ኮቢያን ባክአፕ- አስተማማኝ የፋይል ማስቀመጫ

Updated9 December 2011

መመሪያው በወቅቱ አልተሻሻለም፤ በቅርቡ ይሰረዛል

ኮቢያን መጠባበቂያ ዲጂታል ፋይሎቻችንን የምናስቀምጥበት (archives) ፕሮግራም ነው። እነዚህን ፋይሎች በኮምፒውተራችን፣ በቢሮ ቦታ መረቦች፣ በተንቀሳቃሽ የማጠራቀሚያ ቋቶች ወይም በኢንተርኔት ሰርቨሮች ላይ ልናስቀምጣቸው እንችላለን።

ዋናው ገጽ (Homepage)

ምን አይነት የኮምፒውተር ኦፐሬቲንግ ሲስተም ያስፈለጋል?

 • XP, 2003, Vista, 2008, Windows 7

በዚህ መመሪያ ጥቅም ላይ የዋለው የኮቢያን (Cobian) አይነቴ

 • 10

የመጠቀም ፈቃድ

 • በነጻ የሚገኝ ምንጩ ክፍት የሆነ ሶፍትዌር (Open-Source Software)

አስፈላጊ ንባብ

የተጠቃሚዎች ደረጃ 1ኛ፤ጀማሪ፣ 2ኛ፤መጠነኛ፣ 3ኛ፤መካከለኛ፣ 4ኛ፤በካር፣ 5፤በጣምየሚያውቅ/የተራቀቀ

ፕሮግራሙን ሥራ ለማስጀመር የሚወስደው ጊዜ፡- 30 ደቂቃ

ከኮቢያን ምን ጥቅም እናገኛለን?

 • ለሁሉም ሰነዶች፣ ፋይሎች እና ማህደሮች የመጠባበቂያ ቅጂ ለመፍጠር ማስቻሉ
 • መጠባበቂያ ፋይሎችን መጠረዝ (compress) እና ለመፍታት (decompress) ያስችላል
 • የተደጎሱ ፋይሎችን (archived files) ኢንክሪፕት እና ዲክሪፕት ማድረግ መቻል

ከጂኤንዩ/ሊኑክስ፣ ከማክ እና ከሌሎች የማይክሮሶፍት ዊንዶውስ ጋራ የሚሠሩ ፕሮግራሞች

የዶክመንቶችን፣ የፋይሎችን እና የማህደሮችን (ፎልደር) የመጠባበቂ ቅጂዎችን መፍጠር ወይም ማስቀመጥ ልክ አንድን ፋይል ከአንድ ቦታ ገልብጦ ወደ ሌላ እንደመውሰድ ቀላል ነው። ይህን ለማድረግ ደግሞ የተለየ መሣሪያ አያስፈልግም። ሆኖም እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸውን ሰነዶችን እና ፋይሎችን መደጎስ (archiving) ስንፈልግ ይህን ለማገዝ ተብሎ የተዘጋጁ የመጠባበቂያ ፋይል መፍጠሪያ ፕሮግራሞች (ለምሳሌ ኮቢያን (Cobian Backup)) ወይም ከፋይል ማሳለጫ (file synchronisation) መሣሪያዎች አሉ። እነዚህ ፕሮግራሞች እና መሣሪያዎች በፋይሎቹ ምንጭ እና በአዲሱ የመጠባበቂያ ክምችት ፍጹም ተመሳሳይ ይዘት እንዲኖራቸው ያደርጋሉ። ከኮቢያን ማከማቻ (Cobian Backup) በተጨማሪ ሰነዶቻችንን በመጠባበቂያ ቅጂ ለማከማቸት የሚያስችሉን ሌሎችም በርካታ መሣሪያዎች አሉ። ከእነዚህ መካከል ልንጠቀምባቸው እንችላለን ብለን በይሁንታ የምናቀርባቸው የሚከተሉት ናቸው።

 • ዩኒሰን ፋይል ሲንክሮናይዘር (Unison File Synchronizer) ለማይክሮሶፍት ዊንዶውስ፣ ለማክ፣ እና ለጂኤንዩ/ሊኑክስ የሚሠራ፣ በነጻ የሚገኝ ፕሮግራም ነው፤

 • ኦልዌይ ሲንክ (Allway Sync)Microsoft Windows ፋይሎችን ከምንጫቸው ጋራ የሚያስማማ መሣሪያ (synchronisation tool) ነው። ሶፍትዌሩ በነጻ የሚገኝ እና ምንጩም ክፍት የሆነ ነው።

 • ፍሪፋይልሲንክ (FreeFileSync) በነጻ የሚገኝ እና ምንጩም ክፍት የሆነ የፋይል ማሳለጫ (files synchronisation) መሣሪያ ነው፤ ለጂኤንዩ/ሊኑክስ እና ማይክሮሶፍት ዊንዶውስ ይሥራል።

 • [**ታይም ማሺን (Time Machine)]](https://secure.wikimedia.org/wikipedia/en/wiki/Time_Machine_%28Mac_OS%29) አፕል (Apple)** ያዘጋቸው መሣሪያ ነው፤ ከማክ (Mac OS) (version 10.5 and up) ጋራ አብሮ ይገኛል።

 • ኡቡንቱ ጂኤንዩ/ሊኑክስ (Ubuntu GNU/Linux) ተጠቃሚዎች Backup Your System የሚለውን መመሪያ እንዲያነቡ ይመከራሉ።

የኮቢያን (Cobian) አጫጫን

 • የአጠቃቀም መመሪያውን አጭር መግቢያ ማንበብ
 • በዚህ ሳጥን ግርጌ የሚታየውን የኮቢያን መለያ ምልክት በመንካት/ክሊክ ይህንን ድረ ገጽ www.educ.umu.se/~cobian/cobianbackup.htm መክፈት
 • በዚህ ድረ ገጽ ላይ የሚታየውን “Download Cobian Backup” የሚለውን ማዘዣ መንካት/ክሊክ
 • መጫኛውን (installer) ማኖር (Save)፣ ከዚያም ባለበት ቦታ በእጥፍ ንኬት ማስጀመር
 • ወደ ቀጣዩ እርምጃ ከመሔድ በፊት “የአጫጫን መመሪያውን” ማንበብ
 • ኮቢያንን በሚገባ ጭነው ከጨረሱ በኋላ የመጫኛ ፕሮግራሙን ከኮምፒውተራችን ልናጠፋው እንችላለን

ኮቢያን (Cobian):

1.1 ስለኮቢያን በቅድሚያ ማወቅ የሚገቡን ነገሮች

ኮቢያን (Cobian Backup) የፋይሎችን እና ዳይሬክተሪዎችን መጠባበቂያ ቅጂ ለመፍጠር ወይም ለመደጎስ የሚረዳ ነው። የመጠባበቂያ ቅጂው በተለዩ ዳይሬክተሪዎች ወይም በኮምፒውተራችን ላይ በሚገኙ የመረጃ ማከማቻዎች ሊቀመጥ ይችላል። ቅጂው በቢሮ መረቦች ጋራ በተገናኙ ሌሎች ኮምፒውተሮች ወይም ደግሞ በተንቀሳቃሽ የመረጃ ማህደሮች (ሲዲ፣ ዲቪዲ እና ዩኤስቢ ስቲክ) ሊቀመጥም ይችላል። ኮቢያን (Cobian Backup) ዳይሬክተሪዎችን እና ፋይሎችን በመደበኛነት በቀላሉ ለመደጎስ ወይም የመጠባበቂያ ቅጂ ለመፍጠር ያስችለናል። ፕሮግራሙ ይህን የሚሠራው ሌላውን ሥራችንን ሳያቆም ወይም ሳይረብሽ እና አስፈላጊ በሆነ ወቅት ብቻ ነው። ከዚህም ሌላ ኮቢያን (Cobian Backup) በመጠባበቂያ ቅጂ ፈጠራው ሒደት ፋይሎቹን መጠረዝ (compress) እና ኢንክሪፕት ማድረግ ይችላል።

ኮቢያን የሚጫነው እና ፋይሎች የሚቀመጡት እንዴት ነው?

