ኪፓስ - አስተማማኝ የይለፍ ቃሎች ማከማቻ

Updated 1 August 2014

መመሪያው በወቅቱ አልተሻሻለም፤ በቅርቡ ይሰረዛል

:Introduction

ዋናው ገጽ (Home page)

ምን አይነት የኮምፒውተር ኦፐሬቲንግ ሲስተም ያስፈለጋል?

 • ሁሉም አይነት የዊንዶውስ አይነቴዎች

በዚህ መመሪያ ጥቅም ላይ የዋለው የኪፓስ (keepass) አይነቴ

 • 1.18

የመጠቀም ፈቃድ

 • በነጻ የሚገኝ ምንጩ ክፍት የሆነ ሶፍትዌር (Open-Source Software)

አስፈላጊ ንባብ

ፕሮግራሙን ሥራ ለማስጀመር የሚወስደው ጊዜ፡- 15 ደቂቃ

ከኪፓስ ምን ጥቅሞች እናገኛለን

 • ሁሉንም የይለፍ (የምሥጢር) ቃሎቻችንን በአንድ አስተማማኝነቱ በተጠበቀ ቦታ ለማስቀመጥ ያስችለናል

 • ብዙ ጠንካራ የይለፍ ቃሎችን ለመፍጠር እና ለማከማቸት ያስችለናል፤ ሁሉንም የይለፍ ቃል ማስታወስ አይኖርብንም

ከጂኤንዩ/ሊኑክስ፣ ከማክ እና ከሌሎች የማይክሮሶፍት ዊንዶውስ ጋራ ያለ ችግር የሚሠሩ ፕሮግራሞች

ለጂኤንዩ/ሊኑክስ (GNU Linux) እና ማክኦሲ (Mac OS) የተዘጋጀውን የኪፓስ አይነቴ ማለትም ኪፓስ-ኤክስ (KeePassX) በቀላሉ ማግኘት ይቻላል። በተጨማሪም ለአይፎንለብላክቤሪለአንድሮይድለፖኬትፒሲ እና ለሌሎቹ የተሠሩት የኪፓስ አይነቴዎችም ይገኛሉ። ሆኖም ከኪፓስ ውጭ ያሉ መሰል የይለፍ ቃል መፍጠሪያና ማከማቻ ፕሮግራሞችን መሞከር ለሚፈልጉ የሚከተሉትን እንዲሞክሩ ይመከራሉ፤

 • ፓስወርድሴፍ (Password Safe)። የፕሮግራሙአይነቴዎች ለማይክሮሶፍት ዊንዶውስ እና ለጂኤንዩ ሊኑክስ ይገኛል።

 • 1ፓስወርድ (1Password)። የፕሮግራሙ አይነቴዎች ለማይክሮሶፍት ዊንዶውስለጂኤንዩ ሊኑክስለአይፎን እና ለአይፓድ ተሠርተዋል።

:Installation instructions

1.1 ስለኪፓስ በቅድሚያ ማወቅ የሚገቡን ነገሮች

ኪፓስ (KeePass) አጠቃቀሙ ቀላል የሆነ፣ ምሥጢራዊነቱ ከፍተኛ የሆነ የይለፍ ቃሎች መፍጠሪያ እና ማጠራቀሚያ መሣሪያ ነው። የኪፓስን ፕሮግራምም ይሁን በውስጡ ያከማቸነውን መረጃ በቀላሉ ወደ ማስታወሻ ቅንጣት (USB memory stick) በመገልበጥ ይዘነው ልንንቀሳቀስ እንችላለን። መረጃዎቹ ራሳችን በምንፈጥረው እናት የይለፍ ቃል (master password) ይዘጋል። ይህ የይለፍ ቃል በማከማቻው ውስጥ ያለውን መረጃ በሙሉ ኢንክሪፕት ለማድረግ ያገለግላል። ራሳችንን የፈጠርናቸውን የይለፍ ቃሎች ኪፓስ ውስጥ ማከማቸት እንችላለን፤ ከፈለግን ደግሞ ኪፓስ ራሱ የይለፍ ቃሉን እንዲፈጥርልንና መዝግቦ እንዲይዝልን ማድረግ እንችላለን። ኪፓስ መገልገል ከመጀመራችን በፊት የሚጠይቀን የአሠራር ምርጫ ውሳኔ (configuration) ወይም የተለየ የአጫጫን መመሪያ የለውም። ለመጠቀም ዝግጁ እስከሆንን ኪፓስ ምንግዜም ዝግጁ ነው!

የኪፓስ አጫጫን እና አጠቃቀም

በዚህ ክፍል የሚዳሰሱ ርእሰ ጉዳዮች፤

2.0 ኪፓስ የሚጫነውእንዴትነው

ደረጃ 1፤ ይህንን የፕሮግራም መጫኛ በእጥፍንኬት መክፈት፤ Open File - Security Warning የሚል የማዘዣ ሳጥን ብቅ ይላል። ከዚህ በታች የሚታየውን ሳጥን ለመክፈት የሚለውን ማዘዣ መንካት/ክሊክ

ስእል 1፤ የቋንቋ መምረጫ ሰሌዳ

ደረጃ 2፤ ይህንን መንካት/ክሊክ፤ ኪፓስን ሥራ የምናስጀምርበትን ገጽ Setup - KeePass Password Safe – Welcome to the KeePass Password Safe Setup Wizard ይከፈታል።

ደረጃ 3፤ የፕሮግራሚ ተጠቃሚዎች ለመሆን “የበጠቃሚዎች የስምምነት ውል” መስማማታችንን ማረጋገጥ አለብን፤ ስለዚህ ስምምነታችንን የምንገልጽበትን የተጠቃሚነት ውል License Agreement ሰሌዳ ለመክፈት ይህንን የሚለውን ማዘዣ መንካት/ክሊክ

ደረጃ 4፤ ስምምነታችንን ካላረጋገጥን ወደሚቀጥለው ደረጃ መሔድ አንችልም። ስለዚህ “ተስማምቻልሁ” I accept the agreement የሚለውን አማራጭ ስንመርጥ “ቀጥል” Next የሚለው ማዘዣ ዝግጁ ይሆናል። ይህንኑ ማዘዣ ስንነካ/ክሊክ ፕሮግራሙን የት ማስቀመጥ እንደምንፈልግ የምንመርጥበት Select Destination Location ሰሌዳ ይከፈታል።

