ፒድጂን ወኦቲአር - አስተማማኝ የፈጣን መልእክት ልውውጥ

Updated 8 August 2014

መመሪያው በወቅቱ አልተሻሻለም፤ በቅርቡ ይሰረዛል

:Introduction

ዋናው ገጽ (Homepage)

ኮምፒውተራችን ምን ያስፈልገዋል?

 • የኢንተርኔት ግንኙነት
 • ማንኛውም የዊንዶውስ አይነቴዎች

በዚህ መመሪያ ጥቅም ላይ የዋሉት አይነቴዎች

 • Pidgin 2.7.11
 • OTR 3.2.0.1

ለመጠቀም የሚያስፈልግ ፈቃድ/ላይሰንስ ነጻ ሶፍትዌር (Freeware)

አስፈላጊ ንባብየኢንተርኔት ደኅንነት መጽሐፍ ምእራፍ [7. የኢንተርኔት ግንኙነታችንን በምሥጢር መያዝ] (/am/chapter-7)

ይህን መሣሪያ መጠቀም ለመጀመር የሚፈጀው ጊዜ

 • 30 ደቂቃ

ከዚህ መሣሪያ ምን ጥቅም እናገኛለን?

 • ብዙዎች የሚጠቀሙባቸውን የፈጣን መልእክት ልውውጥ አገልግሎቶች በአንድ ፕሮግራም ለማደራጀትና ለማስተዳደር ያስችላል
 • ምሥጢራዊነቱ የተጠበቀ አስተማማኝ ቻት ማድረግ እንችላለን

ከጂኤንዩ ሊኑክስ (GNU Linux)፣ ማክ (Mac OS) እና ከሌሎች የማይክሮሶፍት ዊንዶውስ ጋራ/ላይ በሚገባ የሚሠሩ ፕሮግራሞች

ፒድጂን (Pidgin) እና ኦቲአር (OTR) ከማይክሮሶፍት ዊንዶውስ እና ጂኤንዩ/ሊኑክስ የሚሠሩ አይነቴዎች አሏዋቸው። ሌላው ለማይክሮሶፍት ዊንዶውስ የሚሠራው ባለብዙ አገልግሎት (multi-protocol) የፈጣን መልእክት ልውውጥ (IM) ፕሮግራም Miranda IM (ሚራንዳ) የሚባለው ነው። ይህ ፕሮግራም ኦቲአር አገልግሎትንም ጨምሮ ይሰጣል። የማክ (Mac OS) ተጠቃሚዎች Adium (አዲየም) የተባለው እንዲጠቀሙ ይመከራሉ። ይኽኛውም ፕሮግራም ኦቲአር ለመጠቀም የሚያስችል ባለብዙ አገልግሎት የፈጣን መልእክት ልውውጥ ፕሮግራም ነው።

:Installation instructions

1.1 ይህን መሣሪያ መጠቀም ከመጀመራችን በፊት ልናውቃቸው የሚገቡ ነገሮች

ፒድጂን (Pidgin) በተለያዩ የፈጣን መልእክት ልውውጥ (Instant Messaging) (IM) አገልግሎት መስጫዎች ያሉንን አድራሻዎች በቀላሉ በአንድ ፕሮግራም ለማደራጀትና ለመከታተል የሚረዳ፣ በነጻ የሚገኝ አገልግሎት ነው። ፒድጂንን (Pidgin) መጠቀም ከመጀመራችን በፊት በፒጅን የምናስመዘግበው የፈጣን መልእክት ልውውጥ (Instant Messaging) (IM) አድራሻ/አካውንት ሊኖረን ይገባል። ለምሳሌ የጂሜይል ተጠቃሚ የሆነ ሰው የጂሜይል የፈጣን መልእክት ልውውጥ (Instant Messaging) (IM) የሆነውን GoogleTalk በፒድጂን ሊጠቀምበት ይችላል። የፈጣን መልእክት አድራሻችንን የምንከፍትበትን መረጃ አድራሻውን በፒድጂን ለማስመዝገብ እንጠቀምበታለን።

ማስታወሻ፦ ሁሉም ተጠቃሚዎች የፈጣን መልእክት አገልግሎት ሰጪዎቻቸው (Instant Messaging Service Provider) የሚተዳደሩበትን የደኅንነት ፖሊሲ በተቻለ መጠን በዝርዝር ለመረዳት እንዲሞክሩ ይመከራሉ።

ፒድጂንን (Pidgin) የሚከተሉትን የአይኤም (IM) ማለትምየፈጣን መልእክት ልውውጥ/ቻት (Instant Messaging) አገልግሎቶች ያስተናግዳል፦ AIMBonjourGadu-GaduGoogle TalkGroupwiseICQIRCMIRCMSNMXitMySpaceIMQQSILCSIMPLESametimeYahoo!Zephyr እና XMPP የተባለውን የመልእክት ስምምነት/አሠራር (messaging protocol) የሚቀበል ማንኛውም አይኤም (IM)

ፒድጂንን በተለያዩ የፈጣን መልእክት አገልግሎት ሰጪዎች መካከል መልእክት መለዋወጥን አይፈቅድም። ለምሳሌ የጉግል ቶክ (Google Talk) ተጠቃሚ የሆነ ሰው ICQ ወይም Yahoo! በሚባለው አገልግሎት ሰጪ ካለ ሰው ጋራ ፈጥን መልእክት መለዋወጥ አይችልም። ተጠቃሚዎቹ እርስ በርስ ፈጣን መልእክት ለመለዋወጥ የግድ በተመሳሳይ አገልግሎት ሰጪዎች በሚከፍቷቸው አድራሻዎች መጠቀም አለባቸው፤ በፒድጂን ለመጠቀቀምም እንዲሁ።

ይህን እንጂ ፒድጂን በተለያዩ አገልግሎት ሰጪዎች ዘንድ የከፈትናቸውን ብዙ አድራሻዎች/አካውንቶች በአንድ ላይ ለማደራጀት በሚያስችለን መልኩ ልንጠቀምበት እንችላለን። ይህ ማለት ለምሳሌ በተመሳሳይ ጊዜ የጂሜይል እና የያሁ! አድራሻዎቻችንን ከፍተን በሌላው ጫፍ የአንዱ ተጠቃሚ ከሆነ ሰው ጋራ ቻት ማድረግ ወይም ፈጣን መልእክት መለዋወጥ እንችላለን። (በፒድጅን የማይሠሩ አገልግሎቶች እንዳሉ ግን መርሳት የለብንም። የሚሠሩት ቀድም ሲል ተዘርዝረዋል።)

ፒድጂን ከሌሎች አገልግሎት ሰጪዎች በጣም የተሻለ አስተማማኝ የደኅንነት ጥበቃ የሚሰጥ በመሆኑ በፈጥን መልእክት ለውውጦች ወቅት እንድንጠቀምበት በጥብቅ እንመከራለን። ፒድጂን ምሥጢራዊነትን እና ደኅንነትን ለአደጋ ሊያጋልጡ ከሚችሉ የማያስፈልጉ አድዌሮች እና ስፓይዌዎች የጸዳ መሆኑ አገልግሎቱን የበለጠ ተመራጭ ያደርገዋል።

Off-the-Record (ኦፍ-ዘ-ሪከርድ) (ኦቲአር (OTR))፦ በተለይ ለፒድጂን ታስቦ የተዘጋጀ የአገልግሎት መጨመሪያ (plugin) ነው። የሚከተሉትን ከደኅንነት እና ምሥጢራዊነት ጋራ የተዛመዱ አገልግሎቶች ይሰጣል።

 • ማረጋገጥ(Authentication)፦ በሌላው ወገን ሆኖ ቻት የሚያደርገን ሰው በእርግጥም እኛ የምናውቅውና የምንፈልገው ሰው መሆኑን ያረጋግጥልናል።
 • የመልእክት ስወራ (Deniability)፦ የፈጣን መልእክት ልውውጣችን ማለትም ቻታችን ከተጠናቀቀ በኋላ የተለዋወጥናቸው መልእክቶች ከሁለታችን የመጡ መሆናቸው እንዳይታወቅ ይሆናል።
 • ኢንክሪፕሽን (Encryption)፦ ፈጣን መልእክቶቻችንን/ቻታችንን ማንም ሰው ሊያገኘው እና ሊያነበው አይችልም።
 • Perfect Forward Security፦ በሆነ አጋጣሚ የመግቢያ የይለፍ ቃላችን በሌላ ሰው እጅ ቢወድቅ እንኳን ከዚያ ቀደም ያደረግናቸውን ልውውጦች ሊያገኛቸው አይችልም።

