ተንቀሳቃሽ ጂፒጂ4ዩኤስቢ

Updated21 July 2014

መመሪያው በወቅቱ አልተሻሻለም፤ በቅርቡ ይሰረዛል

ጂፒጂ4ዩኤስቢ (gpg4usb) የኢሜይል መልእክቶችን እና ፋይሎችን ኢንክሪፕት ለማድረግ የሚያገለግል፣ በነጻ የሚገኝ፣ ምንጩ/መሠረታዊ መዋቅሩ በይፋ የሚገኝ (open source) እና በተንቀሳቃሽ የመረጃ ቅንጣቶች ላይ ሊሠራ የሚችል ፕሮግራም ነው። እንደ ከጂፒጂ እና ፒጂፒ ፕሮግራሞች ጋራ ተመሳሳይ የሆነ የአደባባይ ቁልፍ ኢንክሪፕሽን/ስወራ የአደባባይ ቁልፍ ኢንክሪፕሽን (Public Key Encryption) አልጎሪዝም ይጠቀማል።

ዋናው ገጽ (Homepage)

ኮምፒውተራችን ምን ያስፈልገዋል?

 • ሁሉም የዊንዶው ዓይነቴዎች ሊሠሩ ይችላሉ።

ለዚህ መመሪያ የተወሰደው ዓይነቴ

 • 0.3.1

ፈቃድ/ላይሰንስ

 • ነጻ ሶፍትዌር

አስፈላጊ ንባብ

ይህን መሣርያ መጠቀም ለመጀመር የሚያስፈልገው ጊዜ፦ 20 ደቂቃ

ከጂፒጂ4ዩኤስቢ ምን ጥቅም እናገኛለን?

 • ከየትኛውም ቦታ (ለምሳሌ በኢንተርኔት ካፌ ወይም በሥራ ቦታ) ሆነን የኢሜል መልእክቶችን እና ፋይሎችን ኢንክሪፕት ማድረግ እንችላለን።
 • ከኢንተርኔት ግንኙነት መስመር ውጪ (off-line) በመሆን ኢንክሪፕት ማድረግ እና ከዚያም ኢንክሪፕት ያደረግናቸውን መልእክቶች የኢንተርኔት ግንኙነት ካለው ኮምፒውተር ላይ መላክ እንችላለን።

የጂፒጂ4ዩኤስቢ አጫጫን

 • በዚህ ሣጥን ግርጌ የሚገኘውን የጂፒጂ4ዩኤስቢ ምልክት በመንካት/ክሊክ ይህንን http://gpg4usb.cpunk.de/download.html የመጫኛ ድረ ገጹን መክፈት
  • Filename ከሚለው በታች የሚገኘውን gpg4usb-x.x.x.zip የሚል መስፈንጠሪያ መንካት/ክሊክ እና ተጠርዞ የተቀመጠውን (zip archive) ፋይል ወደኮምፒውተራችን መውሰድ።*
 • gpg4usb-x.x.x.zip የሚለውን የተጠረዘ ፋይል ካኖርንበት ቦታ ፈልጎ ማግኘት (Locate) እና መፍታት (unzip)
 • የተጠረዘውን ፋይል (zipped) ከፈታነውና (unzipped) በውስጡ የሚገኙትን ፋይሎች አውጥትን ወደ ኮምፒውተራችን ከወሰድን በኋላ (extracted) ጥራዙን (.zip file) ልናጠፋው እንችላለን።

ጂፒጊ4ዩኤስቢ (gpg4usb)

1.1 ይህንን መሣሪያ መጠቀም ከመጀመራችን በፊት ማወቅ ያለብን ጉዳዮች

ጂፒጂ4ዩኤስቢ ፋይሎችን እና የኢሜይል መልእክቶችን ኢንክሪፕት ወይም ዲክሪፕት ለማድረግ የምንጠቀምበት እና በተንቀሳቃሽ የመረጃ ማስቀመጫ ቋቶች በቀላሉ የሚያዝ ፕሮግራም ነው። ጂፒጂ4ዩኤስቢ በአደባባይ ቁልፍ ኢንክሪፕት የማድረግ ስልት (public-key cryptography) ላይ የተመሠረተ ነው። በዚህ አሠራር መሠረት እያንዳንዱ ተጠቃሚ የግሉን መንትያ ቆልፎች መፍጠር ይኖርበታል። አንደኛው መንትያ የግል ቁልፍ (private key) ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ለሌላ ማንኛውም አካል በፍጹም አሳልፈን የማንሰጠው በይለፍ ቃል የተጠበቀ ቁልፍ ነው ነው።

