ቶር - ማንነትን መደበቅ እና እገዳን ማለፍ

Updated 1 August 2014

መመሪያው በወቅቱ አልተሻሻለም፤ በቅርቡ ይሰረዛል

:Introduction

ዋናው ገጽ (Homepage)

https://www.torproject.org

ኮምፒውተራችን ምን ያስፈልገዋል?

 • ቶር በሁሉም የዊንዶውስ አይነቴዎች ይሠራል
 • የኢንተርነቴ ግንኙነት (connection)
 • ከዋና ዋናዎቹ የመካነ ድር ማሰሻዎች (web browsers) ጋራ ይሠራል፤ በተለይም ከሞዚላ ፋየርፎክስ (Mozilla Firefox) ጋራ መጠቀም ይመከራል

በዚህ መመሪያ ጥቅም ላይ የዋለው አይነቴ (Version)

 • Tor Browser: 1.3.18

ለመጠቀም የሚያስፈልግ ፈቃድ/ላይሰንስ

 • አገልግሎቱ በነጻ የሚሰጥ እና ምንጩም በግልጽ የሚገኝ (Open-Source) ሶፍትዌር

አስፈላጊ ንባብ

 • የኢንተርኔት ደኅንነት መጽሐፍ ምእራፍ [**8. ማንነትን መደበቅ እና የኢንተርኔት ሳንሱርን/እገዳን ማለፍ] (/am/chapter-8)

ይህን መሣሪያ መጠቀም ለመጀመር የሚፈጀው ጊዜ፡ 20 - 30 ደቂቃ

ቶርን በመጠቀም ምን እናገኛለን?

 • የምንጎበኘው ድረ ገጽ ዲጂታል ማንነታችንን እንዳያውቅ ለማድረግ ያስቸለናል
 • የኢንተርኔት አገልግሎት ሰጪያችን (Internet Service Providers (ISPs)) ወይም ሌላ የስለላ ዘዴ የሚጠቀም አካል ኦንላይን የምናደርገውን እንቅስቃሴ መዳረሻ እንዳያውቁ ያደርግልናል
 • የኢንተርኔት ሳንሱር እና እገዳዎችን ለማለፍ ያስቸለናል

ከጂኤንዩ ሊኑክስ፣ ከማክ እና ከሌሎችም የማይክሮሶፍት ዊንዶውስ ጋራ የሚሠራ ፕሮግራም ነው

የቶር (Tor) የማንነት መሰወሪያ መረብ ለጂኤንዩ ሊኑክስለማክ እና ለማይክሮሶፍት ዊንዶውስ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ተጠቃሚዎች በሙሉ ተዘጋጅቷል። የኢንተርኔት እና ኦንላይን እንቅስቃሴዎቻችንን ምሥጢራዊነት እና ደኅንነት ለመጠበቅ ቶር (Tor) በብዙዎች የሚመረጥ እና በየጊዘዌውም ጥልቅ ፍተሻና መሻሻል የሚደረግለት መሣሪያ ነው። ሆኖም ከቶር የተለየ አማራጭ ለሚፈልጉ የሚከተሉትን መፍትሔዎች እንጠቁማለን፤

ለተጨማሪ ግንዛቤ ሲሳዌ (Sesawe) ያሰናዳውን ሰነድ ማንበብ እጅግ ይመከራል። ድርጅቱ ተጠቃሚዎች ሳንሱር ያልተደረገ መረጃ የሚያገኙበት የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ የሚታገሉ ድርጅቶች ዓለም አቀፍ ትብብር ነው።

:Installation instructions

1.1 ይህን መሣሪያ መጠቀም ከመጀመራችን በፊት ልናውቃቸው የሚገቡ ነገሮች

ቶር የኢንተርኔት እንቅስቃሴዎቻችንንና ልማዶቻችንን ምሥጢራዊነት እና ደኅንነት ለማሻሻል ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ማንነታችንን እና የኦንላይን ሐሰሳችንን ከተለያዩ አይነት የኢንተርኔት ስለላዎች ይሰውርልናል። ማንነታችንን መደበቅ ፈለግንም አልፈለግን ቶር የኢንተርኔት ነጻነትን ለማስፋፋት፣ ሳንሱሮችንና ክልከላዎችን በማለፍ ለማንበብና ለመጻፍ ያስቸለናል።

ቶር የማንነታችንን ምሥጢራዊነት የሚያስጠብቀው ግንኙነታችንን በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በሚገኙ የሰርቨሮች መረብ በኩል በማስተላለፍ ነው። እነዚህ ሰርቨሮች በበጎ አድራጊዎች የሚተዳደሩ ናቸው። ይህም የኢንተርኔት ግንኙነታችንን ለመሰለል የሚፈልጉ ወገኖች የምንጎበኛቸውን ድረ ገጾች እንዳያውቁብን፣ ድረ ገጾቹም ራሳቸው ያለንበትን ቦታ/አካባቢ እንዳያውቁ ለማድረግ ያስችለናል። ከቶር ፕሮክሲ ሰርቨር አስተዳዳሪዎች የተወሰኑት ቶርን እየተጠቀምን መሆኑን ለማወቅ ይችሉ ይሆናል፤ ሌሎቹ ደግሞ የጎበኘነውን ድረ ገጽ ያውቁ ይሆናል፤ ሆኖም ሁለቱንም (ቶርን መጠቀማችንን እና የጎበኘነውን ድረ ገጽ) ማወቅ የሚችል አይኖርም።