በዚህ ክፍል የሚዳሰሱ ርእሰ ጉዳዮች፤

2.0 ኮቢያንን መጫን (Install Cobian Backup)

የአጫጫን ማስታወሻ፤ ኮቢያንን ወደ መጫን ከመሔዳችን በፊት የMicrosoft Windows Installer እና Microsoft.NET Framework የመጨረሻ አይነቴ (ቨርዥን) እንዳለን ማረጋገጥ አለብን።

ኮቢያንን (Cobian Backup) መጫን በአንጻራዊነት በቀላሉ እና በፍጥነት ሊከናወን የሚችል ነው። ኮቢያንን (Cobian Backup) ለመጫን የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል ይገባል።

ደረጃ 1፤ ይህንን የመጫኛ ማስጀመሪያ በእጥፍ-ንኬት (Double click) መክፈት፤ ከዚያም Open File - Security Warning የሚል ሳጥን ይከፈታል። ሳጥኑ ከተከፈተ የሚለውን ማዘዣ በመንካት/ክሊክ ውሃ ሰማያዊ ቀለም ያለውን Extracting the resource የሒደት ማሳያ ሥራ ማስጀመር።

ስእል 1፤ የኮቢያን የአሠራር መወሰኛ የቋንቋ መምረጫ መስኮት

ደረጃ 2፤ “ቀጥል” የሚለውን ማዘዣ በመንካት/ክሊክ የስምምነት ውል መቀበያውን ማለትም የPlease read and accept the license agreement ገጽ ይከፈታል። በዚህ ገጽ ላይ መቀበላችንን ለማረጋገጥ I accept የሚለውን መምረጥ፤ አስከትሎ ከታች በስእሉ የሚታየውን ገጽ ለመክፈት ይህንን መንካት/ክሊክ

ስእል 2፤ የመጫኛ ዳይሬክተሪ መምረጫ (Select an installation directory) መስኮት

*ደረጃ 3፤ አሁንም የሚለውን ማዘዣ በመንካት በስእሉ የሚታየውን ገጽ መክፈት፤

ስእል 3፤ የአጫጫን አይነትን የአገልግሎት መምረጫ (Installation type and Service options) መስኮት

ደረጃ 4፤ በService options ካሉት አማራጮች ውስጥ Use Local System account የሚለውን ስንመርጥ ገጻችን ከላይ በስእል 3 የሚታየውን ይመስላል።

ማስታወሻ፤ ይህ አማራጭ ኮቢያን በሰጠነው መርሐ ግብር መሠረት ሌላውን የኮምፒውተራችንን ሥራ ሳያደናቅፍ ውስጥ ለውስጥ የመጠባበቂያ ቅጂውን እንዲያዘጋጅ የሚያስችለው ነው።

ደረጃ 5፤ ከዚህ በታች የሚገኘውን መልእክት ለማግኘት ይህን መንካት/ክሊክ

ስእል 4፤ የኮቢያን ባክአፕ 10 የማስቀጠያ መልእክት

ደረጃ 6፤ የመጫኛ ገጹን ለመክፈት መንካት/ክሊክ። ቀጥሎም ማዘዣ መንካት/ክሊክ

ደረጃ 7*፤ የመጫን ሒደቱን ለማጠናቀቅ መንካት/ክሊክ። ፕሮግራሙ ተጭኖ ሲጠናቀቅ የኮቢያን ባክአፕ መለያ አርማ በዊንዶውስ ሲስተም ትሬይ ላይ እንዲህ ይታያል።

2.1 የፋይልና የዳይሬክተሪ መጠባበቂያ ቅጂ የሚፈጠረው እንዴት ነው

በዚህ ንኡስ ክፍል አንድን ፋይል እና/ወይም ማህደር (ፎልደር) ለመደጎስ ወይም የመጠባበቂያ ቅጂውን ለመፍጠር የሚቻልበትን ቀላል ዘዴ እንመለከታለን። ኮቢያን ባክአፕ backup task አለው፤ ይህም የተመረጡ የፋይል ወይም/እና የፎልደር አይነቶችን እንዲያካትት አድርግን እንድናስቀምጠው ያስችላል፤ በምንፈልገው ቀንና ሰዓት የመጠባበቂያ ቅጂውን እንዲያደርግም አስቀድመን ልናዘው እንችላለን።

አዲስ የመጠባበቂያ ቅጂ ሥራ ለማዘዝ የሚከተሉትን ደረጃዎች መከትል ነው።

ደረጃ 1፤ ይህንን ምልክት በመንካት/ክሊክ አዲስ የሥራ መርሐ ግብር የምንፈጥርበትን የNew task መስኮት በስእሉ እንደሚታየው መክፈት፤

ስእል 2፤ የ New task ገበታ

የገበታው የግራ ጠርዝ የተለያዩ የአገልግሎት አይነቶች እና ተዛማጅ ገጾቻቸው ይገኛሉ፤ የቅጂ ማስቀሪያ አማራጮችን ለመምረጥና ለመወሰን ያስችሉናል። General በሚለው ኪስ (ታብ) ማዘዣ ስር ያሉት አማራጮቸች ከዚህ እንደሚከተለው ተብራርተዋል።

2.1.1 የአማራጮች ማብራሪያ

Task Name፡ ለቅጂ ሥራው የተለየ ስም እንድንሰጠው ይፈቅድልናል። ስለዚህም ከቅጂው ምንነት ጋራ የተዛመደ ስም መስጠት ይመረጣል። ለምሳሌ የመጠባበቂያ ቅጂው የቪዲዮ ፋይሎችን የሚይዝ ከሆነ፣ Video Backup የሚል ስም ልንሰጠው እንችላለን።፡

Disabled፡ ይህ ምርጫ ሳይመረጥ መተው (unchecked) አለበት።

ማስጠንቀቂያ፤ ቀደም ሲል እንዳይሠራ ተደርጎ የነበረ (Disabled) አማራጭ እንዲሠራ ሲታዘዝ (Enable) ሌሎቹን ምርጫዎቻችንን ሁሉ ሊቀይራቸውና የቅጂ ፈጠራ (backup) ሥራውን ሊያስቆመው ይችላል።

Include Subdirectories፤ ይህ አማራጭ ለቅጂ ፈጠራ የሚያገለግሉንን ሁሉንም ንዑስ-ዳይሬክተሪዎች/ማህደሮችን (ፎልደሮች) በአንድ ዳይሬክተሪ/ማህደር እንድናጠቃልላቸው ይፈቅድልናል። ብዛት ላላቸው ማህደሮች እና/ወይም ፋይሎች የመጠባባቂያ ቅጂ ለመፍጠር በጣም የተመቸ አማራጭ ነው። ለምሳሌ ያህል በዚህ አሠራር የMy Documents ማህደርን ብንመርጠው በውስጡ የሚገኙት ፋይሎች እና ማህደሮች በሙሉ መጠባበቂያ ቅጂ ፈጠራ ውስጥ ይጠቃለላሉ።

