ፋየርፎክስ ከማከያዎቹ ጋራ- አስተማማኝ የድር ማሰሻ

Updated 1 August 2014

መመሪያው በወቅቱ አልተሻሻለም፤ በቅርቡ ይሰረዛል

:Introduction

ዋና ገጽ

ሞዚላ ፋየርፎክስን ለመጫን ኮምፒውተራችን ምን ያስፈላገዋል?

 • ሁሉም ዓይነት የዊንዶውስ አይነቴዎች ይሠራሉ

በዚህ መመሪያ ጥቅም ላይ የዋሉ አይነቴዎች

 • Firefox 4.0.1
 • NoScript 2.1.0.5
 • Adblock Plus 1.3.8
 • Better Privacy 1.5.1
 • Beef Taco 1.3.3
 • GoogleSharing 0.20
 • HTTPS Everywhere 0.9.6

ለመጠቀም የሚያስፈልግ ፈቃድ/ላይሰንስ

 • በነጻ የሚገኝ እና ምንጩ የተገለጠ ሶፍትዌር ነው

ይህን መሣርያ መጠቀም ለመጀመር የሚፈጀው ጊዜ፦ 20 - 30 ደቂቃ

ምን ጥቅም እናገኛለን

 • ዓይነታቸው በበዛ ማከያዎች የተነሣ የድር መሳሻችን በርካታ አገልግሎቶችን ይሰጠናል፣ የኢንተርኔት ግንኙነታችን ምሥጢራዊነትና ደኅንነትም በእጅጉ ይጨምራል፤
 • ከአደጋኛ ፕሮግራሞች እና ከበካይ መካነ ድሮች ራሳችንን መከላከል እንችላለን
 • የሐሰሳ ታሪካችንን ሊጠቁም የሚችሉ፣ ማለትም የጎበኘናቸውን ድረ ገጾችና ያደረግነውን ነገር ሊጠቁም የሚችሉ አሻራውችን ከኮምፒውተራችን ላይ በአስተማማኝ ሁኔታ ማስወገድ እንችላለን።

ጄኤንዩ ሊኑክስ፣ ማክ እና እና ሌሎች የማይክሮሶፍት ዊንዶውስ ፕሮግራሞች፤

የሞዚላ ፋየርፎክስ ማሰሻ ለጂኤንዩ ሊኑክስለማክ ኦፐሬቲንግ ሲስተምለማይክሮሶፍት ዊንዶውስ እና ለሌሎች ፕሮግራሞች የሚሆኑ አይነቴዎች አሉት። ድረ ገጽ ማሰሻዎች ለማልዌር ብክለት መከስት ምክንያት ስለሚሆኑ ደኅንነታቸው የተረጋገጠ እንዲሆን ማድረግ በጣም አስፈላጊ ነው። ስለዚህም ደኅንነቱ አስተማምኝ ለሆነ የኢንተርኔት አገልግሎት ሞዚላ ፋየርፎክስ እና ለእዚሁ ጉዳይ የተሰናዱ ማከያዎችን መጠቀም ይመከራል። ከአስተማምኝ የደኅንነት ዋስትና አንጻር ሲመዘን ከነጻ ምንጮች የሚገኘው ፋየርፎክስ እንደ ኢንተርኔት ኤክስፕሎረር ካሉ እና ለገበያ ከሚቀርቡ የመካነ ድር ማሰሻዎች የተሻለ ጠቀሜታ ይሰጣል። ይኹንና ከሞዚላ ፋየርፎክስ ሌላ አማራጭ የመካነ ድር ማሰሻ ለመጠቀም ከወሰንን፣ ለጂኤንዩ ሊኑክስማክ እና ማይክሮሶፍት ዊንዶውስ የሚሆኑትን አማርጮች ከግርጌ ተዘርዝረዋል።

:Installation instructions

1.1 ይህን መሣሪያ መጠቀም ከመጀመራችን በፊት ልናውቃቸው የሚገቡ ነገሮች

የድር ማሰሻ (web browser) ምን እንደሆነ እናውቃለን ተብሎ ስለሚገመት ይህ ምዕራፍ ሞዚላ ፋየርፎክስ እንዴት እንደምንጠቀም አያብራራም። የምእራፉ ዋነኛ ዓላማ ተጨማሪ አገልግሎቶችን በመጠቀም እንዴት አስተማምኝ አሰሳ እንደምናደርግ መግለጽ ነው።

የሞዚላ ፋየርፎክስ ማከያዎች (Add-ons) ማሰሻው የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች አይነትና ጥራት የሚጨምሩ አስተማምኝ አነስተኛ ፕሮግራሞች ናቸው።

የሞዚላ ፋየርፎክስ ተሰኪዎች (Plugins) በአብዛኛው በሦስተኛ ወገኖች የሚሠሩ አነስተኛ ሶፍትዌሮች ሲሆኑ እነዚህ አካሎች ሶፍትዌራቸው ከፋየርፎክስ ማሰሻ ጋራ ተያይዞ አገልግሎት እንዲሰጠን ያደርጋሉ።

በእዚህ ምዕራፍ ከፋየርፎክስ የምናገኘው አገልግሎት ምሥጢራዊነት እና ደኅንነትን ለማሳደግ፣ በአጠቃላይ የኢንተርኔት አጠቃቀማችንን ደኅንነትና ጥራት ለማጎልበት የሚረዱ ሞዚላ ማከያዎችን እንዴት እንደምንጭን እና እንደምንጠቀም እንመለከታለን።

የኖስክሪፕት (NoScript) ማከያ (add-on) በዚህ ክፍል ተለይቶ ይገኛል 4.0 የኖስክሪፕት ማከያ አጠቃቀም ። ሌሎች ማከያዎች ደግሞ በዚህኛው ማህደር ይገኛሉ ተጨማሪ የፋየርፎክስ ማከያዎች

ማስታወሻ፦ አብዛኞቹ የማልዌር እና ስፓይዌር ብክለቶች የሚተላለፉት በመካነ ድሮች ናቸው። ድረ ገጾችን በተለይም በኢሜይል አድራሻዎቻችን የሚመጡትን ከመክፈታችንና መጎብኘታችን በፊት ደኅንነቱ የተጠበቀ መሆኑን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው። ድረ ገጹን ከመክፈታችን በፊት ከግርጌ በተዘረዘሩት የድረ ገጽ መፈተሻ (scanners) መፈተሽ ይመከራል፤

በተጨማሪ የሚከተሉትን መፈተሻዎች (scanners) በመጠቀም የመካነ ድሩን የተአማኒነት ደረጃ ማረጋገጥ እንችላለን።

የፋየርፎክስ አጫጫን እና አጠቃቀም

በእዚህ ክፍል የሚገኙ ርእሰ ጉዳዮች

2.0 ስለ ፋየርፎክስ

ፋየርፎክስ ኢንተርኔት በምንጠቀምበት ጊዜ የግንኙነታችንን ምሥጢራዊነትና ደኅንነት ለመጠበቅ የሚያስቸሉ ለአጠቃቀም ቀላል የሆኑ በርካታ የአሠራር ቀመሮች (settings) አሉት። እነዚህን ቀመሮች በፈለግን ጊዜ መቀየር እንችላለን፤ ምን ያህል ጊዜ መቀየር እንዳለብን የሚወሰነው በተለያዩ ሁኔታዎች ነው፤ ለምሳሌ