ሁለተኛው መንትያ በአንጻሩ የአደባባይ ቁልፍ (public key) ተብሎ የሚጠራ ሲሆን መልእክት ተለዋዋጮቹ የሚቀባበሉትና የሚጠቀሙበት ነው። መረጃ የምንለዋወጠውን ሰው የአደባባይ ቁልፍ ካገኘን፣ እርሱም የእኛ የአደባባይ ቁልፍ እንዲደርሰው ካደረግን፣ ከእርሱ ጋራ ኢንክሪፕት የተደረጉ ፋይሎችን መላላክ እንችላለን። በሌላ አገላለጽ የአደባባይ ቁልፍ የተለዋወጡ ተጠቃሚዎች ብቻ ኢንክሪፕት ተደርገው የተላኩ ትን መረጃዎች ዲክሪፕት ማድረግ ይችላሉ ማለት ነው። የአደባባይ ቁልፋችንን መረጃ ለምንለዋወጣቸው ባልጀሮቻችን ከላክን እንዲሁ መንትያውን እና የግል ቁልፋችንን በጥንቃቄ መያዝ ከቻልን የሚላኩልንን ኢንክሪፕትድ ኢሜይሎች ማንበብ እንችላለን።

በተጨማሪም የመልእክቶቻችንን ምሥጢራዊነትና ደኅንነት የበለጠ ለማረጋገጥ ዲጂታል ፊርማ መጠቀም እንችላለን። ትክክለኛው የአደባባይ ቁልፋችን ያለው ሰው የደረሰው የኢሜይል መልእክት በትክክል ከእኛ መላኩን፣ እንዲሁም መልእክቱ በመንገድ ላይ በሦስተኛ ወገን ተጠልፎ አለመነካካቱን ማረጋገጥ ይችላል። እኛም በተመሳሳይም የደረሰን የኢሜይል መልእክት በትክክልም ከምንፈልገው ሰው መምጣቱን በዲጂታል ፊርማው ማረጋገጥ እንችላለን።

በጂፒጂ4ዩኤስቢ ፕሮግራም ስውር መንትያ ቁልፎችን ለመፍጠር፣ መረጃ ከምንለዋወጣቸው ሰዎች ጋራ የምንቀባበለውን የአደባባይ ቁልፍ (public keys) ለማስተላለፍ (export)፣ መልእክቶችን ለመጻፍ እና ኢንክሪፕት ለማድረግ ያስችለናል። የአደባባይ ቁልፋችንን እና/ወይም ኢንክሪፕት የተደረገውን መልእክት ከጂፒጂ4ዩኤስቢ መገልበጥና (copy) በኢሜይላችን የመልእክት መጻፊያ ገበታ ላይ መለጠፍ (paste) እንችላለን። አለበለዚያም የአደባባይ ቁልፋችንን እና/ወይም ኢንክሪፕት የተደረገውን መልእክት እንደሌላ ፋይል በኮምፒውተራችን ላይ ማኖርና በአባሪነት አያይዘን መላክ እንችላለን። ሰነዶች እና ፋይሎችም ኢንክሪፕ ሊደረጉ እንደሚችሉ ማስታወስ ያሻል።

ማስታወሻ፦ ኢንክሪፕትድ ያልሆኑት የመጀመሪያ (ኦርጅናል) ፋይሎችና ሰነዶች ቅጂ በኮምፒውተራችን ላይ ሊቀር ስለሚችል እነዚህን ቅጂዎች ከራሳችንም ሆነ ከመልእክት ተቀባያችን ኮምፒውተር ማስወገድ አስፈላጊ እና ጠቃሚ መሆኑን ማስታወስ ጠቃሚ ነው።

ጂፒጂ4ዩኤስቢ ከተመሳሳይ ጂፒጂ ወይም ፒጂፒ ፕሮግራሞች ጋር ቁልፎችን እና ኢንክሪፕት የተደረጉ መልእክቶችን ለመለዋወጥ ያስችላል።

ጂፒጂ4ዩኤስቢን መጫን እና መንታ ቁልፍ መፍጠር

በዚህ ገጽ የሚዳሰሱ ርእሰ ጉዳዮች፤

2.0 ጂፒጂ4ዩኤስቢን መጫን

ጂፒጂ4ዩኤስቢን መጫን ቀላል እና ግልጽ የሆኑ ደረጃዎች አሉት። ለመጀመር የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል ያስፈልጋል።

ደረጃ 1የጂፒጂ4ዩኤስቢ የተጠረዘ መዝገብ/ፋይል (zipped archive file) መክፈት፤ ከዚያም በውስጡ የሚገኙትን ፋይሎች በሙሉ ወደ ተንቀሳቃሽ የመረጃ ቋት ወይም በኮምፒውተራችን ላይ ወደፈጠርነው ማህደር/ፎልደር ማሸጋገር (extract)

ስዕል 1፤ የጂፒጂ4ዩኤስቢ ፕሮግራም ማስቀመጫ ሥፍራ

ደረጃ 2የጂፒጂ4ዩኤስቢን ፕሮግራም ሥራ ለማስጀመር ይህንን ፋይል በእጥፍ-ንኬት (double click) መክፈት። ተከትሎ የጂፒጂ4ዩኤስቢ ማህደር/ፎልደር ይከፈታል። በማህደሩ/ፎልደሩ ውስጥ ከሚገኙት ይህንን ማዘዣ በእጥፍ ንኬት (double click) በመክፈት Open File - Security Warning የሚለውን መስኮት መክፈት።