Create separated backups using timestamps፤ ወደፊት የቅጂ ፈጠራ እንዲከናወን የምንፈልግበትን ቀን እና ሰዓት የምንወስነበት አገልግሎት ነው። በዚህ በተወሰነው ጊዜ የተመረጡት ማህደሮችና ፋይሎች በሙሉ በመረጥንወ የመጠባበቂያ ቅጂ ፋይል ውስጥ ይገባሉ። ይህ ማለት የመጠባበቂያ ቅጂ ያደረግንበትን ቀን በትክክል ማወቅ/ማስታወስ እንችላለን ማለት ነው።

Use file attribute logic፤ ይህ አገልግሎት የሚያስፈልገን (incremental) ወይም (differential) የመጠባበቂያ ቅጂ ለመፍጠር በምንፈልግበት ጊዜ ብቻ ነው። ዝርዝር ከታች ቀርቧል።

ማስታወሻ፤ ከዚህ ቀጥሎ የሚቀርቡት አማራጮች ዊንዶውስ ኤክስፒ ወይም ከዚያ በኋላ የመጡ የዊንዶውስ ኦፐሬቲንግ ሲስትም አይነቴዎችን የሚገለገሉ ተጠቃሚዎች ብቻ የሚያገኙዋቸው ናቸው።

Use Volume Shadow Copy፤ የተቆለፉ ፋይሎችን ጭምር በመጠባበቂያ ቅጂ ለመያዝ የሚያስችለን አማራጭ ነው።

ኮቢያን ባክአፕ (Cobian Backup) የእያንዳንዱን ፋይል የመጠባበቂያ ቅጂ ሲፈጥር ባለፈው ጊዜ ቅጂው ከተፈጠረ በኋላ በምንጩ ፋይል/ማህደር ላይ ለውጥ መደረግ አለመደረጉን ያጣራል። ከዚያም Differential ወይም Incremental የመጠባበቂያ ቅጂ እንዲፈጥር ስናዘው በምንጩ እና በመጠባበቂያው መካከል ያለው ልዩነት ተከትሎ መጠባበቂያ ቅጂውን ይፈጥራል።

ማስታወሻ፤ ይህን አማራጭ እንዳይሠራ ከሰነከልነው () ልንጠቀም የምንችለው ሙሉ ወይም 'ደሚ ባክአፕ (dummy backup)' የሚባለውን ብቻ ይሆናል። ('dummy backup' ዘግየት ብሎ ይብራራል።)

2.1.2 የመጠባበቂያ ቅጂ አይነቶች

Full (ሙሉ ቅጂ)፤ በምንጩ ወይም ፋይሎቹን ከምንገለብጥበት ቦታ የሚገኝ እያንዳንዱ ነጠላ ፋይል ወደ መጠባበቂያ ቅጂ ማውጫው (directory) የሚገለበጥበት/የሚቀዳበት አማራጭ ነው። Create separated backups using timestamp የሚለውን አማራጭ ቀስቅሰነው ከሆነ (enabled)፣ በምንጩ የሚገኝ አንድ ፋይል በመጠባበቂያ ቅጂው ብዙ ቅጂዎች ኖረውት እናገኛለን፤ እነዚህ የአንድ ፋይል ግልባጭ የሆኑ ቅጂዎች የሚለያዩት በተቀዱበት ቀን እና ሰዓት ይሆናል።) እንዲህ ካልሆነ ግን ኮቢያን ባክአፕ ቅጂውን ሲያካሒድ ብዙ ቅጂዎችን በማስቀመጥ ፋንታ ባለፈው ላይ እየጻፈ ይጓዛል፤ ይህም ማለት የአንድ ፋይል ቅጂ ከነበረ፣ በቀጣዩ ጊዜ ተጨማሪ ቅጂዎችን አይፈጥርም፣ የነበረውን ያሻሽለዋል እንጂ እንደማለት ነው።

Incremental(ኢንክሪመንታል)፤ ባለፈው ጊዜ የመጠባበቂያ ቅጂ ከተፈጠረ ወዲህ ፋይሎቹ መለወጣቸውን ወይም አለመለወጣቸውን የሚያጣር አማራጭ ነው። ይህ አማራጭ ምንም ለውጥ ያልተደረገባቸውን ፋይሎች ፕሮግራሙ እንዲዘላቸው ስለሚያደርገው የመጠባበቂያ ቅጂ ለመፍጠር የሚወስደውን ጊዜ ይቆጥባል። ይህን አማራጭ ለመጠቀም Use file attribute logic የሚለውን ማዘዣ መመረጥ (checked) አለበት።

Differential፤ ባለፈው ጊዜ full (ሙሉ ቅጂ) ከተካሔደ ወዲህ ፋይሎቹ ከምንጫቸው መቀየራቸውን የሚያጣራበት አማራጭ ነው። ፋይሉ ለውጥ ካልተደረገበትና ድጋሚ መቅዳት አስፈላጊ ካልሆነ ያልፈዋል፤ ይህም ጊዜ ይቆጥባል። ከዚህ ቀደም ሙሉ የመጠባበቂያ ቅጂ የፈጠርንላቸውን ፋይሎች ድጋሚ ለምቅዳት ስንሞክር በዚህ መንገድ መጠቀም እንችላለን።

Dummy task፤ ይህ አንድን ፕሮግራም ወይም ኮምፒውተራችንን በሆነ በምንመርጠው ሰዓት ለመዝጋት የሚያገለግለን ነው። ይህ አገልግሎት የመጠባበቂያ ቅጂ መፍጠር ሒደት ጋራ የተያያዘ አይደለም።

ደረጃ 2፤ ቀደም ሲል የዘረዘርናቸውን እና ሌሎችንም ምርጫዎቻችንን ካደረግን በኋላ ይህንኑ ለማጽደቅ ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ

2.2 የመጠባበቂያ (Backup) ፋይል የሚፈጠረው እንዴት ነው

የመጠባበቂያ ቅጂ ፈጠራውን ለመጀመር የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል ይገባል።

ደረጃ 1፤ በNew task መስኮት ውስጥ በግራ በኩል ከሚገኘው ንኡስ ሳጥን ውስጥ ካሉት አማራጮች መካከል ይህንን “ፋይል” የሚለውን መጫን/ክሊክ፤ በስእሉ የሚታየውን የመሰለ ገጽ ይከፈትልናል፤

ስእል 3፤ የመጠባበቂያ ቅጂ ለመፍጠር የሚያስችለን ገጽ የፋይሎቹን ምንጭ እና መሔጃ ያስመርጠናል

ደረጃ 2፤ መጠባበቂያ ቅጂ ልንፈጥርላቸው የምንፈልጋቸውን ፋይሎች መምረጥ። (በስእል 3 ምሳሌ My Documents ተመርጦ ይታያል።)

ደረጃ 3Source በሚለው ገበታ ውስጥ የሚገኘውን ይህንን አማራጭ መጫን/ክሊክ፤ ከታች በስእሉ የሚታየውን የመሰለ የአማራጭ ገበታ ይከፈታል

ስእል 4፤ በSource (ምንጭ መምረጫ) ገበታ ውስጥ የመጨመሪያው ማዘዣ Add

ደረጃ 4፤ አንድ ዳይሬክተሪ ለያዛቸው ፋይሎች በሙሉ የመጠባበቂያ ቅጂ ልንፈጥርለት ከፈለግን Directory የሚለውን መምረጥ፤ በተቃራኒው ፋይሎቹን በተናጠል መቅዳት ከመረጥን ደግሞ Files የሚለውን መምረጥ። ነጠላ ፋይሎችን እና ዳይሬክተሪዎችን ለመምረጥ Manually የሚለውን መምረጥ፤ ከዚያም ለመጠባበቂያ ቅጂያችን የፋይሉን አድራሻ ወይም ዳይሬክተሪውን መጻፍ።