 • የግላችንን ኮምፒውተር የምንጠቀም እንዲሁም ሌሎች እንዲጠቀሙ የማንፈቅድ ከሆነ የአሠራር ቀመሩን (settings) አንድ ጊዜ ብቻ መምረጣና ማስቀመጥ ይበቃል።

 • በሥራ ቦታ ወይም ሕዝባዊ አገልግሎቶች በሚሰጡባቸው ሥፍራዎች ባለ የኢንተርኔት ግንኙነት የምንጠቀም ከሆነ ግን የአሠራር ቀመሩን (settings) እየደጋገሙ መቀያየር ይኖርብን ይሆናል።

 • ማስታወሻ*ፋየርፎክስን በተንቀሳቃሽ የመረጃ ማጠራቀሚያ ማህደር (ዩኤስቢ) ላይ በማኖር ይዘነው ልንንቀሳቀስ እንችላለን። ይህም የፋየርፎክስን አሠራር እንደምርጫችን አስተካከለን በኢንተርኔት ካፌ ጭምሮ በማንኛውም ኮምፒውተር ላይ ከፍተን ልንጠቀምበት እንችላለን። ሰለ ተንቀሳቃሽ ፋየርፎክስ ለመረዳት ተንቀሳቃሽ ፋየርፎክስ የሚለውን የተንቀሳቃሽ የደኅንነት መሣሪያዎች ክፍል መመልከት።

2.1 የፋየርፎክስ አጫጫን

የፋየርፎክስ አጫጫን ቀላል እና ቀጥተኛ ነው። ፋየርፎክስን ለመጫን የሚከተሉትን ደረጃዎች መመልከት፤

ደረጃ 1፦ ይህንን የመጫኛ ፋይል በእጥፍ ንኬት መክፈት፤ በመቀጠልም Open File - Security Warning የሚለው ሳጥን ይከፈታል። ከዚያም ይህንን ማዘዣ በመንካት ፋይሎቹን ከተጠረዙበት የሚፈቱበትን ሒደት Extracting የሚያሳየውን መከታተያ ሥራ ማስጀመር።

ከአፍታ በኋላ Welcome to the Firefox Setup Wizard የሚለው የመርጃ መስኮት ይከፈታል።

ደረጃ 2፦ መርጃው የሚያሳየንን የአጫጫን ደረጃዎች መከተል፤ በሒደቱም ተመርጠው የምናገኛቸውን መደበኛ የአሠራር ቀመሮች እና ምርጫዎች እንዳሉ እየተቀበሉ መሔድ።

ማስታወሻ፦ አዲሱ ምርጫችን ምን ለውጥ እንደሚያስከትልና ለምን እንደምናደርገው እርግጠኛ ካልሆንን በቀር ተመርጠው የምናገኛቸውን መደበኛ የአሠራር ቀመሮች እና ምርጫዎች እንዳሉ መተው ይመከራል።

2.2 የአጠቃላይ (General) አሠራሮች አማራጮች ክፍል አወቃቀር (Configure)

ፋየርፎክስን ለመውቀር የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል፤

ደረጃ 1በፋየርፎክስ የአገልግሎት አማራጮች ዝርዝር (ሜኑ) ውስጥ የሚከተለውን መንገድ መከተል Tools > Options...

ስዕል 1፤ Tools በሚባለው ክፍል ስር ከሚገኙት ምርጫዎች መጨራሻ ላይ የሚገኘው የOptions አማራጭ ተመርጦ ይታያል

ይህን ተከትሎ ከታች በስእሉ እንደሚታየው Options ራሱን በቻለ መስኮት ይከፈታል

ስዕል 2፤ በOptions መስኮት ከሚገኙት መካከል General የሚለው ንኡስ ክፍል በመደበኛ (default) አወቃቀሩ ተዋቅሮ ይታያል

ጥቆማበስዕል 2 እንደሚታየው General የሚለው ክፍል ወዲያውኑ ካልታየ ይህንን የመክፈቻ ምልክቱን መንካት/ክሊክ

General የሚባለው ንኡስ ክፍል መሠረታዊና ለሁሉም የሚሠሩ የፋየርፎክስ መዋቅሮችን ለመወሰን ያስችላል። ለምሳሌ ያህን ማሰሻው ሲከፈት ቀድሞ የሚከፈተውን ዋና ድረ ገጽ (home page) እንዲሁም ፋይሎችን ከኢንተርኔት ወደ ኮምፒውተራችን ስንገለብጥ ወይም ስንጭን የት እንደሚቀመጥ የምንወስነው በዚህ General ንኡስ ክፍል ነው።

When Firefox starts የሚለው ቁልቁል ተዘርጊ ሜኑ መደበኛ መዋቅር Show my home page ሲሆን የተመረጠው መደበኛ ዋና ገጽ ደግሞ Mozilla Firefox Start Page ነው።

ጥቆማ፦ ዋና ገጻችን እንዲሆን የምንፈልገውና የምንተማምንበት ሌላ ድረ ገጽ ካለ ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ

2.3 የምሥጢራዊነት (Privacy) አማራጮች ክፍል አወቃቀር (Configure)

Privacy ንኡስ ክፍል የማሰሻውን የምሥጢራዊነት እና የደኅንነት መጠበቂያ አማራጮችን የምንቆጣጠርበት ነው።

ደረጃ 1፦ ከታች በስእሉ የሚታየውን መስኮት ክፍል ለመክፈት ይህንን ምልክት/ማዘዣ መንካት/ክሊክ

ስዕል 3፤ የOptions መስኮት የPrivacy ንኡስ ክፍል

Privacy ክፍል በስሩ ሁለት ንኡስ ክፍሎች አሉት፤ እነርሱም History እና Location bar ይባላሉ።

 • የHistory ንኡስ ክፍል

  የHistory ክፍል የፋየርፎክስ ማሰሻን መጠቀም ከጀመርንበት ጊዜ አንስቶ የተጎበኙ ገጾችን ዝርዝር የሚያከማችበትን ‘'history (ታሪክ)’ ሥፍራ ለመቆጣጠር ያስችላል። Firefox will: በሚለው ማዘዣ ስር ያለው መደበኛ አወቃቀር Remember history የሚለው ነው። ይህ ማለት ማሰሻው የጎበኘናቸውድ ድረ ገጾች ዝርዝር ታሪክ ያስቀምጣል ማለት ነው። ስለዚህም የኢንተርኔት እንቅስቃሴያችንን ሚሥጢራዊነትንና ደኅንነት ለመጠበቅ ይቻል ዘንድ ምርጫው መቀየር አለበት።

የተጎበኙ ገጾችን ታሪክ ለማስወገድ የሚከተለውን ደረጃ መከተል ያስፈልጋል፤

ደረጃ 1Firefox will: የሚለውን ቁልቁል ተዘርጊ የምርጫ ዝርዝር መክፈት፤ ከዚያም በስእል 3 እንደሚታየው Never remember history የሚለውን መምረጥ

ደረጃ 2፦ ይህንን መክፈቻ መንካት/ክሊክ፤ ተከትሎ ከታች የሚታየው ሳጥን ይከፈታል።

ስዕል 4፤ የሐሰሳ ታሪካችንን ሁሉ የሚያጠፋው Clear All History መስኮት

ደረጃ 3፦ የተዘረዘሩትን የሚጠፉ/የሚደመሰሱ የሐሰሳ ታሪክ አይነቶች መምረጥ፤ ከዚያም ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክከፋየርፎክስ የሐሰሳ ታሪካችን ጋራ የተያያዙ መረጃዎችን ይጠፋሉ። በመጨረሻም ወደ Privacy ክፍል መመለስ።