ደረጃ 5፤ አሁንም “ቀጥል” የሚለውን ይህንን ማዘዣ በመንካት/ክሊክ መደበኛውን የአጫጫን መንገድ ተከትለን መሔድ እንችላለን።

ደረጃ 6፤ ከታች በስእሉ የሚታየውን ሰሌዳ ለመክፈት አሁንም “ቀጥል” የሚለውን መዘዣ መንካት/ክሊክ

ስእል 2፤ ኪፓስ እንዲየሰጠን የምንፈልገውን አገልግሎት የምንመርጥበት (Select Additional Tasks) ሰሌዳ

ደረጃ 7በስእል 7 በሚታየው ሳጥን ውስጥ ካሉት ምርጫዎች የሚለውን መምረጥ/ክሊክ

ማስታወሻበስእል 7 ከሚታዩት ምርጫዎች Create a Start Menu folder የሚለውን (ጭምር) ከመረጥን የኪፓስ ሥራ መወሰኛ Setup - KeePass Password Safe ወዲያውኑ የኪፓስን Quick Launch (ፈጣን ማስጀመሪያ) በኮምፒውተራችን Start የፕሮግራሞች ዝርዝር ውስጥ ይከተዋል/ይፈጥራል።

ደረጃ 8፤ አሁንም “ቀጥል” የሚለውን ማዘዣ በመንካት/ክሊክ ፕሮግራሙን ለመጫን ዝግጁ የሚያደርገውን Ready to Install የሚለውን ሰሌዳ መክፈት፤ በሰሌዳውም “ጫን” የሚለውን መንካት/ክሊክ። ይህን ጊዜ ፕሮግራሙ መጫን ይጀምራል፤ የመጫን ሒደቱ በየቅጽበቱ የሚደርስበትን ደረጃም ያሳየናል።

ከጥቂት ሰከንዶች በኋላ መጫኑ መጠናቀቁን የሚያበስረው ሰሌዳ ይገለጣል፤ Completing the KeePass Password Safe Setup Wizard

ደረጃ 9Launch KeePass የሚለውን አማራጭ መምረጥ፤ ከዚያም መንካት/ክሊክኪፓስ ወዲያውኑ ይከፈታል። ኮምፒውተራችን ከኢንተርኔት ጋራ ተገናኝቶ ከሆነ በቀጥታ የተለያዩ ተጨማሪ አገልግሎቶችና መርጃዎች ማለትም Plugins and Extensions ወደሚገኙበት ወደ ኪፓስ ድረ ገጽ ይመራናል።

2.1 አዲስ የይለፍ ቃል ማከማቻ (Database) የሚፈጠረው እንዴት ነው?

በዚህ ክፍል እናት የይለፍ ቃል እንዴት እንደሚፈጠር፣ አዲስ የፈጠርነውን መረጃ እንዴት እንደምናስቀምጠው፣ ግብታዊ የይለፍ ቃሎችን (random password) ስለመፍጠር፣ የይለፍ ቃሎች ስብስባችንን መጠባበቂያ ቅጂ ስለመፍጠር፣ እና ያስቀመጥነውን የይለፍ ቃል ስንፈልገው እንዴት እንደምናገኘው/እንደምናወጣው እንመለከታለን።

ኪፓስን ለመክፈት የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል ይገባል፤

ደረጃ 1፤ የሚከተሉትን እየመረጡ መሔድ Start > Programs > KeePass Password Safe > KeePass ወይም በኮምፒውተራችን የፊት ሰሌዳ (desktop) ላይ የሚገኘውን ይህንን የኪፓስ ምልክት በመንካት/ክሊክ በስእሉ የሚታየውን ዋናውን ገጽ መክፈት፤

ስእል 3፤ የኪፓስ የይለፍ ቃል ማከማቻ ዋሻ

2.1.1 አዲስ የይለፍ ቃል ሳጥን የሚፈጠረው እንዴት ነው?

አዲስ የይለፍ ቃሎች ማከማቻ ሳጥን ለመፍጠር ሁለት ደረጃዎች አሉ። በመጀመሪያ የይለፍ ቃሎቻችን የሚከማቹበትን ሳጥን የምንቆልፍበት ጠንካራ እናት የይለፍ ቃል መፍጠር አለብን።ከዚያ የይለፍ ቃል ሳጥኑን (database) ማኖር (ሴቭ ማድረግ)።

አዲስ የይለፍ ቃል ሳጥን ለመፍጠር የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል ያስፈልጋል።

ደረጃ 1፤በስእሉ እንደሚታየው የሚከተሉትን ደረጃዎች መሔድ File > New

ስእል 4፤ የኪይፓስ ገጽ የአዲስ የይለፍ ቃል መፍጠሪያው File > Newተከፍቶ

ይህ መስኮት በተራው የአዲስ የይለፍ ቃል ማጠራቀሚያ መፍጠሪያውን ማዘዣ Create New Password Database ይከፍትልናል

ስእል 5፤ የኪፓስ አዲስ የይለፍ ቃል መፍጠሪያ ወይም ማጠራቀሚያ (Create New Password Database) ገጽ

ደረጃ 2፤ ቀደም ሲል የፈጠርነውን እናት የይለፍ ቃል ( Master Password) እዚህ በሚገኘው ቦታ *ማስገባት/መጻፍ**

ስእል 6፤ የኪፓስ የእናት የይለፍ ቃል ማስገቢያ ለመከፈት ተዘጋጅቶ

ከይለፍ ቃል ማስገቢያው ስር አረንጓዴ-ብርቱካንማ ቀለም ያለው የምናስገባውን የይለፍ ቃል ጥንካሬ ደረጃ የሚያሳይ መከታተያ እንመለከታለን። በይለፍ ቃላችን ውስጥ የምንጠቀምባቸው ምልክቶች ብዛትና ውስብስብነት በጨመረ መጠን የይለፍ ቃሉ ጥንካሬ እያደገ ከሆነ የአረንጓዴው ቀለምመጠንም ይጨምራል።

ጥቆማ፤ ቢያንስ ቢያንስ የይለፍ ቃል ጥንካሬ ማሳያው እስከ ግማሽ ድረስ በአረንጓዴ ቀለም እንዲሸፈን ለማድረግ መሞከር ያስፈልጋል።