ደረጃ 3፦ ይህንን በመንካት/ክሊክ የጂፒጂ4ዩኤስቢ ፕሮግራምን እንደሚከተለው መክፈት፤

ስዕል 2: የጂፒጂዩኤስቢ ዋና የመቆጣጠሪያ መስኮት

2.1 የጂፒጂ4ዩኤስቢን መንታ ቁልፍ መፍጠር

መዛግብትን፣ ፋይሎችን እና የኢሜይል መልእክቶችን ኢንክሪፕት ወይም ዲክሪፕት ከማድረጋችን አስቀድሞ፣ መንታ ቁልፍ መፍጠር ይኖርብናል። ይሁንና ለሌሎች የሚላከውን መረጃ ኢንክሪፕት ከማድረጋችን በፊት ተቀባዮቹ የአደባባይ ቁልፋቸውን ሊልኩልን፣ የእኛንም ልንሰጣቸው እንደሚገባ እንዳለባቸው ማስታወስ ያሻል። የአደባባይ ቁልፍን ለሌሎች ማጋራት የሚቻልበት መንገድ በሚቀጥለው ክፍል ተብራርቷል። አሁን መንታ ቁልፍ ለመፍጠር እንችል ዘንድ የሚረዱትን ቀጣዮቹን ደረጃዎች እንመልከት፤

ደረጃ 1፦ ይህንን መግቢያ በመንካት/ክሊክ የሚከተለውን መስኮት መክፈት፤

ስዕል 3፤ የቁልፎች መፍጠሪያ ክፍሉ Keymanagement መስኮት Generate Key ክፍል

ደረጃ 2Key በሚለው ክፍል (ሜኑ) ስር የሚገኘውን ይህንን Generate Key በመምረጥ የ Generate Key መስኮት እንዲከፈት ማድረግ።

ደረጃ 3፦ ተገቢውን መረጃ በተጓዳኝ በሚታየው የጽሑፍ ማስገቢያ ላይ ማስገባት እና የከፈትነው መስኮት የሚከተለውን እንዲመስል ማድረግ፤

ስዕል 4፡ የተሟላ የመንታ ቁልፍ መፍጠሪያ ቅጽ ምሳሌ

አስፈላጊ መረጃ፦ የግል ቁልፋችንን ደኅንነት ለመጠበቅ አስተማማኝ የይለፍ ቃል ማዘጋጀት ይኖርብናል። ስለይለፍ ቃል ( 3. አስተማማኝ የይለፍ (የምስጢር) ቃል መፍጠር እና መጠቀም የሚለውን ምእራፍ ማየት ይጠቅማል።)

ማስታወሻ፦ ለመንታ ቁልፎቹ የአገልግሎት ዘመን ማብቂያ ቀን ከመወሰናችን በፊት Never Expire የሚለውን ሳጥን ባለመምረጥ (disable) የቀን መወሰኛው የቀን መቁጠሪያ እንዲሠራ ማድረግ ይኖርብናል።

ማስታወሻKeySize in Bit የሚለው ክፍል የመንታ ቁልቾቹን መጠን ለመወሰን ያገለግላል። የቁልፉ መጠን በጨመረ መጠን ፋይሎችን ኢንክሪፕት እና ዲክሪፕት ለማድረግ አስተማማኝ ቢኾንም ለመፍጠር ግን በአንጻራዊነት ረዘም ያለ ጊዜ እንደሚሻ ማስታዋስ ያስፈልጋል።

ደረጃ 4፦ መንታ ቁልፍ ለመፍጠር ይህንን ማዘዣመንካት/ክሊክ። መንታ ቁልፉ በተሳካ ኹኔታ ከተፈጠረ በኋላ፣ ገጹ የሚከተለውን ይመስላል፤

ስዕል 5፤ የKey Management መስኮት-አዲስ የተፈጠረውን መንታ ቁልፍ ያሳያል

ከላይ እንደተገለጸው አዲሱ መንታ ቁልፍ በተሳካ ሁኔታ ተፈጥሯል። ቀጥሎ ደግሞ የአደባባይ ቁልፋችንን ከሌሎች ሰዎች ጋራ ለመጋራት የምንችልበትን፣ እንዲሁም የተላኩልንን የሌሎች ሰዎች የአደባባይ ቁልፎች እንዴት እንደምንቀበል እንመለከታለን።

የአደባባይ ቁልፎችን ማቀበል (Export) እና መቀበል (Import)

በዚህ ገጽ የሚገኙ ክፍሎች፤

3.1 የአደባባይ ቁልፍን በጂፒጂ4ዩኤስ ማቀበል (Export)

መልእክት የምንለዋወጠው ሰው ኢንክሪፕት የተደረገ ነገር ለመላክ እንዲችል በቅድሚያ የተቀባዩን የአደባባይ ቁልፍ (Public Key) ማግኘት ይኖርበታል።

በጂፒጂ4ዩኤስቢ በመጠየአደባባይ ቁልፍን ለማቀበል የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል ያስፈልጋል፤