 • የLocation bar ንኡስ ክፍል

  Location bar ንኡስ ክፍል በፋየርፎክስ የምናደርገውን ሐሰሳ ቀላል ለማድረግ መጻፍ የጀመርነውን የድረ ገጽ አድራሻ Universal Resource Locator (URL) በራሱ ለመሙላት ይሞክራል። ለዚህም የማሰሻ አድራሻዎችን፣ ኩኪዎችን (cookies)፣ እንዲሁም ቡክማርክ ከተደረጉ መካነ ድሮች የሚገኙ መረጃዎችን፣ እና የተመዘገቡ የድረ ገጽ ታሪኮችን ይጠቀማል። When using the location bar, suggest: የሚለው አገልግሎት መደበኛው የአሠራር መዋቅር History and Bookmarks የሚለው ነው። ሆኖም የኢንተርኔት ግንኙነታችንን ምሥጢራዊነት እና ደኅንነት ለመጠበቅ ይህ አማራጭ መለወጥ ይኖርበታል።

የሐሰሳ ታሪካችንን እና ልማዳችንን የሚያሳዩ መረጃዎችን ለማስወገድ የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል፤

ደረጃ 1When browsing, suggest የሚለውን ባለቁልቅል ተዘርጊ የምርጫ ዝርዝር መክፈት፤ ከዚያም ከታች በስእል 5 እንዲሁም ከላይ በስእል 3 እንደሚታየው ካሉት አማራጮች Nothing የሚለውን መምረጥ

ስዕል 5፤ የLocation bar ሳጥን Nothing የሚለው ተመርጦ ይታያል

ደረጃ 2፦ የመረጥነውን የአሠራር መዋቅር በማጽደቅ ወደ Options መስኮት ለመመለስ ይህንን ማረጋገጭ መንካት/ክሊክ

ማስታወሻ፦ ጊዜያዊና ቋሚ መረጃዎችን ፈጽሞ ስለማጽዳት ሰፊ መረጃ ለማግኘት ስለ ሲክሊነር የሚያወሳውን ምእራፍ መመልከት ይጠቅማል።

2.4 የደኅንነት (Security) አማራጮች ክፍል አወቃቀር (Configure)

የደኅንነት ክፍል ለሁለት ንኡስ ክፍሎች አሉት፤ የመጀመሪያው ክፍል ከውጭ የሚመጡ አዋኪ ሁኔታዎች ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሲሠራ፣ ሁለተኛው ወይም የPasswords ክፍሉ ደግሞ ከይለፍ ቃል ጋራ የተያያዙ ጉዳዮችን የምንቆጣጠርበት ነው።

ማስታወሻ፦ የይለፍ ቃልን እንዴት መፍጠር እና ማስቀመጥ እንደሚቻል የበለጠ መረጃ ለማግኘት ስለ ኪፓስ የሚያስረዳውን ምእራፍ መመልከት ይጠቅማል።

ደረጃ 1ከፋየርፎክስ ማሰሻ ራስጌ ከሚገኙት የአገልግሎት ክፍሎች Tools የሚለውን ከፍቶ በስሩ ከሚገኙት መካከል Optionsን መምረጥ Tools > Options...፤ ይህን ተከትሎ የOptions መስኮት ይከፈታል። በዚህ መስኮት Security የሚለውን ንኡስ ክፍል በመንካት/ክሊክ ከታች የሚታየውን ገጽ መክፈት፤

ስዕል 6፤ በOptions መስኮት ከሚገኙት የአገልግሎት ምርጫ ንኡስ ክፍሎች የ Security ክፈል ይታያል

ደረጃ 2፦ በመጀመሪያው ክፍል ተመርጦ የምናገኘውን መደበኛ የአሠራር ቀመር እንዳለ ለመቀበል (Accept)

 • የይለፍ ቃል ክፍል

የይለፍ ቃል ክፍል የይለፍ ቃሎችን ለመቆጣጠር ያስችለናል። ፋየርፎክስን ለመጀመሪያ ጊዜ ስንጭንና ስንጠቀም Remember passwords for sites የሚለው አገልግሎት በመደበኛ የአሠራር ቀመርነት ተመርጦ ወይም እንዲሠራ ተደርጎ እናገኘዋለን። ሆኖም የይለፍ ቃሎቻችንን ምሥጢራዊነትና ደኅንነት ለመጠበቅ ይህ አገልግሎት እንዳይሠራ መደረግ አለበት።

ደረጃ 1Remember passwords for sites የሚለው አገልግሎት እንዳይሠራ ለማድረግ በአንጻሩ የሚገኘውን (አል)መምረጫ ሳጥን መንካት/ክሊክ። ከዚያም የSecurity (የደኅንነት) ንኡስ ክፍሉን አሠራር አወቃቀር ለማጠናቀቅ በOptions መስኮት ግርጌ የሚገኘውን ይህንን ማረጋገጭ መንካት/ክሊክ

2.5 የተራቀቁ (Advanced) አማራጮች አወቃቀር (Configure)

ስሙ እንደሚጠቁመው Advanced የሚለው ንኡስ ክፍል የተዘጋጀው ልምድ ያላቸውን የፋየርፎክስ ተጠቃሚዎች ታሳቢ በማድረግ ነው። ይሁንና ሁሉም ዓይነት ተጠቃሚዎች በGeneral ንኡስ ክፍል ካሉት መካከል የሚከተሉትን ሁለት ምርጫዎች ቢያነቁ/ቢተገብሩ (enabling) የበለጠ ተጠቃሚ ይሆናሉ።

 • Warn me when websites try to redirect or reload the page የሚለውን ምርጫ ማንቃት/ማሠራት (enable) ፋየርፎክስ በቀጥታ ወደ ሌሎች ድረ ገጾች እንዳይወስደን ወይም ገጾቹ እኛ ሳናውቀው ራሳቸውን ወደ ኮምፒውተራችን በድጋሚ እንዳይጭኑ ለመከላከል ያግዛል።

 • Tell web sites I do not want to be tracked የሚለው ምርጫ ፋየርፎክስ የምንጎበኛቸው መካነ ድሮች የሐሰሳ ልምዳችንና እንቅስቃሴያችንን እንዳይመዘግቡና እንዳይከታተሉ ጥያቄ ለማቅረብ ያስችለናል። ምንም እንኳን መካነ ድሮች በሕግም ይሁን በቴክኒክ ይህን ጥያቄ እንዲያከብሩ የሚያስገድዳቸው ነገር ባይኖርም፣ አገልግሎቱን እንዲሠራ ማድረግ (ማንቃት) ጥቃት የማድረስ እድል ላላቸው የኢንተርኔት/ኦንላይን ማስታወቂያዎች ያለንን ተጋላጭነት መቀነስ እንችላለን። በሕግም ይሁን በቴክኒክ ይህንን ክልከላ የሚጥሱ ቢሆንምኳ ይህንን ምርጫ መጠቀም ከአደገኛ የኦንላይ ማስታወቂያዎች ተጋላጭነትን መቀነስ ይቻላል።