ማስታወሻ፤ የፈለግነውን ያህል ፋይሎች እና ዳይሬክቲዎችን መጨመር እንችላለን። በኤፍቲፒ (FTP) ሰርቨር ላይ ለሚገኙ ፋይሎቻችን የመጠባበቂያ ቅጂ ለመፍጠር ከፈለግንም ኤፍቲፒ (FTP) የሚለውን መምረጥ ነው። ይህን ለማድረግ ግን ወደ ሰርቨሩ ለመግባት የሚያስችለን የተጠቃሚ ስም እና የይለፍ ቃል ያስፈልገናል።

የመረጥናቸው ፋይሎች እና/ወይም ማህደሮች (ፎልደሮች) Source (ምንጭ) በሚለው ቦታ ይታያሉ። በስእል 3 እንደሚታየው My Documents የሚባለው ማህደር ተመርጦ ይታያል፤ ይህ ማለት ይህ ማህደር በሚፈጠረው የመጠባበቂያ ቅጂ ውስጥ ከነይዘቱ ይኖራል ማለት ነው።

Destination የሚባለው ገበታ ደግሞ የተመረጡት ፋይሎች እና ማህደሮች የመጠባበቂያ ቅጂ የት እንደሚቀመጥ ያሳያል።

ደረጃ 5፤ ከታች በስእሉ የሚታየውን የመሰለ ገጽ ለመክፈት በDestination pane (በመዳረሻ ወይም ማስቀመጫ ገበታ) ላይ የሚገኘውን ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ

ስእል 5፤ በDestination pane* የአማራጮች ማቅረቢያ*

ደረጃ 6Directory የሚለውን በመምረጥ የመጠባበቂያ ፋይላችን የሚቀመጥበትን የመድረሻ ማህደር (destination folder) የምንመርጥበትን መስኮት መክፈት።

ማስታወሻ፤ የመጠባበቂያ ቅጂውን ፋይል በብዙ አይነቴ ማስቀመጥ የምንፈልግ ከሆነ እዚህ የምንፈልገውን ያህል ማህደር መምረጥ ወይም ማመልከት አለብን። Manually የሚለውን ከመረጥን የመጠባበቂያ ቅጂው እንዲቀመጥ የምንፈልግበትን ቦታ በራሳችን በዝርዝር መስጠት አለብን። የመጠባበቂያ ቅጂውን በኢንተርኔት ሰርቨር ላይ ለማስቀመጥ ከፈለግን FTP site የሚለውን መምረጥ ይኖርብናል፤ ሥራውን ለማጠናቀቅ ግን የማስቀመጫው ሰርቨር መግቢያ የይለፍ ቃል የግድ ያስፈልገናል።

ይህን ካጠናቀቅን በኋላ የኮቢያን ገጽ በስእሉ እንደታየው በምንጭ ገበታው (source area) ላይ ፋይል/ፋይሎች እና/ወይም ፎልደሮች ይታያሉ፤ በተመሳሳይም በመዳረሻ ክፍሉ (destination area) አንድ ወይም ከዚያ በላይ ማህደሮች (ፎልደሮች) ይኖራሉ። ሆኖም ሥራችንን ገና ስላላጠናቀቅን OK የሚለውን ማዘዣ መንካት የለብንም፤ ከዚያ በፊት የመጠባበቂያ ቅጂው እንዲፈጠር የምንፈልግበትን መርሐ ግብር መወሰን አለብን።

2.3 ለመጠባበቂያ ቅጂ ፈጠራ መርሐ ግብር ማውጣት

የመጠባበቂያ ቅጂ ፈጠራውን በቀጥታ ያለእኛ ዝርዝር ክትትል እንዲካሔድ () ከፈለግን ይኸው የሚፈጸምበትን መርሐ ግብር (Schedule) ከወዲሁ መወሰን አለብን። ይህ ክፍል የመጠባበቂያ ቅጂው የሚከናወንበትን ጊዜ እንድንወስን ይረዳናል።

ይህን ለማድረግ የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል ነው።

ደረጃ 1፤ በስተግራ ጠርዝ ከተደረደሩት አማራጮች መካከል የሰዓት ምልክት የሆነውን ይህንን የአገልግሎት ክፍል መምረጥ። ከታች በስእል የሚታየው ገጽ ይከፈታል፤

ስእል 6፤ የቅጂ ማከናወኛ ጊዜ የምንወስንበት የ Schedule type ገጽ

Schedule type የሚለው አማራጭ በውስጥ የያዛቸው ተጨማሪ አማራጮች ምንነት እንደሚከተለው ተብራርተዋል።

Once፤ የመጠባበቂያ ቅጂው በቀንና ሰዓት (Date/Time) መምረጫው ባስቀመጥነው መሠረት ለአንድ ጊዜ ብቻ ይከናወናል።

Daily፤ የመጠባበቂያ ቅጂው በቀንና ሰዓት (Date/Time) መምረጫው ባስቀመጥነው ሰዓት መሠረት በየዕለቱ ይከናወናል።

Weekly፤ የመጠባበቂያ ቅጂው በተመረጡት የሳምንቱ ቀኖች ይካሔዳል። ቀደም ሲል በተሰጠው ምሳሌ፣ ቅጂው በየሳምነቱ ዓርብ ይፈጠራል። ሌሎች ቀኖችንም መምረጥ እንችላለን። የመጠባበቂያ ቅጂው በቀንና ሰዓት (Date/Time) መምረጫው ባስቀመጥነው ቀን መሠረት ይከናወናል።

Monthly፤ የመጠባበቂያ ቅጂው በቀንና ሰዓት (Date/Time) መምረጫው በመረጥናቸው የወሩ ቀኖችና ሰዓት መሠረት ይከናወናል።

Yearly፤ የመጠባበቂያ ቅጂው በቀንና ሰዓት (Date/Time) መምረጫው በመረጥነው ወር፣ ከወሩም በወሰንነው ቀንና ሰዓት ይዘጋጃል።

Timer፤ ማንኛውም የመጠባበቂያ ቅጂ ዝግጅት በቀንና ሰዓት (Date/Time) መምረጫው ውስጥ በወሰንነው የጊዜ ልዩነት መሠረት እየተደጋገም ይፈጸማል።

Manually፤ የመጠባበቂያ ቅጂው ከዋናው የኮቢያን መስኮት ገጽ በራሳችን ማከናወን አለብን ማለት ነው።

ደረጃ 2፤ የመረጥነው ዝርዝር የቅጂ ማከናወኛ ጊዜ፣ የቅጂ ምንጭና መድረሻ ወዘተ ለማጽደቅ የሚለውን ማዘዣ መጫን/ክሊክ

ስእል 7፤ የNew task መስኮት የመጠባበቂያ ቅጂ የሚፈጥርበት መርሐ ግብር ተወስኖለት

የመጠባበቂያ ቅጂ ማዘጋጃ መርሐ ግብሩን ከመረጥንና ካጸደቅን በኋላ ሥራችን አጠናቀናል ማለት ነው። ከዚህ በኋላ በወሰንነው ዝርዝር መሠረት የመጠባበቂያ ቅጂው ማህደሮች ይፈጠራሉ።

ፋይሎችን መጠረዝ (Compress) እና መፍታት (Decompress) የሚቻለው እንዴት ነው?