ደረጃ 1፦ ይህንን ማዘዣ በእጥፍ ንኬት በመንካት የጂፒጂ4ዩኤስቢን ፕሮግራም መክፈት።

ደረጃ 2፦ ይህንን ማዘዣ በመንካት/ክሊክ የሚከተለውን ገጽ መክፈት፤

ስዕል 1፤ የቁልፍ መቆጣጠሪያው (Key Management) መስኮት ሁሉንም ጥንድ ቁልፎች ያሳያል

ደረጃ 3፦ ከላይ በስእል 1 እንደሚታየው የራሳችንን ቁልፍ መምረጥ (Check)

Step 4Key በሚለው ክፍል/ሜኑ ስር የሚገኘውን Export To File የሚለውን ማዘዣ መምረጥ

ስዕል 2፤ የቁልፍ መቆጣጠሪያው (Key Management) መስኮት “Export To File” የሚለው የማቀበያ/መላኪያ አገልግሎቱ ተመርጦ

ይህም የሚከተለው መስኮት እንዲከፈት ያደርጋል፤

ስዕል 3፤ የ “Export To Folder” የማሰሻ መስኮት

ደረጃ 5፦ ይህንን ማዘዣ በመንካት/ክሊክ ጥንድ ቁልፎቹን በጂፒጂ4ዩኤስቢ ፕሮግራም ማህደር ውስጥ ማስቀመጥ።

ማስታወሻ፦ የአደባባይ ቁልፎችን በሌላ ሥፍራ ለማኖር የምንፈልግ ከሆነ ደግሞ የExport To Folder ማሰሻን በመጠቀም ተፈላጊውን መስኮት መክፈት እንችላለን።

ደረጃ 6፦ የአደባባይ ቁልፋችንን ከሚላከውን ፋይል ጋራ እንደ አባሪ በማጣመር መላክ

3.2 የሌላኛውን ወገን የአደባባይ ቁልፍ በጂፒጂ4ዩኤስ መቀበል (Import)

መረጃዎችን ኢንክሪፕት ከማድረግ እና ከመላክ አስቀድሞ የተቀባዩን የአደባባይ ቁልፍ መቀበል ያስፈልጋል። ጂፒጂ4ዩኤስቢን በመጠቀም የመረጃ ተለዋዋጩን ሰው የአደባባይ ቁልፍ ለመቀበል የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል ያስፈልጋል፤

ደረጃ 1፦ ይህንን ማዘዣ በእጥፍ ንኬት በመንካት የጂፒጂ4ዩኤስቢ ፕሮግራምን መክፈት።

ደረጃ 2፦ ከታች የሚታየውን መስኮት ለመክፈት ይህንን መንካት/ክሊክ

ስዕል 4፤ Import Key የተባለው የአደባባይ ቁልፍ መቀበያ ሳጥን

ደረጃ 3፦ የአደባባይ ቁልፉን አድራሻ መምረጥ ፤ ከዚያም ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ የሚከተለውን ገጽ መክፈት፤

ስዕል 5፤ የጂፒጂ4ዩኤስቢ መስኮት ለምሳሌነት ከተፈጠረችው ከሳሊማ አካውንት ጋር የተጣመረውን አዲስ የአደባባይ ቁልፍ ያሳያል።

አሁን መረጃ ልንለዋወጠው ያሰብነውን ሰው የአደባባይ ቁልፍ በትክክል አምጥተናል/ተቀብለናል። በመቀጠል የቁልፉን ትክክለኝነት ማረጋገጥ ማድረግና መፈረም ይጠበቃል።

3.3 ጂፒጂ4ዩኤስቢን በመጠቀም የአደባባይ ቁልፍን ትክክለኛነት ማረጋገጥ

የተቀበልነው የአደባባይ ቁልፍ በትክክልም ከምንፈልገው ሰው የተላከ መሆኑን ማረጋገጥ አለብን። መልእክት ለመለዋወጥ ያቀድነው ሁለቱም ወገኖች (መልእክት ተለዋዋጮቹ ወይም ላኪና ተቀባይ) የተቀባበልነው የአደባባይ ቁልፍ በእርግጥም ከምንፈልገው ሰው መላኩንና ትክክለኛ መሆኑን መፈተሽ ያስፈልገናል።

የተለዋወጥናቸው የአደባባይ ቁልፎች ትክክለኛ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል፤

ደረጃ 1፦ የማጣራቱን ሥራ ለማከናወን ላኪና ተቀባይ ከኢሜይል ውጭ በሆነ የመገናኛ ዘዴ መገናኘት አለባቸው።

ማስታወሻ፦ ከትክክለኛው ሰው ከራሱ ጋራ መገናኘታችንን እርግጠኛ እስከሆንን ድረስ ለማጣራቱ ስራ በስልክ፣ በአጭር መልእክቶች፣ ስካይፕን በመሳሰሉ የድምጽ አገልግሎቶች (Voice over Internet Protocol (VoIP)) ወይም በሌሎች መንገዶችን መጠቀም እንችላለን። በጥንቃቄ የታቀደ ከሆነ የቴሌፎን ቅብብሎሽ እና የፊት ለፊት ግንኙነት ዋስትና ይሰጣሉ።

ደረጃ 2፦ ተቀባይ እና አቀባይ የተለዋወጥነውን የአደባባይ ቁልፎች “መለያ አሻራ ('fingerprints')” ማረጋገጥ ይኖርብናል።

