ስፓይቦት፤ ጸረ ስፓይዌር

Updated7 December 2014

መመሪያው በወቅቱ አልተሻሻለም፤ በቅርቡ ይሰረዛል

Spybot Search & Destroy (በአጭሩ ስፓይቦት) ማልዌር፣ አድዌር እና ስፓይዌሮችን ለማደን እና ከኮምፒውተር ለማስወገድ ያገልግላል። ስፓይቡት የኢንተርኔት ማሰሻችን (Internet browser) በታወቁ ማልዌሮች እንዳይጠቃ ዘላቂ መከላከያ ወይም ክትባት ይሰጣል። የስፓይቦት የተሻሻሉ ቅጂ በየጊዜው በነጻ ሊገኝ ይችላል።

መነሻ ገጽ (Homepage)

ኮምፒውተሩ ምን ያስፈልገዋል?

 • ሁሉም የዊንዶውስ አይነቴዎች ሊሠሩ ይችላሉ

ለዚህ መመሪያ የተወሰደው አይነቴ

 • 1.6.2

ፈቃድ/ላይሰንስ

 • ነጻ ሶፍትዌር (Freeware)

አስፈላጊ ንባብ

ይህን መሣሪያ መጠቀም ለመጀመር የሚፈጀው ጊዜ፤ 20 ደቂቃ

ምን ጥቅም እናገኛለን

 • የተለያዩ ማልዌሮችን እና/ወይም ስፓይዌሮችን ለማስወገድ (remove) እንችላለን
 • ኮምፒውተራችን ለአደጋ ከመጋለጡ በፊት እንዳይበከል የሚያደርገው ክትባት ያገኛል

ከጂኤንዩ ሊኑክስ፣ ከማክ ኦኤስ እና ከሌሎች ማይክሮሶፍት ዊንዶውስ ጋራ ሊሠሩ የሚችሉ ፕሮግራሞች

ጂኤንዩ ሊኒክስ እና ማክ ኦኤስን የመሳሰሉት ኦፐሬቲንግ ሲስተሞች ከማልዌሮች (ስፓይዌር፣ ቫይረስ፣ ወዘተ) ነጻ ናቸው። ሆኖም የበለጠ አስተማማኝ ጥበቃ ለማግኘት የሚከተሉትን የጥንቃቄ እርምጃዎች እንድንወስድ እንመከራለን፤ (1) ኦፕሬቲንግ ሲስተማችንን እና በእርሱ ላይ የተጫኑ ፕሮግራሞችን የተሻሻሉ አይነቴዎች በየጊዜው መጫን/ማግኘት (update)፤ (2) በአቫስት (Avast) ምእራፍ የተዘረዘሩትን ጸረ ቫይረስ ፕሮግራሞች መጠቀም፤ (3) በኮሞዶ (Comodo) መመሪያ ውስጥ የሚገኙትን ፋየርዎል ፕሮግራሞች አገልግሎት ላይ ማዋል፤ (4) ፋየርፎክስን (Firefox) የመሳሰሉ ማሰሻዎችን መጠቀም፤ ማሰሻዎቹን ከድረ ገጾች ጋራ ከሚከፈቱ ጥቃቶች ለመከላከል የሚያስችለውን ኖስክሪፕት (NoScript) አጋዥ መሣሪያ አብሮ መጠቀም። እነዚህ የጥንቃቄ እርምጃዎች ኮምፒውተራችን የሚጠቀምበትን ጂኤንዩ ሊኑክስ ወይም ማክ ኦኤስ ከመበከል ይጠብቅልናል።

የደኅንነት ዋስትና ጥያቄው ማይክሮሶፍት ዊንዶውስን ለሚጠቀሙ ኮምፒውተሮች ቀደም ሲል ካልነው የተለየ ነው። በየእለት በሺህ የሚቆጠሩ አዳዲስ ማልዌሮች ይፈጠራሉ። የጥቃት ስልቶቹም በየጊዜው ውስብስብ እየሆኑ ነው። ከዚህ በፊት ባለው አንቀጽ የተዘረዘሩት የጥንቀቄ እርምጃዎች ማይክሮሶፍት ዊንዶውስን ለሚጠቀሙ ኮምፒውተሮች ሁሉ የግድ አስፈላጊ ናቸው። ከዚህ በተጨማሪ ግን በዚህ ምእራፍ እንደሚብራራው ስፓይቦት (Spybot) እንድንጠቀም በጥብቅ ይመከራል።

እነዚህን ሁሉ የጥንቃቄ እርምጃዎች ወስደንም ኮምፒውተራችን በቫይረስ ከተጠቃ ወይም ከተበከለ፣ እና ተጨማሪ አጋዥ መሣሪያዎች ካስፈለጉ የሚከተሉት አማራጮች ይመከራሉ፤

 1. SuperAntiSpyware የተባለውን ጸረ ስፓይዌር መጫን (Install) ፣ የተሻሻለ የስፓይዌር መከታተያ ዝርዝር አይነቴውን ማግኘት (update)፤ ከዚያም ኮምፒውተሩን እንደ አዲስ መፈተሽ (ስካን)

 2. Malwarebytes Anti-Malware የሚባለውን ጸረ ማልዌር መጫን (Install) ፤ ፈጣን ፍተሻ (Quick Scan) ማድረግ፤ ከዚያም በውጤት ማሳያው (Show Results) ላይ የሚታዩትን የተገኙ ማልዌሮች ማስወገድ (remove)፤

 3. በነጻ የሚገኙ ጸረ ስፓይዌር ፕሮግራሞችን መጠቀም። ለምሳሌ ያህል Microsoft Windows DefenderAd-Aware Internet Security እና SpywareBlaster

ስፓይቦትን መጫን (Downloading Spybot)

 • የአጠቃቀም መመሪያውን አጭር መግቢያ ማንበብ
 • በዚህ ሳጥን ግርጌ የሚገኘውን የስፓይቦት ምልክት በመንካት/ክሊክ ይህንን www.safer-networking.org/en/mirrors/ የመጫኛ ድረ ገጹን መክፈት
 • Download here የሚለውን በመንካት/ክሊክ ፕሮግራሙ የሚጫንበትን ቦታ መምረጥ
 • የፕሮግራሙን የመጫኛ/ማሠሪያ (installation) ፕሮግራም፤ ከዚያም ሁለት ጊዜ በመንካት (እጥፍ ንኬት/ doubleclick) መቀጠል።
 • ስፓይቦትን በትክክል ተጭኖ ካለቀ በኋላ የመጫኛ ፕሮግራሙን ከኮምፒውተራችን ልናጠፋው እንችላለን።

ስፓይቦት (Spybot) ፤

1.1 ይህን መሣሪያ መጠቀም ከመጀመራችን በፊት ልናውቃቸው የሚገቡ ነገሮች

Spybot S&D በነጻ የሚገኝ የተለያዩ የአድዌር (adware)፣ ማልዌር (malware) እና ስፓይዌር (spyware) አይነቶችን ከኮምፒውተራችን ላይ አድኖ የሚያገኝ እና የሚያስወግድ የታወቀ ፕሮግራም ነው። በተጨማሪም ስፓይቦትን ከጫንን በኋላ ኮምፒውተራችንን ከአድዌር፣ ማልዌር እና ስፓይዌር ጥቃት እንዳይጋለጡ የሚያደርግ ክትባት ነው።