ማስታወሻከኦቲአር (OTR) በፊት ፒድጂንን መጫን አለብን።

የፒድጂን እና ኦቲአር ሶፍትዌርን መጫን፤ በፒድጅን መመዝገብና አድራሻ መፍጠር

በዚህ ክፍል የሚዳሰሱ ርእሰ ጉዳዮች

2.0 ስለ ፒድጂን

ፒድጂን እና ተዛማጁ ኦፍ-ዘ-ሪከርድ (ኦቲአር/OTR) በትክክል ሥራቸውን እንዲያከናውኑ በተለይም የቀጥታ ኢንክሪፕሽን እና የማረጋገጫ ኢንጂኖቻቸው (automated encryption and authentication engine) በሚገባ መጫን አለባቸው። ደግነቱ የሁለቱም ፕሮግራሞች አጫጫን ቀላል እና በጥቂት ደቂቃዎች የሚከናወን ነው።

2.1 የፒድጂን አጫጫን

ደረጃ 1፦ ይህንን መጫኛ በእጥፍ ንኬት መክፈት፤ ወዲያውኑ Open File - Security Warning የሚል ሳጥን ይከፈታል። ይህ ከሆነ የሚለውን ማዘዣ በመንካት/ክሊክ ከታች በስእሉ የሚታየውን ገጽ መክፈት፤

ስእል 1፤ የመጫኛ ቋንቋ መምረጫና ማረጋገጫ ሳጥን

ደረጃ 2፦ ይህንን ማረጋገጫ መንካት/ክሊክWelcome to the Pidgin 2.7.11 Setup Wizard የተባለው ገጽ ይከፈታል።

ደረጃ 3 የሚለውን ማዘዣ በመንካት License Agreement (የስምምነት ሰነድ) ያለበትን ገጽ መክፈት። ስምምነቱን ካነበብን በኋላ መስማማታችንን ለመግለጽ አሁንም የሚለውን ማዘዣ መንካት፤ ተከትሎ Pidgin 2.7.11 Setup - Choose Components የሚል መስኮት ይከፈታል።

ደረጃ 4፦ አሁንም የሚለውን ማዘዣ በመንካት/ክሊክ Pidgin 2.7.11 Setup - Choose Install Location የሚለውን መስኮት መክፈት።

ደረጃ 5፦ በመደበኛነት ተመርጦ የሚቀመጠውን የአጫጫን መንገድ ተቀብሎ ለመቀጠል ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ፤ ይህም የፒድጂን ሶፍትዌርን መጫኛ የሆነውን Pidgin 2.7.11 Setup - Installing መስኮት ሥራ ያስጀምረዋል።

የተለያዩ ፋይሎች እና ፎልደሮች በተከታታይ መጫን ይጀምራሉ። ይህ የመጫን ሒደት እንደተጠናቀቀ ፒድጂን 2.7.11 ተጭኖ መጠናቀቁን የሚገልጽ መስኮት (Installation Complete window) ይከፈታል።

ደረጃ 6 የሚለውን ማዘዣ በመንካት/ክሊክ የፒድጂንን የቀመር መወሰኛ Completing the Pidgin 2.7.11 Setup Wizard መርጃ መክፈት።

ቀጣዩ ደረጃ ግዴታ አይደለም፤

ደረጃ 7ፒድጂን ወዲያውኑ እንዲከፈትልን የምንፈልግ ከሆነ በዚህች ባዶ ቦታ ምልክት ማድረግ ነው።

ማስታወሻ፦ በመጫን ሒደቱ ደረጃ 3 ላይ ፒድጂንStart > Programs ዝርዝር ውስጥ እንዲታይ ተመርጦ ነበር። ስለዚህም ከፈለግን ፒድጂንን ከዚህም ማስጀመር እንችላለን።

ደረጃ 8የፒድጂን የመጫን ሒደት መጠናቀቁን ለማረጋገጥ ይህንን መንካት/ክሊክ

2.2 የኦፍ-ዘ-ሪከርድ (ኦቲአር/OTR) ኤንጂንን (Engine) መጫን

ደረጃ 1፦ በእጥፍ ንኬት (Double click) ይህንን ስንከፍተው Open File - Security Warning የሚል የአማራጮች ሳጥን ይከፈታል። ከሳጥኑ ውስጥ ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ

ስእል 2፤ የፒድጂን-ኦቲአር 3.2.0-1 የመጫኛ መርጃ (Setup Wizard)

ደረጃ 3 የሚለውን ማዘዣ በመንካት License Agreement (የስምምነት ሰነድ) ያለበትን ገጽ መክፈት። ስምምነቱን ካነበብን በኋላ መስማማታችንን ለመግለጽ አሁንም የሚለውን ማዘዣ መንካት፤ ተከትሎ pidgin-otr 3.2.0-1 Setup - Choose Install Location የሚል መስኮት ይከፈታል፤ የምንጭንበትን ቦታ ያስመርጠናል።

ደረጃ 4፦ የመጫን ሒደቱን ለማስጀመር ይህንን ማዘዣ መንካት

ደረጃ 5የፒድጂን-ኦቲአርን የመጫን ሒደት ለማጠናቀቅ ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ

ፒድጂንን እና ኦቲአርን በትክክል ጭነን ስንጨርስ ከታች በስእሉ የሚታየው ምልክት በኮምፒውተራችን ግርጌ በስተግራ በሚገኘው ታስክ ባር ላይ ይታያል፤

ስእል 3፤ የፒድጂን-ኦቲአር መለያ ምልክት

የምስራች! አሁን ፒድጂን እና ኦቲአር የተባሉትን ፕሮግራሞች በሚገባ ጭነን ጨርሰናል።

2.3 በፒድጂን የአድራሻ ምዝገባ እና አሠራር ቅመራ

በፒድጂን የምዝገባ እና የአሠራር ቅመራ (setup process) አራት መሠረታዊ ደረጃዎች አሉ። እነርሱም ለፈጣን መልእክት (IM) ማለትም ለቻት የምንጠቀምበትን አድራሻ/አካውንት በፒድጂን ማስመዝገብ፣ በሌላው ጫፍ ሆኖ መልእክት የሚለዋወጠንን ሰው ወይም በፒድጂን ቋንቋ buddy በጓደኝነት መጨመር/ማቀላቀል (adding)፣ ጓደኛችንም በተመሳሳይ እኛን በጓደኝነት ወይም buddy እንዲቀበለን/እንዲቀላቅለን ማድረግ፣ እና በመጨረሻም ለመጀመሪያ ጊዜ ቻት ለማድረግ የቻት መስኮት መክፈት ናቸው።

ፈጣን የመልእክት ለውውጥ ወይም ቻት በሁለት ሰዎች መካከል የሚፈጸም ነው። በዚህ ምሳሌም በምዝገባና በአሠራር ቅመራ ሒደት መስኮቱ ለለሁለቱ ተለዋዋጮች ወይም “buddies” የሚታይበትን የተለያየ ቅርጽ እንመለከታለን። ምሳሌዎቹ በሙሉ የተሰጡት በጉግል ቶክ (Google Talk) የተሰጡ ሲሆን ተለዋዋጮቹም ሰዎችም ዋሚ እና ኡጁሉ ብለን ሰይመናቸዋል።

ማስታወሻፒድጂንን መጠቀም ከመጀመራችን በፊት የፈጣን መልእክት መለዋወጫ (የቻት) አድራሻ/አካውንት ሊኖረግ ይገባል። አካውንቱ/አድራሻው በክፍል 1.1 ስር ከተጠቀሱት የአገልግሎቱ ሰጪዎች መካከል መሆን አለበት። አዲስ የፈጣን መልእክት መለዋወጫ (የቻት) አድራሻ የሚፈጥሩ ሰዎች ጉግል ቶክን እንዲጠቀሙ ይበረታታሉ። ስለዚሁ በክፍል 4.0 የጉግል ቶክ አድራሻ የሚፈጠረው እንዴት ነው? ስር ተጨማሪ መረጃና መመሪያ ይገኛል።

2.4 የፈጣን መልእክት አድራሻችንን በፒጅን ማስመዝገብ

የፈጣን መልእክት መለዋወጫ (የቻት) (IM) አድራሻችንን በፒድጂን ለማስመዝገብ የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል ይገባል፤

ደረጃ 1ፒድጂንን ለመክፈት ይህንን ምልክቱን መንካት/ክሊክ ወይም በStart በኩል ፒድጂን (Pidgin) (Start > Pidgin) መክፈት። ፒድጂን (Pidgin) ለመጀመሪያ ጊዜ ስንከፍት ከታች በስእሉ የሚታየው ገጽ ይተለጣል፤