ስዕል 8፤ የ Advanced ንኡስ ክፍል ስር General የሚባለው አገልግሎት በመደበኛ አወቃቀር ይታያል

ደረጃ 1በስዕል 8 እንደሚታየው Warn me when websites try to redirect or reload the page የሚለውን አገልግሎት ሥራ ለማስጀመር (ለመቀስቀስ/Enable) ከፊቱ የሚገኘውን ሳጥን መንካት።

ደረጃ 2በስዕል 8 እንደሚታየው Tell web sites I do not want to be tracked የሚለውን አገልግሎት ሥራ ለማስጀመር (ለመቀስቀስ/Enable) ከፊቱ የሚገኘውን ሳጥን መንካት።

ደረጃ 3፦ ቀደም ሲል ያደረግናቸውን ለውጦች አረጋግጦ ሥራ ለማስጀመር እና ከAdvanced ንኡስ ክፍል ለመውጣት ይህንን ማረጋገጫ መንካት/ክሊክ

እንኳን ደስ ያለን! እነሆ ፋየርፎክስ ምሥጢራዊ እና ደኅንነቱ የተጠበቀ አሰሳ ለማድረግ በሚገባ ተዋቅሯል።

የፋየርፎክስ ማከያዎች (Add Ons) አጫጫን

በዚህ ገጽ የሚዳሰሱ ርእሰ ጉዳዮች

3.0 ስለ ሞዚላ ማከያዎች (Add-ons)

ከሞዚላ ምርቶች አኳያ ካየነው ማከያዎች (Add-ons) አዳዲስ አገልግሎቶችን ለማቅረብ እና ያሉትን ለማሻሻል የሚዘጋጁ ቀላል ፕሮግራሞች ናቸው። ማከያዎች አልፎ አልፎ ጭማሪዎች (extensions) ተብለው የሚጠሩም ሲሆን .xpi በሚል የፋይል ስያሜ መታወቂያ ይለያሉ። ለምሳሌ NoScript** የሚባለው የማከያ ፋይል ስያሜ *noscript-2.0.7-fx+sm+fn.xpi ይሆናል። የፋይሉ ስያሜ የመጨረሻ መለያ .xpi መሆኑን ልብ ይሏል።

plugin (ተሰኪዎች) የሚባሉት በሦስተኛ ወገኖች የሚዘጋጁና ሶፍትዌሮቻቸው ከፋየርፎክስ ማሰሻ ጋራ ተስማምተው እንዲሠሩ የሚያስችሉ ሶፍትዌሮች ናቸው። ለምሳሌ ከሚጠቀሱት መካከል ፍላሽ (Flash) ተሰኪ ይገኝበታል። ይህ ተሰኪ በAdobe Flash የተዘጋጁ ይዘቶችን በፋየርፎክስ ማሰሻ ከፍቶ ለማየት ያግዛል።

3.1 የሞዚላ ማከያዎችን መጫን

የሞዚላ ማከያዎችን ማውረድ እና መጫን ፈጣን እና ቀላል ሂደት ነው። የተለያዩ ማከያዎችን ለማውረድ እና ለመጫን የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል ይገባል፤

ደረጃ 1ፋየርፎክስ ለመክፈት Start > Mozilla Firefox የሚለውን መንገድ መከተል ወይም በኮምፒውተራችን የፋየርፎክስን ምልክት በእጥፍ ንኬት መክፈት።

ደረጃ 2በፋየርፎክስ ማሰሻ የአድራሻ ማስፈሪያ ላይ ይህንን መጻፍ/ማስገባት https://addons.mozilla.org/ እና Enter የሚለውን ማዘዣ መንካት። ይህም በቀጥታ Mozilla Add-ons for Firefox ወደሚለው የሞዚላ የማከያዎች መካነ ድር ይወስዳል።

ደረጃ 3፦ የምንፈልገውን ማከያ ስም በሞዚላ የማሰሻ ገጽ የማፈላለጊያ ቦታ ላይ መተየብ (ለምሣሌ Adblock Plus የተባለው ማከያ በማሳያነት ተመርጧል) ፤

ስእል 1፤ የሞዚላ ፋየርፎክስ ማከያዎች ማፈላለጊያ መደብ ላይ አድብሎክ ፕላስ (Adblock Plus) ተመርጦ ይታያል

ደረጃ 4፦ ከታች በስእሉ የሚታየው ገጽ ለመክፈት ይህንን ማዘዣ መንካት ወይም Enter የሚለውን ማዘዣ መንካት፤

ስእል 2፤ የፍለጋውን ውጤት የሚያሳየው የKeyword Match ገበታ ውጤቱን ያሳያል

ደረጃ 5፦ ይህንን ማዘዣ በመንካት/ክሊክ የሚከተለውን ገጽ መክፈት፤

ስእል 3፤ የማከያዎች ፍለጋ ውጤት ማሳያው ያገኘውን አድብሎክ ፕላስ (Adblock Plus) ያሳያል፤ መስኮቱ የAdd-on Search Results for Adblock Plus :: Add-ons for Firefox window ይባላል

ስእል 4፤ ከአድብሎክ ፕላስ ጋር የተዛመደው የሶፍትዌር መጫኛ መስኮት

ደረጃ 6፦ ማከያው ለአገልግሎት እንዲነቃ ከተደረገ (enabled) በኋላ ማከያውን መጫን ለመጀመር ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ። ፕሮግራሙ ተጭኖ ሲያበቃ ቀጥሎ የሚታየው ገጽ ይከሰታል፤

ስዕል 5፤ የAdd-on Search Results for Adblock Plus :: Add-ons for Firefox መስኮት

ደረጃ 7፦ የመጫን ሒደቱን ለማጠናቀቅ ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ

ይህን ተከትሎ ፋየርፎክስ በቀጥታ ራሱን ዘግቶ እንደገና ይጀመራል

ጥቆማፋየርፎክስ ወዲያውኑ ራሱን አጥፍቶ እንዳይጀምር ከፈለግን ይህንን ምልክትን መንካት፣ ከዚያም በስሩ ከሚዘረዘሩት ምርጫዎች Not Now የሚለውን መምረጥ

ደረጃ 8፦ ከታች የሚታየውን ገጽ ለመክፈት በፋየርፎክስ ቱልስ (Tools) ክፍል ከተዘረዘሩት መካከል Add-ons የሚለውን መምረጥ

ስእል 6፤ የቱልስ (Tools) ክፍል የማከያዎች መጨመሪያው Add-ons ተመርጦ ይታያል

ስእል 7፤ የማከያዎች መቆጣጠሪው (Add-ons Manager) አዲስ የተጫነውን የአድብሎክ ፕላስ ማከያ ያሳያል

ማስታወሻ፤ ከማይታወቁ ምንጮች የሚገኙ ማከያዎችን ፈጽሞ መጫን የለብንም። ደኅንነታችንን ለማረጋገጥ ምንግዜም ማከያዎችን መጫን የሚገባን ከዚህ ከራሱ ከሞዚላ መካነ ድር ብቻ ነው፤ https://addons.mozilla.org