ደረጃ 3፤ ያስገባነውን የይፈለፍ ቃል ለመላክ ይህንን “ይሁን/አዎን” የሚል ማዘዣ ስንነካ፣ የይለፍ ቃሉን በድጋሚ እንድናረጋግጥ የሚጠይቀን ሌላ የማረጋገጫ መስኮት Repeat Master Passwordይከፈታል።

ስእል 7፤ የኪፓስ የይለፍ ቃል ማረጋገጫ ገጽ

ደረጃ 4፤ ቀደም ሲል ያስገባነውን/ የጻፍነውን የይለፍ ቃል መልሶ መጻፍ/ማስገባት፣ ከዚያም “ይሁን” የሚለውን ማዘዣ መጫን/ክሊክ

ደረጃ 5፤ ይቺን በይለፍ ቃል ማስገቢያው አጠገብ የምትገኝ ምልክት በመንካት ያስገባነው የይለፍ ቃል ትክክል መሆኑን ለማየት እንችላለን። ይቺ ምልክት ወደ ጥቁር ነጥብነት እየተለወጠ የሚቀመጠውን የይለፍ ቃል ወደምናነበው ምልክትነት መልሶ ስለሚያሳየን ትክክለኝነቱን ለማረጋገጥ እንችላለን።

ማስጠንቀቂያ፤ ከጀርባችን ሆኖ የምንሠራውን የሚከታተል ሰው ካለ ግን ይህን ማድረግ የለብንም። ምክንያቱም የይለፍ ቃላችንን በግልጽ ሊያየው ስለሚችል ነው።

እናት የይለፍ ቃሉን ሁለት ጊዜ በትክክል ካስገባን በኋላ ከታች በስእሉ የሚታየው የኪፓስ ዋና ገጽ ይከፈታል።

ስእል 8፤ የኪፓስ የይለፍ ቃል ማስቀመጫ ዋና ገጽ ተከፍቶ

አንድን የይለፍ ቃል ማጠራቀሚያ ከፈጠርን በኋላ ማስቀመጥ/ማኖር (save) አለብን። የይለፍ ቃሉን ማጠራቀሚያውን ለማኖር የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል ይኖርብናል፤

ደረጃ 1፤በስእሉእንደሚታየውመጀመሪያ FileቀጥሎSave As የሚሉትን መምረጥ/ክሊክ (Select File > Save As)

ስእል 9፤ የኪፓስ የይለፍ ቃል ማስቀመጫ ገጽ

ይህ ምርጫችን ከታች የሚታየውን Save As የሚባለውን የማኖሪያ ምርጫ መስኮት ይከፍተዋል

ስእል 10፤ የ Save As ገጽ

ደረጃ 2፤ ለይለፍ ቃል ማጠራቀሚያው የመረጥነውን ስም መስጠት/መጻፍ

ደረጃ 3፤ ማጠራቀሚያውን ለማኖር የሚለውን ማዘዣ መጫን/ክሊክ

ጥቆማ፤ ማጠራቀሚያውን (database) ያኖርንበትንቦታ/አድራሻ ማስታወስ አለብን። መጠባበቂያ ቅጂ ልንፈጥረለት ስንፈለግ በቀላሉ እንድናገኘው ይረዳናል።

የምስራች! አሁን አስተማማኝ የይለፍ ቃሎች ማጠራቀሚያ መዝገብ ፈጥረናል ማለት ነው። እንግዲህ አሁን የምንጠቀምባቸውንም ይሁን ወደፊት የሚኖሩንን የይለፍ ቃሎች በዚህ መዝገብ ውስጥ ማሰባሰብ እንችላለን።

2.2. አዲስ የይለፍ ቃል መረጃ ማስገባት የሚቻለው እንዴት ነው?

Add Entry የሚባለው ማዘዣ ገጽ አዲስ በፈጠርነው የይለፍ ቃሎች ማከማቻ ውስጥ አድራሻዎችን፣ የተጠቃሚ መታወቂያ/መግቢያ ስሞችን፣ የይለፍ ቃሎችን እና ሌሎችም አስፈላጊ የምንላቸውን መረጃዎች መጨመር እንችላለን። ቀጥሎ በምናየው ምሳሌ ለተለያዩ የኢሜይል አድራሻዎች እና ድረ ገጾች የሚያገለግሉ የተጠቃሚ ስሞችን እና የይለፍ ቃሎችን ወደ ማከማቻው መጨመር የሚቻልበትን መንገድ እንመለከታለን።

ደረጃ 1በኪፓስ የPassword Safe (የይለፍ ቃል ማከማቻ) ገጽ መጀመሪያ Select Edit ከዚያም Add Entry የሚሉትን ማዘዣዎች በመምረጥ Add Entry የሚለውን የአዲስ አድራሻዎች መጨመሪያ መክፈት። (Select Edit > Add Entry)

ስእል 11፤ በኪፓስ የይለፍ ቃል ማከማቻ የአዲስ አድራሻ/መረጃ ማስቀመጫ ማዘዣ (Edit > Add Entry)

ስእል 12፤ የኪፓስ አዲስ መረጃ ማስቀመጫ (Add Entry) ገጽ ተከፍቶ

ማስታወሻየAdd Entry ገጽ በርካታ መረጃዎችን የምናስገባበት/የምንጽፍበት ብዙ ቦታ/ጥያቄ ያቀርብልናል። ሆኖም ሁሉንም ቦታዎች መሙላት ግዴታ አይደለም። እዚህ የምናስገባቸው መረጃዎች እኛኑ ለመርዳት የሚውሉ እንደመሆናቸው የፈለግነውን መምረጥ እንችላለን። ሆኖም ዝርዝር መረጃዎቹ አንዱን አድራሻና የይለፍ ቃል ከሌሎቹ ለመለየት እና ተያያዥ ዝርዝሮችን ለማስታወስ ይረዱናል።

የተለያየ መረጃ እንድናስገባ ስለሚጠይቁን ስለእነዚህ ጥያቄዎች ወይም ባዶ ቦታዎች አጭር መግለጫ ቀርቧል።

 • Groupኪፓስ የይለፍ ቃሎቻችንን በተለያየ ቡድን እንድንከፋፍላቸው ይፈቅድልናል። ቡድኖቹን አስቀድመን መፍጠር ወይም መሰየም እንችላለን። ለምሳሌ ኢንተርኔት ('Internet') የሚል የይለፍ ቃሎች ቡድን በመፍጠር ከድረ ገጽ አድራሻዎች ጋራ የተያያዙትን የይለፍ ቃሎች በአንድ ቦታ ማኖር እንችላለን። እንዲሁ ለማኅበራዊ ሚዲያ () ወይም በምሥጢር ለምንገናኝባቸው አድራሻዎቻችን የተለያየ ቡድን መፍጠር እንችላለን።