ቶር አንድን ድረ ገጽ ለማግኘት/ለመክፈት እየሞከርን መሆኑን ማንም እንዳያውቅ ሊደብቅልን ይችላል፤ ሆኖም የኢንተርኔት ግንኙነታችንን ይዘት ለመደበቅ ታስቦ አልተዘጋጀም። ስለዚህም ከጂሜይል (Gmail) እና ራይዝአፕ (RiseUp) ጋራ ከተጠቀምንበት ቶር ተጨማሪ ጥበቃ ሊሰጠን ይችላል። ሆኖም ቶር ሆትሜይል (Hotmail) እና ያሁ (Yahoo) ከመሳሰሉት የኢሜይል አገልግሎቶች ጋራ ልንጠቀምበት አይገባም። ቶርን ስሱ መረጃዎችን ደኅንነቱ ባልተጠበቀ http ግንኙነት ከሚልኩና ከሚቀበሉ ድረ ገጾች ጋራ መጠቀምም አይመከርም።

ትርጉሞች/ፍቺዎች (Definitions)

 • ፖርት (Port)፦ በዚህ ምእራፍ ውስጥ አንድ ሶፍትዌር በሌላ መረብ በተገናኙ ኮምፒውተሮች ላይ ከሚገ አገልግሎቶች ጋራ የሚገናኝበት ነጥብ ፖርት ተብሎ ይጠራል። ለምሳሌ www.google.com የሚለው ዩአርኤል (URL) የሆነ አገልግሎት የሚገኝበት አድራሻ ('street address') ከሰጠን፣ ፖርቱ ደግሞ በቦታው ከደረስን በኋላ የትኛውን ‘በር (door)’ መጠቀም እንዳለብን ይጠቁመናል። በመካነ ድር (Web) አሰሳ ወቅት ደኅንነታቸው አስተማማኝ ያልሆኑ ድረ ገጾችን (ለምሳሌ http://mail.google.com) ስንጎበኝ በመደበኛነት የምንጠቀመው “port 80” የተባለውን ሲሆን ደኅንነታቸው የተጠበቁ ድረ ገጾችን (https://mail.google.com) ስንጎበኝ የምንጠቀምበት ፖርት 443 ነው።

 • ፕሮክሲ (Proxy)፦ በኮምፒውተራችን ወይም በአካባቢ/ቤት መረብ (local network) ካልሆነም በኢንተርኔት ላይ ሆኖ የሚሠራና መረጃችንን ወደ ታሰበው ቦታ የሚያስተላልፍ፣ በእኛና በመረጃችን መዳረሻ መካከል አገናኝ ሆኖ የሚሠራ ሶፍትዌር ነው።

 • ራውት (Route)፦ በኢንተርኔት ግንኙነት በእኛ ኮምፒውተር እና በመዳረሻችን ሰርቨር መካከል የሚፈጠረው መስመር/መንገድ ነው።

 • ብሪጅ ሪሌይ (Bridge Relay)፦ ወደ ቶር የስውር ተጠቃሚዎች መረብ (anonymity network) ለመግባት የሚያስችለን የመጀመሪያ የቶር ሰርቨር ነው። ብሪጆችን መጠቀም አማራጭ እንጂ ግዴታ አይደለም፤ ሆኖም ሰዎች ቶርን መጠቀም እንዳይችሉ ለማድረግ እገዳ በሚደረግባቸው አገሮች የሚኖሩ ተጠቃሚዎችን ታሳቢ መማድረግ የተዘጋጀ ነው።

የቶር ማሰሻ እስርን (Bundle) መፍታት

2.0 የቶር ማሰሻ እስርን (Browser Bundle) መፍታት

የቶር ማሰሻ እስር (Browser Bundle) ደኅንነቱ የተጠበቀ የኢንተርኔት ሐሰሳ ለማድረግ የሚያስፈልገንን ነገር ሁሉ አካቶ ይዟል። እነዚህም የቶር ፕሮግራም፣ ፖሊፖ (Polipo)ቪዳሊያ (Vidalia)፣ ተንቀሳቃሽ (portable) የፋየርፎክስ (Firefox) አይነቴ እና በፋየርፎክስ (Firefox) ቅጥያነት (add-on) የሚሰራው ቶርበተን (Torbutton) ናቸው።

የቶር ማሰሻ እስርን (Browser Bundle) ለመፍታት (Extract) የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል ይገባል።

ደረጃ 1፦ ይህንን የፋይል መክፈቻ በእጥፍ ንኬት (Double click) መክፈት። ተከትሎ Open File - Security Warning የሚል ሳጥን ሊከፈት ይችላል። ሳጥኑ ከተከፈተ በቀጥዩ ስእል የሚታየውን ገጽ ለመክፈት ይህንን ማዘዣ መንካት

ስእል 1፤ የ7-Zip self-extracting archive ገጽ

ማስታወሻየቶር ማሰሻ እስር (Browser Bundle) ራሱን በቀጥታ ወደ C:\Program Files ዳይሬክተሪ አይጭንም። ይህም ከብዙዎቹ በዚህ መጽሐፍ ከተዳሰሱት መሣሪያዎች ለየት ያደርገዋል።

ማስታወሻየቶር ማሰሻ እስርን (Browser Bundle) በተንቀሳቃሽ የማስታወሻ ቋት ማለትም ዩኤስቢ (USB memory stick) ላይ መጫንና መጠቀምም እንችላለን። ይህ አሠራር ቶርን በኮምፒውተራችን ላይ እንደምንጠቀም እንዳይታወቅ ለማድረግ ሊጠቅመን ይችላል።

ደረጃ 2፦ መደበኛውን የማህደር አቀማመጥ እንዳለ ለመቀበል ይህንን ማዘዣ መንካት፤ ወይም ይህንን በመንካት በስእሉ የሚታየውን Browse for Folder መስኮት መክፈት፤

ስእል 2፤ የBrowse for Folder መስኮት

ደረጃ 3የቶር ማሰሻ እስርን (Browser Bundle) ለመጫን የምንፈልገውን ፎልደር መፈለግ (Navigate)፤ ከዚያም ይህንን ማዘዣ በመንካት ምርጫችንን ማረጋገጥ፤ እዚህ በስእሉ እንደሚታየው፤