3.2 የሞዚላ ማከያዎችን መሰንከል (Disable) ወይም ማስወገድ

በስእል 7 እንደሚታየው * Add-ons (የማከያዎች)* ንኡስ ክፍል የተጫንናቸውን ማከያዎች በሙሉ ያሳያል። በዚህ ዝርዝር የሚታይ ማንኛውም የሞዚላ ማከያ በቀላሉ በጊዜያዊነት መሰነከል (disabled) ይችላል፤ ይህን ለማድረግ ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ ነው። ማከያውን ከነጭራሹ ለማስወገድ ደግሞ ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ በቂ ነው። ይሁንና እነዚህ ትእዛዞቻችን ተግባር ላይ እንዲውሉ ፋየርፎክስ ተዘግቶ እንደገና እንዲጀምር ማድረግ ይገባል።

3.3 የሞዚላ ማከያዎችን የተሻሻሉ አይነቴዎች መጠቀም

ሁልጊዜም እንደሚሆነው ሁሉም ማከያዎች የሚዘጋጁት በየጊዜው ከሚሻሻለው የፋየርፎክስ አይነቴ ጋራ ተስማምተው እንዲሠሩ ታስቦ ነው። ማከያአዎቹም ይህንን ተከትሎ የተሻሻሉ አይነቴዎች ይዘጋጅላቸዋል። ስለዚህ እንደ ኔትወርኩ ጥንካሬ አዳዳዲስ ስሪት ማከያዎችን በቀጥታ (አውቶማቲካሊ) በራሳቸው እንዲጫኑ ማዘዝ ወይም በራሳችን መጫን ይኖርብናል።

ደረጃ 1፦ ይህንን ምልክት በመንካት ተዛማጁን የምርጫ ዝርዝር መክፈት፤ ከዚያም በስዕል 8 እንደሚታየው አዳዲስ ስሪቶችን በራሳችን መርጠን ለመጫን Check for updates የሚለውን መምረጥ

ስዕል 8፤ የማከያዎች መቆጣጠሪው (Add-ons Manager) ቁልፍ ተዘርጊ አማራጮችን ዘርዘሮ ያሳያል

ደረጃ 2፦ ሌላው አማራጭ በስዕል 8 እንደሚታየው የማከያዎች አዳዲስ አይነቴዎች በቀጥታ ለመጫን ይህንን Update Add-ons Automatically መምረጥ

3.4 የሞዚላ ተሰኪዎችን (Plugins) የተሻሻሉ አይነቴዎች መጠቀም

አልፎ አልፎ ጥቂት ተሰኪዎች (Plugins) የተሻሻ አይነቴያቸውን በራሳቸውን በቀጥታ መጫን አይችሉም፤ በመሆኑም ተጠቃሚዎች አዳዲስ ሞዚላ ተሰኪ (Mozilla Plugins) አይነቴዎችን እየፈለጉ እንዲጭኑ ይመከራሉ።

በጣም አስፈላጊ፦ ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ አዳዲስ ስሪቶችን እየፈለግን የተሻሻሉትን አይነቴዎች እንድንጭን እንመከራለን። በየጊዜው የሚለዋወጡ ከደኅንነት ጋር የተገናኙ ችግሮችን ለመቅረፍ ተሰኪዎች በየጊዜው መታደስ እና መሻሻል ይኖርባቸዋል።

ተሰኪዎቹን () በራሳችን አግኝተን ለመጫን ይህንን https://www.mozilla.com/plugincheck መስፈንጠሪያ በመንካት በቀጣዩ ስእል የሚታየውን መካነ ድር መክፈት፤

ስዕል 9፤ የሞዚላ ፋየርፎክስ ተሰኪዎች ማመሳከሪያ (Mozilla Firefox Plugins Check) ገጽ

የተሻሻሉ አይነቴዎቻቸው በኮምፒውተራችን ላይ ያልተጫኑትን ተሰኪዎች መርጦ መጫን። ይህን ለማድረግ ተዛማጁን አዝራር () መንካትና በገጹ የሚታየውን ትእዛዝ መከተል ነው።

የማይታወቅ ወይም የማያስፈልግ ተሰኪ ለመሰንከል (disable) የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል፤

ደረጃ 1የማከያ መቆጣጠሪያውን (Add-ons Manager) ለመክፈት በፋየርፎክስ ማሰሻ ውስጥ የሚከተለውን መንገድ መከተል Tools > Add-ons

ደረጃ 2የሞዚላ ፋየርፎክስን (Mozilla Firefox) ሙሉ የተሰኪዎች (Plugins) ዝርዝር ለመመልከት Plugins የሚለውን ክፍል መንካት/ክሊክ። በመቀጠልም ለመሰንከት () የፈለግነውን ተሰኪ መለየትና ይህንን ማዘዣ መንካት

የኖስክሪፕት ማከያ አጠቃቀም

በዚህ ገጽ የሚዳሰሱ ርእሰ ጉዳዮች ዝርዝር

4.0 ስለኖስክሪፕት (NoScript)

ኖስክሪፕት (NoScript) በጣም ጠቃሚ የሆነ የሞዚላ ማከያ ሲሆን ኮምፒውተራችን በአደገኛ መካነ ድሮች እንዳይጠቃ ይከላከላል። ኖስክሪፕት እምነት የምንጥልንባቸውን ደረ ገጾች የሚመዘግብበት ‘ነጭ መዝገብ (white list)’ አለው። በዚህ መዝገብ ያላካተትናቸው ሌሎቹ መካነ ድሮች በሙሉ ደኅንነታችንን ለአደጋ ሊያጋልጡ የሚችሉ ተደርገው ይቆጠራሉ፤ ስለዚህም ማእቀብ ይደረግባቸዋል፤ በከፈትናቸው ቁጥር ምርመራ ተደርጎባቸው ልናሳልፋቸው ይገባል ማለት ነው። በዚህ ወቅት መካነ ድሩን ወደ መጩ መዝገብ ልናስገባው እንችላለን።

ኖስክሪፕት (NoScript) ሁሉንም በድረ ገጾች ላይ የሚታዩ ቋሚ ማስታወቂያዎች (banners)፣ ብቅጥልቅ ባይ ማስጣወቂያዎች (pop-up advertisements)፣ ጃቫስ-ክሪፕት (JavaScript) እና ተዛማጅ የጃቫ (Java) ኮዶችን እንዲሁም ሌሎች አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ የመካነ ድር አካሎችን ያግዳል። ኖስክሪፕት የከፈትነውን መካነ ድር በትክክል ለማሳየት የሚያስፈልጉትን ይዘቶች ከጎጂዎቹ መለየት አይችልም። ስለዚህም ሙሉ ይዘታቸውን የምናምናቸውን መካነ ድሮች በመለየት እንዳይታገዱ ማድረግ የተጠቃሚው ድርሻ ነው።

4.1 ኖስክሪፕትን መጠቀም

ኖስክሪፕት መጠቀም ከመጀመራችን በፊት በትክክል መጫኑን ማረጋገጥ አለብን። ይህን ለማረጋገጥ በሞዚላ ማሰሻ ውስጥ ** Tools > Add-ons** በሚለው መንገድ በመሔድ የማከያ (Add-ons) መስኮቱን መቀስቀስ (activate) እና በትክክል መጫኑን ማረጋገጥ አለብን።