 • Title፤ ለምናኖረው ለእያንዳንዱ የይለፍ ቃል የምንሰጠው የመለያ ስም ነው። ለምሳሌ “የጂሜይል የይለፍ ቃል” ወይም “የፌስቡክ የይለፍ ቃል” የሚል ስም ሊሆን ይችላል።

 • User name፤ ከይለፍ ቃሉ ጋራ የተያያዘው የተጠቃሚ ስም ነው። ለምሳሌ የተጠቃሚው ስም securitybox@gmail.com ሊሆን ይችላል።

 • URL፤ ከይለፍ ቃሉ ጋራ የተያያዘው የኢንተርኔት መካን (internet site) ነው። ለምሳሌ https://mail.google.com እንደማለት ነው።፡

 • PasswordAdd Entry የሚለው ገጽ እንደተከፈተ ይህ Password የሚለው ቦታ ወዲያውኑ በራሱ የይለፍ ቃል ይፈጥርልናል፤ የይለፍ ቃሉም እዚያው ይታያል። አዲስ የኢሜይል አድራሻ እየፈጠርን ከሆነ ይህንኑ ‘መደበኛ’ 'default' የይለፍ ቃል መጠቀም እንችላለን። ከዚህ በፊት ስንጠቀምበት የነበረውን የይለፍ ቃል ኪፓስ በሚፈጥረው ውስብስብ የይለፍ ቃል ለመቀየር ስንፈልግም የምንመጣው ወደዚሁ Password ወደሚለው ቦታ ነው። ኪፓስ የይለፍ ቃሎቹን ስለሚያስታውስልን ሁሉንም በቃል ለመያዝ መቸገር አያስፈልግንም፤ ሌላው ቀርቶ በይለፍ ቃሎቹ ውስጥ ያሉትን ምልክቶችና ፊደሎች ማየት እንኳን አስፈላጊያችን አይደለም። በድንገቴ ፈጠራ (randomly generated) የሚቀመሩ የይለፍ ቃሎች ጠንካራ እንደሚሆኑ ይታመናል፤ ሦስተኛ ወገኖች በቀላሉ በግምት ሊያገኟቸው አይችሉም።

በቀጣዩ ክፍል በድንገቴ ፈጠራ ወይም በአቦ ሰጡኝ (randomly generated) የሚፈጠሩ የይለፍ ቃሎችን ለመፍጠር የምንችለበት መንገድ ተብራርቷል። ሆኖም ማንኛውንም የይለፍ ቃል በማንኛውም ጊዜ ራሳችን በፈጠርነው የይለፍ ቃል መተካት እንደምንችል ማስታወስ ይገባል። ለምሳሌ ያህል ከዚህ ቀደም ስንጠቀምበት የቆየነውን አንድ አድራሻ ከነይለፍ ቃሉ በኪፓስ ማከማቻ ማኖር ፈለግን እንበል። ይህን ስናደርግ ኪፓስ ራሱ በቀጥታ የሚፈጥርልንን የይለፍ ቃል በማጥፋት ራሳችንን ስንጠቀምነት የቆየነውን የቀድሞውን የይለፍ ቃል ማስገባት/መጻፍ እንችላለን።

 • Repeat Password፤ ያስገባነውን የይለፍ ቃል በድጋሚ በመስጠት የምናረጋግጥበት ቦታ።
 • Quality፤ የይለፍ ቃሉ ጥንካሬ የሚለካና የሚያሳይ። ጥንካሬው የሚለካው በቃሉ ርዝመት እና ባካተታቸው ምልክቶች ድንገቴተነት (randomness) ነው። በጥንካሬ መለኪያው ላይ አረንጓዴ በበዛ መጠን፣ የይለፍ ቃሉ ጥንካሬ ይጨምራል።
 • Notes፤ ይህ ስፍራ ስለኖርነው አድራሻው ወይም ስለ ገጹ አስፈላጊ የምንለውን ተጨማሪ መረጃ ሁሉ የምንመዘግብበት ነው። ለምሳሌ ከኢሜይል አድራሻው ጋራ የተያያዙ ይህን መሰል መረጃ ሊሆን ይችላል፤ Mail server settings: POP3 SSL, pop.gmail.com, Port 995; SMTP TLS, smtp.gm ail.com, Port: 465

ማስታወሻኪፓስ ውስጥ ያኖርነውን የይለፍ ቃል መቀየር ብቻውን በቀጥታ የአድራሻውን የመግቢያ የይለፍ ቃል አይቀይረውም! ኪፓስን ልክ እንደ ኤሌክትሮኒክ የአድራሻ መመዝገቢያ ማስታወሻ (ደብተር) መቁጠር ይቻላል። ይህ ማስታወሻ እኛ የጻፍንበትን ይይዛል እንጂ ከዚያ አልፎ የሚያደርገው ነገር አይኖርም።

ለምሳሌ ከይለፍ ቃል ቡድኖች (Group) መካከል Internet የሚለውን መርጠን አዲስ የኢሜይል አድራሻ አስገብተን ከሆነ ገጹ የሚከተለውን ሊመስል ይችላል፤

ስእል 13፤ የኪፓስ አዲስ የይለፍ ቃል ማኖሪያ (Add Entry) ገጽ ተሟልቶ ሲታይ

ደረጃ 2፤ ቀደም ሲል በደረጃ 1 በተገለጸው መልኩ አዲሱን የይለፍ ቃል አስፈላጊና ትክክለኛ ከምንላቸው ተያያዥ መረጃዎች ጋራ ካሟላን በኋላ ይህንኑ በማከማቸው ለማኖር ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ

ያስገባነው አዲሱ አድራሻና የይለፍ ቃሉ *Internet * በሚለው ቡድን ስር ይታያል

ስእል 14፤ የኪፓስ የይለፍ ቃል ማከማቻ ገጽ

ማስታወሻ፤ በዚህ መስኮት ግርጌ የተመረጠውን አድራሻ የሚመለከቱ ዝርዝር መረጃዎች ይታያሉ። ምዝገባው የተደረገበትን ቀን፣ የታረመበት/የተለወጠበት ቀን፣ የይለፍ ቃሉ እንዲቀየር የወሰንበት ጊዜ፣ ስለ አድራሳው ያስገባነው ተጨማሪ መረጃና ማስታወሻ ሁሉ ይገኛል። የይለፍ ቃሉን ግን አያሳይም።