ማስታወሻ፦ “መለያ አሻራ ('fingerprints')” ከእያንዳንዱን ቁልፍ ጋራ የተያያዘ፣ የቁልፉን ትክክለኝነት የሚያረጋግጥ የአሃዞች እና የፊደላት ስብስብ ነው። “የመለያ አሻራው” በራሱ ሚስጥራዊ አይደለም፤ መዝግበን ልናስቀምጠውና እና ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ለማራጋገጫነት ልንጠቀምበት እንችላለን።

የፈጠርናቸውን መንታ ቁልፎች የመለያ አሻራ እንዲሁም የተቀበልናቸውን የአደባባይ ቁልፎች አሻራ ለመመልከት የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል ይጠበቃል፤

ደረጃ 1፦ አንድ ቁልፍ መምረጥ እናም በቀኝ ንኬት ተዛማጅ የሆነውን ድንገቴ መስኮትን መክፈት።

ደረጃ 2በስዕል 6 እንደሚታየውን ከሚቀርቡት አማራጮች መካከል Show Keydetails የሚለውን መምረጥ

ስዕል 6፤ ድንገቴ መስኮት የቁልፎች ዝርዝርና ተጣማሪ መረጃዎችን ያሳያል

ተከትሎ ቀጥሎ በስእሉ የሚታየው መስኮት ይከፈታል።

ስዕል 7፤ ድንገቴ መስኮቱ ከቴሬንስ ተጋሪ ጋር መረጃ የምትለዋወጠውና የአደባባይ ቁልፏን የላከችለትን የሳሊማን ቁልፍ ዝርዝር መረጃ ያሳያል፤ የቁልፉ ልዩ የመለያ አሻራ በጥቁር ቀለም ተከቦ ይታያል

ደረጃ 3፦ የተለዋወጥናቸውን የአደባባይ ቁልፎች የመለያ አሻራ ትክክለኝነት በጂፒጂ4ዩኤስቢ ፕሮግራም ውስጥ በማነጻጸር ማረጋገጥ።

እያንዳንዱ ጥንድ ቁልፍ የራሱ ልዩ የመለያ አሻራ (fingerprint) አለው። የአደባባይ ቁልፍ የላክንለት ሰው/ተቀባይ ከቁልፉ ጋራ የሚያገኘው የመለያ አሻራ እኛ ካለን አሻራ ጋራ ተመሳሳይ መሆን አለበት፤ በተመሳሳይም እርሱዋ የላከችልን የአደባባይ ቁልፍ አሻራ እርሱዋ ካላት የራሱዋ አሻራ ጋራ ተመሳሳይ መሆኑን በጂፒጂ4ዩኤስቢ ፕሮግራም ማነጻጸር ይኖርባታል።

የአደባባይ ቁልፍ ተጋሪዎች የተለዋወጧቸውን ቁልፎች የመለያ አሻራ ትክክለኛነት መናበብባ ማረጋገጥ አለባቸው። የመለያ አሻራዎቹ ካልተመሳሰሉም አዲስ የአደባባይ ቁልፎችን እንደገና በመፍጠር መለዋወጥ አለባቸው። የመለያ አሻራዎቹ በትክክል ከተመሳሰሉ ኢንክሪፕት የተደረጉ መልእክቶችን እና ፋይሎችን በሚስጥራዊ ኹኔታ መለዋወጥ ይቻላል።

መልእክቶችን ኢንክሪፕት እና ዲክሪፕት ማድረግ

በዚህ ንዑስ ክፍል የሚዳሰሱ ጉዳዮች፤

4.0 መልዕክቶችን በጂፒጂ4ዩኤስቢ ኢንክሪፕት ማድረግ

መልእክቶችን (text messages) ኢንክሪፕት የማድረግ ቀላል እና በአፍታ የሚከናወን ነው። በሚከተለው ምሳሌ እንደሚታየው ቴሬንስ ለጓደኛው ሳሊማ ኢንክሪፕት የተደረገ መልእክት ይልካል፤

ደረጃ 1ጂፒጂ4ዩኢስቢን መስኮት ለመክፈት ይህንን እጥፍ ንኬት ማድረግ።

ደረጃ 2፤ ከዚህ በታች እነደሚታየው መልዕክቱን መጻፍ

ስዕል 1: የጂፒጂ4ዩኤስቢ መስኮት የመልዕክት አጻጻፍ ማሳያ

ደረጃ 3፤ የመልዕክቱን ተቀባዮች የማረጋገጫ ሳጥን እንደሚከተለው ማመሳከር

ስዕል 2፤ የጂፒጂ4ዩኤስቢ መስኮት መልዕክት ተቀባዮቹን በጥቁር ቀልሞ ተከቦ ይታያል

ማስታወሻ ፦ አንድን ኢንክሪፕት የተደረገ መልእክት ከአንድ በላይ ለሆኑ ተቀባዮች መላክ እንችላለን። ነገር ግን ከተቀባዮቹ ጋራ የአደባባይ ቁልፎቻችንን አስቀድመን መቀባበል ይኖርብናል። ከዚያ Encrypt for በሚለው ቦታ መልእክቱ እንዲላክላቸው ከመረጥናቸው ተቀባዮች አጠገብ የሚገኘውን ሳጥን በመምረጥ ይኖርብናል። በተጨማሪ መልእክቱን ኢንክሪፕት አድርጎ ቅጂውን ማስቀረት ለራሳችን የወደፊት ፍላጎት ሊጠቅመን ይችላል።