ጥቆማ፦ ምንም እንኳ ኖስክሪፕት ለመጀመሪያ ጊዜ ስንጠቀምበት ፈታኝ ቢመስልም (አዘውትረን የምንጎበኛቸው መካነ ድሮች በአግባቡ ተከፍተው ለመታየት ባለመቻላቸው)፤ ሆኖም በሒደት ፕሮግራሙ በቀጥታ በራሱ በሚያደርገው እገዳ ተጠቃሚዎች እንሆናለን። በተደጋጋሚ የሚመጡ አብሻቂ ማስታወቂያዎችን፣ ብቅ ጥልቅ ባይ መልእክቶችን እና መካነ ድር ታከው የሚመጡ አደገኛ ገጾችን በማገድ ያገለግለናል።

ኖስክሪፕት() ጃቫስክሪፕት (JavaScript)አዶቤ ፍላሽ (Adobe Flash) ወይም ሊላ ስክሪፕት መሳይ ነገር መኖሩን እስኪያረጋግጥ ድረስ ከእይታ ውጭ ሆኖ ተግባሩን ያከናውናል። ኖስክሪፕት የተገኘውን ስክሪፕት ሲያግድ በሚከተለው ማሳያ ላይ እንደተገለጸው መረጃው በፋየርፎክስ መስኮት ግርጌ ይታያል፤

ስእል 1፤ የኖስክሪፕት መግለጫ ሰሌዳ

የኖስክሪፕት መግለጫ ሰሌዳ የትኞቹ ነገሮች (objects) (ለምሳሌ ማስታወቂያዎች እና ብቅ ጥልቅ ባይ መልዕክቶች) እና ስክሪፕቶች በኮምፒውተራችን ሲስተም ላይ ለመከፈት እንዳይችሉ እንደተደረጉ ያሳያል። የሚከተሉት ሁለት ስእሎች በሥራ ላይ የሚገኝ ኖስክሪፕት ዋነኛ ማሳያዎች ናቸው። ስእል 2ኖስክሪፕት አዶቤ ፍላሽ ፕሌየር ውስጥ የተሠራ ማስታወቂያን በተሳካ ሁኔታ አግዶ ይታያል።

ስዕል 2፤ ኖስክሪፕት በንግድ ድረ ገጽ ውስጥ የተካተተን ብቅ ጥለቅ ባይ ማስታወቂያ ሲያግድ የሚያሳይ ምሳሌ

በስእል 3 የትዊተር መካነ ድር፣ ገጹን ለመመልከት (ቢያንስ ለጊዜያው) ጃቫስክሪፕትን መቀስቀስ/እንዲሠራ ማድረግ (enabled) የግድ እንደሚያስፈልግ የሚያስታውስ መልእክት ያሳያል።

ስእል 3፤ የትዊተር ገጽ ጃቫስክሪፕት እንዲቀሰቀስ ሲጠይቅ

ኖስክሪፕት በአደገኛ እና በአስተማምኝ ኮዶች መካከል ያለውን ልዩነት ስለማይለይ እጅግ ጠቃሚ የሆኑ አገልግሎቶች (ለምሳሌ የቱልባር ቁልፍ) ሊሰወሩ ይችላሉ። አንዳንድ ድረ ገጾች ስክሪፕት ወይም ስክሪፕት መለስ ይዘቶችን ሊይዙ ይችላሉ። ለምሳሌ እንደ www.youtube.com ያሉ ዌብሳይቶች ሦስት የስክሪፕት ምንጮች አሏቸው፤

ስእል 4፤ የኖስክሪፕት መግለጫ ሰሌዳ የOptions ንኡስ ክፍል ምሳሌ

በእንዲህ ያለ ሁኔታ የታገዱ ስክሪፕቶችን ለመፍታት/ለምፍቀድ ይህንን Temporarily Allow [website name] የሚለውን ማዘዣ መምረጥ ይቻላል፤ (በዚህ ማሳያ የሚከተለውን ይመስላል Temporarily allow youtube.com)። ይህንንም አድርገን ገጹን ማየት አዳጋች ከሆነ ለማየት የምንፈቀድናቸውን መካነ ድሮች ዝቅተኛ ቁጥር በሙከራ መወሰን ይኖርብናል። ዩቲዩብን (YouTube) በሚገባ ለመመልከት፣ Temporarily allow youtube.com እና Temporarily allow ytimg.com የሚሉትን አማራጮች መምረጥ አለብን።

ማስጠንቀቂያ!፦ በምንም ሁኔታ ቢሆን Allow Scripts Globally (dangerous) የሚለውን አማራጭ መጠቀም የለብንም፤ ። በተቻለ መጠን ይህንን Allow all from this page የሚለውን አማራጭም ከመምረጥ መቆጠብ አለብን። በጊዜ ሂደት ስክሪፕቶችን እንድንፈቅድ የሚያስገድድ ነገር ቢፈጠር ለማናምናቸው ገጾች ብቻ መፍቀድ እና እሱም በጊዜያዊነት መሆን ይኖርበታል። የኢንተርኔት ግንኙነታችንን አደጋ ላይ ለመጣል ለአንዲት ቅጽበት በአደገኛ ገጽ መጠቃት ብቻ እንደሚበቃ አለመርሳት ነው።

4.2 ስለ ክሊክጃኪንግ እና ክሮስ-ሳይት ስክሪፕቲንግ (XXS) ጥቃት

ኖስክሪፕት የኮንፒውተሩ ሲስተማችንን ከክሮስ-ሳይት ስክሪፕቲንግ (Cross-site scripting) እና ከክሊኪጃኪንግ (clickjacking) እንዲከላከልልን አድርገን ልናዋቅረው እንችላለን። ክሮስ-ሳይት ስክሪፕት ሰርጎ ገቦች (ሃከሮች) እና ሌሎች ሰርሳሪዎች አደገኛ ኮዶችን ወደ ድረገጽ ውስጥ ለማስገባት የሚችሉበት የኮምፒውተሮች ደካማ ጎን ነው። ለምሳሌ ያህል ክሊክጃኪንግ ከሚከሰትባቸው አጋጣሚዎች አንዱን ብናይ፣ አንድ ተግባር ለመፈጸም አንድ ቁልፍ ስንጫን በቁልፉ ትእዛዝ ውስጥ የተደበቀ ሌላ ኮድ ወይም ስክሪፕት ጥቃት ሊያደርስብን ይችላል። ኖስክሪፕት እስካልተጠቀምን ድረስ ሁለቱም ጥቃቶች ከእይታችን ውጪ ሊያጠቁን ይችላሉ።

የክሊክጃኪንግ ጥቃት ሲፈጸምብን ወይም ጥቃቱ እየተካሔድ ሳለ ከታች በስእሉ የሚታየውን የመሰለ መስኮት ይከፈታል፤

ስዕል 5፤ የክሊክጃኪንግ ምሳሌ / UI Redressing Attempt window

የክሊክጃኪንግን ጥቃት ለመከላከል በዊንዶው ላይ የሚስተዋሉትን መመሪያዎች መከተል ያስፈጋል። በመቀጠል ይህንን ማዘዣ መንካት

ተጨማሪ የፋየርፎክስ ማከያዎች

በዚህ ገጽ የሚገኙ ርእሰ ጉዳዮች

5.0 ስለ ማከያዎች (Add-ons)

በዚህ ክፍል የተዘረዘሩት ሞዚላ ፋየርፎክስ ማከያዎች የኢንተርኔት ሐሰሳችንን ምሥጢራዊነትና ደኅንነት እንዲሁም ማንነታችን መደበቁን ለማረጋገት የሚጠቅሙ ናቸው። ማከያዎቹን ለመጫን ይህንን ፋየርፎክስ የሚለውን ክፍል ማንበብ ይጠቅማል።