ስእል 4፤ የአድራሻ/አካውንት ማረጋገጫ መስኮት (Accounts confirmation window)

ደረጃ 2፦ ከታች በስእሉ እንደሚታየው የአድራሻ/አካውንት መጨመሪያ ወይም ማስመዝገቢያውን Add Account ለመክፈት ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ

ስእል 5፤ የAdd Account ገጽ Basic፣ Advanced እና Proxy ከተባሉት ክፍሎቹ ጋራ

ደረጃ 3Protocol ከሚለው አጠገብ የሚገኘውን ቀስት በመንካት ቁልቁል ተዘርጊ ዝርዝሩን መክፈት። በስእሉ እንደሚታየው ዝርዝሩ በፒድጂን የሚደገፉ ወይም ሊሠሩ የሚችሉ የፈጣን መልእክት አይነቶች (IM) የያዘ ነው።

ስእል 6፤ የAdd Account የሚደገፉ አገልግሎቶች (protocols) ዝርዝር

ደረጃ 4፦ ተገቢውን የፈጣን መልእክት (IM) ፕሮቶኮል መምረጥ

ማስታወሻ፦ የተለያዩ የፈጣን መልእክት (IM) አገልግሎት ሰጪዎች በየራሳቸውን የምንሞላውን ክፍት ቦታ ያሳዩናል። አንዳንዶቹ ክፍት ቦታዎች እዚያው በራሳቸው ተሞልተው ሊገኙ ይችላሉ (ለምሳሌጉግል ቶክን መርጠን ከሆነ Domain በሚለው ቦታ ተሞልቶልን እናገኘዋለን)። ሆኖም ሁሉም የተጠቃሚ ስም (username) እና የይለፍ ቃል (password) እንድንሰጥ ይጠይቁናል።

ደረጃ 5Username በሚለው ቦታ የኢሜይል አድራሻችንን (ለምሳሌ terence.t.thester@gmail.com) መጻፍ

ደረጃ 6፦ ለዚህ አድራሻ/አካውንት የምንመርጠውን የይለፍ ቃል Password በሚለው ቦታ መጻፍ

ደረጃ 7Local Alias በሚለው ቦታ ላይ እንድንታወቅበት/እንድንጠራበት የምንፍልገውን የቅጽል ስም መጻፍ። ይህን ስም መስጠት ግን ግዴታ አይደለም።

ማስታወሻ፦ ምሥጢራዊነትን እና የደኅንነት ጥበቃችንን የበለጠ ለማሳደግ ፕሮግራሙ በራሱ የይለፍ ቃላችንን ባያስታውስ ይመረጣል፤ ስለዚህም Remember password የሚለውን አገልግሎት እንዲሠራ (enable) ማድረግ የለብንም። ወደ ቻት አድራሻችንን በገባን ቁጥር ፒድጂን የይለፍ ቃላችንን መዝግቦ እንዲይዘው እንፈልግ እንደሆነ ይጠይቀናል። የይለፍ ቃላችንን በራሳችን መያዛችን ምናልባት ኮምፒውተራችንን በሆነ መንገድ ማግኘት የቻለ ሰው በእኛ ስም ገብቶ የማንፈልገውን መልእክት እንዳያስተላልፍብን ይጠብቀናል። ቻት አድርገን በጨረሰኝ ቁጥር Buddies በሚለው ስር ካለው ቁልቁል ተዘርጊ ዝርዝር መካከል Quit የሚለውን መምረጥ መርሳት የለብንም።

የAdd Account ገጽ በሚገባ ተሞልቶ ሲጠናቀቅ የሚከተለውን ይመስላል፦

ስእል 7፤ ተሞልቶ የተጠናቀቀ የAdd Account ገጽ

ጥቆማGoogle TalkIRCSILC እና XMPP በቀላሉ ኢንክሪፕትድ የሆነ ግንኙነት መመሥረት ይችላሉ። ለበለጠ መረጃ በክፍል 4.1 ደኅንነቱ የተጠበቀ ግንኙነት ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው? የተብራራውን መመልከት ይገባል።

ደረጃ 8፦ አድራሻችንን/አካውንታችንን ወደ ፒድጂን ለመደመር የጀመርነውን ሥራ ለማጠናቀቅ ይህንን ማዘዣ መንካት፤ በተመሳሳይ ጊዜም አዲሱን አድራሻ ያካተተው የጓደኞች ዝርዝር Buddy List በስእሉ እንደሚታየው ይሆናል፤

ስእል 8፤ የተሻሻለ የአድራሻዎች መስኮት*፣ *ስእል 9፤ Buddy List በሥራ ላይ

እነዚህን ደረጃዎች በሚገባ ከጨረስን የፒጂን ተገናኞቻችንን (buddies) መረጃ በማስገባት መመዝገብ እንችላለን ማለት ነው።

2.5 ጓደኛን ወደ ፒድጂን ማምጣት (Add a Buddy)

ጓደኞቻችንን ወይም ተገናኞቻችንን (buddies or correspondents) ወደ ፒድጂን መጨመር አድራሻቸውን በማስገባትና በማኖር በቀላሉ የሚከናወን ነው። በቀጣዩ ምሳሌ ቴረንስ በዚሁ መንገድ ሳሊማን እንደ ጓደኛ/ተገናኝ (buddy) ሲቀበላት እንመለከታለን።

አንድን ሰው/ተገናኝ ወደ ፒጂን የፈጣን መልእክት (IM) አካውንታችን ለመጨመር የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል ይገባል።

ደረጃ 1Buddies የሚለውን በመንካት የአገልግሎት ዝርዝር መክፈት፤ ከዚያም በስእሉ እንደሚታየው + Add Buddy... የሚለውን መምረጥ

ስእል 10፤ Buddy List በተባለው ክፍል "Add Buddy..." ተመርጦ

ይህ የሚከተለውን ገጽ ይከፍተዋል፤

ስእል 11፤ የጓደኛ መጨመሪያ Add Buddy መስኮት

ደረጃ 2፦ በርካታ አድራሻዎች/አካውንቶች ካሉን እንደጓደኛ ልንቀበለው ከፈለግነው የገለግነው ሰው ከሚጠቀምበት ጋራ የሚመሳሰለውን መምረጥ አለብን።

ማስታወሻ፦ ሁለት ቻት ለማድረግ የፈለጉ ሰዎች ተመሳሳይ የፈጣን መልእክት አገልግሎት መጠቀም ይኖርባቸዋል። ይህ ፒጂንን ባንጠቀም እንኳን የሚሠራ ነው። ለምሳሌ ICQ ወይም MSN የሚጠቀምን ሰው በGoogle Talk ጓደኝነት መጨመር/መቀበል አይቻልም። ይሁንና በፒድጂን በመመዝገብ ከተለያዩ የተለያዩ አገልግሎቶችን ከሚጠቀሙ ጓደኞቻችን/ተገናኞቻችን ጋራ ለየብቻ ግን በተመሳሳይ ጊዜ ቻት ማድረግ እንችላለን፤ ከአንዱ ጋራ በICQ ከሌላው በMSN ከሦስተኛው ጋራ ደግሞ በGoogle Talk ፈጣን መልእክት መለዋወጥ እንችላለን።

ደረጃ 3Username በሚለው ቦታ የጓደኛችንን (buddy) የኢሜይል አድራሻ መጻፍ

ቀጣዩ ደረጃ አስገዳጅ አይደለም።

ደረጃ 4፦ ቀጥሎ (Optional) Alias በሚለው ቦታ ጓደኛችንን ልንለይበት የምንፈልገውን Alias ወይም ቅጽል ስም መጻፍ፤ ተከታዩን ስእል የመሰለ ገጽ ይከፈታል፤

ስእል 12፤ ተሞልቶ የተጠናቀቀ የAdd Buddy ቅጽ

ደረጃ 5፦ ጓደኛችንን ለመቀበል/ለመጨመር ይህንን ማዘዣ መንካት

ማስታወሻ፦ ይህ የመቀበል/የመጨመር እርምጃችን ጓደኛ ልናደርገው ለፈለግነው ሰው የጓደኝነት ጥያቄ ይልክለታል፤ ጥያቄው የደረሰው ሰው ጥያቄውን መቀበል ይኖርበታል። ጥያቄውም በተቀባዩ Buddy List ውስጥ እንደሚከተለው ሆኖ ይታያል፤

ስእል 13፤ የቴረንስ Buddy List ሳሊማን እንደጓደኛ መዝግቦ ይታያል

እዚህ ላይ ግብዣውን የደረሰው ሰው የሚከተለውን ደረጃ መፈጸም አለበት።

ደረጃ 6፦ ይህንን የመቀበያ ማረጋገጫ መንካት፤ ይህን ጊዜ የጋበዘን ሰው በተቀባዮቹ “የጓደኞች ዝርዝር” Buddy List ውስጥ ይታያል።

ስእል 14፤ በሳሊማ የጓደኞች ዝርዝር (Buddy List) የግብዣ መቀበያ ይታያል

ማስታወሻ፦ ከላይ በሚታየው ምሳሌ የሳሊማ ቅጽል መጠሪያ (Alias) ይታያል፤ ይህም ማንነትን ለመደበቅ ተጨማሪ ከለላ ይሰጣል።

2.6 በፒድጂን የሚገኝ ሌላው ወገን እኛን እንደጓደኛ የሚቀበለን እንዴት ነው?