አድዌር (adware) በኮምፒውተራችን ላይ ማስታወቂያዎችን የሚከፍትብን/የሚያሳይብን ሶፍትዌር ነው። አንዳንድ አድዌሮች ልክ እንደስፓይዌር ግላዊ ቀጣናችንን እና ደኅንነታችንን የሚዳፈሩ ናቸው።

ማልዌር (malware) የኮምፒውተራችንን አሠራር ከፈቃዳችን እና ከእውቅናችን ውጭ ለመጥለፍ ወይም ከፍተኛ ጉዳት ለማስከተል ታስቦ የሚዘጋጅ ፕሮግራም ነው። ትሮጃን (trojans) እና ዎርምስ (worms) የሚባሉት ጥሩ የማልዌር ምሳሌዎች ናቸው።

ስፓይዌር (Spyware) ከእውቅናችንና ከፈቃዳችን ውጭ የግል መረጃዎቻችንን እና በኢንተርኔት የምናደርጋቸውን ነገሮች የሚሰልል፣ የሚመዘግብና ለሌላ ሦስተኛ ወገን አሳልፎ የሚሰጥ ፕሮግራም ነው። እንደማልዌር ብዙውን ጊዜ በኮምፒውተራችን ላይ መኖሩን እንዳናውቅ ራሱን ለመሰወር ይችላል ወይም ይሞክራል። ስፓይቦትን የመሰሉ ፕሮግራሞች ከስፓይዌር ወረራ ይጠብቁናል።

ስፓይቦት (Spybot) ስንጭን በራሱ **ቲታይመር (TeaTimer) የተባለ ተጨማሪ አፕሊኬሽን ይጭንልናል። ይህም ኮምፒውተራችን በአዳዲስ ማልዌሮች እንዳይበከል ይከላከልልናል።

ማስታወሻዊንዶውስ ቪስታ (Windows Vista) ከመሠረቱ አብሮት የተሠራ ዊንዶውስ ዲፌንደር (Windows Defender) የተባለ ጸረ ስፓይዌር አለው። ሆኖም ዊንዶውስ ቪስታ (Windows Vista) በተጨማሪ ስፓይቦትን መጠቀም ግጭት አይፈጥርበትም።

የስፓይቦት (Spybot) አጫጫን እና አጠቃቀም

በዚህ ገጽ የሚገኙት ክፍሎች

2.0 ስፓይቦትን መጫን (Install)

ደረጃ 1፤ ይህንን የስፓይቦት ምልክት ሁለት ጊዜ መንካት (እጥፍ-ንኬት) Open File - Security Warning የሚለውን ሳጥን መክፈት። ሳጥኑ ሲከፈት ይህንን በመጫን/ክሊክ ከዚህ በታች የሚታየውን መስኮት ማስጀመር ይቻላል።

ስእል 1፤ ፕሮግራሙን ለመጠቀም የምንጠቀምበትን ቋንቋ የምንመርጥበት መስኮት

ደረጃ 2፤ ይህንን የይሁንታ ማረጋገጫ ምልክት በመንካት Setup - Spybot Password Safe – Welcome to the Spybot - Search & Destroy Setup Wizard የሚለውን ቀጣይ መስኮት መክፈት፤

ደረጃ 3፤ ይህን ምልክት በመጫን ወደሚቀጥለው ክፍል መሔድ፤ እዚህ በፕሮግራሙ የመጠቀም ስምምነት (License Agreement) መግለጫውን እናገኛለን። ስምምነታችንን ከማረጋገጣችና ፕሮግራሙን መጫን ከመጀመራችን በፊት ግን ስምምነቱን ማንበብ ጠቃሚ ነው።

ደረጃ 4፤ በማስከተል በተጠቃሚነት ስምምነቱ መስማማታችንን ለመግለጽ I accept the agreement የሚለውን ስንነካ/ክሊክ ወደ ቀጣዩ ክፍል ለማምራት የሚያስችለን * Next * የሚለው አማራጭ ይመጣል። ይህንን ስንነካው ፕሮግራሙን የምናስቀምጥበትን ቦታ የሚያስመርጠን የSelect Destination Location ይመጣል።

ደረጃ 5 የሚለውን ምርጫ በመንካት ከዚህ በታች የሚታየውን የመሰለ መስኮት መክፈት፤

ስእል 2፤ የምንፈልገውን የፕሮግራሙን አገልግሎት የምንመርጥበት የSelect Components መስኮት

ደረጃ 6በስእል 2 የሚታየውን በሚመስል ሁኔታ ተገቢዎቹን አገልግሎቶች መመረጥ፤ ከዚያም “ቀጥል” የሚለውን ይህንን አማራጭ በመንካት Select Start Menu Folderን መክፈት

ደረጃ 7፤ “ቀጥልን” በመጫን Select Additional Tasks ወደሚለው መስኮት መሔድ

ደረጃ 8፤ አሁንም በድጋሚ “ቀጥል” የሚለውን መንገድ በመከተል Ready to Install የሚለውን መስኮት ለሥራ ማዘጋጀት፤ ወዲያውም “ጫን” የሚለውን ማዘዣ መንካት። ፕሮግራሙ እየተጫነ መሆኑን የሚያሳየን Installing መስኮት ይታያል።

ደረጃ 9ን በመንካት የመጫን ሒደቱ መጠናቀቁን ማረጋገጥ እና Spybot - Search & Destroy ሥራ ማስጀመር።

2.1 ስለ ስፓይቦት

ስፓይቦትን በሚገባ ለመጠቀም የሚያስችሉ ሁለት መሠረታዊ ደረጃዎች አሉ።

 • የስፓይቦትን የምርመራ መመሪያ (Detection Rules) እና “የክትባት ዝርዝር” (Immunization databases) የተሻሻሉ አይነቴዎች በየጊዜው ማግኘት (Updating)

 • ስፓይቦትን መጠቀም/ማሠራት። በየጊዜው በምናገኘው የክትባት ዝርዝር የኮምፒውተራችንን ሲስተም “መከተብ”(immunize)፤ ከዚያም ኮምፒውተራችን ከስፓይዌር ነጻ መሆኑን ማረጋገጥ እና ማጽዳት ያስፈልጋል።

ማስታወሻ፤ እጅግ የተራቀቁ የስፓይቦት አማራጭ አገልግሎቶችን በተመለከተ በክፍል 3.0 የተራቀቁ አማራጮች 3.0 Advanced Options ያለውን መመልከት ይጠቅማል።

2.2 ስፓይቦትን ለመጀመሪያ ጊዜ መጠቀም

ፕሮግራሙን ከጫንን እና ምንጫዎቻችንን ከወሰንን በኋላ ስፓይቦት በቀጥታ በራሱ ሥራ ይጀምራል፤ አስከትሎም ከዚህ በታች የሚታየውን የሕጋዊ ጉዳዮች ስምምነትን የሚያሳየው መስኮት ይከፈታል።