ደረጃ 4፦ መልእክቱን ኢንክሪፕት ለማድረግ ይህንን የማዘዣ ምልእክት መንካት/ክሊክ ወይም ከ Crypt በሚለው ክፍል ውስጥ Encrypt የሚለውን መንካት/ክሊክ

ስዕል 3፤ የጂፒጂ4ዩኤስቢ መስኮት ኢንክሪፕት የተደረገ መልእክት ምሳሌ

ደረጃ 5፦ ሁሉንም ኢንክሪፕት የተደረገውን መልእክት በሙሉ ለመምረጥ ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ ፤ ከዚያም መልእክቱን ወደ ጊዜያዊ ማስቀመጫ ቦታ (Clipboard) ለመገልበጥ (ኮፒ ለማድረግ) ይህንን ማዘዣ መጫን

ማስታወሻ፦ እነዚህን ትእዛዞች ለማስተላለፍ አማራጭ አጭር መንገዶችን መጠቀም እንችላለን፤ ለምሳሌ አሁን በመጨረሻ ያየነውን ትእዛዝ በመንካት/ክሊክ ፋንታ Ctrl + E በሚል አጭር መንገድ ልናስፈጽመው እንችላለን።

ደረጃ 6፦ የኢሜል አድራሻን መክፈት፤ በመቀጠልም የአዲስ መልእክት ማርቀቂያውን ገጽ መክፈት እና በመጨረሻ (በደረጃ 5) የገለበጥነውን ኢንክሪፕት የተደረገ መልእክት በመጻፊያው ቦታ ላይ መለጠር (ፔስት)። የመልእክት መጻፊያው ገጽ የሚከተለውን ይመስላል፤

ስዕል 4፤ በጂፒጂ4ዩሴቢ ኢንክሪፕት የተደረገ መልእክት በጂሜል የመልእክት መጻፊያ ቦታ ላይ ተለጥፎ (ፔስት) ይታያል

ማስታወሻRich Text Formats (RTF) የሚባለው የጽሑፍ አጣጣል ማበልጸጊያ ስልት ኢንክሪፕት የተደረጉ መልእክቶች በአግባቡ እንዳይነበቡ ሊያደርግ ይችላል። Rich Text Formats (RTF) ፊደላትን ቦልድ (መደረብ)፣ አይታሊክስ ወዘተ ለማድረግ የሚረዳን ነው። ስለዚህም መልእክቶቻችንን ማሳመሪያ ጭማሪ ያልተደረገለት ሌጣ የፊደል አጣጣል (plain text) በመጠቀም ማዘጋጀት ይመረጣል። በጂሜይል የኢሜይል አድራሻ RTF/አርቲኤፍ ን ወደ plain text ለመቀየር ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ ያስፈልጋል።

4.1 መልእክቶችን በጂፒጂ4ዩኤስቢ ዲክሪፕት ማድረግ

ኢንክሪፕት ተደርጎ የተላከን የኢሜይል መልእክት ዲክሪፕት ለማድረግ የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል ያስፈልጋል።

ደረጃ 1የጂፒጂ4ዩኤስቢ ፕሮግራምን ለመክፈት ይህንን ማዘዣ በእጥፍ ንኬት መንካት።

ደረጃ 2፦ የኢሜል አድራሻን መክፈት እና ኢንክሪፕት ተደርጎ የተላከውን መልእክት መክፈት

ደረጃ 3፦ ኢንክሪፕት የተደረገውን መልእክት ይዘት መምረጥ (Select)፣ ቀጥሎ መገልበጥ (ኮፒ ማድረግ) እና የተገለበጠውን መልእክት በስእሉ እንደሚታየው untitled1.txt በሚለው የጂፒጂ4ዩኤስቢ መስኮት ላይ መለጠፍ (paste)

ስዕል 5፤ በጂፒጂ4ዩሴቢ መስኮት ዲክሪፕት ለመደረግ የተዘጋጀ መልእክት ይታያል

ማስታወሻ፦ ኢንክሪፕት የተደረገው መልእክት በስዕል 6 እንደሚታየው መስመሮቹ በድርብ ክፍተቶች ከተለያዩ ጂፒጂ4ዩኤስቢ መልእክቱን በቀጥታ ዲክሪፕት ላያደርገው ይችላል። የድርብ መስመሮቹን ለማጥፋት Edit በሚለው ክፍል ውስጥ ከሚገኙት ምርጫዎች Remove double Linebreaks የሚለውን መምረጥ ፤ ከዚያም በደረጃ 4 እንደተመለከተው ዲክሪፕት የማድረጉን ሒደት መቀጠል።