የፒድጂን የቻት ጓደኛችንን ከተቀበልንና ካረጋገጥን በኋላ ጓደኛችን በተራው ይህንኑ ማድረግ አለበት/አለባት።

በዚህ ክፍል በምሳሌያችን በመቀጠል ሳሊማ በተራዋ ቴሬንስን በቻት ጓደኝነት (chat buddy) ወደ ፒድጂን አድራሻዋ ዝርዝር ስታስገባው/ስትቀበለው እንመለከታል። በዚህም ሳሊማ ቀደም ሲል በነበረው ክፍል 2.5 ጓደኛን ወደ ፒድጂን ማምጣት (Add a Buddy) ስር ከደረጃ 1 እስከ 6 የተዘረዘሩትን ደረጃዎች ትተገብራለን።

ሳሊማ ከደረጃ 1 እስከ 3 ያሉትን ስታጠናቅቅ፣ Add Buddy የሚለው የጓደኛ መቀበያ/መጨመሪያ መስኮቷ በስእሉ የሚታየውን መስሎ ይከፈታል፤

ስእል 15፤ የሳሊማ የጓደኛ መቀበያ (Add Buddy) መስኮት

ሳሊማ ይህንን ማዘዣ በመንካት በአንድ ጊዜ ቴሬንስን እንደጓደኛ መቀበል/መጨመር እና ለእርሱም የማረጋገጭ ጥያቄ (authorisation request) መላክ ትችላለች፤ በስእሉ ይታያል።

ስእል 16፤ የጓደኝነት መቀበያ/ማረጋገጫ (Authorize buddy) ለቴሬንስ እንደሚታየው

ማስታወሻ፦ የጓደኞቻችን ዝርዝር በሚቀርብበት Buddy List በተባለው ክፍል የማውሳችንን መጠቆሚያ (ከርሰር) በአንዱ ጓደኛችን ላይ ስናሳርፍ ስለእርሱ ያለን መረጃ በስእሉ እንደሚታየው በድንገቴ መስኮት ይታየናል፤

ስእል 17፤ የሳሊማ የጓደኞች ዝርዝር መስኮት ቴረንስ አዲስ ጓደኛዋ መሆኑን ያሳያል

2.7 በፒድጂን ውስጥ የቻት መስኮት መክፈት

በፒድጂን ውስጥ የፈጣን መልእክት (IM) የቻት መስኮት ለመክፈት የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል ያስፈልጋል፦

ደረጃ 1፦ በBuddy List (በዲ ሊስት) ማለትም በጓደኞቻችን ዝርዝር ውስጥ ቻት ልናደርገው የፈለግነውን ሰው ስም በቀኝ ንኬት ስንከፍተው ልናከናውን የምንችላቸውን ነገሮች የሚዘረዝር የድንገቴ መስኮት ይከፈታል፣ ከታች በስእሉ እንደሚታየው፤

ስእል 18፤ The Buddy tasks menu (ለጓደኞቻችንን ምን ማድረግ እንደምንፈልግ የሚዘረዝር መስኮት)

ደረጃ 2፦ በድንገቴ መስኮቱ ከተዘረዘረው ውስጥ IM የሚለውን መምረጥ፣ በስእሉ የሚታየው የተለመደውን አይነት የቻት መስኮት ይከፈታል፤

ስእል 19፤ የተለመደው አይነት የቻት መስኮት/ዊንዶው በፒድጂን ተከፍቶ

አሁን ከመረጥነው ጓደኛችን () ጋራ በፒድጂን ቻት ለማድረግ ዝግጁ ሆነናል ማለት ነው። ቻቱን ከመጀመራችን በፊት ግን የቻታችን ምሥጢራዊነት እና ደኅንነት የተረጋገጠ እንዲሆን የኦቲአር (OTR) ኤንጂኑ እንዲሠራ ማዘጋጀት (configure) ይኖርብናል።

2.8 የፒድጂን አድራሻን እንደገና ሥራ ማስጀመር (Re-enable)

በየጊዜው የፒድጂን አድራሻችን/አካውንታችን እንዳይሠራ ተደርጎ (disabled) ልናገኘው እንችላለን። ወይም የኢንተርኔት ግንኙነታችን ተቋርጦብን አለዚያም ኮምፒውተራችን ቆሞ (frozen) ሊሆን ይችላል። በእነዚህ ሁኔታዎች የፒድጂን አድራሻችን/አካውንታችን አላግባብ ተዘግቶ ወይም እንዳይሠራ ተደርጎ (disabled) ሊሆን ይችላል። ደግነቱ ግን ፒድጂን ይህን አካውንት ዳግም-ማስቻል (re-enable) የሚቻልባቸው የተለያዩ አማራጮች ይሰጣል።

አንድን አድራሻ/አካውንት ዳግም-ለማስቻል (re-enable) የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል ያስፈልጋል፦

ደረጃ 1ፒድጂንን ለመክፈት ይህን ምልክት መንካት/ክሊክ ወይም በStart በኩል Pidgin መክፈት (Start > Pidgin) ይቻላል።

ደረጃ 2፦ በመስኮቱ ራስጌ አግድም ከተደረደሩት መካከል Accounts የሚለውን መምረጥ፤ ከዚያ በስእሉ እንደሚታየው ከሚከፈቱት አማራጮች Manage Accounts የሚለውን መምረጥ

ስእል 20፤ በAccounts አማራጮች *Manage Accounts ተመርጦ*

ይህ ምርጫችን የሚከተለውን ገጽ ይከፍትልናል

ስእል 21፤ በAccounts መስኮት እንዳይሠራ የተደረገ (disabled) አድራሻ/አካውንት ይታያል

ደረጃ 3፦ በአድራሻው/አካውንቱ አጠገብ የሚገኘውን ሳጥን መንካት/መምረጥየፒድጂን የይለፍ ቃላችንን የሚጠይቅ መስኮት ተከትሎ ይከፈታል፤

ስእል 22፤ የፒድጂን የይለፍ ቃል እንድናስገባ የሚጠይቅ ሳጥን

ደረጃ 4የፒድጂን አድራሻችንን የይለፍ ቃል በተሰጠው ቦታ መጻፍ፤ ሳጥኑ በስእሉ የሚታየውን ይመስላል።

ስእል 23፤ የፒድጂን የይለፍ ቃል ጠያቂ ሳጥን ቃሉ ተጽፎበት

ደረጃ 5፦ አድራሻችንን/አካውንታችንን በስእሉ እንደሚታየው በድጋሚ-ለማስቻል () የጀመርነውን ሒደት ለማጠናቀቅ ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ

ስእል 24፤ በድጋሚ-ማስቻል ወደ አገልግሎት የተመለሰ አድራሻ

ደረጃ 6፦ የAccountsን መስኮት ለመዝጋት ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ

በኦቲአር ደኅንነቱ የተረጋገጠ ቻት ለማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?