ስእል 3፤ The Legal stuff screen

ማስታወሻ፤ በሚቀጥለው ጊዜ ስፓይቦትን ሥራ ለማስጀመር በእጥፍ-ንኬት (double click) መቀስቀስ ወይም የሚከተለውን መንገድ መከተል select Start > All Programs > Spybot - Search & Destroy > Spybot - Search & Destroy

ደረጃ 1፤ * Spybot - Search & Destroy* እና * Create registry backup* የተባሉትን ሁለት እጅግ በጣም አስፈላጊ የስፓይቦት አገልግሎቶች ሥራ ለማስጀመር ይህንን መጫን/ክሊክ፤

ስእል 4፤ የስፓይቦት ምርመራና ማጽጃ የምዝገባ ማስጀመሪያ መስኮት

ማስታወሻ፤ ለፕሮግራሙ የመጠባበቂያ ቅጂ መፍጠር (backup of the registry) እጅግ የሚመከር የጥንቃቄ እርምጃ ነው። ስለ ዊንዶውስ ሬጂስትሪ (Windows Registry) ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ሲክሊነር (CCleaner)

ደረጃ 2በስእል 4 እንደሚታየው ይህንን በመጫን/ክሊክ የፕሮግራሙን ምዝገባ የመጠባበቂያ ቅጂ መፍጠር

ደረጃ 3፤ ይህንን በመጫን/ክሊክ የስፓይቦት ማሻሻያ (Spybot - Search for Updates) ገጽ መክፈት። ከኢንተርኔት ጋራ ግንኙነት ካለን ወደሚቀጥለው ደረጃ መሔድ።

ደረጃ 4፤ ይህንን በመንካት የማሻሻያ መፈለጊያ (Search for Updates) መስኮቱን መክፈት፤ ከዚያም ወደ ክፍል 2.3 የስፓይቦትን የክትትል መመሪያ እና የክትባት መረጃ ማሻሻል (Update) መሔድ።

 • የኢንተርኔት ግንኙነት ከሌለን የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል፤

ደረጃ 5፤ ይህንን በመንካት/ክሊክ የክትባት ማስጀመሪያ (Immunize this system) መስኮቱን መክፈት፤ ቀጥሎም ከታች እንደሚታየው ክትባቱን ማስጀመር፤

ስእል 5፤ “የክትባት” (immunization) ሒደት መከታተያ

ማስታወሻ፤ ክትባቱን ለማስጀመር በምናዝበት ወቅት ያልዘጋነው ማሰሻ (browser) ካለ ክትባቱ ከመጀመሩ በፊት እዚህ የሚታየው አይነት ገጽ ይከፈታል፤

ስእል 6፤ ያልተዘጋ ማሰሻ መኖሩን የሚያሳይ ገጽ

ደረጃ 6፤ የተከፈቱ የድረ ገጽ ማሰሻዎችን መዝጋት (Close)፣ አስከትሎም ይህንን በመጫን/ክሊክ ክትባቱን (immunising) ማስጀመር

ደረጃ 7ክትባቱ (Immunize) ሳይቋረጥ ወደ ስፓይቦት፤ ፍለጋና ማጽዳት (Spybot - Search & Destroy) ለመመለስ በቅድሚያ ይህንን ከዚያም ይኽኛውን መጫን/ክሊክ

ስእል 8፤ ስፓይቦት- ፍለጋና ማጽዳት በስውር ሒደት ላይ

2.3 የስፓይቦትን የክትትል መመሪያ እና ‘የክትባት’ መረጃ ማሻሻል (Update)

እጅግ አስፈላጊየስፓይቦትን የመጨረሻ አይነቴዎች በየጊዜው ማግኘትና ፕሮግራማችንን ማሻሻል እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው።

ደረጃ 1በSpybot-S&D በስተግራ ካሉት አማራጮች ይህንን በመጫን/ክሊክ የስፓይቦት ማሻሻይ (Spybot-S&D Updater) ሥራ ማስጀመር ፤ እዚያም ማሻሻያውን ልናገኝባቸው የምንችላቸው ድረ ገጾች ዝርዝር ይቀርብልናል።

ደረጃ 2፤ ከቀረቡት የድረ ገጽ ዝርዝሮች መካከል እኛ ካለንበት አገር በቅርብ ርቀት የሚገኘውን (አገር) መምረጥ (Choose)፤ እርሱንም በቀኝ-ንኪት (right click) በመክፈት በስእል 9 እንደሚታየው Set this server as the preferred download location የሚለውን መምረጥ (select)

 • የመመርመሪያ ዝርዝራችንን (detection rules) በቅርቡ አሻሽለነው (updated) ከሆነ፣ No newer updates are available የሚል ማስታወሻ ያሳየናል።

 • የመመርመሪያ ዝርዝራችንን (detection rules) በቅርቡ አሻሽለነው ካልሆነ ግን የስፓይቦት ማሻሻያ (Spybot-S&D Updater) ማሻሻያዎቹን ልናገኝባቸው የምንችላቸውን ሰርቨሮች ዝርዝር ያሳየናል፤

ስእል 9፤ የስፓይቦት ማሻሻያ መስኮት (Spybot-S&D Updater window)

ደረጃ 3፤ ይህንን በመጫን/ክሊክ ማሻሻያውን ለመጫን (download) የምንችልበትን መስኮት ማለትም Spybot-S&D Updater - Please select the updates to download here መክፈት

ደረጃ 4፤ በመስኮቱ የሚታዩትን ምርጫዎች ሁሉ መምረጥ (Check)፤ ከዚያም በመንካት/ክሊክ ማሻሻያውን መጫን መጀመር።

ስእል 10፤ የስፓይቦት የምርመራ ዝርዝር እና የክትባት መረጃ

ማስታወሻ፤ ይህንን ማሻሻያ ስንጭን () ችግር ከገጠመን፣ ስፓይቦት በድጋሚ እንድንሞክር ይጋብዘናል። በመጨረሻ ማሻሻያውን በተሳካ ሁኔታ ጭነን ስንጨርስ ከዚህ በታች እንደሚታየው ኮምፒውተራችንን እንድንከትብ እና ችግሮች ካሉ ለማግኘት ምርመራውን እንድናስጀምር ይጠይቀናል።

ስእል 11፤ የመረጃ ገጽ

ደረጃ 6፤ በመጀመሪያ ይህንን ቀጥሎም ይህኛውን መንካት/ክሊክ

ወደ ስፓይቦት የምርመራና ማጽዳት (Spybot - Search & Destroy) ዋና ገጽ ይመልሰናል

ማስታወሻየስፓይቦትየማሻሻያ ሒደት በማንኛውም ጊዜ ልናከናውነው እንችላለን፤ ለዚህም የሚከተለውን መንገድ መከተል ይበቃል፤ Select Start > All Programs > Spybot - Search&Destroy > Update Spybot -S&D

2.4 የኮምፒውተራችን ክትባት (How to Immunise Your System)