ስእል 3፤ የቶር ማሰሻ እስርን (Browser Bundle) ለመጫን የተመረጠ አድራሻ ምሳሌ

ደረጃ 4፦ ይህንን ማዘዣ በመንካት የቶር ማሰሻ እስር (Browser Bundle) ፋይሉን ከፍተን ማውጣት (Extracting) ስንጀምር ሒደቱን የሚያሳየው ሳጥን በስእሉ እንደሚታየው ይከፈታል፤

ስእል 4፤ የExtracting ሒደት ማሳያ

በዚህ ምሳሌ ፋይሎቹን የማውጣት (extraction) ሒደቱ ከተጠናቀቀ በኋላ የ የቶር ማሰሻ እስር (Tor Browser Bundle) በኮምፒውተራችን ላይ የሚገኘው C: Program Files\Tor Browser በሚለው አድራሻ ነው፤ በስእሉ እንደሚታየው፤

ስእል 5፤ የቶር ማሰሻ እስር በፕሮግራም ፋይሎች ዳይሬክተሪ ላይ ተጭኖ ይታያል

እዚህ ስንደርስ የቶር ማሰሻ እስርን (Tor Browser Bundle) በሚገባ ጭነን ጨርሰናል ማለት ነው።

በማስከተል በቶር ኔትወርክ ኢንተርኔት መጠቀም የሚቻለው እንዴት ነው? የሚለውን ክፍል በመረዳት ደኅንነቱና ምሥጢራዊነቱ የተጠበቀ የኢንተርኔት ግንኙነት ማድረግ ስለምንችልበት መንገድ በተግባር መማር እንችላለን።

በቶር ኔትወርክ ኢንተርኔት መጠቀም

በዚህ ገጽ የሚዳሰሱ ርእሰ ጉዳዮች

3.0 በቶር ኔትወርክ ከኢንተርኔት ጋራ መገናኘት

ማንነታችንን ሰውረን የኢነትርኔት ግንኙነት ለመፍጠር በቅድሚያ የቶር ማሰሻ (Browser) ፕሮግራምን ሥራ ማስጀመር ይኖርብናል። ይህም በቅድሚያ ከቶር ኔትወርክ ጋራ ያገናኘናል። ኮምፒውተራችን ከቶር ኔትወርክ ጋራ ግንኙነት ከፈጠረ በኋላ የቶር ማሰሻ (Browser) በራሱ በቶር ማሰሻ እስር (Tor Browser Bundle) ውስጥ የሚገኘውን የፋየርፎክስ ፖርቴብል በቀጥታ ይከፍተዋል።

ማስታወሻ፦ ማንነትን በመሰወር እና በግንኙነታችን ፍጥነት መካከል አንዱን መምረጥ ሊያስፈልገን ይችላል። ምክንያቱም ቶር ማንነታችንን ለመሰወር ቢያስችለንም ፍጥነቱ ግን በኮምፒውተራችን በሌሎች ማሰሻዎች (browser) ከምናገኘው የዘገየ መሆኑ ስለማይቀር ነው። ቶር በኢንተርኔት የምናቀርባቸውን ጥያቄዎች (ትራፊክ) በቅድሚያ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ወደሚገኙ የበጎ ፈቃደኞች ኮምፒውተር ይለከዋል። ይህን የሚያደርገውም የተጠቃሚዎችን ግንኙነት ምሥጢራዊነት እና ደኅንነት ለመጠበቅ ነው።

3.1 ከቶር ኔትወርክ ጋራ መናኘት

ከቶር ኔትወርክ ጋራ ለመገናኘት የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል ይገባናል።

ደረጃ 1፦ ወደ Tor Browser ማህደር/ፎልደር በመሔድ ይህንን መግቢያ በእጥፍ-ንኬት መክፈት፤ ቀጣዩ መስኮት ይታያል

ስእል 1፤ የቪዳሊያ መቆጣጠሪያ (Vidalia Control Panel) ከቶር ኔትወርክ ጋራ ግንኙነት በመፍጠር ላይ ሳለ

የቪዳሊያ መቆጣጠሪያ (Vidalia Control Panel) ከቶር ጋራ ግንኙነት በመፍጠር ላይ ሳለ ይህ ቢጫ ሽንኩርት የሚመስል ምልክት በኮምፒውተራችን ግርጌ በስተቀኝ በሚገኘው ሲስተም ትሬይ ላይ ይታያል። ኮምፒውተራችን ከቶር ኔትወርክ ጋራ መገናኘቱ ሲረጋገጥ ቢጫው ምልክት እዚህ እንደሚታየው ወደ አረንጓዴ ይለወጣል።

ማስታወሻየቪዳሊያ መቆጣጠሪያውን (Vidalia Control Panel) በጥሩ ሁኔታ ስለመጠቀም ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የቪዳሊያን መቆጣጠሪያ ማማ መመልከት እና ማስተካከል (Configure) የሚለውን ገጽ መመልከት ይጠቅማል።

ከጥቂት ሰከንዶች በኋላ የቶር ማሰሻ ከታች በስእሉ እንደሚታየው የሞዚላ ፋየርፎክስ ማሰሻውን በመክፈት ከቶር ጋራ መገናኘታችንን የሚያረጋግጥ መልእክት ያሳየናል።

ስእል 2፤ ሞዚላ ፋየርፎክስ “Are you using Tor?” በሚል ክፍል ከቶር ጋራ መገናኘታችንን ያረጋግጥልናል

የቶር ማሰሻ (ብራውዘር) ፕሮግራምን በከፈትን ቁጥር አስከትሎ የቪዳሊያ መቆጣጠሪያውን (Vidalia Control Panel) በቀጥታ ይከፍትልናል (ስእል 1)፤ ቀጥሎም ይህ የቶር ድረ ገጽ https://check.torproject.org/ ይከፈታል (ስእል 2)። የቶርበተን (Torbutton) ተጨማሪ አገልግሎት (add-on) በገጹ ግርጌ ይታያል፤ በዚህ ስእል እንደሚታየው