በዚህ ክፍል የሚዳሰሱ ርእሰ ጉዳዮች፦

3.0 ስለፒድጂን እና ኦቲአር

ከጓደኛችን/ተገናኛችን (correspondent) ጋራ ምሥጢራዊና ደኅንነቱ የተጠበቀ የፈጣን መልእክት ለውውጥ (Instant Messaging) (IM) ክፍለ ጊዜ ከመጀመራችን በፊት ሁልጊዜም ሁለታችንም የኦቲአር ተሰኪ (plugin) ሥራ ማስጀመር አለብን። የኦቲአር ተሰኪ (plugin) በተለይ ፒድጂን ተብሎ የተዘጋጀ እንደመሆኑ በሁለታችንም ወገን ኦቲአርን ሥራ ስናስጀምረው በራሱ መናበብ ይችላል።

ማስታወሻኦቲአርን ላልጫነ እና ሥራ እንዲጀምር ላላደረገ ጓደኛችን ጋራ ምሥጢራዊና ደኅንነቱ የተረጋገጠ ቻት ለመጀመር ብንሞክር ወዲያውኑ የኦቲአር ተሰኪውን እንዴት ማግኘት እንደሚችል የሚገልጽ መልእክት ይላክለታል።

3.1 የፒድጂን-ኦቲአርን ተሰኪ (Plugin) ውቅር ማስተካከል

የኦቲአር ተሰኪን ሥራ ለማስጀመር የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል ይገባል፦

ደረጃ 1ፒድጂንን ለመክፈት እና የBuddy List (የጓደኞች ዝርዝር) መስኮትን ለመክፈት እንችል ዘንድ ይህንን የፒድጂን ምልክት በእጥፍ ንኬት መክፈት ወይም ደግሞ በStart > Programs > Pidgin በኩል መክፈት። (ስእል 1 መመልከት)

ደረጃ 2Tools የሚለውን ክፍል መክፈት፤ በዚያ ከሚገኙት አማራጮችም Plugins የሚለውን ከታች በስእሉ እንደሚታየው መምረጥ፤

ስእል 1፤ Buddy List መስኮት በ Tools ስር ከሚገኙት ምርጫዎች Plugins ተመርጦ ይታያል

ይህን ጊዜ የተሰኪዎች (Plugins) መስኮት በቀጣዩ ስእል እንደሚታየው ይከፈታል።

ደረጃ 2፦ በመስኮቱ ከተዘረዘሩት አማራጮች መካከል Off-the-Record Messaging የሚለውን ለማግኘት ወደታች በመሸብለል (Scroll) ከአጠገቡ የሚገኘውን ሳጥን መንካት

ስእል 2: ‘በፒድጂን ተሰኪ’ (Pidgin Plugins) መስኮት Off-the-Record Messaging ተመርጦ

ደረጃ 3፦ የOff-the-Record Messaging መስኮቱን አሠራር ለመወሰን ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ

የቻት ልውውጦቻችንን ምሥጢራዊነት እና ደኅንነት ለማረጋገጥ የሚያስችለንን ኦቲአር በትክክል ሥራ ለማስጀመርና አሠራሩን ለመወሰን ወይም ውቅራት ለማከናወን 3 እርምጃዎች አሉ። እነዚህ እርምጃዎች ቀጥሎ ተብራርተዋል።

 • እርምጃ አንድ፦ ይህ እርምጃ አድራሻችንን ለመቆጣጠር የሚረዳን ልዩ ቁልፍ እና አሻራ የምንፈጥርበት ነው።

ሌሎቹ ሁለት እርምጃዎች ደግሞ የፈጥን መልእክት ለውውጦቻችንን (ቻት) ምሥጢራዊነት እና ደኅንነት የምናረጋገጥበት፣ ከዚያ ደግሞ የመልእክት ተለዋዋጮቻችንን ወይም ጓደኞቻችንን (buddies) እውነተኛ ማንነት የምናረጋግጥበት ነው።

 • እርምጃ ሁለት፦ ይህ እርምጃ ኦንላይን ከሆነ ሁለቱ ወገኖች አንዱ ሌላውን ምሥጢራዊነቱ እና ደኅንነቱ የተጠበቀ የመልእክት ልውውጥ ለመጀመር ጥያቄ የሚያቀርብበት ነው።

 • እርምጃ አንድ፦ እዚህ ደግሞ የፒድጂን ጓደኛችንን (buddy) እውነተኛ ማንነት የምናረጋግጥበት (authenticating) ነው። (ማስታወሻበፒድጂን አጠራር ፈጣን መልእክት የሚለዋወጠንን ወይም ቻት የሚያደርገንን ሰው buddy ወይም ጓደኛ ብለን እንጠራዋለን። በዚህ ደረጃ ቻት ሊያደርገን የተዘጋጀው ጓደኛችንን በእርግጥም እኛ የምንፈልገውና የምናሰበው ሰው ራሱ መሆኑን የማረጋገጥ ሥራ እናከናውናለን፤ ይህ ስራ በፒድጂን አጠራር authentication ይባላል።)

3.2 እርምጃ 1 - ምሥጢራዊ ቁልፍ መፍጠር እና አሻራን ማሳየት የሚቻለው እንዴት ነው?

በፒድጂን ምሥጢራዊነቱ የተጠበቀ ቻት ለማድረግ ለተገቢው አድራሻ/አካውንት private key ማለትም የምሥጢር ቁልፍ መፍጠር እንችላለን። የOff-the-Record (ኦቲአር) መስኮት በሁለት ንኡስ ክፍሎች ይከፈላል፤ አንደኛው Config*፣ ሁለተኛው ደግሞ *Known fingerprints ይባላሉ። Config የተባለው ክፍል ለእያንዳንዱ አድራሻችን የተለየ ቁልፍ እንድንፈጥርለት እና የኦቲአር ምርጫዎችን እንድናደርግለት ይፈቅድልናል። Known fingerprints የሚለው ክፍል ደግሞ የጓደኞቻችንን ቁልፎች (friends' keys) የያዘ ነው። ይህ ማለት በምሥጢር ቻት ልናደርገው ለምንፈልገው ጓደኛችን (buddy) የግድ ቁልፍ ሊኖረን ይገባል ማለት ነው።

ስእል 3፤ የ*Off-the-Record (ኦቲአር) ገጽ Config ክፍል*

ደረጃ 1፦ የደኅንነት ጥበቃችንን የበለጠ ለማሻሻል Config በሚለው ክፍል የሚገኙትን Enable private messagingAutomatically initiate private messaging እና Don't log OTR conversations የሚሉትን አገልግሎቶች በስእል 3 እንደሚታየው መምረጥ (check)

ደረጃ 2፦ የምሥጢር ቁልፋችንን ለመፍጠር (generating) ይህንን ማዘዣ መንካት። ከዚያም የምሥጢር ቁልፍ መፍጠራችንን የሚያስታውስ ገጽ በስእሉ እንደሚታየው ይከፈታል፦

ስእል 4፤ የምሥጢር ቁልፍ መፈጠሩን የሚያረጋግጥ ሳጥን

ማስታወሻ፦ ጓደኛችን (buddy) በተመሳሳይ ደረጃዎች ለራሷ/ለራሱ አድራሻ/አካውንት ቁልፍ ማውጣት አለባቸው።

ደረጃ 3፦ ከታች በስእሉ የሚታየውን የሚመስለው የምሥጢር ቁልፋችን ከተፈጠረ በኋላ ይህንን መንካት/ክሊክ

ስእል 5፤ በኦቲአር ኤንጂን የተፈጠረ የቁልፋችን አሻራ (fingerprint of the key)

ማስታወሻ፦ አሁን ለአድራሻችን/አካውንታችን የምሥጢር ቁልፍ ፈጥረናል። ይህም የቻት መልእክታችንን ኢንክሪፕት ስለሚያደርገው ማንም ሰው የቻታችንን ይዘት ማየት አይችልም፤ ሦስተኛ ወገኖች የቻት ልውውጣችን መኖሩን መከታተል ቢችሉም ይዘቱን ግን ማግኘት አይችሉም።
አሻራ (fingerprint) ለአንድ አድራሻ/አካውንት የፈጠርነውን ቁልፍ ለመለየት የሚያስችል ረጅም የቁጥሮችና የፊደሎች ድብልቅ የሆነ መለያ ነው፤ ከላይ በስእል 5 ይታያል።

ፒድጂን የእኛን እና የጓደኞቻችንን አሻራ በቀጥታ ያኖራል፣ ትክክለኝነቱንም ያጣራል። ስለዚህ ይህን አሻራ በቃል ማስታወስ አያስፈልገንም።

3.3 እርምጃ 2 - የቻት ልውውጥ ክፍለ ጊዜን ትክክለኛነት መረጋገጥ የሚቻለው እንዴት ነው?