ስፓይቦት ኮምፒውተራችን በሚታወቁ ስፓይዌሮች እንዳይጠቃ “ለመከተብ” (“immunizing”) ያስችለናል። ይህ ልክ ሰዎች በአዳዲስ ተላላፊ በሽታዎች እንዳይያዙ ክትባት እንደሚከተቡት አይነት ነው።

ኮምፒውተራችንን ለመከተብ የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል ይገባል።

ደረጃ 1በ Spybot-S&D የምርጫዎች ሳጥን የሚገኘውን ይህንን ወይም ይህንን በመንካት/ክሊክ በስእል 6 እንደሚታየው ክትባቱን በቀጥታ ማስጀመር።

በክትባት ሰሌዳው ላይ የምናገኛቸው መከላከያዎች ዝርዝር ይገኛል። ዝርዝሩን ሙሉ በሙሉ ለመመልከት መስኮቱን በስፋት መክፈት (maximise) ያስፈልገን ይሆናል።

ማስታወሻ፤ ክትባቱ የኮምፒውተራችንን አሰራር ይጎዳዋል ወይም ፍጥነቱን ይቀንስብናል ብለን ካመንን ክትባቱን ማስቆምና መተው እንችላለን። ይህንን ለማድረግ ይህንን በመጫን/ክሊክ ክትባቱን ማስቆም እና ኮምፒውተራችን ቀድሞ ወደ ነበረበት ሁኔታ እንዲመለስ ማድረግ ይቻላላ።

2.5 ችግሮችን መመርመር (How to Check for Problems)

ጥቆማ፤ አስጊ ችግሮችን መመርመር ከመጀመራችን በፊት የስፓይቦትን የመመርመሪያ ዝርዝር (Detection rules) እና የክትባት መዘርዝር( Immunization databases) ማሻሻል (update) ያስፈልጋል።

አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ ስጋቶችን ለመመርመር የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል ይገባል።

ደረጃ 1፤ ይህንን ምልክት በመንካት የስፓይቦት ምርመራና ጽዳት (Search and Destroy) ገጽ ሥራ መስጀመር፤

ደረጃ 2፤ ይህንን “ችግሮችንን መርምር” የሚል ማዘዣ በመንካት ምርመራውን ማስጀመር (ኮምፒውተራች ውስጥ በርካታ ዳታ፣ ማኅደሮች፣ ፕሮግራሞች ወዘተ ካለ ይህ ሒደት ከ20 ደቂቃ እስከ አንድ ሰዓት ሊወስድ ይችላል።) እዚህ ታች የሚታየው የስፓይቦት ገጽ ወዲያውኑ ይከፈታል፤

ስእል 12፤ ስፓይቦት አደጋዎች በመመርመር ላይ

ምእራፍ 3፤ ይህንን “ይሁን/ይደረግ” የሚል ማዘዣ በመጫን በኮምፒውተራችን ውስጥ ሊኖሩ የሚችሉ አደጋዎችን የመመርመሩ ሒደት በትክክል እንዲጀመር ስናዝ ይህንኑ የሚያሳይ መስኮት ይከፈታል።

ስእል 13፤ ስፓይቦት በምርመራ ላይ

ፍተሻው ሲጠናቀቅ የተገኙት ችግሮች አይነትና ብዛት ከዚህ በታች እንደሚታየው ይቀርባል

ስእል 14፤ ስፓይቦት በፍተሻው ያገኛቸው የአደጋ ምንጭ ሊሆኑ የሚችሉ ችግሮችና ስጋቶች ዝርዝር

ደረጃ 4፤ እንዲወገዱ (delete) የምንፈልጋቸውን ችግሮች በዝርዝሩ ውስጥ መምረጥ (Check)። በስጋትነት ከተዘረዘሩት መካከል አንዳንዶቹ የምንፈልጋቸው የማርኬቲንግ ሶፍትዌሮች ሊሆኑ ይችላሉ።

ጥቆማ፤ በዝርዝሩ ውስጥ በቀይ ቀለም የሚጻፉት በአጠቃላይ እንደ ችግር ወይም የስጋት ምንጭ ይታያሉ። በአረንጓዴ ቀለም የሚጻፉት ደግሞ የኢንተርኔት አጠቃቀማችንን የሚከታተሉና የሚመዘግቡ ናቸው። በዚህ ዝርዝር ከተመዘገቡት መካከል ባለበት እንዲቆይ የምንፈልገው ካለ አብሮት ባለው የመምረጫ ሳጥን አለመምረጥ (un-check) ነው።

አስፈላጊ ማስታወሻ፤ የተገኙትን ማልዌሮች ከማስወገድ ወይም ባሉበት እንዲቀመጡ ከመወሰን በፊት የእያንዳንዱን ምንጭ እና አሠራር/ዓላማ በቅርበት መመልከት በጥብቅ ይመከራል።

ደረጃ 5በስፓይቦት የፍተሻ ውጤት መስኮት በስተቀኝ የሚታየውንን ይህንን ምልክት በመንካት ስለተገኙት ማልዌሮች ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይቻላል። በዚህ ውስጥ ተጨማሪ መረጃ ከሌለ በኢንተርኔት መፈለግ ይቻላል። በዚህም ማልዌሮቹ እንዴት እንደሚሠሩ፣ የኮምፒውተራችንን ደኅንነት ለአደጋ ሊያግልጥ የሚችልባቸውን ሁኔታዎች መረዳት ይቻላል። ምንጊዜም ስለችግሮቹ የተሻለ እውቀት እና መረጃ ማግኘት ራስን ለመጠበቅ ያስቸላናል።

ስእል 15፤ የስፓይቦት ተጨማሪ መረጃ ማቅረቢያ ገጽ

ደረጃ 6፤ ይህን ትእዛዝ በመጫን የማልዌሮች ማስወገጃውን (deletion) ማስጀመር።

የተገኙትን ችግሮችና የስጋት ምንጮች በሙሉ ማስወገድ እንፈልግ እንደሆነ ይህንኑ እንድናረጋግጥ የሚጠይቀን ሳጥን

ደረጃ 7፤ ሁሉም እንዲወገዱ የምንፈልግ ከሆነ Yes የሚለውን መምረጥ

ማስታወሻ፤ በየሳምንቱ ኮምፒውተርን መፈተሽ ይመከራል።*

2.6 ቲታይመር (Resident TeaTimer)

ቲታይመር (Resident TeaTimer) ስፓይቦትን በማንጠቀምበት ጊዜ ጭምር ከጀርባ (running in the background) ሥራውን የሚያከናውን የስፓይቦት ፕሮግራም ነው። በጣም አስፈላጊ የሆኑ የኮምፒውተራችንን ክፍሎች ያለማቋረጥ ይከታተላል። ያለእውቅናችን የፕሮግራሞች አሠራር እንዳይነካም ይጠብቃል። ቲታይመር አጠራጣሪ ወይም አደገኛ ነገሮችን ሲያገኝ ወዲያውኑ ለተጠቃሚቹ ያሳውቃል፤ እርምጃ እንድንወስድም አማራጭ ያቀርብልናል፤ የተገኘው ነገር አደጋ ሊያስከትል የሚችል ከሆነ እንዲቆም ማድረግ (Deny) አለዚያም እንዲቀጥል መፍቀድ (Allow) እንችላለን። የሚከተለው መስኮት ይህንን የሚያሳይ ነው፤