 • Expires፤ የይለፍ ቃሉን በየጊዜው ለምሳሌ በየሦስት ወሩ ለመቀየር ከፈለግን ኪፓስ ይህንኑ እንዲያስታውሰን ማድረግ እንችላለን። Expires የሚለው አገልግሎትም ይህ ነው። በመጀመሪያ አጠገቡ የሚገኘውን ሳጥን በመንካት (Check) አገልግሎቱን ማስጀመር፤ ቀጥሎም የይለፍ ቃሉን የአግልግሎት ማብቂያ ጊዜ መምረጥ። ከዚህ በኋላ የአገልግሎት ጊዜው ሲያበቃከታች በምሳሌው እንደሚታየው ከስሙ አቅራቢያ በቀይ ቀለም የኤክስ () ምልክት ይታያል።

ስእል 15፤ የይለፍ ቃል የመቀየሪያ ጊዜ ማለፉን የሚያሳይ ምልክት

2.3 የይለፍ ቃል መረጃዎችን መለወጥ የሚቻለው እንዴት ነው

በኪፓስ ውስጥ ያኖርነውን ማንኛውንም መረጃ በፈለግን ጊዜ መለወጥ እንችላለን። ለእያንዳንዱ ምዝገባ/አድራሻ የይለፍ ቃሉን ለመቀየር ወይም ሌሎች ቀድሞ ያስገባናቸውን ከአድራሻው ጋራ የተያያዙ መረጃዎችን ማስተካከል እንችላለን። (የይለፍ ቃሎችን በየሦስት ወይም ስድስት ወሩ መቀየር ጥሩ ልማድ ነው።)

አንድን ምዝገባ/አድራሻ ለማረም የሚከተሉትን ደረጃዎች መከትል ያስፈልጋል።

ደረጃ 1፤ ለማስተካከል የፈለግነው አድራሻ የሚገኝበትን Group ቡድን/ስብስብ መምረጥ Select

ደረጃ 2፤ ተፈላጊውን አድራሻ (entry) መምረጥ (Select)፤ ከዚያም ከዚህ በታች የሚታየውን መስኮት ለመክፈት አድራሻውን በቀኝ ንኬት (right click) መክፈት፤

ስእል 16፤ የኪፓስ የይለፍ ቃል ማከማቻ የማረሚያ ማዘዣ (Edit menu)

ደረጃ 3፤ የይለፍ ቃሉን ጨምሮ ያሉትን መረጃዎች ለማስተካከል በቅድሚያ ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ

አስቀድሞ ራሳችንን ፈጥረን/ቀምረን ያስገባነውን የይለፍ ቃል ኪፓስ ራሱ በሚፈጥርልን የይለፍ ቃል ለመተካት ከፈለግን በቀጣዩ ክፍል የተጻፈውን ማንበብ ይጠቅማል።

2.4 ግብታዊ የይለፍ ቃል የሚፈጠረው እንዴት ነው?

ረጅም፣ በግብታዊነት ወይም በአቦ ሰጡኝ የሚቀናበሩ የይለፍ ቃሎች ጠንካራ እንደሆኑ ይቆጠራሉ። በግብታዊነታቸው በሒሳባዊ መርሖች ላይ የተመሰረተ በመሆኑ የይለፍ ቃላችንን በግምት ለማግኘት ለሚሞክር ማንኛውም ሰው ሥራው እጅግ ከባድ ይሆንበታል። ኪፓስ በዚህ መንገድ የሚፈጠሩ የይለፍ ቃሎችን ለመቀመር የሚረዳን የይለፍ ቃል መፍጠሪያ Password Generator አለው። ቀደም ሲል እንዳየነው አዲስ አድራሻ ወይም ምዝገባ ስናደርግ ኪፓስ በቀጥታ በግብታዊ ፈጠራ የተቀመረ የይለፍ ቃል ያቀርብልናል።

በዚህ ክፍል ይህንን በራሳችን እንዴት ልናደርገው እንደምንችል እንመለከታለን።

ማስታወሻ፤ የይለፍ ቃል ማቀናበሪያውን ማለትም Password Generator ሥራ ለማስጀመር Add Entry እና Edit/View Entry ከሚሉት አማጭ ማዘዣዎች በአንዱ መሔድ ይቻላል። ሌላው አማራጭ Tools > Password Generator መሔድ ነው።

ደረጃ 1በAdd Entry ወይም በEdit/View Entry በኩል ሔዶ ይህንን ምልክት በመንካት/ክሊክ ከዚህ በታች እንደሚታየው Password Generator ገጽ ሥራ ማስጀመር

ስእል 17፤ የኪፓስ የይለፍ ቃል መቀመሪያ (Password Generator) ገጽ

የይለፍ ቃል መቀመሪያው አዲስ የይለፍ ቃል ለመፍጠር የሚያስችሉ የተለያዩ አማራጮችን ያቀርብልናል። የሚፈጠረውን የይለፍ ቃል ርዝመት መወሰን እንችላለን፤ በይለፍ ቃሉ ውስጥ አገልግሎት ላይ የሚውሉ የምልክት አይነቶችንም መመረጥ እንችላለን። ለዚህ ምሳሌ፣ የተለመዱት መደበኛ አማራጮችን እንዳሉ እንወስዳቸዋለን። ይህ ማለት የይለፍ ቃሉ ርዝመት 20 ምልክቶች (characters) ይሆናል፣ እንዲሁም የእንግሊዝኛው ፊደሎች ትልቅና ትንሽ አይነቶች እና ቁጥሮች ይደባለቁበታል ማለት ነው።

ደረጃ 2፤ ይህን ፍጠር/ቀምር የሚለውን ማዘዣ መንካት/ክሊክ። ቅመራው ሲጠናቀቅ ኪፓስ በእኛ ምርጫ የተፈጠረውን አዲሱን የይለፍ ቃል ያቀርብልናል።