ደረጃ 1፦ ቻት ሊያደርገን የተዘጋጀውንና ኦንላይን ያለውን ጓደኛችንን (buddy) አካውንት በእጥፍ ንኬት መክፈት። ሁለታችንም የኦቲአርን ተሰኪ በትክክል ከጫንን እና አሠራሩን ከመረጥን በቻት ማድረጊያ መስኮታችን ግርጌ በስተቀኝ በኩል የኦቲአር አዝራር (button) እንመለከታለን፤

ስእል 6፤ የፒድጂን መልእክት መስኮት የኦቲአር መለያ በጥኩር ተከቦ ይታያል

ደረጃ 2፦ በስእሉ ተከቦ ያየነውን ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ፤ ተከትሎ ከሚከፈተው የአማራጮች ዝርዝርም Start private conversation የሚለውን ከታች በስእሉ እንደሚታየው መምረጥ

ስእል 7፤ ምሥጢራዊ ቻት የሚያስጀምረው “Start private conversation” አማራጭ ተመርጦ ይታያል

ከዚህ በኋላ የፒድጂን ቻት (IM) መስኮታችን እዚህ በስእሉ የሚታየውን ይመስላል

ስእል 8፤ በፒድጂን የቻት መስኮት Unverified የተባለው አዝራር (button) በጥቁር ተከቦ ይታያል

ማስታወሻፒድጂን በቀጥታ ከጓደኛችን የቻት (IM) ፕሮግራም ጋራ መገናኘት ይጀምራል፤ ምሥጢራዊና የተጠበቀ ግንኙነት ለመጀመር በሞከርን ቁጥርም መልእክቶችን ያሳየናል። በውጤቱም ይህ የሚለው የኦቲአር አዝራር ወደ ይቀየራል። ይህም ከጓደኛችን ጋራ ኢንክሪፕትድ የተደረገ ልውውጥ/ቻት ማድረግ እንደምንችል የሚጠቁም ነው።

ማሳሰቢያ፦ በዚህ ደረጃ የግንኙነታችን ደኅንነት የተጠበቀ ቢሆንም በዚያኛው ጫፍ ሆኖ ቻት የሚያደርገን ሰው ማንነት ገና አልተረጋገጠም። ሌላ ሰው ጓደኛችንን መስሎ ሊቀርብና ሊያወራን እንደሚችል መዘንጋት አይገባም።፡

3.4 እርምጃ 3 - ቻት የሚያደርገንን ሰው ማንነት ማረጋገጥ የሚቻለው እንዴት ነው?

የፒድጂን ጓደኛችንን ትክክለኛ ማንነት ለማረጋገጥ ካሉት ሦስት መንገዶች አንዱን መጠቀም እንችላለን። ሦስቱ መንገዶች (1) አስቀድሞ በሌላ መንገድ የተለዋወጥነው የምሥጢር መነጋገሪያ ኮድ ቃል ወይም ሐረግ፤ (2) ሁለታችን ብቻ መልሱን የምናውቀው ጥያቄና መልስ፤ ወይም (3) የፒድጂን ቁልፋችንን አሻራ በሌሎች መንገዶች ተለዋውጦ ቻቱን ከመጀመር በፊት እርሱን መለዋወጥ ነው።

የምሥጢር ቃል ወይም ሐረግ ኮድ

ወደ ቻቱ ከመምጣታችን በፊት በአካል በመገናኘት ወይም በሌላ መንገድ (በስልክ፣ በስካይፕ…) የምሥጢር ኮዱን ቃል ወይም ሐረግ (መለያውን) መለዋወጥ። ከዚያም ሁለታችንም ተመሳሳይ ኮድ በማረጋገጫው ቦታ ስንጽፍ የቻት ክፍለ ጊዜያችን ማንነታቸውን በሚተዋወቁ ሰዎች መካከል የሚደረግ መሆኑ የተረጋገጠ (authenticated) ይሆናል።

ማስታወሻየኦቲአር የምሥጢር ኮድ ቃል ማረጋገጫ የእንግሊዝኛው ፊደላት ለሚጻፉበት አይነት (A,B,C ወይም a,b,c) ጥንቃቄ ማድረግ አለብን። ቃሉ ትክክል እንኳን ሆኖ ፊደሉ በትልቅ ወይም በትንሽ መጻፍ ለፒድጂን ማረጋገጫ ለውጥ አለው። ስለዚህም ኮዱን ስንፈጥርም ሆነ ስናስገባ/ስንጽፍ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል።

ደረጃ 1፦ በቻት መስኮት ውስጥ ያለውን የኦቲአር አዝራር (button) መንካት፤ ከዚያም Authenticate Buddy የሚለውን በስእሉ እንደሚታየው መምረጥ

ስእል 9፤ ከUnverified የድንገቴ ምርጫ ዝርዝር Authenticate buddy የሚለው ተመርጦ

ወዲያውኑ Authenticate Buddy የሚል መስኮት ይከፈታል፤ የምንፈልገውን የማረጋገጫ መንገድ እንድንመርጥ ይጠይቀናል።

ደረጃ 2፦ በስእሉ እንደሚታየው ይቺን ምልክት በመጠቀም ከሚገኙት ዝርዝሮች መካከል Shared Secret የሚለውን መምረጥ

ስእል 10፤ የጓደኛ ማረጋገጫ ገጹ ከቁልቁል ተዘርጊ ዝርዝሮቹ ጋራ

ደረጃ 3፦ የመረጥነውን የምሥጢር ቃል ወይም ሐረግ ማስገባት/መጻፍ፤ በስእሉ እንደተመለከተው፤

ስእል 11፤ የምሥጢር ኮዶች ማረጋገጫው Shared Secret ገጽ

ደረጃ 4፦ ይህንን በመንካት ከታች የሚታየውን ገጽ መክፈት፤

ስእል 12፤ Authenticate Buddy መስኮት

ማስታወሻ፦ እዚህ ላይ በሌላው ጫፍ የሚገኘው ጓደኛችን በስእል 13 የሚታየውን መስኮት ይመለከታል፤ ስለዚህም የምሥጢር ቃሉን ወይም ሐረጉን ማስገባት ይኖርበታል። በሁለቱም ጫፍ የገቡት ቃሎች/ሐረጎች ተመሳሳይ ከሆኑ ግንኙነቱ የተረጋገጠ ማለትም በሚተዋወቁ ሰዎች መካከል እንደሚካሔድ የታወቀ ይሆናል።*

ስእል 13፤ የጓደኛ ማረጋገጫ (Authenticate Buddy) መስኮት

አንድ የግንኙነት ክፍለ ጊዜ ማረጋገጫ ከተሰጠው በኋላ የኦቲአር አዝራር (button) ቀለም ተቀይሮ ይህንን ይመስላል። ይህ ማለት ከዚያ በኋላ ግንኙነታችን ደኅንነቱ የተጠበቀ እና የምናወራው (ቻት የምናደርገው) ጓደኛችን ማንነት የተረጋገጠ ሆኗል ማለት ነው።

የጥያቄ እና መልስ መንገድ

በቻት ለመነጋገር የፈለጉ ሁለት ወገኖች አንዱ የሌላውን ትክክለኛ ማንነት ሊያረጋግጡ የሚችሉበት ሌላው መንገድ ጥያቄና መልስ ነው። ይህም የጋራ ጥያቄ ፈጥሮ ለእርሱ ተገቢውን መልስ መስጠት ነው። ጥያቄውን ካነበብብ በኋላ መልሱን እንጽፋለን፤ ሌላኛው ጓደኛችንም እንዲሁ ለዚሁ ጥያቄ ፍጹም ተመሳሳይ መልስ ከሰጠ ማንነታችን ወዲያውኑ ተጣርቷል ማለት ነው።

ደረጃ 1፦ በተከፈተ የቻት መስኮት የኦቲአርን (OTR) የአማራጮች ዝርዝር (ሜኑ) በመንካት/ክሊክ የድንገቴ ምርጫዎቹን () መክፈት፤ ከዚያም Authenticate Buddy የሚለውን መምረጥ (ስእል 9ን መመልከት)፤

ስእል 14፤ የፒድጂን ቻት መስኮት የኦቲአርን ምልክት ያሳያል

Authenticate Buddy መስኮት የጓደኛችንን ማንነት ለማረጋገጥ የምንፈልግበትን መንገድ እንድንመርጥ ይጠይቀናል።

ደረጃ 2፦ ቁልቁል ተዘርጊ ሜኑውን መንካት እና Question and Answer የሚለውን አማራጭ ከታች በስእሉ እንደሚታየው መምረጥ

ስእል 15፤ የጓደኛ ማረጋገጫ ገጽ (Authenticate buddy)

ደረጃ 3፦ ጥያቄውን እና መልሱን ማስገባት/መጻፍ። ይህን ጥያቄ ለጓደኛችን ይላክለታል።

ስእል 16፤ የጥያቄ እና መልስ ገጽ

ጥያቄው የደረሰው ጓደኛችን (buddy) የሚሰጠው መልስ እኛ ከሰጠነው ጋራ የሚመሳሰል ከሆነ የሁለታችንም ማንነት ትክክለኛነት ይረጋገጣል።