በዚህ ክፍል የሚዳሰሱ ጉዳዮ

3.0 የመጠበበቂያ ቅጂዎችን መጠረዝ/መጠቅጠቅ (Compress)

ደረጃ 1፤ በዚሁ ምእራፍ 2.3 የመጠባበቂያ (Backup) ፋይል የሚፈጠረው እንዴት ነው በሚለው ክፍል በተብራራው መሠረት እንዲደጎሱ (archive) የምንፈልጋቸውን የመጠባበቂያ ቅጂ ፋይሎች መፍጠር

ደረጃ 2፤ በመስኮቱ በስተግራ ከተደረደሩት የአገልግሎት ዝርዝሮች ይህንን “አርካይቭ” የሚለውን ክፍል መክፈቻ በመምረጥት/ክሊክ ከታች የሚታየውን የመሰለ አዲስ የሥራ ማስጀመሪያ ገጽ New task መክፈት፤

ስእል 1፤ አዲስ ሥራ የማስጀመሪያ ገጹ ከመጠረዣ (Compression) እና የጠንካራ ኢንክሪፕሽን (Encryption) ማዘዣዎች ጋራ

የመጠረዣ (Compression) ማዘዣው የመጠባበቂያ ቅጂውን ለመጠረዝ የምንመርጠውን መንገድ የምንወስንበት ነው።

ማስታወሻ፤ መጠረዝ (Compression) አንድ ፋይል በሚቀመጥበት ቦታ የሚይዘውን ቦታ ይቀንሳል። ብዙ ጊዜ የማንጠቀምባቸው ወይም የማንከፍታቸው፣ ነገር ግን የምንፈልጋቸው የቆዩ ፋይሎች፣ በሚቀመጡበት ስፍራ ብዙ ቦታ በማይፈጁበት መልክ ማስቀመጥ በጣም ይመረጣል። ጥረዛ (Compression) የሚሠራው በአንድ ሰነድ/ዶክመንት ውስጥ የሚገኙ አስፈላጊ ያልሆኑ ኮዶችን በማጥፋት እና አስፈላጊዎቹን ባሉበት በመተው ነው። ጥረዛ (Compression) ሰነዶቻችን የያዙትን መረጃ አያጠፋም። ሆኖም ፋይሎች እንደተጠረዙ (compressed) ሊነበቡ ወይም ሊታዩ አይችሉም፤ ስለዚህ ለመክፈት ከፈለግን ፋይሉ መፈታት ('decompressed') አለበት።

በጥረዛ አይነቶች Compression type ሥር ያሉት አማራጮች የሚከተሉት ናቸው፤

No Compression፤ ይህ አማራጭ ፋይሎች እንዲጠረዙ (compression) እንደማንፈልግ የሚያረጋግጥ ነው።

Zip Compression፤ ይህ ለዊንዶውስ ሲስተም የሚሠራና መደበኛ የጥረዛ (compression) ዘዴ ነው፤ ለአጠቃቀም ምቹም ነው። በዚህ ጥረዛ የተፈጠረ መጠባበቂያ ቅጂ በመደበኛ የዊንዶውስ መሣሪያዎች በቀለሉ ሊከፈት ይችላል፤ ይህ ካልሆነም መክፈቻውን ከዚህ መጫን እንችላለን፤ ZipGenius program to access them) ።

የጥረዛ (compression) አይነቱን ስንመርጥ Split options የሚባለው ንኡስ ክፍልና ተያያዡ አገልግሎቶች በቀጥታ ይከፈታሉ።

Split options የሚሠራው ፋይሎችን በተንወሳቃሽ ማጠራቀሚያዎች (ሲዲ፣ ዲቪዲ፣ ፍሎፒ ዲስክ፣ የመረጃ ቋት) ስናስቀምጥ ነው። የተለያዩት ንኡስ አማራጮች የመጠባበቂያ ቅጂዎቹን ከመረጥነው ማጠራቀሚያ መጠን (size) ጋራ በሚስማማ መልኩ ይከፋፍሏቸዋል።

ምሳሌ፤

ለምሳሌ ከፍተኛ መጠን ያላቸውን ፋይሎች ለመደጎስ እና ወደ ሲዲ ለመገልበጥ እንፈልጋለን እንበል። ለማስቀመጥ የፈለግናቸው ፋይሎች መጠን ከ700 ሜጋባይት (ሜባ) በላይ ሆኗል፤ ይህም ከአንድ ሲዲ የመያዝ አቅም በላይ ነው። መከፋፈያው (splitting function) ፋይሎቹን 700ሜባ ወይም ከዚያ ባነሰ መጠን ይከፋፍላቸዋል፤ ይህም በቀላሉ ወደ ሲዲው እንድንገለብጠው ያስችለናል። የመጠባበቂያ ቅጂው በኮምፒውተራችን ሐርድ ዲስክ ላይ ለማስቀመጥ ከመረጥን፣ ዌይም የፋይሎቹ መጠን ከመረጥነው የማጠራቀሚያ መጠን የሚያንስ ከሆነ ይህን ከፍል መዝለል እንችላለን።፡

ከዚህ በታች የሚታዩት አማራጮች የሚታዩን Split options በሚለው ስር ነው። ምርጫችን እንደምንጠቀምበት ተንቀሳቃሻ የማጠራቀሚያ ቋት አይነት ይወሰናል።

ስእል 2፤ Split Options ንኡስ አማራጮች

 • 3,5" - ፍሎፒ ዲስክ (Floppy disk)፣ ይህ አማራጭ ለጥቂት ሰነዶች (ዶክመንቶች) የመጠባበቂያ ቅጂ ለመፍጠር የሚጠቅም ነው፤

 • ዚፕ (Zip) - ዚፕ ዲስክ (Zip Disk)፣ ልዩ ዚፕ ድራይቭ (Zip Drive) እና ለዚሁ የተሠራ ዲስክ በኮምፒውተራችን ላይ ሊኖረን ይገባል። የምንጠቀምበትን ዲስክ የመያዝ አቅም አስቀድመን ማረጋገጥ እንችላለን።

 • ሲዲ (CD-R) - ሲዲ ዲስክ (CD disk)፣ በቅድሚያ የምንጠቀምበትን ሲዲ የመያዝ አቅም ማረጋገጥ አለብን። ይህን ለመጠቀም ኮምፒውተራችን የሲዲ መጻፊያ (CD Writer) እና የሲዲ መጻፊያው ፕሮግራም ሊኖረን የግድ ነው። (ለበለጠ ማብራሪያ ይህን መጎብኘት ነው፤ DeepBurner Free ወይም disk burning tools

 • ዲቪዲ (DVD) - ዲቪዲ ዲስክ (DVD disk)፣ ኮምፒውተራችን ዲቪዲ መጻፊያ (DVD Writer) እና የዲቪዲ መጻፊያ ፕሮግራም ሊኖረው ይገባል። (ለበለጠ ማብራሪያ ይህን መጎብኘት ነው፤ DeepBurner Free ወይም disk burning tools

የመጠባበቂያ ቅጂያችንን በተለያዩ ተንቀሳቃሽ የመረጃ ማጠራቀሚያ ቋቶች () የምናስቀምጥ ከሆነ በየቦታው የምናስቀምጠውን መረጃ መጠን መወሰን ይኖርብን ይሆናል።

ይህን ለማድረግ የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል ያስፈልጋል።

ደረጃ 1Custom size (bytes) በሚለው ሥፍራ የምንፈልገውን መጠን መምረጥ፤ ከዚያም የመጠባበቂያ ቅጂውን መጠን በስእሉ እንደሚታየው በባዶው ቦታ መሙላት፤