ስእል 18፤ በኪፓስ የተቀመረ የይለፍ ቃል ማሳያ

ማስታወሻ የተቀመረውን የይለፍ ቃል ዝርዝር ምንነት ለማየት ይህንን መንካት/ክሊክ እንችላለን። በዚህ ጊዜ በጥቁር ነጥቦች መልክ ብቻ የሚታው የይለፍ ቃል በትክክል ወደወከላቸው ምልክቶች ተቀይሮ እንመለከተዋለን። ሆኖም ቀደም ሲል እንደተቀስነው አጠገባችን ሰው የይለፍ ቃሉን በግልጽ እንዲመለከትብን ሊያደርግ ይችላል። ይህን በተመለከተ በሌላ ክፍል 3.0 የኪፓስ የይለፍ ቃሎችን መጠቀም በስፋት እንመለስበታለን።

ደረጃ 3፤ የተፈጠረውን የይለፍ ቃል ለማጽደቅ ይህንን “ተቀብያለሁ/አጽድቄያለሁ” የሚል ማዘዣ መንካት/ክሊክ። ይህም ወደ Add Entry ገጽ ይመልሰናል።

ስእል 19፤ የኪፓስ Add Entry ገጽ

ደረጃ 4፤ ይህንን በመንካት/ክሊክ አድራሻውን ወይም ምዝገባውን ማኖር (save)።

ደረጃ 5፤ በድጋሚ ወደ File > Save በመሔድ በአጠቃላይ በማከማቻው ውስጥ ያደረግነውን ለውጥ ማኖር (save)፡

2.5 ኪፓስን መዝጋት፣ ማሳነስ እና መልሶ መክፈት (Minimize and Restore)

የከፈትነውን የኪፓስ ፕሮግራም በማንኛውም ሰዓት ማሳነስ (minimize) ወይም መዝጋት እንችላለን። ሆኖም አንድ ጊዜ ካሳነስነው ወይም ከወጣን በኋላ መልሰን ለመክፈት ስንፈልግ እናት የይለፍ ቃላችንን (Master Password) እንድናስገባ እንጠየቃለን።

ኪፓስ ራሱን ሊያሳንስ (minimize) ይችላል፤ በዚህ ጊዜ በኮምፒውተራችን ግርጌ በስተቀኝ በኩል ባለው ሲስትም ትሬይ ምልክቱ ይታያል።

ኪፓስ ፕሮግራሙን የምንቆልፍበት አማራጭም ይሰጣል። ይህን ለማድረግ የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል ነው፤

ደረጃ 1፤ መጀመሪያ File ከዚያም Lock Workspace በመምረጥ ከዚህ በታች የሚታየውን ገጽ መክፈት፤

ስእል 20፤ ኪፓስ የመቆለፊያ ገጽ (Safe Before Close/Lock prompt screen)

ደረጃ 2፤ እዚህ ከላይ በሚታየው ሳጥን ውስጥ ያለውን “ይሁን” የሚል ምርጫ መንካት/ክሊክ፤ ይህን ማድረግ ያደረግናቸውን ለውጦች ካሉ ያኖራቸዋል (save)፣ ከዚያም የኪፓስን አገልግሎቶች በሙሉ ይዘጋቸውና በስእል 3 የሚታየውን ይመስላል። * በሲስትም ትሬይ (System Tray)* ላይ ከታች የሚታየው ምልክት ይታያል፤

ደረጃ 1፤ ይህንን ምልክት በእጥፍ ንኬት በመክፈት ኪፓስን ወደ መደበኛ ቦታው መመለስ ይቻላል፤ ይህን ጊዜ የሚከተለውን የመሰለ ገጽ ይከፈታል፤

ስእል 21፤ የኪፓስ የማከማቻ መክፈቻ ገጽ (Open Database - NetSecureDb.kdb)

ደረጃ 3ኪፓስን ለመክፈት እናት የይለፍ ቃላችንን ማስገባት

ኪፓስን ለመዝጋት ደግሞ የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል ነው፤

ደረጃ 1የኪፓስን ፕሮግራም ሙሉ በሙሉ ለመዝጋት File ከዚያም Exit መምረጥ ይገባል።

ምናልባት ያላኖርነው (unsaved) መረጃ ካለ ኪፓስ ይህንኑ እንድናደርግ ይጠይቀናል።

2.6 የይለፍ ቃል ማከማቻውን የመጠባበቂያ ቅጂ መፍጠር

በኮምፒውተራችን ላይ የሚቀመጠው የኪፓስ ክምችት .kdb (.ኬዲቢ) በሚል የፋይል ተቀጽላ ስያሜ ይለያል፡ ይህንን ፋይል ወደ ተንቀሳቃሽ የመረጃ ቋት (USB memory stick) መቅዳት ይቻላል። እናት የይለፍ ቃሉ እስካልተሰጠ ድረስ ፋይሉን የትም ቢሆን መክፈት አይቻልም።

ደረጃ 1፤ ወደ File ሔዶ Save Asን መምረጥ፤ ከዚያም የክምችቱን ቅጂ ለማኖር አዲሱን ቦታ መርጦ መምራት ነው።

የኪፓስ ፕሮግራምን በተንቀሳቃሽ መረጃ ቋታችን () እንዳለ ልንከፍተውና ልንጠቀምበትም እንችላለን። ለዝርዝር መረጃ Portable KeePass መመልከት ይጠቅማል።

2.7 እናት የይለፍ ቃልን መለወጥ የሚቻለው እንዴት ነው?

እንደ ሌሎቹ ሁሉ የኪፓስን እናት የይለፍ ቃል መቀየር ይቻላል። ይህን ለማድረግ መጀመሪያ ማከማቻውን በቀድሞው እናት የይለፍ ቃል መክፈት ያስፈልጋል። ከዚያ የሚከተሉትን ሁለት ደረጃዎች መከተል ነው።

ደረጃ 1፤ መጀመሪያ File ከዚያ Change Master Key የሚለውን ማዘዣ መምረጥ። (File > Change Master Key)