5.1 ስለ አድብሎክ ፕላስ (Adblock Plus) አጠቃቀም

አድብሎክ ፕላስ ማስታወቂያዎች በራሳቸው እየተከፈቱ እንዳያውኩን ለማጣራትና ለማገድ የተዘጋጀ ማከያ ነው። ፋየርፎክስ ተዘግቶ ከተከፈተ እና የአድብሎክ ፕላስ ማከያ በአግባቡ ከተጫነ በኋላ Add Adblock Plus filter subscription የሚለው መስኮት ይከፈታል።

ደረጃ 1Please choose a filter subscription የሚለውን ባለ ቁልቁል ተዘርጊ የምርጫ ዝርዝር መክፈት፤ በመቀጠልም በስእሉ እንደሚታየው የምንጠቀምበትን ቋንቋ መምረጥ

ስእል 1፤ የአድብሎክ ፕላስ ማጣሪያ መምረጫ (Add Adblock Plus filter subscription) መስኮት ከፋንቦይ (Fanboy) ዝርዝር ጋር

ደረጃ 2፦ ይህንን ምርጫ ለማጽደቅ ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ። ከዚህ በኋላ በማጣሪያው የተዘረዘሩት ማስታወቂያዎች ሁሉ መታየት ያቆማሉ።

5.2 ስለ ቤተር ፕራይቬሲ (Better Privacy) አጠቃቀም

ቤተር ፕራይቬሲ (Better Privacy) ማለት የሞዚላ ፋየርፎክስ ማከያ ሲሆን ኤልኤስኦ (LSO) (Local Shared Objects) የሚባሉ ኩኪዎችን ለመከላከል የሚጠቅም ነው። እነዚህ ኩኪዎች በፍላሽ ስክሪፕት አማካይነት በኮንፒውተራችን ላይ ሊጫኑ የሚችሉ ናቸው። እነዚህ ኩኪዎች በተለመደው የፋየርፎክስ ማጽጃ የማይወገዱ ናቸው።

5.3 ስለ ቢፍ ታኮ (Beef Taco) አጠቃቀም (Targeted Advertising Cookies Opt-Out)

ቢፍ ታኮ (Beef Taco) የሞዚላ ፋየርፎክስ ማከያ ሲሆን እንደ ጉግልማይክሮሶፍት እና ያሁ ያሉ ኩባንያዎች ከሚለቋቸው ማስታወቂያዎች ጋር ተያይዘው የሚመጡትን ኩኪሶች ለመቆጣጠር ይረዳል። Targeted Advertising Cookies Opt-Out የሚባሉትን ኩኮዎች በቀጥታና እንዲያጠፋቸው ተደርጎ ሊዋቀር ይችላል። ይሁንና ልምድ እና የተሻለ እውቀት ያላቸው ተጠቃሚዎች የሚፈልጓቸውን እና የማይፈልጓቸውን ኩኪዎች ለይተው እንዲያስቀምጡ ምርጫዎች አሉት።

5.4 ስለ ጉግልሼሪንግ (GoogleSharing) አጠቃቀም

ጉግልሼሪንግ ልዩ የሆነ ተገልጋዩን የሚሸሽግ የፕሮክሲ ብልሃት ሲሆን ጎግል የትኛው ጥያቄ ከየትኛው ወገን እንደመጣ እንዳያውቅ የሚያደርግ ነው። ይህም ጉግል ከማሰሻ ደረ ገጻችን መረጃ እንዳይሰበስብ ጉግልሼሪንግ ይከላከላል። ከዚህም በላይ ጉግል ያልሆኑ ትራፊኮች እንቅስቃሴያቸው አይቋረጥም እንዲሁም ወደሌላ አቅጣጫ እንዲሄዱ አይገደዱም።

በተሳካ ሁኔታ ጉግልስሃሪንግን ከጫንን በኋላ ከተዛማጅ ቁልፉ ጋር በፋየርፎክስ ማከያዎች ሰሌዳ በስተግርጌ በቀኝ በኩል እንደሚከተለው ይታያል፤

ጉግልሼሪንግ ምንም መዋቀር ሳያስፈልገው ከጀርባ በጸጥታ ሥራውን ይሰራል። በሁሉም የደህንነት እና ሚስጢር ብልሃት አማራጮች ላይ እንደሚሆነው፣ የደህንነት ጥራቱ እየጎለበተ ሲሄድ በፍጥነት እና በጥራት ላይ የግልብጥ ምዝነት ይኖራል። ፍጥነት የምንፈልግበት ሁኔታ ላይ ካለን በቀላሉ ጉግልሼሪንግ የሚለውን ለማግኘት ቁልፉን እንደሚከተለው መጫን

5.5 ስለ ኤችቲቲፒኤስ (HTTPS Everywhere) አጠቃቀም

ኤችቲቲፒኤስ ኤቭሪዌህር (HTTPS Everywhere) የሞዚላ ፋየርፎክስ ቅጥያ ሲሆን ከተወሰኑ መካነ ድሮች ጋር ኢንክሪፕት የተደረገ (https) ግንኙነት እንዲኖረን የሚያረጋግጥልን ነው። በርካታ መካነ ድሮች/ዌብሳይቶች ኢንክሪፕት የማድረግ አገልግሎት ቢኖራቸውም ብዙ ጊዜ ግን ኢንክሪፕትድ ያልሆነ (http) አድራሻ ሲጠቀሙ ሊገኙ ይችላሉ።

ስእል 2፤ የHTTPS Everywhere አገልግሎት አማራጮች ማሳያ ገጽ

የኤችቲቲፒኤስ (HTTPS Everywhere) ማከያ ሁሉንም የድረ ገጽ አድራሻ ምርጫዎች ወደ HTTPS ፕሮቶኮል በመቀየር ችግሩን ይፈታልናል። ከፈለግናቸው መካነ ድሮች ጋራ የምናደርገው ግንኙነት ደኅንነቱና ምሥጢራዊነቱ የተጠበቀ መሆኑን ያረጋግጥልናል።

ተንቀሳቃሽ ፋየርፎክስ

1.0 በሚጫነው (Installed) እና በተንቀሳቃሹ የፋየርፎክስ (Firefox) አይነቴዎች መካከል ያለው ልዩነት

ተንቀሳቃሽ መሣሪያዎቹ በምንጠቀምበት ኮምፒውተር ላይ አይጫኑም፣ ይህም ፕሮግራሞቹ እንዳሉንም ሆነ እንደምንጠቀምባቸው እንዳይታወቅብን ሊያደርግልን ይችላል። ሆኖም ተንቀሳቃሽ የውጫዊ ቅንጣቶቻችን (external device) ወይም የማስታወሻ ቋታችን (USB memory stick) እና የተንቀሳቃሽ መሣሪያዎቻችን (portable tools) ደኅንነት እንደምንጠቀምበት ኮምፒውተር ጤንነት እንደሚወሰን መዘንጋት የለብንም። ኮምፒውተሩ የተበከለ ከሆነ ለአድዌር፣ ለማልዌር፣ ለስፓይዌር እና ለቫይረስ ሊጋለጡ ይችላሉ።

በተንቀሳቃሽ ፋየርፎክስ (Portable Firefox) አይነቴ እና በኮምፒውተር ላይ በሚጫነው አይነቴ መካከል ምንም የአገልግሎት ልዩነት የለም።