ስእል 16፤ የቲታይመር የማስጠንቀቂያ መስኮት፤ የመፍቀጃ/መከልከያ (Allow/Deny change) ገጽ

ብዙ ፕሮግራሞች (አስፈላጊዎቹም ይሁኑ አደገኛዎቹ) ሥራ ለመጀመር የኮምፒውተራችን መሠረታዊ ክፍል (internal processes) ማግኘት ይኖርባቸዋል። ስለዚህም ቲታይመር በተደጋጋሚ ፍቀድ (Allow) ወይም ከልክል (Deny) የሚለውን አማራጭ/ትእዛዝ እንድንመርጥ ይጠይቀናል። እዚህ በሚታየው ምሳሌ እንደሚታየው ስካይፕን ከዊንዶውስ ስታርት ዝርዝር ለማጥፋት ተፈልጓል። ይህ የሚሆነው ብዙውን ጊዜ ፕሮግራሙን ኢ-መጫን (uninstalled) ስናደርግ ነው። ይህም አነስተኛ ለውጥ የሚያስከትል ትክክለኛ ጥያቄ ነው፤ ለውጡንም መፍቀድ አለብን።

ጥቆማበቲታይመር መስኮት የቀረበልንን ጥያቄ በትክክል ካልተረዳነው ተጨማሪ መረጃ ለማግኝት ይህን “መረጃ” የሚለውን መጫን/ክሊክ ከታች የሚታየውን የሚመስል ገጽ ይመጣል፤

ስእል 17፤ የስፓይቦት ስታርትአፕ (Startup) ገጽ

አንድ ፕሮግራም ሥራ እንዲጀምር እንድንፈቅድ ወይም እንድናግድ ምርጫ በሚቀርብልን ጊዜ ምርጫችን የሚያስከትለውን ለውጥ በተመለከተ እርግጠኛ ካልሆንን ከመፍቀድ ይልቅ ማገዱ ይመረጣል። ሆኖም ጥያቄው ከምናምነው ምንጭ የመጣ ከሆነ ውሳኔያችንን ስፓይቦት እንዲያስታውሰው ይህንን * Remember this decision* የሚለውን ከመረጥንለት ስፓይቦት ይህንኑ ፕሮግራም በተመለከተ በድጋሚ ተመሳሳይ ጥያቄ አያቀርብልንም።

ማስታወሻ፤ አዲስ ፕሮግራም ለመጫን በምንሞክርበት ጊዜ ቲታይመር (TeaTimer) ሒደቱን ለመከታተል ሥራ ሲጀምር ልንመለከት እንችላልን። ፕሮግራሙን ለማጥፋት/ኢ-መጫን (uninstall) ስንሞክርም ተመሳሳይ ነገር እንመለከታለን።

ጥቆማ፤ አዲስ የቲታይመር ማሻሻያ አይነቴ ሲኖር እየተከታተሉ ማሻሻያውን ማድረግ በጥብቅ ይመከራል።

2.7 የጠፉ ፋይሎችን መልሶ ማግኛ መሣሪያዎችን መጠቀም (Recovery Tool)

የማገገሚያ (Recovery) መሣሪዎች ከዚህ ቀደም የተወገደ (deleted) ወይም የተጠገነ (repaired) በኮምፒውተራችን ውስጥ የሚገኝ ነገርን መልሰን እንድናገኘው ያስችሉናል። ስፓይቦት ለሚያስወግዳቸው ማናቸውም ነገሮች የመጠባበቂያ ቅጂ ማስቀመጡ መልሶ የማይግኘቱን ሥራ ቀላል አድርጎታል። አንድን ማልዌር በማስወገዳችን የኮምፒውተራችን አሠራር እክል ከገጠመው፣ የማገገሚያ (Recovery) መሣሪያውን በመጠቀም ማልዌሩን ወደነበረበት መመለስ ይቻላል።

የተወገደ ነገርን መልሶ ወደነበረበት ለመመለስ የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል ይገባል።

ደረጃ 1፤ ይህንን ምልክት በመንካት የማገገሚያ ክፍሉን መስኮት መክፈት

ስእል 18፤ የስፓይቦት የማገገሚያ/ Recovery ገጽ

ደረጃ 2፤ ከዚህ ቀደም ከተወገዱ ነገሮች ዝርዝር ውስጥ ወደ ነበረበት እንዲመለስ የምንፈልገውን ከፊት ለፊት በሚገኙት ሳጥኖች ውስጥ ማመልከት (Check)፤ ከዚያም ይህንን በመንካት የማገገሙን ሒደት ማስጀመር።

*ቀድሞ ተወግዶ የነበረው ነገር ሙሉ በሙሉ ወደነበረበት እንዲመለስ ማዘዛችንን የሚያረጋግጥ ሳጥን ይታያል፤ ሳጥኑ ከዚህ በታች የሚታየውን ይመስላል፤

ስእል 19፤ የማረጋገጫ ሳጥን

ደረጃ 3፤ መልሶ የማግኘት ትእዛዛችንን ለማረጋገጥ “አዎን/ይደረግ” የሚለውን ይህን ማዘዣ መጫን

ደረጃ 4**፤ የተመረጡትን ነገሮች ወደ ቀደመ ቦታቸው በመመለስ ፋንታ እስከወዲያኛው ለማጥፋት ይህንን አማራጭ መከተል ይቻላል። ሆኖም በዚህ መንገድ የጠፉ ነገሮች ተመልሰው እንደማይገኙ ማስታወስ ይገባል።

ስፓይቦትን በተራቀቀ መንገድ መጠቀም

3.0 ስለ ስፓይቦት የተራቀቀ አሠራር (Advanced Mode)

ስፓይቦት በሁለት ማለትም በመደበኛ (Default) እና በተራቀቀ (Advanced) አሠራር ተግባሩን ያከናውናል። የተራቀቀው (Advanced) አሠራር የፕሮግራሙን መሠረታዊ መዋቅር (settings) እንድንቆጣጠር እና ተጨማሪ መሣሪያዎችን እንድንጠቀም ያስችለናል።

3.1 የስፓይቦትን የተራቀቀ አሠራር ማስጀመር

ስፓይቦትን በተራቀቀ (Advanced) የአሠራር ደረጃው ለመጠቀም የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል ያስፈልጋል።

ደረጃ 1፤ ከዚህ በታች በሚገኘው እንደሚታየው በቅድሚያ Mode የሚለውን መምረጥ፣ ከዚያ Advanced mode (Select Mode > Advanced mode) መምረጥ።