ስእል 10፤ የመጠን መወሰኛ ስፍራ (Custom size)

ስለመጠን (sizes) ጥቂት ነጥቦች

 • 1 ኪባ/KB (ኪሎባይት/kilobyte) = 1024 ባይትስ (bytes) - በኦፕን ኦፊስ የተጻፈ አንድ ገጽ ሰነድ 20ኪባ (kb) ገደማ ይሆናል።

 • 1 ሜባ/MB (ሜጋባይት/megabyte) = 1024 ኪባ/KB - በዲጂታል ካሜራ የተነሳ አንድ ፎቶ በግምት ከአንድ እስከ ሦስት ሜባ ይሆናል።

 • 1 ጂቢ/GB (ጊጋባይት/gigabyte) = 1024 ሜባ/MB - የግማሽ ሰዓት የዲቪዲ ጥራት ያለው ፊልም ተመሳሳይ መጠን ሊኖረው ይችላል።

ማስታወሻ፤ የመጠባበቂያ ቅጂያችንን ለሲዲ እና ለዲቪዲ በሚሆኑ የተለያዩ መጠኖች ስንከፋፍል (split) ኮቢያን እነዚህን ተከፋፍለው የተቀመጡ ፋይሎች በቀጥታ ወደ ተንቀሳቃሽ ማጠራቀሚያዎቹ አይገለብጣቸውም። ኮቢያን የፋይሎቹን የመጠባበቂያ ቅጂ የሚፈጥራቸውና የሚያስቀምጣቸው እዚያው ኮምፒውተራችን ላይ ነው። ስለዚህ ፋይሎቹን ወደ ሲዲ ወይም ዲቪዲዎቹ መገልበጥ (burn) እንዳለብን መዘንጋት የለብንም።

Password Protect፤ ይህ አገልግሎት ለመጠባበቂያ ቅጂዎቹን በይለፍ ቃል እንድንቆልፋቸው ያስችለናል። የመረጥነውን የይለፍ ቃል ለዚሁ በተተወዉት ሁለት ሳጥኖች ውስጥ መጻፍ በቂ ነው። ከዚያ ፋይሉን ለመፍታት/ለመክፈት (decompress) ስንፈልግ በቅድሚያ የይለፍ ቃሉን መስጠት አለብን ማለት ነው።

ማስታወሻ፤ ለመጠባበቂያ ቅጂዎቻችን የበለጠ ጥበቃ ለማድረግ ከፈለግን በይለፍ ቃል ከመቆለፍ የተለዩ ዘዴዎችን ማሰብ ይኖርብናል። ኮቢያን ባክአፕ (Cobian Backup) የመጠባበቂያ ቅጂዎችን በቀላሉ ኢንክሪፕት እንድናደርግ ያስችለናል፤ ዝርዝሩ በዚሁ ምእራፍ ክፍል 4. የመጠባበቂያ ቅጂ ፋይሎችን ኢንክሪፕት ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው በሚለው ርእስ ተዳሷል። በተጨማሪም በኮምፒውተራችንም ይሁን በውጫዊ ተንቀሳቃሽ ማጠራቀሚያዎች ውስጥ የሚገኙ መረጃዎችን ኢንክሪፕት ስለማድረግ VeraCrypt Hands-on Guide በሚለው ክፍል ሰፊ መረጃ ማግኘት ይቻላል።

Comment፤ ይህ ምርጫ ስለተደጎሰው የመጠባበቂያ ቅጂ ተጨማሪ መረጃዎችን እንድናሰፍር ይፈቅድልናል። ይህን ማስታወሻ መጻፍ ግን ግዴታ አይደለም።

3.1 የመጠበበቂያ ቅጂዎችን መፍታት/መዘርገፍ (Decompress)

ጠርዘን (compress) ያስቀመጥነውን የመጠባበቂያ ቅጂ ለመፍታት (decompress) የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል ያስፈልጋል።

ደረጃ 1፤ በቅድሚያ ቱልስ (Tools) ወደሚለው ክፍል መሔድ፣ ከዚያም በስሩ ከሚከፈቱት በርካታ አማራጮች መካከል “Decompressor” የሚለውን መምረጥ። በአጭሩ Select > Tools > Decompressor። ስእሉ ይህንን ያሳያል።

ስእል 3፤ የቱልስ (Tools) ሜኑ የዲኮምሬሰር (Decompressor) አማራጭ

ቀጥሎ የDecompressor መስኮት ይከፈታል፤ በስእሉ እንደሚታየው።

ስእል 4፤ የኮቢያን 10 ባክአፕ የዲኮምፖዘር መስኮት

ደረጃ 2፤ ቀጥሎ ይህንን ማዘዣ መጫን/ክሊክ፣ ለመክፈት የምንፈልገውን የተጠረዘ ፍይል ካለበት እንድንመርጥ ይጠይቀናል።

ደረጃ 3፤ በቅድሚያ (.zip or .7x file) የሚለውን መምረጥ፤ አስከትሎ የሚለውን መንካት/ክሊክ

ደረጃ 4፤ ተጠርዞ የተቀመጠውን ፋይል የምንፈታበትን (unpack) የምናደርግበትን ዳይሬክተሪ መምረጥ

ደረጃ 5፤ መጠባበቂያ ቅጂውን በውስጡ የምንፈታበትን ማህደር/ፎልደር የምንመርጥበትን መስኮት ለመክፈት ይህንን ማዘዣ መጫን/ክሊክ

ደረጃ 6፤ አንድ ማህደር/ፎልደር መምረጥ እና በመጫን/ኪሊክ ምርጫችንን ማረጋገጥ።

ወደዚህ ወደመረጥነው ፎልደር የገቡትን ፋይሎች ለማየት ዊንዶውስ ኤክስፕሎረርን (Windows Explorer) መጠቀም አለብን።

የመጠባበቂያ ቅጂ ፋይል ኢንክሪፕት የሚደረገው እንዴት ነው?

በዚህ ምእራፍ የሚዳሰሱ ጉዳዮች

4.0 ኢንክሪፕሽን (Encryption) ምንድን ነው

የመጠባበቂያ ቅጂዎቻቸውን ያልተፈቀለት ሰው እንዳያገኘው ወይም እንዳይከፍተው ማድረግ ለሚፈልጉ ሰዎች የኢንክሪፕሽን (Encryption) ተጠቃሚዎች ሊሆኑ ይችላሉ።

ኢንክሪፕሽን ያለን ዳታ የያዘውን መረጃ ወይም መልክእት በተለያየ መንገድ (encoding or scrambling) ሊነበብ የማይችል አድርጎ የሚያስቀምጥ ነው። በዚህ መልክ የተቀመጠን ዳታ በትክክል ለማግኘት፣ ለመክፈትና ለማንበብ የይለፍ ቃሉን የግድ ማግኘት ግዴታ ነው። ስለኢንክሪፕሽን ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት በኢንተርኔት ደኅንነት መጽሐፍ ምእራፍ 4. በኮምፒውተራችን ውስጥ ያሉ ስሱ መረጃዎችን እንዴት መጠበቅ ይቻላል? የሚለውን ማንበብ ይጠቅማል።

4.1 የመጠባበቂያ ቅጂን ኢንክሪፕት ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?