2.0 ተንቀሳቃሽ ፋየርፎክስ መጫን እና መጠቀም (Download and Extract)

ተንቀሳቃሽ ፋየርፎክስን (Firefox Portable) ለመጫን እና አውጥቶ/ገልብጦ (extracting) ለመጠቀም የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል ያስፈልጋል።

ደረጃ 1፦ ወደ መጫኛው ድረ ገጽ ለመሔድ ይህንን http://portableapps.com/apps/internet/firefox_portable መስፈንጠሪያ መንካት/ክሊክ

ደረጃ 2፦ ይህንን የመጫኛ ማዘዣ በመንካት/ክሊክ የመጫኛውን ገጽ ምንጭ መክፈት።

ደረጃ 3፦ ይህንን ማዘዣ በመንካት/ክሊክ የመጫኛውን ፋይል በምንፈልገው ቦታ ማኖር/ማስቀመጥ (save)። ከዚያም ወዳኖርንበት ቦታ መሔድ።

ደረጃ 4፦ ፋይሉን ወዳኖርንበት ቦታ በመሔድ ይህንን በእጥፍ ንኬት መክፈት፤ ተከትሎ Open File - Security Warning የሚለው የማዘዣ ሳጥን ይከፈታል። በሳጥኑ ውስጥ የሚታየውን የሚለውን ማዘዣ መንካት/ክሊክMozilla Firefox, Portable Edition | Portableapps.com Installer የሚል መስኮት ይከፈታል።

ደረጃ 5፦ ከታች የሚታየውን ገጽ ለመክፈት ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ

ስእል 2፤ የመጫኛ ቦታ መምረጫ (Choose Install Location) መስኮት

ደረጃ 6፦ አሁንም ከታች የሚታየውን የፎልደር ማሰሻ መስኮት መስኮት ለመክፈት ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ

ስእል 3፤ የፎልደር ማሰሻ (Browse for Folder) መስኮት

ደረጃ 7በስእል 3 እንደሚታየው ወደምንፈልገው ተንቀሳቃሽ የማስታወሻ ቅንጣት ወይም የማስታወሻ ቋት (USB memory stick) መሔድ፤ ከዚያም የሞዚላ ፋየርፎክስ ተንቀሳቃሽ አይነቴ (Mozilla Firefox, Portable Edition) እንዲቀመጥበት የመረጥነውን ትክክለኛ መዳረሻ መሆኑን ለማረጋገጥ ይህንን ማዘዣ መንካት። ወደ መጫኛ ቦታ መምረጫ (Choose Install Location) መስኮት መመለስ።

ደረጃ 8ተንቀሳቃሽ ፋየርፎክስን (Portable Firefox) የመገልበጥ (extracting) ሒደት ለመጀመር ይህንን ማዘዣ መንካት። ሒደቱ ሲጠናቀቅም ይህንኑ ለማረጋገጥ የሚለውን መንካት። ወደ ተንቀሳቃሽ የማስታወሻ ቅንጣት ወይም የማስታወሻ ቋት (USB memory stick) በመሔድ የሞዚላ ፋየርፎክስ ተንቀሳቃሽ አይነቴ (Mozilla Firefox, Portable Edition) ፋይል መኖሩን ማረጋገጥ።

ደረጃ 9፦ ተንቀሳቃሽ የማስታወሻ ቅንጣት (removable device) ወይም የማስታወሻ ቋት (USB memory stick) ስንከፍተው በስእሉ የሚታየውን መምሰል አለበት።

ስእል 4፤ አዲስ የተጫነው የሞዚላ ፋየርፎክስ ተንቀሳቃሽ አይነቴ በተንቀሳቃሽ ቅንጣቱ/ቋቱ ፎልደር/ማህደር ውስጥ በሰማያዊ ቀልሞ ይታያል

ደረጃ 10የተንቀሳቃሽ ፋየርፎክስ (Firefox Portable) ማህደር/ፎልደርን መክፈት፤ ከዚያም ይህንን ፋይል በእጥፍ-ንኬት በመክፈት ተንቀሳቃሽ ፋየርፎክስን መጠቀም መጀመር።

ስለ ፕሮግራሙ አሠራርና አጠቃቀም ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ስለ ፋየርፎክስ (Firefox) የሚያወሳውን ምእራፍ መመልከት ይጠቅማል።

የሚዘወተሩ ጥያቄዎች እና ክለሳ

6.0 የሚዘወተሩ ጥያቄዎች እና ክለሳ

ጸጋዬ እና ገብረ መድኅን ስለ ጥቂት የፋየርፎክስ ማከያ የተሰጣቸውን ማብራሪያ እና ጥቅሙን በሚገባ ተረድተዋል። ይሁንና ስለ ሌሎቹ ማከያዎች ተጨማሪ ጥየቄዎች አሏቸው። ቤተልሔም ጠጠር ያሉትን ማከያዎች ምንነት ለማስረዳት ዝግጁ ነች።

*ጥያቄ፦ ራሳችንን ከአደገኛ ዌብሳይቶች ለመጠበቅ ብዙ የተለያዩ ማከያዎችን የምንጠቀመው ለምንድን ነው? ለምሳሌ ኖስክሪፕት ከአደገኛ ስክሪፕቶች የሚጠብቀኝ ከሆነ ለምድን ነው ተመሳሳይ አገልግሎት የሚሰጡ ማከያዎችን የምንጠቀመው?*

*መልስ፦ በአጠቃላይ ተመሳሳይ የደህንነት ስጋቶችን ለመቀነስ ከአንድ በላይ መሣሪያ መጠቀም የሚመከር ሐሳብ ነው። (ፀረ ቫይረስ ፕሮግራሞች እርስ በርስ ስለሚጋጩ ይህ ሕግ አይመለከታቸውም።) እነዚህ የፋየርፎክስ ማከያዎች ማሰሻችንን ከተለያየ ጥቃት ለመከላከል የተለያየ ብልሃት ይጠቀማሉ። ለምሳሌ ኖስክሪፕት ከማናውቃቸው መካነ ድሮች የሚመጡ ስክሪፕቶችን ያግዳል። ይሁንና ተጠቃሚዎች ብዙ ጊዜ የሚጎበኟቸውን መካነ ድሮች 'በነጩ መዝገብ (whitelist)' እንዲካተቱ የማድረግ አዝማሚያ ስላላቸው መካነድሮቹ አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ ስክሪፕቶችን ወደ ሲስተማችን ሊጭኑብን ይችላሉ። የኖስክሪፕት ተጠቃሚዎች የማያውቋቸው ገጾች በጊዜያዊነት ተከፍተው ስክሪፕቶቻቸውን እንዲጭኑና ገጹን ማየት እንዲችሉ ያደርጋሉ። ይህም ቢሆን አደጋ ሊኖረው ይችላል።*

6.1 የክለሳ ጥያቄዎች

 • በማሰሻችን ላይ የሚቀሩ ጊዜያዊ የኢንተርኔት አሰሳ ታሪክቻችንን፣ ኩኪዎችን እና ካቺ (cache) ከማሰሻው ፈጽሞ ማጥፋት የሚቻለው እንዴት ነው?
 • ኖስክሪፕት የኮንፒሚውተር ሲስተማችንን የሚጠብቅልን ከምን ዓይነት ጥቃትን ነው?