዘዣ በመንካት/ክሊክ ይህንን የመጫኛውን ፋይል በምንፈልገው ቦታ ማኖር/ማስቀመጥ (save)። ከዚያም ወዳኖርንበት ቦታ መሔድ።

ደረጃ 3፦ ይህንን የመጫኛውን ፋይል በእጥፍ-ንኬት በመክፈት በስእል 1 የሚታየውን የዊንዶውስ የድንገቴ ምርጫ መስኮት መክፈት፤ ከዚያም Extract files... የሚለውን መምረጥ

ስእል 1፤ በዊንዶውስ ድንገቴ መስኮት Extract files... የሚለው ተመርጦ

ይህን ተከትሎ ቀጣዩ መስኮት ይከፈታል

ስእል 2፤ ፋይሉን የምናስቀምጥበትና የምንከፍትበት መንገድ ማግኛ

ደረጃ 5በስእል 2 እንደሚታየው ተንቀሳቃሽ/ተነቃይ ቅንጣቱን (removable device) ወይም የማስታወሻ ቋቱን (USB memory stick) ፈልጎ ማግኘት፤ ከዚያም ይህንን የመጫኛ ፋይል ለማስቀመጥ የሚያገለግለንን አዲስ ማህደር/ፎልደር ለመክፈት ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ

ደረጃ 6፦ ከታች በስእል 3 እንደሚታየው በዶክመንት ዛፉ ውስጥ ለአዲሱ ፎልደር/ማህደር የምንፈልገውን አዲስ ስም መጻፍ/ማስገባት

ስእል 3፤ ፋይሉን የምናስቀምጥበትና የምንከፍትበት መንገድ ማግኛ በዶክመንት ዛፉ ውስጥ

ሌላው አማራጭ የፎልደሩን ስም በቁልቁል ተዘርጊ (drop-down) ዝርዝር ውስጥ ማስገባት እንችላለን።

ማስታወሻ፦ ለዚህ ምሳሌ ሲባል የፎልደሩ/ማህደሩ ስም “ተንቀሳቃሽ ሲክሊነር (Portable CCleaner)” ተብሎ ቢሰየምም፣ ተጠቃሚዎች የፕሮግራሙን መኖር ለመደበቅ ሌላ ስም ሊሰጡት ይችላሉ።

ደረጃ 7፦ የፕሮግራሙን ይዘት አዲስ ወደተፈጠረው ፎልደር/ማህደር ለመውሰድ/ለመገልበጥ ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ

ደረጃ 8፦ ከታች በስእል 4 እንደሚታየው ተንቀሳቃሽ/ተነቃይ ቅንጣቱን (removable device) ወይም የማስታወሻ ቋቱን (USB memory stick) በመክፈት የተንቀሳቃሽ ሲክሊነር (Portable CCleaner) ፕሮግራሙ በትክክል መገልበጡን/መቀዳቱን ማረጋገጥ።

ስእል 4፤ የሲክሊነር ፕሮግራም ከተቀመጠበት ተንቀሳቃሽ የመረጃ ቋት ፎልደር/ማህደር ለመከፈት ዝግጁ ሆኖ ይታያል

ደረጃ 9ተንቀሳቃሽ ሲክሊነርን (Portable CCleaner) ከሚገኝበት ተንቀሳቃሽ የማስታወሻ ቋት ለመክፈት ይህንን ፋይል በእጥፍ-ንኬት መክፈት።

ስለ ፕሮግራሙ አሠራርና አጠቃቀም ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ስለ ሲክሊነር (CCleaner) የሚያወሳውን ምእራፍ መመልከት ይቻላል።