Strong encryption የሚለው ገበታ የምንፈልገውን የኢንክሪፕሽን ዘዴ እንድንመርጥ ያደርገናል።

ደረጃ 1Encryption type የሚለውን የአማራጮች ከረጢት ስንነካ/ክሊክ በስእሉ እንደሚታየው የተለያዩ የኢንክሪፕሽን መንገዶች ይዘረዘራሉ፤

ስእል 1፤ የኢንክሪፕሽን አይነቶች መዘርዘሪያ

ነገሩን ቀለል ለማድረግ፣ ከተዘረዘሩት መካከል Blowfish ወይም Rijndael (128 bits) የሚሉትን ዘዴዎች መምረጥ የተሻለ ይሆናል። እነዚህ ዘዴዎች ለመጠባበቂያ ቅጂዎቻችን አስተማማኝ ጥበቃ ይሰጡልናል፤ ኢንክሪፕት አድርገን ያስቀመጥነውን ፋይልም ትክክለኛውን የይለፍ ቃል በመስጠት በቀላሉ ልናገኘው እንችላለን።

ደረጃ 2፤ የምንፈልገውን የኢንክሪፕሽን አይነት መምረጥ

ማስታወሻRijndael እና Blowfish የተባሉት የኢንክሪፕሽን አይነቶች በሚሰጡት የደኅንነት ጥበቃ ደረጃ ተቀራራቢ ናቸው። DES የተባለው ኢንክሪፕት ለማድረግ በሚወስደው ጊዜ ፈጣን ነው፤ ሆኖም በጥበቃ ጥንካሬው ግን ደካማ ነው።

ደረጃ 3፤ ከታች በሚታዩት ሁለት ክፍት ቦታዎች/ሳጥኖች ውስጥ የመረጥነውን ጠንካራ የይለፍ ቃል ማስገባት/መጻፍ

ስእል 2፤ የኢንክሪፕሽን አይነት እና የይለፍ ቃል ማስገቢያ ቦታዎች

የምናስገባው የይለፍ ቃል ጥንካሬ 'Passphrase quality' በሚለው ቦታ ይታያል። ይህ ማመልከቻ ወደቀኝ በሔደ መጠን የይለፍ ቃሉ ጥንካሬ ይጨምራል። በኢንተርኔት ደኅንነት መጽሐፍ 3. አስተማማኝ የይለፍ (የምሥጢር) ቃል መፍጠር እና መጠቀም የሚለውን ምእራፍ እንዲሁም በአጠቃቀም መመሪያ ውስጥ አስተማማኝ የይለፍ ቃሎችን ስለመፍጠርና ሰለማከማቸት የሚያወሳውን ኪፓስ (KeePass) መመልከት ይጠቅማል።

ደረጃ 4፤ ይህንን በመንካት/ክሊክ ሒደቱን ማጠናቀቅ።

4.2 የመጠባበቂያ ቅጂን ዲክሪፕት ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?

ኢንክሪፕት ተደርጎ የተቀመጠን የመጠባበቂያ ቅጂ ዲክሪፕት (decrypt) ማድረግ ቀላልና ጊዜ የማይወስድ ሥራ ነው። የሚከተሉትን ደረጃዎች በመከተል የፈለግነውን ፋይል ዲክሪፕ ማድረግ ወይም መክፈት እንችላለን።

ደረጃ 1፤ ከታች በስእሉ እንደሚታየው መጀመሪያ “Tools” የሚለውን፣ ቀጥሎ በዚያ ከሚዘረዘሩት “Decrypter and Keys” የሚለውን መምረጥ። በአጭሩ ሲቀመጥ Select > Tools > Decrypter and Keys

ስእል 3፤ በቱልስ (Tools) ማስመረጫ ስር Decrypter and Keys አማራጭ ተመርጦ

ይህ ምርጫ ዲክሪፕት የማድረጊያውን ማለትም የ Decrypter and Keys መስኮት እንዲከፈት ያደርገዋል

ስእል 4፤ የኮቢያን ባክአፕ ዲክሪፕት ማድረጊያ ገጽ

ደረጃ 2፤ ዲክሪፕት ለማድረግ ማለትም ለመክፈት የምንፈልገውን ፋይል ለመምረጥ ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ

ደረጃ 3፤ ፋይሉ ዲክሪፕት ከተደረገ ወይም ከተከፈተው በኋላ የት እንደሚቀመጥ ለመወሰን ደግሞ ይህኛውን ማዘዣ መንካት/ክሊክ

ደረጃ 4፤ በክፍል 4.1 የመጠባበቂያ ቅጂን ኢንክሪፕት ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው? የመረጥነውን የኢንክሪፕሽን አይነት እዚህም Methods በሚለው ሥር ከሚቀርቡልን ምርጫውች መካከል መልሶ መምረጥ

ስእል 5፤ የዲክሮፕሽን ዘዴዎች (New Methods) አማራጮች ዝርዝር

ደረጃ 4፤ ከቀረቡት አማራጮ መካከል የመጠባበቂያ ቅጂ ፋይሉን ኢንክሪፕት ካደረግንበት ጋራ የሚመሳሰለውን ዘዴ መምረጥ

ደረጃ 5Passphrase በሚለው ቦታ ቀደም ሲል የሰጠነውን የይለፍ ቃል መጻፍ/ማስገባት

ደረጃ 6፤ ዲክሪፕት የሚለውን ይህን ማዘዣ መጫን/ክሊክ

ፋይሉ/ፋይሎቹ ቀደም ሲል በመረጥንላቸው ቦታ ይከፈታሉ ወይም ዲክሪፕት ይሆናሉ። ፋይሎቹ ኢንክሪፕት ከመደረጋቸው በፊት ተጠርዘው (compressed) ከሆነ ለመነበብ 3.1 የመጠበበቂያ ቅጂዎችን መፍታት/መዘርገፍ (Decompress) በተጠቀሰው መሠረት መፈታት (decompress) ይኖርባቸዋል።

የሚዘወተሩ ጥያቄዎች እና ክለሳ

5.0 የሚዘወተሩ ጥያቄዎች እና ክለሳ

ሣራ እና ሞቲ ለሰነዶቻቸው/ዶክመንቶቻቸው የመጠባበቂያ ቅጂ መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን ያውቃሉ። ከዚህ ቀደም በጋራ የሚጠቀሙበት ኮምፒውተር በቫይረስ በመጠቃቱ በርካታ ፋይሎች ጠፍተውባቸዋል። ከዚህ አኳያ ኮቢያን ባክአፕ () የመጠባበቂያ ቅጂዎችን በቀጥታ እና በየጊዜው ለማዘጋጀት እንደሚያስችል ተረድተዋል። ፕሮግራሙን ሥራ ለማስጀመር እና አሠራሩን በዝርዝር ለመረዳት ትንሽ ጊዜ እንደሚወስድም ተገንዝበዋል።

ሣራ ኮቢያን ባክአፕ በመደበኛነት የሚሰጠው መሠረታዊ አገልግሎት እንዴት እንደሚሠራ ስትረዳ መጠቀም እንዳለባት ወስናለነች። በዚህ መደበኛ አገልግሎት መጠባበቂያ ቅጂውን በተንቀሳቀሻ የመረጃ ማጠራቀሚያዎች (ዲቪዲ፣ ዩኤስቢ…) በመቅዳት ከቢሮዋ ውጭ በምትፈልገው ቦታ ልትሸሽገው እንደምትችል ማወቋ አስደስቷታል። የመጠባበቂያ ቅጂዎችን ጠርዞ ማስቀመጥ () በኮምፒውተሯ ላይ ያለውን ቦታ ለመቆጠብ ማስቻሉም ኮቢያን የወደደችበት ሌላው ምክንያት ነው። ሞቲ በበኩሉ፣ አንድ ፕሮግራም ዶክመንቶችን ኢንክሪፕት ማድረግ እና ለመጠባበቂያነት ቀድቶ ማሰቀመጥ መቻሉ ደስ አሰኝቶታል። ዶክመንቶቹን ከእርሱ በጣም ሩቅ በሆነ ሰርቨር ላይ ለማስቀመጥ ይህንኑ ለማድረግ የሚያስችለውን የኮቢያን አገልግሎት Backup to ftp server የበለጠ ለመረዳት እቅድ ይዟል።

ሁለቱም ስለ ኮቢያን ባክአፕ እንዲመለሱላቸው የሚፈልጓቸው ጥያቄዎች አሏቸው።

ጥያቄ፤ በዲቪዲ ላይ ያስቀመጥኩትን የመጠባበቂያ ቅጂ፣ የእኔ ባልሆነ ኮምፒውተር መፍታት (decompress) እና ዲክሪፕት (decrypt) ማድረግ እችላለሁ? ኢንተርኔት ካፌ ውስጥ ብከፍታቸውስ ችግር አለው?