ስእል 22፤ የኪፓስ የእናት የይለፍ ቃል መቀየሪያ ገጽ

ደረጃ 2፤ አዲሱን እናት የይለፍ ቃል በሚቀርብልን ባዶ ቦታ ሁለት ጊዜ ማስገባት/መጻፍ

ስእል 23፤ የኪፓስ የእናት የይለፍ ቃል መቀየሪያ ገጽ

የኪፓስ የይለፍ ቃሎችን መጠቀም

3.0 የኪፓስ የይለፍ ቃሎችን መጠቀም

ጠንካራና ውስብስብ የይለፍ ቃሎችን በቀላሉ ማስተወስ አይቻልም። ስለዚህም በኪፓስ ውስጥ ያከማቸናቸውን ጠንካራ የይለፍ ቃሎች በሙሉ አስታውሶ መጻፍ አስቸጋሪ መሆኑ አይቀርም። ኪፓስ ለዚህ መፍትሔ አለው፤ በማከማቻችን ውስጥ የሚገኙትን የይለፍ ቃሎች ከኪፓስ ገልብጠን (ኮፒ አድርገን) የምንፈልገው የኢሜል አድራሻ ወይም ድረ ገጽ ላይ ማስገባት (ፔስት ማድረግ) እንችላለን። የይለፍ ቃል ጥበቃውን የበለጠ አስተማማኝ ለማድረግ ማንኛውም የተገለበጠ (ኮፒ የተደረገ) የይለፍ ቃል ከ10 ሰከንድ በኋላ በራሱ ይጠፋል፤ መልሰን ልንጠቀምበት አንችልም ማለት ነው። ስለዚህም የምንፈልገውን የይለፍ ቃል በመገልበጥ በተገቢው ቦታ በመለጠፍ በቀላሉ መጠቀም እንችላለን፤ ጊዜያችንን እንቆጥባለን።

ደረጃ 1፤ የምንፈልገውን የይለፍ ቃል በቀኝ ንኬት(Right click) ስንከፍት አማራጭ ማዘዣዎች ቁልቁል ይዘረዘራሉ።

ደረጃ 2፤ ቁልቁል ከተዘረዘሩት አማራጮች መካከል ከታች በስእሉ እንደሚታየው Copy Password የሚለውን መምረጥ፤

ስእል 1፤ የኪፓስ የይለፍ ቃል ማከማቻ ገጽ

ደረጃ 3፤ ከዚያም ከገለበጥነው የይለፍ ቃል ጋራ ወደሚዛመደው አድራሻ ወይም ድረ ገጽ በመሔድ የይለፍ ቃሉ መለጠፍ (paste)

ስእል 2፤ በጂሜይል አድራሻ የይለፍ ቃል ተለጥፎ

ጥቆማ፤ በተሻለ ቅልጥፍና ለመገልበጥ፣ ለመለጠፍ እና ከአንዱ መስኮት ወደሌላው ለመሻገር የመተየቢያ ገበታውን አቋራጭ መጠቀም ይመከራል። የይለፍ ቃሉን ለመገልበጥ (ኮፒ ለማድረግ) በጀመሪያ በመተየቢያ ገበታችን ያለውን Ctrl (ኮንትሮል) የሚባለውን ቁልፍ ተጭኖ መያዝ (Press and hold)፤ ከዚያም Cን መጫን። በመቀጠል የይለፍ ቃሉ ወደሚገባበት ትክክለኛ ቦታ ሔዶ ለመለጠፍ (ፔስት) በቅድሚያ Ctrlን (ኮንትሮል)ተጭኖ መያዝ (Press and hold)፣ አስከትሎም Vን መጫን። ከአንዱ መስኮት ወደሌላው ለመሸጋገር ደግሞ Altን ተጭኖ መያዝና ደርቦ tabን መንካት። ይህ ከተከፈቱት ፕሮግራሞች እና መስኮቶች መካከል በቀላሉ እንደንመርጥ ያስችለናል።

ማስታወሻኪፓስን ሁልጊዜም የምንጠቀም ከሆነ የይለፍ ቃሎቻችንን ዝርዝር ቅንብር ማወቅ ቀርቶ ላናየውም እንችላለን። ቀድቶ የመለጠፍ (copy/paste) አቋራጩ የይለፍ ቃሉን ከማከማቻው ወደሚፈለገው መስኮት የመውሰዱን ሥራ እጅግ ያቀለዋል። ከነጭራሹም የይለፍ ቃሉን በድንገቴ ቅንብር (Random Generator) ፈጥረነው ከሆነ የይለፍ ቃሉን ምልክታዊ ይዘት ፈጽሞ አይተነው ላናውቅ እንችላለን። ሆኖም የኪፓስ ተጠቃሚዎች የይለፍ ቃሉን ዝረዝር የግድ ማወቅም ሆነ ማስታወስ አያስፈልገንም!

ተንቀሳቃሽ ኪፓስ

1.0 በሚጫነው (Installed) እና በተንቀሳቃሹ የኪፓስ (KeePass) አይነቴዎች መካከል ያለው ልዩነት

ተንቀሳቃሽ መሣሪያዎቹ በምንጠቀምበት ኮምፒውተር ላይ ስለማይጫኑ፣ ፕሮግራሞቹ እንዳሉንም ሆነ እንደምንጠቀምባቸው ላይታወቅ ይችላል። ሆኖም ተንቀሳቃሽ የውጫዊ ቅንጣቶቻችን (external device) ወይም የማስታወሻ ቋታችን (USB memory stick) እና የተንቀሳቃሽ መሣሪያዎቻችን ደኅንነት እንደምንጠቀምበት ኮምፒውተር ጤንነት እንደሚወሰን መዘንጋት የለብንም። ኮምፒውተሩ የተበከለ ከሆነ ለአድዌር፣ ለማልዌር፣ ለስፓይዌር እና ለቫይረስ ሊጋለጡ ይችላሉ። ከዚህ ውጭ በተንቀሳቃሽ ኪፓስ (Portable KeePass) አይነቴ እና በኮምፒውተር ላይ በሚጫነው አይነቴ መካከል ምንም የአግልግሎት ልዩነት የለም።

2.0 ተንቀሳቃሽ ኪፓስን መጫን እና መጠቀም (Download and Extract)

ደረጃ 1፦ ወደ መጫኛው ድረ ገጽ ለመሔድ ይህንን http://keepass.info/download.html መስፈንጠሪያ መንካት/ክሊክ

ደረጃ 2፦ ይህንን የፋይል ማዘዣ በመንካት/ክሊክ የመጫኛውን ገጽ ምንጭ መክፈት።

ደረጃ 3፦ ይህንን የተንቀሳቃሽ ኪፓስ የመጫኛ ፋይል በኮምፒውተራችን ላይ ለማኖር “ይሁን” የሚለውንን ይህን ማዘዣ መንካት/ክሊክ። ከዚያም ካኖርንበት ቦታ ፈልጎ ማግኘት።