ስእል 1፤ የስፓይቦትን የአሠራር ደረጃ (Mode) መምረጫ

ወዲያውኑ ይህ ገጽ ይቀለጣል

ስእል 2፤ የማስጠንቀቂያ ገጽ

ደረጃ 2፤ የተራቀቀውን አሠራር መምረጣችንን ለማረጋገጥ ይህንን መጫን።

በተራቀቀ አሠራር በስፓይቦት መስኮት በስተግራ የሚረደረደሩት የአገልግሎት አማራጮች ቁጥር ይጨምራል

ስእል 3፤ የስፓይቦት የተራቀቀ አሠራር/ደረጃ መሠረታውያን

ደረጃ 3Settings የሚለውን በእጥፍ-ንኬት (Double click) መክፈት፤ ከዚህ በታች እንደሚታየው የተለያዩ አማራጮችን የሚያሳየን መስኮት ይከፈታል

ስእል 4፤ የመሠረታውያን (Settings) ገጽ

ደረጃ 4Tools የሚለውን በእጥፍ-ንኬት (Double click) በመክፈት በመደበኛ ፍተሻ ያልተገኙ ስፓይዌሮችን ለማግኘት የሚያስችሉንን መሣሪያዎች እናገኛለን፤ በእነርሱም ኮምፒውተራችንን በድጋሚ መፈተሽ/ማሰስ (rescan)።

ስእል 5፤ የመሣሪያዎች ገጽ

ስለምንጠቀምበት ስፓቦት አይነቴ፣ አሁን Spybot 1.6.2፣ አጠቃላይ መረጃ እና የመጠቀም ፈቃድ ለማወቅ Info & License የሚለውን በእጥፍ-ንኬት (Double click) መክፈት።

3.2 የተራቀቀ አሠራር መሣሪያዎች (Advanced Mode Tools)

የተራቀቀ አሠራር () ተጠቃሚዎች ስፓይቦት በሚሰጣቸው በሚከተሉት ተጨማሪ አማራጮች መደሰታቸው አይቀርም፤ አይኢ ትዊክስ (IE tweaks), ሽሬደር (Shredder), ሲስተም ኢንተርናልስ (System Internals) እና ሲስተም ስታርትአፕ (System Startup)

3.2.1 አይኢ ትዊክስ (IE tweaks)

የአይኢ ትዊክስ (IE tweaks) አማራጭ የሚያገለግለው ለኢንተርኔት ኤክስፕሎረር (Internet Explorer) ነው። ኢንተርኔት ኤክስፕሎረር ሁለት አስፈላጊ የደኅንነት ጥበቃ እርምጃዎችን እንድወስድ ያስችለናል። እርምጃዎቹ በተለይ በሲስተሙ ከአንድ ሰው በላይ የሚጠቀም ከሆነ ጠቀሜታቸው የጎላ ይሆናል።

ስእል 6፤ የአይኢ ትዊክስ (IE tweaks) ገጽ

በዚህ ምሳሌ ላይ እንደሚታየው የመጀመሪያውን አማራጭ መመረጡን (checked) ማረጋገጥ አለብን።

3.2.2 ሽሬደር (Secure Shredder)

ይህ መሣሪያ ጊዜያዊ የዊንዶውስ እና የኢንተርኔት ማሰሻ ፋይሎችን ለማጽዳት በጣም ጥሩ አማራጭ ነው። ጊዜያዊ ፋይሎችን እና ማጽዳትን በተመለከተ በኢንተርኔት ደኅንነት መጽሐፍ ምእራፍ 6. ስሱ መረጃዎችን በጥንቃቄ ማጥፋት የሚቻለው እንዴት ነው? ተጨማሪ ማብራሪያ ይገኛል።

ደረጃ 1፤ ከዚህ በታች የሚታየውን መስኮት ለመክፈት ይህንን መንካት/ክሊክ።

ስእል 7፤ በሴኪዩር ሽሬደር ስክሪን የሚታይ በንኬት የሚከፈት የአማራጮች ዝርዝር

ደረጃ 2በስእል 7 እንደሚታየው Templates በመንካት ለአጭር ወቅት የሚታየውን ዝርዝር መክፈት፤ ከዚያም የስፓይቦትን ሴኪዩር ሽሬደር እንዲጠቀምበት የምንፈልገውን ከዝርዝሩ ውስጥ መምረጥ፤

ስእል 8፤ የስፓይቦት የሽሬደር ገጽ

ደረጃ 3፤ የሚወገደውን ማኅደር/ፋይል መምረጥ**

ደረጃ 4፤ የመረጥነው ፋይል ለምን ያህል ጊዜ “እንዲጠፋ/እንዲሰረዝ”(shredded) እንደሚደረግ ከዚህ በታች እንደሚታየው መወሰን (Set)**

ስእል 9፤ የሴኪዩር ሽሬደር የብዛት መወሰኛ

**ደረጃ 5፤ የመረጥነው ፋይል ለምን ያህል ጊዜ “እንዲጠፋ/እንዲሰረዝ”(shredded) መደረግ እንዳለበት ከወሰንን በኋላ ይህንን ትእዛዝ መጫን/ክሊክ።

ስፓይቦት እነዚህን የማያስፈልጉ ጊዜያዊ ፍይሎች ከኮምፒውተራችን እስከወዲያኛው ያጠፋቸዋል።

ሴኪዩር ሽሬደር ሌሎች ፋይሎችንም ለማጥፋት ያገለግላል። ይህን ለማድረግ የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል ያስፈልጋል፤

ደረጃ 1፤ ከዚህ በታች የሚታየውን ገጽ ለመክፈት “Add file(s) to the list...” የሚለውን መምረጥ። (Select > Add file(s) to the list...)

ስእል 10፤ በሽሬድ የማሰሻ መስኮት የሚገኘው የፋይል መምረጫ

ደረጃ 2፤ እስከወዲያኛው “እንዲጠፋ/እንዲሰረዝ”(shred) የምንፈልገውን ፋይል መምረጥ (Select)

ደረጃ 3በስእል 8 የሚታየውን ፋይል ለመክፈት ይህንን “ክፈት” የሚል ትእዛዝ መጫን፤ ከዚያም ፋይሉን ለማጥፋትና ለማጽዳት ይህንን በመንካት ማዘዝ።

3.2.3 ሲስተም ኢንተርናልስ (System Internals) (በቂ እውቀት ላላቸው ተጠቃሚዎች ብቻ!)

ሲስተም ኢንተርናልስ (System Internals) በኮምፒውተራችን የዊንዶውስ መዝገብ (Windows Registry) ውስጥ የተሳሳተ ወይም የተለያየ ስያሜ የተሰጣቸውን ፋይሎች ፈልጎ የሚያገኝ መሣሪያ ነው። ስለ የዊንዶውስ መዝገብ (Windows Registry) ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ስለ ሲክሊነር (CCleaner) የተጻፈውን ማንበብ ይጠቅማል።

ስእል 11፤ የሲስተም ኢንተርናል ገጽ

ደረጃ 1በዊንዶውስ መዝገብ (Windows Registry) ውስጥ የሚገኙ ስሕተቶችን ለመፈለግ ይህንን “ፈልግ/ፈትሽ” የሚል ማዘዣ መጫን።

ደረጃ 2፤ ፍተሻው ከተጠናቀቀ በኋላ፣ የተገኙትን ችግሮች ለማረም ይህን ይህንን ትእዛዝ መንካት።

3.2.4 ሲስተም ስታርትአፕ (System Startup) (በቂ እውቀት ላላቸው ተጠቃሚዎች ብቻ!)