መልስ፤ የኮቢያን ባክአፕ ፕሮግራም የተጫነበት እስከሆነ ድረስ በማንኛውም ኮምፒውተር የመጠባበቂያ ቅጂዎቹን መክፈት ይቻላል።

ጥያቄ፤ ኮምፒውተሬ በብዙ ፋይሎች ተሞልቷል፤ የቀረኝ ባዶ ቦታ ጥቂት ነው። ስለዚህም ፋይሎችን በመጠረዝ (compressing) ምን ያህል ቦታ ልቆጥብ እንደምችል አላውቅም። ይህን የሚያስረዳ ቀላል ምሳሌ ላገኝ እችላለሁ?

መልስ፤ ብዙውን ጊዜ በኮምፒውተራችን ላይ ካለው ቦታ አብዛኛው የሚያዘው በፎቶዎች፣ በቪዲዮ እና በድምጽ/ኦዲዮ ፋይሎች ነው። እነዚህ ፋይሎች ምን ያህል ቦታ እንደያዙብን ለማወቅ ማህደሮቻቸውን (ፎልደሮቻቸውን) በቀኝ-ንኬት ከፍቶ “ፕሮፐርቲስ (properties)” የሚለውን በመምረጥ ማረጋገጥ እንችላለን። ለምንፈልገው ጉዳይ በኮምፒውተሮቻችን ላይ በቂ ቦታ ካላገኘን፣ ቀደም ሲል የጠቀስናቸውን ፋይሎች በመጠባበቂያ ቅጂ መልክ ወደሌላ ተንቀሳቃሽ ማጠራቀሚያ በመገልበጥ ከኮምፒውተራችን ላይ ልናጠፋቸው እንችላለን።

ጥያቄ፤ ከኢንተርኔት ያገኘኋቸው ፕሮግራሞች በየጊዜው የተሻሻለ አይነቴ እንዳላቸው በመጥቀስ ይህንኑ እንድጭን ይጠይቁኛል። የኮቢያን ባክአፕን የተሻሻለ አይነቴ እንድጭን (download) ተጠይቄ ይህንኑ ባደርግ በፕሮግራሙ ጠርዤ እና ኢንክሪፕትድ አድርጌ ያስቀመጥኳቸውን ፋይሎች ድጋሚ አላገኛቸው ወይም ልከፍታቸው አልችል ይሆናል ብዬ እሰጋለሁ። ታዲያ የተሻሻሉ አይነቴዎችን መጫን አለብኝ?

መልስ፤ የተሻሻሉ አይነቴዎች አዳዲስ አሠራሮችን እና የደኅንነት ጥበቃ ማረጋገጫዎችን አካተው ሊመጡ ስለሚችሉ በተገኙ ጊዜ መጫኑ አግባብ ነው። የተሻሻለውን አይነቴ በመጫናችን ስንጠቀምበት የቆየነው ኮቢያን ባክአፕ ሥራው አይደናቀፍም። ማንኛውም የማሻሻያ አይነቴ ከቀድሞው ጋራ እንዲጣጣም ተደርጎ የሚሠራ ስለሆነ ቀደም ሲል በፈጠርናቸው የመጠባበቂያ ቅጂዎች ላይ የሚፈጥረው ችግር የለም።

ጥያቄ፤ ይህ ፕሮግራም በኮምፒውተሬ ላይ እንዳለ መታወቁ በራሱ ኢንክሪፕት ያደረጓቸው ነገሮች እንዳሉ አያጋልጥም?

መልስ፤ ኢንክሪፕት የተደረገ የመጠባበቂያ ቅጂን በኮምፒውተራችን ላይ መተው የለብንም። በተጨማሪም ኮቢያን ባክአፕ ኢንክሪፕት በማድረጊያነቱ ብዙም አይታወቅም፤ በእርግጥም ቀዳሚ አገልግሎቱ እርሱ አይደለም።

ጥያቄ፤ ፋይሎችን ኢንክሪፕት* ለማድረግ ከVeraCrypt ይልቅ ይህኛውን መጠቀም ይሻላልን?*

መልስ፤ በኮምፒውተራችን ላይ የሚገኙ ፋይሎችን ኢንክሪፕት ለማድረግ ትሩክሪፕትን መጠቀም ይመረጣል። ፕሮግራሙ ኢንክሪፕት የሚያደርግበት ዘዴ ጠንካራ ነው፣ በተጨማሪም ኢንክሪፕት ከተደረገው ቮልዩም ውስጥ የሚገኙ ፋይሎችን ማጥፋት ወይም አዲስ መጨመር ይቻላል። ኮቢያን ባክአፕን በመጠቀም በትሩክሪፕት ለተፈጠረ ቮልዩም የመጠባበቂያ ቅጂ መፍጠር እንደምንችል ግን መዘንጋት የለበትም።

ጥያቄየኮቢያን ባክአፕ 'Backup to ftp server' መጠቀም ከመጀመሬ በፊት ላውቀው የሚገባኝ ነገር አለ?

መልስ፤ በቅድሚያ የምንጠቀምበት ሰርቨር FTP የተባለውን አገልግሎት ይሰጥ እንደሆነ ማጣራት ይገባል። አገልግሎቱ ካለ ወደ ሰርቨሩ ለመግባት የሚያስችለውን ዝርዝር መረጃ (የተጠቃሚ ስም እና የይለፍ ቃል) ማወቅ አስፈላጊ ነው። የሚቻል ከሆነ የደኅንነት ደረጃው ላቅ ያለውን የFTP አይነቴ ማለትም SFTP የሚባለውን መጠቀም የተመረጠ ነው።

5.1 የክለሳ ጥያቄዎች

 • በኢንክሪመንታል () እና ዲፈረንሺያል () የመጠባበቂያ ቅጂ አፈጣጠር መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?
 • የመጠባበቂያ ቅጂዎች ምሥጢራዊ ደኅንነት አስተማማኝ ለማድረግ የተሻለው መንገድ የቱ ነው?
 • 1ጂቢ () መጠን ያለውን የመጠባበቂያ ቅጂ በዲቪዲ ዲስክ ላይ ለማስቀመጥ የሚቻለው እንዴት ነው?
 • ከመጠባበቂያ ቅጂ ውስጥ አንድ ፋይል ብቻ ለመክፈት (restore) የሚቻለው እንዴት ነው?
 • ኮምፒውተራችን በየሳምነቱ አርብ በቀጥታ ወይም በራሱ የመጠባበቂያ ቅጂውን እንዲያሻሽል ማዘዝ እንችላለን? መንገዱ እንዴት ነው?