ደረጃ 4፦ ፋይሉን ወዳኖርንበት ቦታ በመሔድ ይህንን በእጥፍ ንኬት መክፈት የምርጫዎች ዝርዝር የያዘውን ድንገቴ-መስኮት (pop-up menu) ይከፍትልናል። በዚያ ከሚታዩት አማራጮች Extract files... የሚለውን መምረጥ። በስእሉ የሚታየው ገጽ ይከፈታል፤

ስእል 1፤ የመክፈቻ መንገድ እና የአማራጮች መስኮት (The Extraction path and options window)

ደረጃ 5በስእል 2 እንደሚታየው ወደምንፈልገው ተንቀሳቃሽ የማስታወሻ ቅንጣት ወይም የማስታወሻ ቋት (USB memory stick) መሔድ፤ ከዚያም ይህንን የኪፓስ ፋይል የምንከፍትበትን አዲስ ማህደር ለመፍጠር የሚረዳንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ

ደረጃ 6፦ ለአዲሱ ማህደር/ፎልደር የምንፈልገውን ስም እዚህ ቦታ ወይም ከታች በስእል 3 እንደሚታየው በዶክመንት ዛፉ ላይ መስጠት/መጻፍ።

ስእል 2፤ የመክፈቻ መንገድ እና አማራጭ የዶክመንት ዛፍ

ማስታወሻለተንቀሳቃሽ ኪፓስ ማህደር/ፎልደር የተለየ ስም መስጠት ፕሮግራሙ እንዳለንም ሆነ እንደምንጠቀምበት እንዳይታወቅብን ሊረዳን ይችላል።

ደረጃ 7፦ የፋይሉን ይዘት አዲስ ወደተፈጠረው ማህደር/ፎልደር ለመውሰድ ይህንን ማዘዣ መንካት

ደረጃ 8፦ ወደ ተንቀሳቃሽ የመረጃ ቅንጣቱ ወይም የማስታወሻ ቋቱ በመሔድ የተንቀሳቃሽ ኪፓስ ማህደሩን መክፈት

ስእል 3፤ ተንቀሳቃሽ የመረጃ ማጠራቀሚያው መስኮት አዲስ የተከፈተውን የኪፓስ ፎልደር/ማህደር ያሳያል

ደረጃ 9ተንቀሳቃሽ ኪፓስን መጠቀም ለመጀመር ይህንን ፋይል በእጥፍ ንኬት መክፈት።

ስለ ኪፓስ አጠቃቀም ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ይህንን ኪፓስ የተባለ ምእራፍ ማንበብ ይመከራል።

የሚዘወተሩ ጥያቄዎች እና ክለሳ

4.0 የሚዘወተሩ ጥያቄዎች እና ክለሳ

ኦላና እና ሰላም ኪፓስ ለመጠቀም ምቹ የሆነ በጣም ቀላል ፕሮግራም እንደሆነ አስበዋል። አንድ ግር የሚላቸውን ነገር ቢኖር በኪፓስ የይለፍ ቃሎችን የመፍጠር ልማድ ለመፍጠር አለመቻላቸው ነው። ሰላም የይለፍ ቃሎቹን ፈጽሞ ሳታይ መጠቀሟን መልመድ ቸግሯታል። እርግጥ የይለፍ ቃሎቹን ሁሉ በቃል ከማስታወስ ይቀላል።

ጥያቄኦላና፣ የኪፓስ ቀላልነትና ምቹነት በጣም ገርሞኛል። ግን አንድ ነገር ያሳስበኛል፤ እናት የይለፍ ቃሉን በሆነ ምክንያት ብረሳው በኪፓስ ማከማቻ የሰበሰብኳቸውን የይለፍ ቃሎች መልሼ ላገኝ የምችልበት እድል መንገድ ይኖር ይሆን?

መልስይህማ በጣም ቀላል ነው፣ ሰላም። መልሱ “የለም” የሚል ነው። እናት የይለፍ ቃልሽን ከረሳሽው በውስጡ ያለውን ነገር መልሰሽ የምታገኚበት ምንም መንገድ የለም። ደግነቱ ግን ሌላ ማንኛውም ሰው ቢሆን መረጃዎቹን ሊያገኛቸው አይችልም። ይህን አደጋ ለመከላከል በኢንተርኔት ደኅንነት መጽሐፍ ምእራፍ 3. አስተማማኝ የይለፍ (የምሥጢር) ቃል መፍጠር እና መጠቀም የተዘረዘሩትን ዘዴዎች መጠቀም አስፈላጊ ነው።

ጥያቄለመሆኑ ኪፓስን ከኮምፒውተሬ ባጠፋው (ኢመጫን) በውስጡ ያከማቸሁት የይለፍ ቃል ምን ይሆናል?

መልስፕሮግራሙ ይወገዳል ()። ነገር ግን በውስጡ ያጠራቀምሽው ነገር ሁሉ በኮምፒውተርሽ ላይ ይቀራል፤ በ.kdb file ቅርጽ ይቀመጣል። እንደገና የኪፓስ ፕሮግራም ጭነሽ፣ በቀድሞው እናት የይለፍ ቃል ይህንን ፋይል መክፈትና በውስጡ ያለውን መረጃ ማግኘት ትችያለሽ።

ጥያቄ፤ ፋይሉን (database file) በስሕተት ሳላጠፋው አልቀረሁም፣ እባክል።*

መልስ፤ የፋይሉን መጠባበቂያ ቅጂ እንደምታኖሪ ተስፋ አደርጋለሁ። በተጨማሪም ፋይሉን የት እንዳስቀመጥሽው መርሳት የለብሽም። ኮምፒውተሩ ውስጥ .kdb የሚል የፋይል ተቀጽላ ያለውን ፋይል ማሰስ (ሰርች) ፋይሉን ለማግኘት ይረዳሽ ይሆናል። ነገር ግን ፋይሉን በእርግጥ አጥፍተውሽው ከሆነ በአጠቃቀም መመሪያ መጽሐፍ ውስጥ ስለ ሪኩቫ (Recuva) የተጻፈውን መመልከት አለብሽ። ፋይሉን መልሶ ለማግኘት ሊረዳሽ ይችላል።*

4.1 የክለሳ ጥያቄዎች

 • አንድን የይለፍ ቃል ጠንካራ የሚያደርገው ምንድን ነው?
 • በኪፓስ ውስጥ ያስቀመጥነውን የይለፍ ቃል መለወጥ የምንችለው እንዴት ነው?
 • ኪፓስን በመጠቀም 30 ምልክቶች (character) ያሉት የይለፍ ቃል መፍጠር የሚቻለው እንዴት ነው?