የሲስተም ስታርትአፕ (System Startup) መርጃ መሣሪያ ዊንዶውስ የጫናቸውን (loaded) ፕሮግራሞች በቅደም ተከተል ያሳየናል። ይህንን የሚያደርገው ኮምፒውተራችንን ስንከፍት ነው። ከፕሮግራሞቹ የሚያስፈልጉንን እና የማያስፈልጉንን እንድንለይ እድል ይሰጠናል።

ጥቆማ፤ የማያስፈልጉንን ፕሮግራሞች ማስወገድ ማለት ዊንዶውስ በተሻለ ፍጥነት እንዲሠራ ያስችለዋል።

ስእል 12፤ የሲስተም ስታርትአፕ ገጽ

*ደረጃ 1**፤ የመረጃ ንኡስ ገጹን ለመክፈት ይህን ማዘዣ መንካት/ክሊክ።

በዚህ የመረጃ ገጽ በተለያየ ቀለም የተቀለሙት ነገሮች እያንዳንዳቸው ያለቸው ባህርይ እና ሥራ ይጠቀሳል። እነዚህ የተዘረዘሩ ነገሮች ዊንዶውስ ሲከፈት አብረው ሥራ እንዲጀምሩ ወይም እንዳይጀምሩ ከመወሰናችን በፊት የእያንዳንዳቸውን ምንነት በሚገባ መረዳት ይኖርብናል። ስለባህርያቸውና ሥራቸው የተጻፈውን ማብራሪያ ማንበብ ለዚህ ይጠቅማል።

ተንቀሳቃሽ ስፓይቦት

1.0 በሚጫነው (Installed) እና በተንቀሳቃሹ የስፓይቡት (Spybot) አይነቴዎች መካከል ያለው ልዩነት

ተንቀሳቃሽ መሣሪያዎቹ በምንጠቀምበት ኮምፒውተር ላይ ስለማይጫኑ፣ ፕሮግራሞቹ እንዳሉንም ሆነ እንደምንጠቀምባቸው ላይታወቅ ይችላል። ሆኖም ተንቀሳቃሽ የውጫዊ ቅንጣቶቻችን (external device) ወይም የማስታወሻ ቋታችን (USB memory stick) እና የተንቀሳቃሽ መሣሪያዎቻችን ደኅንነት እንደምንጠቀምበት ኮምፒውተር ጤንነት እንደሚወሰን መዘንጋት የለብንም። ኮምፒውተሩ የተበከለ ከሆነ ለአድዌር፣ ለማልዌር፣ ለስፓይዌር እና ለቫይረስ ሊጋለጡ ይችላሉ። ከዚህ ውጭ በተንቀሳቃሽ ስፓይቦት (Portable Spybot) አይነቴ እና በኮምፒውተር ላይ በሚጫነው አይነቴ መካከል ምንም የአገልግሎት ልዩነት የለም።

ማስታወሻ፦ ቫይረሶችን፣ አድዌርን፣ ማልዌርን እና ስፓይዌርን ለማጥፋት ስለሚያስችሉ ተንቀሳቃሽ መሣሪያዎች በአጠቃቀም መመሪያ አቫስትን በመጠቀም ቫይረሶችን ማደን እና ማስወገድ በሚለው የአቫስት ምእራፍ 4.9 የተራቀቁ የቫይረስ አወጋገድ መንገዶች የሚለውን ክፍል መመልከት በጣም ይጠቅማል።

2.0 ተንቀሳቃሽ ስፓይቦትን መጫን እና መጠቀም (Download and Extract)

ስፓይዌር አዳኙን ተንቀሳቃሽ ስፓይቦት ለመጫን እና አውጥቶ ለመጠቀም የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል ነው።

ደረጃ 1፦ ወደ መጫኛው ድረ ገጽ ለመሔድ ይህንን http://portableapps.com/apps/security/spybot_portable መስፈንጠሪያ መንካት/ክሊክ

ደረጃ 2፦ ይህንን የፋይል ማዘዣ በመንካት/ክሊክ የመጫኛውን ገጽ ምንጭ መክፈት።

ደረጃ 3፦ ይህንን ማዘዣ በመንካት/ክሊክ ይህንን የመጫኛውን ፋይል በምንፈልገው ቦታ ማኖር/ማስቀመጥ (ሴቭ)። ከዚያም ወዳኖርንበት ቦታ መሔድ።

ደረጃ 4፦ ፋይሉን ወዳኖርንበት ቦታ በመሔድ ይህንን በእጥፍ ንኬት መክፈት፤ ተከትሎ Open File - Security Warning የሚለው የማዘዣ ሳጥን ይከፈታል፤ በሳይኑ ውስጥ የሚታየውን የሚለውን ማዘዣ መንካት/ክሊክ። ተከትሎ ቀጣዩን ገጽ የመሰለ ይከፈታል፤

ስእል 1፤ የቋንቋ መጫኛ መስኮት

ደረጃ 5፦ በስእሉ የሚታየውን ገጽ ለመክፈት ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ

ስእል 3፤ የስፓይቦት የተንቀሳቃሽ አይነቴ Portable Edition | Portableapps.com የመጫና መስኮት

ደረጃ 6፦ በመቀጠል የተጠቃሚነት ስምምነት (License Agreement) መግለጫውን መስኮት ለመክፈት ይህንን ማዘዣ መንካት

ደረጃ 7፦ የተጠቃሚነት ስምምነት ውሉን ካነበቡ በኋላ መቀበላችንን የምናረጋግጥበትን ይህንን መስመር መንካት/ክሊክ፤ ከዚይም ወደ ቀጣዩ ደረጃ ለመሔድ ይህንን ማዘዣ መንካት። ወዲያውኑ ቀጣዩ ገጽ ይከፈትልናል፤

ስእል 4፤ ፕሮግራሙን የምናስቀምጥበትን ቦታ መምረጫ መስኮት

ደረጃ 8፦ ከታች በስእሉ የምንመለከተውን ገጽ ለመክፈት ይህንን የመፈለጊያ ማዘዣ መንካት/ክሊክ

ስእል 5፤ የማህደር/ፎልደር ማሰሻ መስኮት

ደረጃ 9በስእል 5 እንደሚታየው ተንቀሳቃሽ የመረጃ ቅንጣቱ (external drive) ወይም የማስታወሻ ቋቱን (USB memory stick) ፈልጎ ማግኘት ከዚያም የSpybot - Search & Destroy Portable ፋይሉን ለማረጋገጥ ይህንን መንካት/ክሊክ። ከዚያ Choose Install Location ወደሚለው መስኮት ተመልሶ ፋይሉን ማግኘት።