ማስታወሻየቶር ማሰሻን ከመክፈታችን በፊት ሌላ የሞዚላ ፋየርፎክስ ከፍተን ከሆነ ቶርበተን (Torbutton) አዲስ በተከፈተው ማሰሻ መስኮት አግልግሎት እንዳይሰጥ ተሰንክሎ (disabled) ይታያል፤ እዚህ እንደሚታየው

የቶርበተን አገልግሎት ፋየርፎክስ ከቶር ጋራ በትክክል እንዲገናኝ ማድረግ ነው። አገልግሎቱን ለማስጀመርም (enable) ሆነ ለመሰንከል (disable) ስንፈልግ ቶርበተን (Torbutton) የሚለውን ምልክት መንካት/ክሊክ እንችላለን።

ሆኖም ከቶር ኔትወርክ ጋራ ካልተገናኘን የቶርበተን (Torbutton) ምልክቱ ከታች በስእሉ እንደሚታየው ተሰንክሎ (disabled) ይታያል።

ስእል 3፤ ሞዚላ ፋየርፎክስ ከቶር ጋራ ግንኙነት አለመጀመራችንን የሚገልጽበት መልእክት (Sorry. You are not using Tor)

ስእል 3 እንደሚያሳየው ቶርበተን ተሰንክሎ ይታያል፤ ድረ ገጹም ባዶ ሆኖ ይታያል። ለተጨማሪ ማብራሪያ 4.0 የቪዳሊያ መቆጣጠሪያ አጠቃቀም የሚለውን ክፍል ማንበብ።

3.2 ከቶር ጋራ የፈጠርነውን ግንኙነት መፈተሽ

ከቶር ጋራ የፈጠርነውን ግንኙነት በራሳችን ለማረጋገጥ የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል እንችላለን።

ደረጃ 1፦ ይህንን የቶር ማረጋገጫ ድረ ገጽ https://check.torproject.org/ መክፈት። ድረ ገጹ ከቶር ኔትወርክ ጋራ በትክክል መገናኘታችንን ወይም አለመገናኘታችንን ያረጋግጥልናል።

የመካነ ድር ማሳሻችን በቶር ኔትወርክ ከኢንተርኔት ጋራ ከተገናኘ ባለንበት አገር እንዳይታዩ የታገዱ ድረ ገጾችን ጭምር መክፈት ያስችለናል፤ በተጨማሪም በኢንተርኔት የምናደርገው እንቅስቃሴ ምሥጢራዊነት የተጠበቀ ይሆናል። አንዳንድ ጊዜ www.google.com እና መሰል ድረ ገጾች ያለንበትን አገር ለውጠው ሲያሳዩ ታዝበን ይሆናል። ቶር ስንጠቀም ይህ መደበኛ አሠራር ነው፤ ማለትም ያለንበት ትክክለኛ አገርና ቦታ አይታይም።

3.3 በቶር በኩል ኢንተርኔትን ማሰስ

የቶር ኔትወርክን በመጠቀም በፋየርፎክስ በቀጥታ ድረ ገጾችን ማሰስ መጀመር ብንችልም የፋየርፎክስን አገልግሎት የበለጠ ውጤታማ በማድረግ የኦንላይን ደኅንነታችንን እና ምሥጢራዊነት ለማረጋገጥ ተከታዩን ክፍል በቅድሚያ ማንበብ ይጠቅማል።

3.3.1 ሞዚላ ፋየርፎክስ ከቶር ጋራ ተጣምሮ እንዲሠራ ማድረግ

ቶርበተን (Torbutton) የሞዚላ ፋየርፎክስን አገልግሎት ለማሻሻል የተዘጋጀ ቅጥያ (add-on or extension) ፕሮግራም ነው። ፕሮግራሙ ማንነታችንን ለመደበቅ እና የግንኙነታችንን ምሥጢራዊነት ለማረጋገጥ ይቻል ዘንድ ከሞዚላ ፋየርፎክስ ጋራ ተያይዘው የሚመጡ የደኅንነት ስጋቶችን ለማስወገድ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

ማስታወሻ፦ አደገኛ ድረ ገጾች ወይም የቶር ሰርቨር ራሱ ስለኢንተርኔት አድራሻችን እና ኦንላይን ስለምናደርገው እንቅስቃሴ ለሦስተኛ ወገን መረጃ አሳልፈው ሊሰጡብን ይችሉ ያሆናል፤ ቶርን እየተጠቀምን ጭምር ማለት ነው። ይሁን እንጂ የቶርበተን መደበኛ አሠራር በራሱ በአንጻራዊነት አስተማማኝ ነው ማለት እንችላለን። ነገር ግን የኦንላይን ደኅንነታችንን እና ምሥጢራዊነታችንን ለማረጋገጥ በማስከተል የተዘረዘሩቱን ማሻሻያዎች እንድናደርግ በጥብቅ እንመከራለን።

ማስታወሻ፦ ከማሰሻዎች (browser) ጋራ የተያያዘ በቂ እውቀት ያላቸው ተጠቃሚዎች አሠራሩን የበለጠ ማሻሻል ይችላሉ።

Torbutton Preferences የሚባለው የቶርበተን አገልግሎት መቆጣጠሪያ መስኮት ሦስት አማራጭ ክፍሎች (ኪሶች/ታብ) አሉት። እነርሱም፦

 • Proxy Settings ኪስ (tab)
 • Security Settings ኪስ (tab)
 • Display Settings ኪስ (tab)

*ቶርበተን በአገልግሎት ላይ ሆነም አልሆነ ማቆጣጠሪያውን የTorbutton Preferences መስኮት መክፈት እንችላለን። የቶርበተን መቆጣጠሪያውን (Torbutton Preferences) ለመክፈት የሚከተሉትን ደረጃዎች መከተል እንችላለን፤