ስዕል 6፤ የጂፒጂ4ዩሴቢ መስኮት በድርብ መስመር የተሰባበረ መልእክትን ጠግኖ ዲክሪፕት ለማደረግ ተዘጋጅቶ

ደረጃ 4፦ ይህንን መንካት/ክሊክ ፤ ቀጥሎም መንታ ቁልፎቹን ስንፈጥር የሰጠነውን የይለፍ ቃለ በስእሉ እንደሚታየው ማስገባት/መጻፍ፤

ስዕል 7፤ የይለፍ ቃል ማስገቢያ መስኮት

ደረጃ 5፦ ይህንን ማዘዣ በመንካት/ክሊክ በስእል 2 የሚታየው የጂፒጂ4ዩኤስቢ ዋና መቆጣጠሪያ መስኮት መክፈት።

4.2 ፋይሎችን በጂፒጂ4ዩኤስቢ ኢንክሪፕት ማድረግ

ፋይልን ኢንክሪፕት የማድረግ ሂደት መልእክቶችን ኢንክሪፕት ከማድረግ ጋር የሚመሳሰል ነው። ቀድሞ በጀመርነው ምሳሌ በመቀጠል ሳሊማ አንድ ፋይል ኢንክሪፕት አድርጋ ለቴረንስ ትልክለታለች።

ደረጃ 1የጂፒጂ4ዩኤስቢ ፕሮግራምን ለመክፈት ይህንን ማዘዣ በእጥፍ ንኬት መንካት።

ደረጃ 2፦ በስእሉ የሚታየውን ገጽ ለመክፈት ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ

ስዕል 8፤ ፋይሎችን ኢንክሪፕት/ዲክሪፕት ማድረጊያው የEncrypt / Decrypt File መስኮት፤ ዲክሪፕት የማድረግ መደበኛ ምርጫ

Encrypt / Decrypt File መስኮት በጥቁር ቀለም ተከቦ የሚታየው ቁልቁል ተንሸራታች ዝርዝር (scroll list) መልእክቱን የምንልክበትን የኢሜይል አድራሻና ከእርሱ ጋራ የሚጣመረውን ኢንክሪፕት የማድረጊያ ቁልፍ እንድንመርጥ ያስችለናል። በምሳሌው የቴረንስ አድራሻ ተመርጦ ይታያል።

ደረጃ 3፦ በመቀጠል በመስኮቱ ራስጌ ካሉት ሁለት አማራጮች Encrypt የሚለውን አዝራር (button) መምረጥ፤ ከዚያም ይህንን ማዘዣ በመንካት/ክሊክ ከታች በስእሉ የሚታየውን ገጽ መክፈት፤

ስዕል 9፤ ኢንክሪፕት የሚደረገውን ፋይል የምንመርጥበት (Open File) የማሰሻ መስኮት

ደረጃ 4፦ ኢንክሪፕት የሚደረገውን ፋይል ለማያያዝ እንዲሁም ወደ Encrypt / Decrypt መስኮት ለመመለስ ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ

ስዕል 10፤ ኢንክሪፕት ለመደረግ የተዘጋጀው ፋይል Encrypt / Decrypt File መስኮት ሲታይ

ደረጃ 5፦ ይህንን ማዘዣ በመንካት/ክሊክ የሚከተለው መስኮት መክፈት፤

ስዕል 11፤ Done የተባለው የማረጋገጫ ሳጥን

የትግበራ Done የማረጋገጫ መስኮት አዲሱ ኢንክሪፕት የተደረገ ፋይል የት እንደተቀመጠ ያሳያል። ኢንክሪፕት የተደረገ ፋይል .asc በሚለው ቅጥያ የፋይል ስም መለያ ሊለይ ይችላል፤ ለምሳሌም Technical White Paper.doc.asc እንደማለት ነው።

ደረጃ 6፦ ኢንክሪፕት የማድረጉን ሒደት ለማጠናቀቅ ይህንን ማረጋገጫ መንካት/ክሊክ

ማስታወሻ፦ኢንክሪፕት የተደረጉ አጭር መልእክቶችን፣ ኢንክሪፕት ከተደረገ ፋይል ጋር በማጣመር መላክ ይቻላል።

ደረጃ 7፦ የኢሜል አድራሻችንን በመጠቀም Done በሚባለው የማረጋገጫ መስኮት (ስዕል 11) የተመለከተውን ፋይል ፈልጎ ማግኘት፤ ከዚያም ኢንክሪፕት የተደረገውን ፋይል እንደማንኛውም ፋይል በኢሜላችን ላይ በአባሪነት ማያያዝ።

ጠቃሚ መረጃ፦ በአባሪነት የምናያይዘው ፋይል ስም ኢንክሪፕት እንደማይደረግ ማስተዋል ያስፈልጋል። ስለዚህ ለፋይሉ የምንሰጠው ስም የማንፈልገውን መረጃ እንደማይሰጥ ማረጋገጥ ያስፈልጋል። በተጨማሪም ኢንክሪፕትድ ያልሆነው የፋይሉ ዋና ቅጂ በኮምፒውተራችን ላይ እንደሚቀር መርሳት የለብንም። ፋይሉን ማጥፋትም ሆነ መደበቅ ካለብን ይህንኑ ማድረግ ያስፈልጋል።