ደረጃ 10ተንቀሳቃሹን የስፓይቦት አድኖ አጥፊ (Spybot - Search & Destroy Portable) ፕሮግራም መጫን ለመጀመር ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ። ሒደቱ ሲጠናቀቅም ይህንኑ ለማረጋገጥ ይህንን መንካት/ክሊክ። በማስከተል ተንቀሳቃሽ ስፓይቦት ወደ ተቀመጠበት ተንቀሳቃሽ የማስታወሻ ቋት መሔድ።

ስእል 7፤ አዲስ የተጫነው ተንቀሳቃሽ የስፓይቦት አይነቴ ፕሮግራም በሰማያዊ ቀልሞ ይታያል

ደረጃ 11የተንቀሳቃሽ ስፓይቦትን ማህደር/ፎልደር መክፈት፤ ከዚያም ይህንን የፕሮግራም ማስጀመሪያ ፋይል በእጥፍ ንኬት በመክፈት ስፓይቦትን ሥራ ማስጀመር።

የተንቀሳቃሽ ስፓይቦትን ፕሮግራም በትክክል ከከፈትን (extracted) በኋላ ስለፕሮግራሙ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከፈለግን ይህንን ስፓይቦት፤ ጸረ ስፓይዌር የሚለውን ምእራፍ ማንበብ እንችላለን።

የሚዘወተሩ ጥያቄዎች እና ክለሳ

4.0 የሚዘወተሩ ጥያቄዎች እና ክለሳ

ሰአዳ እና እንዳለ ስፓይቦት (Spybot) ለአጠቃቀም የቀለለ እና ሁሉን አቀፍ ሆኖ አግኝተውታል። ዋና ሥራው ማለትም ኮምፒውተርን ከስፓይዌር መከላከል በቀላሉና በቀጥታ የሚከናወን መሆኑን ተረድተዋል። ቲታይመር (TeaTimer) በየጊዜው የሚያቀርበው ለውጦችን የመፍቀድ (allowing) እና የመከልከል (denying) ጥያቄ በመጠኑ ግራ የሚያጋባና የሚያሳስብ ቢሆንባቸውም በሒደት በልምድ በቀላሉ አደገኛዎቹን ከጤነኞቹ መለየት እንደሚችሉ ያምናሉ።

ጥያቄስፓይቦትን አንኢንስቶል/ኢ-መጫን (uninstall) ባደርገው ከዚያ ቀደም በስፓይቦት ፈልጌ ያገኘኋቸው ስፓይዌር ፕሮግራሞች ምን ይሆናሉ? በኮምፒውተሬ “የማቆያ (quarantine)” ክፍል ይቀመጣሉ ወይስ ይወገዳሉ (removed)?

መልስስፓይቦትን ከኮምፒውተራችን ብናስወግደው (ኢ-መጫን/አንኢንስቶል) በማቆያው ውስጥ የተጠራቀሙ ነገሮች በሙሉ አብረው ይወገዳሉ።

ጥያቄሰአዳ፣ ጠቃሚ የሆኑ ኩኪስ (cookies) እና ትራከሮች (trackers) እየጠፉብኝ ተቸግሬያለሁ። እነዚህ ነገሮች እንዳይቀየሩ ወይም እንዳይወገዱ ምን ማድረግ እችላለሁ?

መልስብዙ አትጨነቅ። ጠቃሚ ኩኪስ (cookies) እና ትራከሮችን (trackers) ለመጠበቅ የሚያስችሉ ሁለት አማራጭ መንገዶች አሉ። መጀመሪያ በስፓይቦት ፍተሻ ስታካሒድ የተገኙትን ጉድለቶች እና አደጋዎች ዝርዝር ያቀርብልሃል። በዚህ ዝርዝር ያሉትን በሙሉ በመምረጥ ስለ እያንዳንዳቸው ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ትችላለህ፤ ይህም እያንዳንዳቸውን በተመለከተ የምትወስደውን ውሳኔ (መፍቀድ ወይም ማገድ) የተሻለ ያደርገዋል። ሌላው አማራጭ ስፓይቦትን ክፈት፤ ቀጥሎ የሚከተለውን ደረጃ ተከተል Mode > Advanced > Settings። እዚህ በማሰስና ማስወገድ ሒደቱ እንዳይነኩ የምትፈልጋቸውን በትክክል መምረጥ ትችላለህ።

ጥያቄስፓይቦትን ማስወገድ/ኢ-መጫን (uninstall) ከባድ ነው?

መልስ፤ *ይህን ማድረግ በጣም ቀላል ነው። የሚከተለውን ቀላል ሒደት ብቻ ተከተል፤ Start > All Programs > Spybot - Search & Destroy > Uninstall Spybot-S&D

ጥያቄየምጠቀምበት የኢንተርኔት ግንኙነት ፍጥነቱ በጣም አዝጋሚ ነው። ታዲያ የምርመራ ዝርዝር እና የክትባት መረጃዎችን (detection rules and immunization database) ከኢንተርኔት በፍጥነት ለማግኘት (ዳውንሎድ ለማድረግ) ምን ማድረግ እችላለሁ?

መልስበመጀመሪያ የዳታቤዝ ማሻሻያ ስንወስድ ከምንኖርበት ክልል ወይም የዓለም ክፍል ከሚቀርብ ቦታ መውሰድ ይጠቅማል። በተቻለ መጠን ካለንበት አካባቢ በሚቀርብ አገር ካለ ምንጭ ማሻሻያውን መውሰድ (ዳውንሎድ) ይመረጣል። አንተ ላለህበት አካባቢ/አገር የሚቀርበው መለየት በጣም ቀላለ ነው፤ ምክንያቱም ሰርቨሮቹ የት አገር እንደሚገኙ የሚያሳየው መረጃ በአገሮቹ ባንዲራ ተወክሎ ስለሚቀርብልን ነው።

ጥያቄለመሆኑ ስፓይቦት ማሻሻያዎችን በራሱ በቀጥታ የማያደርገው ለምንድን ነው?

መልስ፤ *በቤት ውስጥ መረብ እና “ፕሮፌሽናል ቨርዥን የሚጠቀሙ የስፓይቦት ተጠቃሚዎች ፕሮግራማቸው በቀጥታ በራሱ (automatically) ማሻሻያዎችን ያደርግላቸዋል። እንደአንተ በነጻ የሚገኘውን የስፓይቦት አገልግሎት የሚጠቀሙ ግን ይህን ማድረግ አይችሉም። በአንጻራዊነት ሲታይ ግን የስፓይቦትን** ማሻሻያ ማድረግ ከባድ አይደለም። ይህን በምስል አስደግፎ የሚያሳይ ገለጻ እዚህ ማግኘት ትችላለህ፤ www.safer-networking.org*

4.1 የክለሳ ጥያቄዎች

 • ማልዌር ምንድን ነው፣ ኮምፒውተራችንን የሚጎዳው እንዴት ነው?
 • የቲታይመር ጥቅምና ዓለማ ምንድን ነው?
 • በስፓይቦት ያጠፋነውን ነገር ቆይተን መልሰን ማግኘት (recover) እንችላለን?
 • ማልዌርን ከማሰስ እና ከማትጥፋት በተጨማሪ ስፓይቦት የሚሰጠቸው ሌሎች አገልግሎቶች ምንድን ናቸው?