ደረጃ 1ቶርበተንን (Torbutton) በቀኝ-ንኬት በመክፈት በስእሉ የሚታየውን መስኮት መክፈት

ስእል 4፤ የቶርበተን አገልግሎት መምረጫ (Torbutton menu)

ደረጃ 2Preferences... የሚለውን ክፍል መምረጥ የሚከተለውን ገጽ ይከፍትልና

ስእል 5፤ የቶርበተን መቆጣጠሪያ መስኮት የፕሮክሲ አሠራር መወሰኛ ኪስን (Proxy Settings tab) ያሳያል

 • Proxy Settings ኪስ/tab

Proxy Settings ኪስ/ታብ ፋየርፎክስ በቶርበተን በኩል ከኢንተርኔት ጋራ እንዴት መገናኘት እንደሚኖርበት የምንወስንበት ነው። በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ነገር መቀየር አይኖርብንም።

 • Security Settings ኪስ/ታብ

Security Settings ክፍል የተዘጋጀው ስለ ኢንተርኔት ደኅንነት እና ስለ መካነ ድር ማሰሻዎች አስተማማኝ ልምድ ወይም እውቀት ላላቸው ተጠቃሚዎች ነው። ሆኖም መደበኛው አሠራር በራሱ ለተጠቃሚዎች ከፍተኛ የደኅንነት ጥበቃ እንደሚሰጥ ማስታወስ ያስፈልጋል። Security Settings ቶርበተን የፋየርፎክስን የማሰሻ ታሪክ (browser history)፣ ካች ሜሞሪ (cache memory)፣ ኩኪስ (cookies) እና ሌሎችም እንዴት እንደሚቆጣጠራቸው ለመወሰን ያስችለናል።

ስእል 6፤ የSecurity Settings ክፍል

Disable plugins during Tor usage የሚለው አማራጭ እንዲሠሩ ልናደርጋቸው (enable) ከሚገቡን ጥቂት አማራጮች አንዱ ነው። ሆኖም ይህን ማድረግ ያለብን በቋሚነት ሳይሆን በጊዜያዊነት (temporarily) ብቻ ነው። ዴይሊሞሽን (DailyMotion)ዘ ሀብ (The Hub) እና ዩ ትዩብ (YouTube) በመሳሰሉ ምንጮች የሚገኙ የቪዲዮ ይዘቶችን በቶር ለመመልከት ከፈለግን Disable plugins during Tor usage የሚለውን አማራጭ መሰንከል (disable) አለብን።

ማስታወሻ፦ የሚታመኑ ድረ ገጾችን ቅጥያዎች (plugins) ብቻ መቀበልና ማሠራት (enable) ይገባል። ከዚያም ድረ ገጹን ጎብኝተን ስንጨርስ ወደ Security Settings ኪስ/ታብ በመመለስ Disable plugins during Tor usage የሚለውን አማራጭ በድጋሚ ማሠራት (enable) ይኖርብናል።

Security Settings ክፍል ውስጥ ስላሉት አማራጮች አገልግሎት ሰፊ ማብራሪያ ለማግኘት ይህንን Torbutton ድረ ገጽ መጎብኘት ይጠቅማል።

 • Display Settings ኪስ/ታብ

Display Settings ቶርበተን በፋየርፎክስ ማሳሻ ላይ እንዴት እንደሚታይ የምንመርጥበት ነው። ቶርበተን የሚታየን በዚህ ወይም ወይም በዚህ ወይም መልኩ ይሆናል። ከእነዚህ አማራጮች የተለየ መመልከቻ መንገድ የለም።

ስእል 7፤ የDisplay Settings ክፍል

ጥቆማ፦ ሐሰሳችንን (browsing) ስንጨርስ ጊዜያዊ (temporary) የኢንተርኔት ካቼና ኮኪሶችን (cache and cookies) ማጥፋት አለብን። ይህን ለማድረግ ፋየርፎክስ ለዚሁ ለማዘዝ የሚከተለውን መንገድ መከተል ያስፈልጋል፤ Tools > Clear Recent History... መምረጥ፤ ከዚያም በገጹ ላይ የሚታዩትን አማራጭ አገልግሎቶች በሙሉ መምረጥ (check)Clear Now የሚለውን አዝራር (button) መንካት/መምረጥ። የበለጠ ማብራሪያ ለማግኘት በአጠቃቀም መመሪያው ውስጥ ያለውን Mozilla Firefox ማንበብ ይጠቅማል።

ስለ ቶርበተን ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ይህንን Torbutton FAQ ገጽ መጎብኘት ይቻላል።

3.3.2 ኢንተርኔት ኤክስፕሎረር ከቶር ጋራ ተጣምሮ እንዲሠራ ማድረግ

ማስታወሻ፦ በመሠረቱ ቶር የተዘጋጀው ከሁሉም የመካነ ድር ማሰሻዎች ጋራ እንዲሠራ ታስቦ ነው። ሆኖም ፋየርፎክስ እና ቶር ሲጣመሩ ከኢንተርኔት ስለላ ለመሰወር፣ ከአደገኛ አጥቂዎች ጥቃት ለመከላከል በጣም ጥሩ አማራጮች ናቸው። ከዚህ አንጻር ኢንተርኔት ኤክስፕሎረር የመጨረሻ አማራጭ ተደርጎ መታየት አለበት።

ሆኖም ኢንተርኔት ኤክስፕሎረርን ከመጠቀም ውጭ ምንም አማራጭ ከሌለን የሚከተሉትን ደረጃዎች በጥንቃቄ መከተል ይኖርብናል።

ደረጃ 1የኢንተርኔት ኤክስፕሎረርን (Internet Explorer) የመካነ ድር ማሰሻ (web browser) መክፈት።

ደረጃ 2፦ በዚህ መንገድ በመሔድ Tools > Internet Options እና በመምረጥ Internet Options የሚለውን ገጽ መክፈት።