4.3 ፋይሎችን በጂፒጂ4ዩኤስቢ ዲክሪፕት ማድረግ

በሚቀጥለው ምሳሌ ቴሬንስ ከሳሊማ የተላከለትን ፋይል እንዴት ዲክሪፕት እንደሚያደርግ እንመለከታለን።

ደረጃ 1የጂፒጂ4ዩኤስቢ ፕሮግራምን ለመክፈት ይህንን ማዘዣ በእጥፍ ንኬት መንካት።

ደረጃ 2፦ የኢሜይል አድራሻን መክፈት ፣ የመልዕክት ሳጥኑን መክፈት እና የተላከልንን ፋይል መገልበጥ (download)

ማስታወሻ፦ መልእክት አቀባያችን ኢንክሪፕት ከተደረገ አባሪ ፋይል ጋራ ኢንክሪፕት የተደረገ መልእክት ሊልክልን ይችላል፤ እኛም መልእክቱን በክፍል 4.1 አጫጭር መልእክቶችን በጂፒጂ4ዩኤስቢ ዲክሪፕት ማድረግ በሚለው ስር በተጠቀሰው መሠረት ዲክሪፕት አድርገን መክፈት እንችላለን።

ደረጃ 3በጂፒጂ4ዩኤስቢ የተጠቃሚዎች መቆጣጠሪያ መስኮት (ከላይስዕል 1 እንደሚታየው)፣ ይህንን ፋይል ኢንክሪፕት የማድረጊያ ምልክት በመንካት/ክሊክ Encrypt / Decrypt File የሚለውን መስኮት መክፈት (ከታች በስዕል 12 እንደሚታየው)።

ደረጃ 4፦ ይህንን የፋይል አድራሻ መፈለጊያ በመንካት/ክሊክ ኢንክሪፕት የተደረገው ፋይል ወደተቀመጠበት ሥፍራ ማምራት፤

ስዕል 12፤ Encrypt / Decrypt (ኢንክሪፕት /ዲክሪፕት) መስኮት ኢክሪፕት የተደረገው ፋይል የተቀመጠበትን ሥፍራ ሲያመለክት

ደረጃ 5፦ ቀደም ሲል በተከፈተው ሳጥን ግርጌ የሚታየውን ይህንን ማረጋገጫ መንካት/ክሊክ እና የሚከተለውን መስኮት መክፈት፤

ስዕል 13፤ Done የሚለው መስኮት የተደረገው ፋይል የተቀመጠበትን ሥፍራ ያሳያል

ጠቃሚ መረጃ፦ በኢንተርኔት ካፌ ወይም በመሥርያ ቤት የኢንተርኔት አገልግሎት የምንጠቀም ከሆነ በ.asc የተቀመጠውን ፋይሉን ወደ ተንቀሳቃሽ የመረጃ ቋታችን (USB or portable drive) ማሸጋገር ይኖርብናል። ፋይሉንም በስውር ሥፍራ ዲክሪፕት ማድረግ እንችላለን።

የሚዘወተሩ ጥያቄዎች እና ክለሳ

መሐመድ እና ሰናይት ጂፒጂ4ዩኤስቢ መጠቀም ቀላል መሆኑን ተገንዝበዋል። ይሁንና አሁንም ጥቂት ጥያቄዎች አሏቸው።

5.0 በጂፒጂ4ዩኤስቢ አጫጭር መልእክቶችን ኢንክሪፕት ማድረግ

ጥያቄጂፒጂ4ዩኤስቢን ከተንቀሳቃሽ የመረጃ ማጠራቀሚያ (ዩኤስቢ) መጠቀም የግዴታ ነው?

መልስ፦ የግድ አይደለም። ፕሮግራሙን በኮምፒውተራችን ሃርድ ዲስክ ላይ መጫን እና መጠቀም ይቻላል።

ጥያቄ፦ ጥንድ ቁልፎችን ለስንት የኢሜል አካውንቶች መፍጠር እችላለሁ

መልስ ገደብ የለውም፤ ላሉን የኢሜይል አድራሻዎች ሁሉ ተጣማጅ ቁልፎቹን መፍጠር እንችላለን

ጥያቄ፦ ቀላል/አቋራጭ ኮፒ እና ፔስት የማድረጊያ መንገዶችን መጠቀማችንን ወድጄዋለሁ

መልስ፦ በትክክል፤ እነዚህ ቀላል መንገዶች ጠቃሚ ናቸው። ነገር ግን የኢሜይል መልእክቱን ርእሰ ጉዳይ (subject) የምንጽፍበት ቦታ ኢንክሪፕት እንደማይደረግ መዘንጋት የለብንም። የመልእክቱን ርእሰ ጉዳይ በምንጽፍበት ቦታ የምናሰፍረው ነገር ኢንክሪፕት የተደረገውን መልእክት ጭብጥ የሚያጋልጥ እንዳይሆን መጠንቀቅ ይገባል።

5.1 የክለሣ ጥያቄዎች

 • የአደባባይ ቁልፍን (public key) በመፈረም (signing) እና በማረጋገጥ (verifying) መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?
 • የመለያ አሻራ (fingerprint) ምንድን ነው? አገልግሎቱስ?