አንድ የቻት ክፍለ ጊዜ ትክክለኝነቱ ከተረጋገጠ በኋላ የኦቲአር አዝራር (button) ተቀይሮ ይህንን ይመስላል። ከዚህ በኋላ የቻት ክፍለ ጊዜያችን ደኅንነቱ የተረጋገጠ ነው፤ መልእክት የምንለዋወጠው ሰው (ጓደኛችን) ትክክለኛ ማንነትም ታውቋል።

በዚህ በሚከተለው መንገድ ማለትም Buddy List > Tools > Plugins > Off The Record Messaging > Configure Plugin ስንከፍት የKnown fingerprints ክፍል የጓደኛችንን አድራሻ/አካውንት ያሰየናል፤ የጓደኛችን ማንነት መታወቁን የሚያረጋግጥ መልእክት እንመለከታለን።

ስእል 17፤ የኦፍ-ዘ-ሪከርድ (Off-the-Record Messaging) ገጽ የታወቁ አሻራዎች (Known Fingerprints) ያሳያል

የምስራች! ከእንግዲህ ቻታችንን በምሥጢር ማድረግ እንችላለን። እንግዲህ ከጓደኞቻችን ጋራ ቻት ማድረግ ከፈለግን (ኮምፒውተር እስካልቀየርን ድረስ) ደረጃ አንድን እና ሦስትን መዝለል እንችላለን። ደኅንነቱ የተጠበቀ ግንኙነት ለማግኘት ጥያቄ ማቅረብ እና ከጓደኛችን ተቀባይነት ማግኘት ብቻ በቂ ነው።

ተንቀሳቃሽ ፒጂን እና ኦቲአር

1.0 በሚጫነው (Installed) እና በተንቀሳቃሹ የፒጂን (Pidgin) አይነቴዎች መካከል ያለው ልዩነት

ተንቀሳቃሽ መሣሪያዎቹ በምንጠቀምበት ኮምፒውተር ላይ አይጫኑም፣ ይህም ፕሮግራሞቹ እንዳሉንም ሆነ እንደምንጠቀምባቸው እንዳይታወቅብን ሊያደርግልን ይችላል። ሆኖም ተንቀሳቃሽ የውጫዊ ቅንጣቶቻችን (external device) ወይም የማስታወሻ ቋታችን (USB memory stick) እና የተንቀሳቃሽ መሣሪያዎቻችን (portable tools) ደኅንነት እንደምንጠቀምበት ኮምፒውተር ጤንነት እንደሚወሰን መዘንጋት የለብንም። ኮምፒውተሩ የተበከለ ከሆነ ለአድዌር፣ ለማልዌር፣ ለስፓይዌር እና ለቫይረስ ሊጋለጡ ይችላሉ። በተንቀሳቃሽ ፒጂን (Portable Pidgin) አይነቴ እና በኮምፒውተር ላይ በሚጫነው አይነቴ መካከል ምንም የአገልግሎት ልዩነት የለም።

2.0 ተንቀሳቃሽ ፒጂን መጫን እና መጠቀም (Download and Extract)

ተንቀሳቃሽ ፒጂን (Portable Pidgin) ለመጫን እና አውጥቶ ለመጠቀም የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል ያስፈልጋል።

ደረጃ 1፦ ወደ መጫኛው ድረ ገጽ ለመሔድ ይህንን http://portableapps.com/apps/internet/pidgin_portable መስፈንጠሪያ መንካት/ክሊክ

ደረጃ 2፦ ይህንን የመጫኛ ማዘዣ በመንካት/ክሊክ የመጫኛውን ገጽ ምንጭ መክፈት።

ደረጃ 3፦ ይህንን የማኖሪያ ማዘዣ በመንካት/ክሊክ ይህንን የመጫኛውን ፋይል በምንፈልገው ቦታ ማኖር/ማስቀመጥ (save)። ከዚያም ወዳኖርንበት ቦታ መሔድ።

ደረጃ 4፦ ይህንን የመጫኛውን ፋይል በእጥፍ-ንኬት መክፈት፤ ተከትሎ Open File - Security Warning የሚል ሳጥን ይከፈታል። በስእሉ የሚታየውን ገጽ ለመክፈት ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ

ስእል 1፤ የቋንቋ መጫኛ መስኮት

ደረጃ 5፦ ተከታዩን ገጽ ለመክፈት ይህንን ማዘዣ መንካት

ስእል 2፤ የተንቀሳቃሽ ፒጂን ማጫኛ መስኮት (The Pidgin Portable | PortableApps.com window)

ደረጃ 6፦ ተከታዩን ገጽ ለመክፈት ይህንን ማዘዣ መንካት

ስእል 3፤ የሚጫነውን ፕሮግራም የመምረጫ መስኮት

ማስታወሻ፦ ከእንግሊዝኛ ተጨማሪ ሌላ ቋንቋ ለመጠቀም ከፈለግን ይህንን አማራጭ በመምረጥ እንዲሠራ ማድረግ (enable) እንችላለን። ኾኖም ይህን አማራጭ የመገልበጡ ሒደት ተጨማሪ ጊዜ ሊወስድ ይችላል።

ደረጃ 7፦ ወደቀጣዩ ደረጃ ለመሔድ ይህንን ማዘዣ መንካት፤ ተከትሎ Choose Install Location የሚለው መስኮት ይከፈታል፤ ቀጥሎ ከታች በስእሉ የሚታየውን ገጽ ለመክፈት ይህንን ማዘዣ መንካት

ስእል 4፤ የማህደር መስኮት ማሰሻ

ደረጃ 8፦ ተንቀሳቃሽ/ተነቃይ ቅንጣቱን (removable device) ወይም የማስታወሻ ቋቱን (USB memory stick) ፈልጎ ማግኘት እና መምረጥ፤ ከዚያም የምርጫችን ቦታ ለማረጋገጥ ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክChoose Install Location ወደሚለው መስኮት መመለስ፤

ደረጃ 9ተንቀሳቃሽ ፒጂንን (Portable Pidgin) ወደ መረጥነው ፎልደር/ማህደር ለመገልበጥ (extract) ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ፤ ከዚያ የማጫን ሒደቱን ለማጠናቀቅ ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ

ደረጃ 10፦ ከታች በስእል 5 እንደሚታየው ፋይሉን የምናስቀምጥበት ተንቀሳቃሽ/ተነቃይ ቅንጣቱን (removable device) ወይም የማስታወሻ ቋቱን (USB memory stick) ፈልጎ ማግኘትና መክፈትየተንቀሳቃሽ ፒጂን (Portable Pidgin) ፕሮግራም በትክክል መኖሩን ማረጋገጥ።

ስእል 5፤ የፎልደር/ማህደር መስኮት ማሰሻ

ተንቀሳቃሽ ፒጂንን (Portable Pidgin) በአስተማማኝ ሁኔታ መጠቀም ከመጀመራችን በፊት፣ አጋዡና ተጨማሪው የሆነውን ተንቀሳቃሽ Off-the-Record (OTR) መጫን ይኖርብናል።

3.0 ተንቀሳቃሽ ፒጂን ኦቲአርን (Pidgin OTR) መጫን እና መጠቀም (Download and Extract)

ደረጃ 1፦ ወደ መጫኛው ድረ ገጽ ለመሔድ ይህንን http://sourceforge.net/projects/portableapps/files/Pidgin-OTR%20Portable/Pidgin-OTR%20Portable%203.2%20Rev%202/ መስፈንጠሪያ መንካት/ክሊክ

ደረጃ 2፦ ይህንን የፋይል መክፈቻ በመንካት የፒጂን-ቲኦራን መጫና Pidgin-OTR_Portable_3.2_Rev_2.paf.exe መስኮት መክፈት። ከዚያም ይህን የመጫኛ ፋይል በኮምፒውተራችን ላይ ለማኖር/ለማስቀመጥ (save) ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ

ደረጃ 3Open File - Security Warning የሚባለውን ገጽ ለመክፈት ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ። ተከትሎ በሚመጣው ገጽ የሚገኘውንን ይህን ማዘዣ መልሶ በመንካት የቋንቋ መምረጫውን Installer Language መስኮት መክፈት። (ስእል 1 መመልከት)።

ደረጃ 4በስእል 2 የሚታየውን የተንቀሳቀሽ ፒጂን-ኦቲአርን (Pidgin-OTR Portable | PortableApps.com) መስኮትን ለመክፈት ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ

ደረጃ 5፦ ወደሚቀጥለው ደረጃ የሚወስድንን ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ፤ ይህም Choose Install Location የሚለውን መስኮት ይከፍትልናል (ዝርዝር መረጃው ከተመሳሳዩ ስእል 3 ጋራ ይገኛል)

ደረጃ 6፦ ይህንን ምልክት በመንካት Browse for Folder የሚለውን የማህደር/ፎልደር ማሰሻ መክፈት (ስእል 4ን ይመልከቱ)

ደረጃ 7፦ ፋይሉን የምናስቀምጥንበትን ተንቀሳቃሽ/ተነቃይ ቅንጣት (removable device) ወይም የማስታወሻ ቋት (USB memory stick) ፈልጎ መክፈት፤ ከዚያም የተቀመጠበትን ቦታ ለማረጋገጥ ይህን መንካት፤ ወዲያውኑ የመጫኛ ቦታ ወደምንመርጥበት መስኮት Choose Install Location ይመልሰናል።

ደረጃ 8ተንቀሳቃሽ ፒጂንን (Portable Pidgin) ወደ መረጥነው ፎልደር/ማህደር ለመቅዳት (extract) ይህን ማስጀመሪያ መንካት፤ ከዚያም የመጫን ሒደቱ መጠናቀቁን ለማረጋገጥ ይህንን ማዘዣ መንካት

ደረጃ 9በስእል 5 እንደሚታየው ፋይሉን ያስቀመጥንበትን ተንቀሳቃሽ/ተነቃይ ቅንጣት (removable device) ወይም የማስታወሻ ቋት (USB memory stick) መክፈት፤ የተንቀሳቃሽ ፒጂን (Portable Pidgin) ፕሮግራም መኖሩን ማረጋገጥ።

ደረጃ 10ተንቀሳቃሽ ፒጂንን ሥራ ለማስጀመር ይህንን ፋይሉን በእጥፍ-ንኬት መክፈት።

ስለ ፕሮግራሙ አሠራርና አጠቃቀም ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ስለ ፒጂን (Pidgin) የሚያወሳውን ምእራፍ መመልከት ይቻላል።

የሚዘወተሩ ጥያቄዎች እና ክለሳ

5.0 የሚዘወተሩ ጥያቄዎች እና ክለሳ

ትዝታ እና ዩሱፍ ፒድጂን እና ተዛማጁን የኢንክሪፕሽንና የማንነት ማረጋገጭ ኤኒጂን የሆነውን ኦቲአርን በሚገባ ጭነው ጨርሰዋል። ለጥቂት ሰዓታትም አገልግሎቱን ለመመራመር እና ለመቃኘት ሞክረዋል፤ በጉግል ቶክ እና በሌሎችም ፒድጂንን በሚደግፉ የቻት ፕሮቶኮሎች እርስ በርስ ቻት ለማድረግ ሞክረዋል።

ይሁንና ዩሱፍ ስለ ፒድጂን-ኦቲአር ጥቂት ጥያቄዎች አሉ።

*ጥያቄበፒድጂን-ኦቲአር ኤምኤስኤን (MSN) እና ያሁን (Yahoo) በመጠቀም ቻት ማድረግ እንችላለን?*

*መልስፒድጂን-ኦቲአር በርካታ የቻት እና የመልእክት አገልግሎቶችን የሚደግፍ ቢሆንም ከጓደኛችን ጋራ ቻት ለማድረግ በተመሳሳይ የፈጣን መልእክት (IM) አገልግሎት መጠቀም ይኖርብናል። ለምሳሌ ሁለታችንም በኤምኤስኤን ወይም በጉግል ቶክ አድራሻችን/አካውንታችን መጠቀም ይኖርብናል እንደማለት ነው። ይሁንና በፒድጂን በተለያዩ አገልግሎት ሰጪዎች የሚሰጡ የፈጣን መልእክት አድራሻዎቻችንን (ጉግል ቶክ፣ ኤምኤስኤን፣ ያሁ…) ማስመዝገብና በተመሳሳይ ጊዜ ኦንላይን ሆነን ቻት ማድረግ እንችላለን። ብዝኀ-ፕሮቶኮል (multi-protocol) የፈጣን መልእክት (IM) አገልግሎቶች ተጠቃሚ መሆን የሚያስገኘው ድንቅ ጥቅምም ይህ ነው።*

*ጥያቄየፒድጂን-ኦቲአር አድራሻዬን በሌላ ኮምፒውተር መክፈትና መጠቀም የምችለው እንዴት ነው?*

*መልስየፈጣን መልእክት (IM) አድራሻችንን/አካውንት በሌላ (ከዚህ ቀደም ባልተጠቀምንበት) ኮምፒውተር ለመክፈት ለአድራሻችን አዲስ የምሥጢር ቁልፍ መፍጠር አለብን። ይህን ቁልፍ በመጠቀም ከጓደኞቻችን ጋራ ቻት ማድረግ እንችላለን። ሆኖም የቻት ክፍል ጊዜያችንን የተነጋጋሪዎች ማንነት እንደ አዲስ ማረጋገጥ (authenticate) አለብን።*

*ጥያቄየፈጣን መልእክት (IM) አድራሻዬን/አካውንት የይለፍ ቃል ብረሳው ወይም የሆነ ሰው የይለፍ ቃሌን ቢሰርቀኝ ምን ማድረግ እችላለሁ? የይለፍ ቃሌን ያገኙት ሰዎች አስቀድሞም ሆነ ከዚያ በኋላ የማደርጋቸውን ቻቶች ያገኙብኛል ማለት ነው? *መልስ፦ በጣም አስፈላጊ ጥያቄ ነው። የይለፍ ቃልህን ከረሳህ አዲስ የፈጣን መልእክት (IM) አድራሻዬን/አካውንት መክፈት ይኖርብሃል። ከዚያ አዲስ አድራሻ መፍጠርህን ለጓደኞችህ በስካይፕ ወይም በሌሎች ምሥጢራዊነቱ በተጠበቀ መንገድ ማስታወቅ አለብህ። በመጨረሻም፣ ከጓደኞችህ ጋራ እርስ በርስ ማንነታችሁን ማረጋገጥ (authenticate) አለባችሁ።*

 • የፈጣን መልእክት (IM) አድራሻህ/አካውንትህን የይለፍ ቃል የሰረቀው ሰው አንተን ተመስሎ ጓደኞችህን ለማሳሳት ይሞክር ይሆናል። ደግነቱ ግን የማንነት ማረጋገጫ ኮዳችሁን ስለማያውቀው የቻት ክፈለ ጊዜውን ማረጋገጥና መቀጠል (authenticate the session) አይችልም። ይህን ጊዜ ጓደኛህ አንተ እንዳልሆንክ ሊጠረጥር ይችላል። ለዚህም ነው በእያንዳንዱ የቻት ክፍለ ጊዜ ማንነትን ማረጋገጥ በጣም ጠቃሚ የሚሆነው። ከዚህም በተጨማሪ ቀደም ሲል እንዳየነው በኦቲአር የ'Config' ክፍል ያለውን አገልግሎት ከመረጥን ልውውጦቻችን ተመዝግበው አይቀመጡም፤ ስለዚህ የይለፍ ቃላችንን የሰረቀ ሰው ከዚያ ቀደም ያደረግናቸውን ልውውጦች ሊያገኛቸው አይችልም።*

5.1 የክለሳ ጥያቄዎች

 • ከአንድ የቻት ጓደኛችን (buddy) ጋራ የሚኖረንን የቻት ክፍለ ጊዜ “ማረጋገጥ” ('authenticate') ያለብን ስንት ጊዜ ነው?

 • በፒድጂን በርካታ የፈጥን መልእክት () አድራሻዎችን ማስመዝገብና በተመሳሳይ ሰዓትም ከተለያዩ ሰዎች ጋራ በተለያዩ አድራሻዎች ቻት ማድረግ ይቻላል?

 • በፒድጂን አሠራር አሻራ ምንድን ነው?

 • ፒድጂን-ኦቲአርን በሌላ ኮምፒውተር ላይ ስንጭን በኦቲአር አድርገነው የነበረው የአሠራር ምርጫ (preferences) (ለምሳሌ ያህል የተቀበልናቸው የአሻራ መለያ ቁልፎች) ምን ይሆናል?

 • በፒድጂን ምሥጢራዊ እና የተካፋዮቹ ማንነት የተረጋገጠለት የቻት ክፍለ ጊዜ ለመጀመር ምን ማድረግ ያስፈልጋል?

 • በፒድጂን አድራሻ ለመፍጠር የሚያስፈልገው ምንድን ነው?