ደረጃ 3Connections የሚለውን ክፍል/ኪስ መንካት/ክሊክ፤ ይህም ከታች በስእል 8 የሚታየውን ገጽ ይከፍተዋል፤

ስእል 8፤ የInternet Options ገጽ የConnections ክፍል/ታብ

ደረጃ 4፦ ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ ከታች እንደሚታየው Local Area Network (LAN) Settings የሚባለውን ገጽ ይከፍትልናል

ስእል 9፤ የአካባቢ መረብ (Local Area Network -LAN) የአሠራር መምረጫ

ደረጃ 5በሰእል 9 እንደሚታየው Use a proxy server... የሚለውን አማራጭ መምረጥ፤ ከዚያም የProxy Settings ገጹን ለመክፈት ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ

ደረጃ 6፦ ከታች እንደሚታየው የፕሮክሲ አሠራሩን (proxy settings) ለመወሰን ቅጹን መሙላት/ማሟላት

ስእል 10፤ የተሞላ የፕሮክሲ አሠራር (Proxy Settings) ምሳሌ

ደረጃ 7Internet Options ከሚለው መስኮት ለመውጣት በእያንዳንዱ የአሠራር መወሰኛ ላይ ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ፤ ከዚያም ወደ ኢንተርኔት ኤክስፕሎረር (Internet Explorer) ማሰሻ መመለስ።

ማስታወሻበቶር መጠቀማችንን ለማቆም ከፈለግን ከደረጃ 1 እስከ 4 ያሉትን ሒደቶች መድገም አለብን። በደረጃ 5 ምትክ የUse a proxy server... አማራጩን መሰንከል (disable) ይኖርብናል።

ጥቆማ፦ የኢንተርኔት ሐሳሰችንን እና ግንኙነታችንን ከጨረስን በኋላ ጊዜያዊ የኢንተርኔት ካቼ (cache)፣ ኪኩስ (cookies) እና የማሰሻ ታሪካችንን (browser history) ለማጣፋት የሚከተሉትን ነገሮች በቅደም ተከተል መፈጸም ይገባናል።

ደረጃ 1፦ በስእሉ የሚታየውን General የተባለውን ክፍል ለመክፈት ይህን መንገድ እየተከተሉ መምረጥ Tools > Internet Options

ስእል 11፤ የኢንተርኔት ኤክስፕሎረር የGeneral ክፍል

ደረጃ 2፦ በTemporary Internet files ክፍል ያለውን ይህንን ማዘዣ በመንካት/ክሊክ ከታች እንደሚታየው የDelete Cookies ማረጋገጫውን ሥራ ማስጀመር

ስእል 12፤ የDelete Cookies ማረጋገጫ ሳጥን

ደረጃ 3፦ ጊዜያዊ የኢንተርኔት ኩኪስን (temporary Internet cookies) ለማጥፋት ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ

ደረጃ 4የDelete Files የማረጋገጫ ሳጥን ለመክፈት ይህንን ማዘዣ መንካት፤ ቀጥሎም ጊዜያዊ የኢንተርኔት ፋይሎችን ለማጥፋት ይህኛውን ማዘዣ መልሶ መንካት

ደረጃ 5፦ የInternet Options ማለትም የኢንተርኔት አማራጮች መወሰኛ ሳጥኑን ለመክፈት ይህንን ማዘዣ መንካት፤ አስከትሎ ይህንን እና ማዘዣዎች መንካት

ማስታወሻበኢንተርኔት ኤክስፕሎረር በኩል የቶር ኔትወርክን ለማግኘት የቶር ማሰሻችንን (Tor Browser) ከቶር ኔትወርክ ጋራ ከተያያዘ ቪዳሊያ ጋራ ማገናኘት ይኖርብናል።

የቪዳሊያ መቆጣጠሪያ አጠቃቀም

4.0 ስለ ቪዳሊያ መቆጣጠሪያ (Vidalia Control Panel)

የቪዳሊያ የመቆጣጠሪያ ማማ (Vidalia Control Panel) ቶርን ለመቆጣጠር የምንችለበት ዋናው ቦታ ነው። ማማው የቶርን የአገልግሎት ምርጫዎች በሚገባ እንድንጠቀምበት ያግዘናል፣ የግንኙነታችንን መለያዎች (connection parameters) ያሳየናል። የቪዳሊያን የመቆጣጠሪያ ማማ (Vidalia Control Panel) ለመክፈት የሚከተለውን መመሪያ መከተል ነው።

የቶር ማሰሻችንን (Tor Browser) ከፍተን እየተጠቀምንበት ከሆን የቪዳሊያ የመቆጣጠሪያ ማማ (Vidalia Control Panel) ** ለመክፈት ይህንን መልክት በእጥፍ ንኬት መንካት።

ጥቆማ፦ አረንጓዴ ቀለምና የሽንኩርት ቅርጽ ያለውን ምልክት በቀኝ-ንኬት ብንከፍተው፣ የቪዳሊያ የመቆጣጠሪያ ማማ (Vidalia Control Panel) በስእሉ እንደሚታየው በድንገቴ ማስታወሻ ሳጥን መልክ ይከፈታል፤

ስእል 1፤ የቪዳሊያ የመቆጣጠሪያ ማማ በድንገቴ ተከፋች መስኮት ይታያል

የቶር ማሰሻችንን (Tor Browser) ከፍተን እየተጠቀምንበት ካልሆነ ወደ ቶር ማሰሻ ማህደር/ፎልደር በመሔድ ይህንን ምልክት በእጥፍ-ንኬት (double-click) በመክፈት የቪዳሊያ የመቆጣጠሪያ ማማን (Vidalia Control Panel) ሥራ ማስጀመር እንችላለን። ይህን በቀጥታ ከቶር መረብ ጋራ ያገናኘናል፤ በስእሉ እንደሚታየው።

ስእል 2፤ የቪዳሊያ የመቆጣጠሪያ ማማ ከቶር መረብ ጋራ የተፈጠረ ትክክለኛ ግንኙነትን ያሳያል

4.1 የቶር ግንኙነትን መመልከት (View)

ደረጃ 1፦ ከታች በስእሉ የሚታየውን ገጽ ለመክፈት ይህንን ምልክት መንካት/ክሊክ

ስእል 3፤ የቶር መረብ ካርታ

የቶር መረብ ካርታ (Tor Network Map) ለአገልግሎት ክፍት የሆኑ የቶር የማንነነት መሰወሪያ መረቦችን የሚደግፉ ሰርቨሮችን ዝርዝር ያሳየናል። በስተግራ በኩል የሚገኘው ዝርዝር ለአገልግሎት ዝግጁ የሆኑ ሰርቨሮችን ከመረጃ የመሸከም አቅማቸው (ብንድዊድዝ) እና ካሉበት ቦታ ጋራ የሚያመላክተን ነው።

 • ይህንን ዝርዝር ሰርቨሮቹ ባሉበት አገር (በእንግሊዝኛው የፊደል ተራ ከፊት ወደኋላ ወይም ከኋላ ወደፊት) ወይም መረጃ በመሸከም አቅማቸው መጠን (ባንድዊድዝ) ቅደም ተከተል ለመደርደር ከፈለግን ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ እንችላለን።

የዓለምን ገጽ ከሚያሳየው ካርታ በታች ሁለት ክፍሎች ይገኛሉ። እነርሱም የConnections እና ዝርዝር መረጃዎች የሚገኝበት ክፍሎች ናቸው። Connections የሚባለው ክፍል በዘፈቀደ የተመረጡ የቶር ሰርቨሮች ዝርዝር ያሳየናል። ማንነታችንን ሰውረን ግንኙነት የምንፈጥረው በእነዚህ ሰርቨሮች በኩል ነው።

 • Connections በሚለው ስር አንድ ሰርቨር በመምረጥ በቶር መረብ የተገናኘንበትን ሰርቨር ለማወቅ እንችላለን። በካርታው ላይ የግንኙነታችንን መንገድ የሚያመለክተው በአረንጓዴ ቀለም የተሰመረው መስመር ነው።

ከአጠገቡ የሚገኘው ሰሌዳ በስተግራ በኩል Relay በሚለው ክፍል ስለሚታየው ሰርቨር ዝርዝር መረጃ የምናገኝበት ነው። ለምሳሌ በስእል 3 በካናዳ የሚገኝ settingOrange ስለተባለ ሰርቨር ዝርዝር መረጃ እንመለከታለን።

ማስታወሻየቶር የግንኙነት መረብ ካርታ (Tor Network Map) የቶርን ውስብስብ አሠራር በቀላሉ የሚያሳይና መረጃዎችን የሚሰጠን ነው።

4.2 የቪዳሊያን መቆጣጠሪያ ማማ መመልከት እና ማስተካከል (Configure)

ደረጃ 1፦ ከታች የሚታየውን ገጽ ለመክፈት ይህንን ማዘዣ መንካታ/ክሊክ

ስእል 4፤ የቪዳሊያ የመቆጣጠሪያ ገጽ (Control Panel) የአሠራር መወሰኛ (Settings) ገጽ

General የሚለው ክፍል ዊንዶውስ ሲከፈት ቪዳሊያ (Vidalia) አብሮ እንዲከፈትና የቶር ፕሮግራም ሥራ እንዲጀምር የምንፈልግ ከሆነ ይህንኑ አሠራር መደበኛ እንዲሆን እንድናዝ ያስችለናል።

ቪዳሊያን (Vidalia) ራሳችን በምንፈልግ ጊዜ ብቻ ሥራ መስጀመር የምንፈልግ ከሆነ Start Vidalia when my system starts የሚለውን ምርጫ መሰንከል (disable) ይኖርብናል።

ማስታወሻ፦ ጀማሪ ተጠቃሚዎች በስእል 4 ያለውን የአሠራር ምርጫ እንዳለ እንዲጠቀሙበት ይመከራል።

ደረጃ 2፦ የመረጥነውን አሠራር ለማረጋገጥ ይህንን ማዘዣ መንካት/ክሊክ

የቶር መደበኛ ቋንቋ እንግሊዝኛ ቢሆንም Appearance በሚለው ክፍል ከሚገኙት ሌሎች ቋንቋች የምንፈልገውን መምረጥ እንችላለን። ይህ ክፍል የመቆጣጠሪያ ማማውን (Vidalia Control Panel) ን ገጽታ ለመቀየር ያስችለናል።

ስእል 5፤ የቫዲሊያ ማማ የገጽታ መቀየሪያ ገጽ

4.3 የቶር ፕሮግራምን ማስጀመርና ማስቆም

ደረጃ 1፦ በሥራ ላይ የሚገኘውን የቶር ፕሮግራም ለማስቆም ስንፈልግ በቪዳሊያ አቋራጭ ማዘዣ (Vidalia Shortcuts) የሚገኘውንን ይህንን ማስቆሚያ መንካት እንችላለን። ወዲያውኑ የቪዳሊያ የሥራ ሒደት መከታተያ/ማመልከቻ Status ከታች በስእሉ የሚታየውን ይመስላል።

ስእል 6፤ የቶር የሒደት ማመልከቻ ቶር ሥራ ማቆሙን ያሳያል

ደረጃ 2የቶር ፕሮግራምን መልሰን ሥራ ማስጀመር ስንፈልግ ይህንን ማዘዣ መንካት እንችላለን። ከጥቂት ሰከንዶች በኋላ የሒደት ማሳያው ፕሮግራሙ ሥራ መጀመሩን ያሳየናል። ስእሉ ይህንን ያሳያል።

ስእል 7፤ የቶር የሒደት ማመልከቻ ቶር ሥራ መጀመሩንና ግንኙነት መፍጠሩን ያሳያል

የሚዘወተሩ ጥያቄዎች እና ክለሳ

6.0 የሚዘወተሩ ጥያቄዎች

ቶር በየጊዜው ጥልቅ ፍተሻ የሚደረግበት በጥንቃቄ የሚሰራ ሶፍትዌር ነው። ቶር በዓለም ዙሪያ የሚኖሩ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሚጠቀሙበት ኔትወርክ ሲሆን በየጊዜው የሚደረግለት ማሻሻያ የበለጠ አስተማማኝና ምሥጢራዊነቱ የተጠበቀ እንዲሆን አድርጎታል። በዚህ ምእራፍ የቀረበው ማብራሪያ በመጠኑ የተወሳሰበ ቢመስልም በአብዛኛው ቶርን በትክክል ለማሠራት 3.0 በቶር ኔትወርክ ከኢንተርኔት ጋራ መገናኘት የሚለውን ክፍል ሳያነቡ ማለፍ የሚመከር አይደለም።

መንሱር በኢንተርኔት ደኅንነት መጽሐፍ ሳንሱርን/እገዳን ሰለማለፍ የሚያወሳውን ምእራፍ 8. ማንነትን መደበቅ እና የኢንተርኔት ሳንሱርን/እገዳን ማለፍ በጥንቃቄ አንብቧል። በተጨማሪም የቶርን መመሪያ አንብቦ ጨርሷል። ሆኖም ጥቂት ጥያቄዎች አሉት፤ ቶርን ለዓመታት በመጠቀም የሚያውቃትን ማክዳን እየጠየቃት ነው።

*ጥያቄ፦ እንደው ለነገሩ፣ ቶርን መጠቀም ያለብኝ ለምንድን ነው?

*መልስ፦ የኢንተርኔት ሳንሱርን አልፎ የሚፈልጉትን ድረ ገጽ ለማግኘት ቶር በጣም ጥሩ መሣሪያ ነው። የኢንተርኔት አገልግሎት ሰጪያችን () የምንጎበኘውን ድረ ገጽ ምንነት እንዳያውቅብን ከፈለግንም ቶር ጥሩ ከለላ ይሰጠናል። ቶር የምንጎበኛቸው ድረ ገጾች ያለንበትን አድራሻ እንዳያውቁብን ለማድረግም ያስችለናል።*

*ጥያቄ፦ በ“Message Log” ላይ የስሕተት ማመልከቻ መልእክቶች (error messages) ደርሶኛል። ምን ማድረግ ይኖርብኛል?*

*መልስ፦ በቅድሚያ መልእክቶቹ በዚህ Tor FAQ የቶር መርጃ ዝርዝር ውስጥ መገኘት አለመገኘታቸውን አረጋግጥ። ሌላው አማራጭ በቪዳሊያ የመቆጣጠሪያ ማማ (Vidalia Control Panel) የሚገኘውን ይህንን ማዘዣ በመንካት የተለመዱ ችግሮችን ለመፍታት የሚረዳንን ይህንን How to Troubleshoot Common Problems in Tor ገጽ መክፈት።*

*ጥያቄየቶር ማሰሻን (Tor Browser) ስጠቀም ሌሎቹ ፕሮግራሞቼ በሙሉ ከኢንተርኔት ጋራ የሚገናኙት በቶር ኔትወርክ በኩል ይሆናልን?*

*መልስ፦ አይደለም፤ የቶር መረብን (Tor network) መገናኘት ያለብን በፋየርፎክስ ብቻ መሆን እንዳለበት መዘንጋት የለብንም፤ ቶርበተን (Torbutton) እንዲሰራ መደረጉንም (enabled) ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ሌሎቹ ፕሮግራሞች በሙሉ ከኢንተርኔት ጋራ የሚገናኙት በቀጥታ ነው። በቶር ኔትወርክ ከኢንተርኔት ጋራ መገናኘታችንን ፍጹም ለማረጋገጥ ይህንን https://check.torproject.org ድረ ገጽ መክፈት እንችላለን። ቶር ተጠቃሚዎች ያልተለመዱ ወይም አዲስ ድረ ገጾችን ሲጎበኙ ተገቢውን ጥንቃቄና ምርጫ ያደርጋሉ የሚል ግምት ይወስዳል።*

*ጥያቄቶር በፋየርፎክስ ማሰሻ የማደርጋቸውን ግንኙነቶች በሙሉ ይጠብቅልኛል?

*መልስቶር በአንተና በቶር መረብ (network) መካከል የሚደረገውን ግንኙነት በሙሉ ኢንክሪፕት ያደርጋል። ሆኖም ቶር በመረቡ እና ከምንገናኛቸው መዳረሻ ድረ ገጾች ጋራ ያለውን ግንኙነት ኢንክሪፕት ማድረግ እንደማያችል ማስታወስ አለብን። ለዚህ መድኀኒቱ የኤችቲቲፒኤስ ፕሮቶኮል (HTTPS protocol) ወይም ሌሎች መሰል የኢንክሪፕሽን አይነቶች መጠቀም ነው። የምንለዋወጣቸውን መረጃዎች ደኅንነትና ምሥጢራዊነት የሚያሳስበን ከሆነ ኢንክሪፕሽን መጠቀም ግዴታ ይሆናል።*

6.1 የክለሳ ጥያቄዎች

 • በቶር መረብ አንድ ግንኙነት ለመፍጠር ጥቅም ላይ የሚውሉት የቶር ሰርቨሮች ስንት ናቸው?
 • ስለእነዚህ ሰርቨሮች ተጨማሪ መረጃ መመልከት የሚቻለው የት ነው?
 • በቶር በኩል ድረ ገጾችን ለማግኘት መለወጥ ያለባቸው አሠራሮች/አጠቃቀሞች () የትኞቹ ናቸው?
 • የቶር መረብን ለማግኘት መመሥራት ያለባቸው ፕሮግራሞች የትኞቹ ናቸው?
 • ዊንዶውስ (Windows) በተከፈተ ቁጥር ቪዳሊያ አብሮ እንዳይከፈት ለማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?